Tuesday, April 2, 2019

ባለቅኔ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን (1929 -1998 ዓ.ም)

ባለቅኔ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን
(1929 -1998 ዓ.ም)

"የማይነጋ ህልም ሳልም
የማይድን በሽታ ሳክም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የሰው ሕይወት ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም"

"የዛሬ 57 ዓመት 1943 ዓ.ም ጃንሆይ የመጀመሪያ ቴአትሬን የዳኒስዮስ ዳኝነትን አምቦ ትምህርት ቤት አዳራሽ አይተው ስሜ በአዲስ ዘመንና በኢትዮዽያን ሄራልድ "ወጣት ደራሲ" ከተባለ ጀምሮ ጋዜጠኞች የሕይወት ታሪኬን እንዳስለፈለፉኝ ነው። ስለሕይወቴና ስለስራዎቼ አጫጭር ሐተታዎች ከፃፉት ከክቡር አሐዱ ሳቦሬ፥ ከብርሃኑ ዘሪሁን፥ከተገኘ የተሻወርቅ ከዻውሎስ ኞኞ ከከፈለ ማሞ፥ ከፍቅረ ማርያም ይፍሩ፥ከሙሉጌታ ሉሌ፥ከስዩም ወልዴ፥ከአጥናፍ ሰገድ ይልማ በተለየና ዘርዘር ባለመልኩ በአሉ ግርማ "የፀጋዬ ዝምታ" በሚል ርዕስ መነን መጽሔት ላይ፥ ማዕረጉ በዛብህ "የቦዳ አቦ የስለት ልጅ" በሚል ርእስ ከእንግሊዘኛው "መስከረም መፅሔት ላይ፥ ሪቻርድ ፓንክረስት "ፀጋዬ" በሚል ርእስ በእንግሊዘኛው "selamta" ላይ፥ አሳምነው ገ/ወልድና ነጋሽ ገ/ማርያም በኢትዮዽያ ሬዲዮና በኢትዮዽያ ቴሌቪዥን ላይ የፃፉትንና የተረኩት ጎላ ብለው ይታወሱኛል። -- ከዚህ ይልቅ ከሕይወት ታሪኬ ውስጥ ለኔ በጣም ጎልተው የሚታዩኝን፥ ሞቼ የተነሳሁባቸውን ዓይነት ልዩ ትዝታዎቼን ለመነሻ ያህል ልጥቀስላችሁ።
" እኔ የስለት ልጅ ነኝ። የስለት ልጅ ደሞ እኔ ባላምንበትም ትክዝተኛና ሕልመኛ፥ ሰበበኛና ሞገደኛ ነው ይባላል። ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ቁሴ ዲነግዴ በተወለዱበት ቦዳ አቦ ከአሰቦ በስተደቡብ ሜጫ ገጠር መንደር ነው እኔም የተወለድኩት 1929 ዓ.ም። አባቴ "ፀጌ፥ቁሴ" ይሉኝ ነበር ቁሴ ማለት በኦሮምኛ "ትክዝያለ" ወይም "ትክዝተኛ" ማለት ነው። እናቴ እኔን እንድትወልድ የተሳለችለትና ክርስትናም የተነሳሁበት ቦዳ ደረባ አቦ ቤተክርስቲያንን የተከሉት ሀብተጊዮርጊስ ናቸው። እና የመጀመሪያው የማይረሳና ትዝታዬ ፥ገና የሁለት ወር ጨቅላ ሁኜ አባቴ ከማይጨው ጦር ሜዳ ሳይመለሱ፥ ቤታችንን ባንዳ አቃጥሎት እናቴ በርራ እሳቱ መሀል ገብታ እንዴት እንዳወጣችኝ ታላቅ እህቴ ወ/ሮ አስካለ ገ/መድኅን ትንሽ ልጅ ሆና "የቦዳ አቦ ተአምር" እያለች ደጋግማ ያጫወተችኝ ታሪክ ነው።
"ሁለተኛው የዛሬ 27 ዓመት 1973 ስኳር በሽታ ዳያቤቲስ በድንገት ጥሎኝ አምስት ቀን ሙሉ "ኮማ" ውስጥ ገብቼ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ICU አጣዳፊ ጣዕር ህክምና ክንፍ ተኝቼ ጥቁር አንበሳ ተብሎ በሆለታ ልጆች መታሰቢያነት እንዲሰየም ለደርግ መንግሥት ጥናት ያቀረብነው አለቃዬ ክቡር ተክለፃዲቅ መኩሪያና እኔ ነን ፥ የነፕሮፌሰር ዕደማርያምና ጀማል፥ በነዶክተር ብሩ፥ባዩ፥ ገብረህይወትና መስፍን ልዩ ጥረት ከመንቃቴ በፊት፥ ስለስለትና ስለእሳት ስለምላጭና ስለብሽሽት፥ ስለሞትና ከሞት በኋላ በህልሜ ያየሁትንና በእንቅልፍ ልቤ የተናገርኩትን ታሪክ ነው።
"ሦስተኛው የዛሬ ዘጠኝ ዓመት 1991 ዓ.ም ሀዋርድ ዩኒቨርስቲ Ethiopia Foot Print of Time ኢትዮዽያ የጊዜ እግር አሻራ የተባለውን ሁለተኛ ቅፅ የእንግሊዘኛ መጸሐፌን ከዩስተን ቴሶሬ ጋር ያዘጋጀነውን የመጀመሪያውን ቅፅ ሀዋርድ ዩኒቨርሲቲ በፊልም ቀርፆታል አጠናቅሬ፥ ሁለተኛውንም በፊልም እንዳስቀርፅ ጋብዞኝ አሜሪካ እንደደረስኩ በቤተሰቤ ግፊት ደንገተኛ ምርመራ ተመርምሬ ኩላሊትህ ፈንድቷል ተብዬ ብሽሽቴን በተቀደድኩበት እኩለ ሌሊት የግማሽ እውንና የግማሽ ህልም እይታዬ ታሪክ ነው።
"ጎልተው ይታዩኛል የምላቸው እነዚህ ሦስት ትዝታዎች፥ በሕይወቴ ከእሳት የተረፍኩበት ሰዓት ጀምሬ ሌሊትና ቀን ስጮህ ብሽሽቴ አብጦ በሁለተኛው ቀን ወ/ሮ ስመኝ የሚባሉ ማህበርተኛ የነበሩ፥ የሴትና ወንድ ሕፃናትን ብልት ገራዥና የተለምዶ መድኃኒት አዋቂ መበለት ከሩቅ ቦዳ ዳርቻ ተጠርተው ደርሰው ብሽሽቴን በምላጭ በጥተው ነው አሉ ዝም ያሰኙኝ።
ገና በዘጠኝ አመቱ የተወነ፥ በ13 ዓመቱ ተኩሉ ድንቅ የተሰኘ ተውኔቱን የደረሰው በ26 ዓመቱ የአፍሪካ አንድነት አህጉራዊ መዝሙር ሥነግጥም ደርሶ ዕፁብ የተሰኘው በ29 ዓመቱ የሀገር የአማተራዊ ሽልማቶችን የተጎናፀፈው ፀጋዬ ገ/መድኅን በኢትዮዽያ፥ በአፍሪካና በዓለም ሥነጽሑፍ ህዋ ላይ - በጥበባት ሞገድ እንደ " አውሎ ሐሳብ " ተዥጎድጉዶ የካቲት 18 ቀን በምድረ አሜሪካ በ69 ዓመቱ፥ አፀደሥጋው አረፈ በሚወዳትና በተሟገተላት ውድ ሀገሩ አርፏል።
ደራሲው ሥራዎች
1. እሳት ወይ አበባ(ግጥምና ቅኔ)
2. የዳኒሲዩስ ዳኝነት(ተውኔት)
3. በልግ(ተውኔት)
4. የደም አዝመራ(ተውኔት)
5. እኔም እኮ ሰው ነኝ(ተውኔት)
6. የከርሞ ሰው(ተውኔት)
7. የእሾህ አክሊል(ተውኔት)
8. ክራር ሲከር(ተውኔት)
9. አስቀያሚ ልጃገረድ(ተውኔት)
10. እኝ ብዬ መጣሁ(ተውኔት)
11. ቴዎድሮስ(ተውኔት)
12. ምኒልክ(ተውኔት)
13. ጴጥሮስ ያቺን ሰአት(ተውኔት)
14. ዘርዓይ ደረስ(ተውኔት)
15. ጆሮ ገድፍ(ተውኔት)
16. ሀሁ በስድስት ወር(ተውኔት)
17. እናት ዓለም ጠኑ(ተውኔት)
18. መልእክተ ወዛደር(ተውኔት)
19. አቡጊዳ ቀይሶ(ተውኔት)
20. ጋሞ(ተውኔት)
21. ሀሁ ወይም ፐፑ(ተውኔት)
22. ቴራቲረኞች [ የምፀት ኮሜዲ፥ አልታየም ] (ተውኔት)
23. ዐፅም በየገጹ (ተውኔት)
24. ሰቆቃወ ዼጥሮስ(ተውኔት)
25. ትንሣኤ ሰንደቅ ዓላማ(ተውኔት)
26. የመቅደላ ስንብት(ተውኔት)
27. ጥላሁን ግዛው(ተውኔት)
28. ዐፅምና ፈለጉ(ተውኔት)

ምንጭ:ብርሀነመስቀል ደጀኔ 2000ዓ.ም ብራና.ማ.ቤ ካሌንደር።

ኣገራዊ ችግርን መደበቅ ያዋጣል ወይስ ኣያዋጣም ?

የተቸገረን ኣንደብቅ ፥ በአግባቡ እሚረዳውን እንርዳ። የተራበ ችግረኛን ደብቀዋል ተብለን ለምን የፈረንጅ ጋዜጠኛና ሴሌብሪቲ መዘባበቻ እንሑን ጎበዝ ?። እነሱ በኛ ረሀብና ችግርና መፈናቀል ቢዝነስ እስኪሰሩብን ድረስ ለምን እንጠብቃለን ? ።

ለምን የፈረንጅ ሴሌብሪቲዎች ረሃብ ፥መፈናቀል ፥  ተደብቆአል ብለው ቢዝነሥ ይሥሩብን ? ረሃብን ኣጋለጡ ተብለው እነርሱ በእኛ ችግር ዝነኛና ታዋቂ ሀብታም ይሁኑበት ? ።በ#BBC ወይም #CNN ኢንተርቪው ይደረጉ ? #Instantly Celebrity ይሁኑ ?
ክርስትናን ኣስቀድማ የተቀበለች እና በላሊበላ ገናን እምታከብር ኣገር #Do they know is it Christmas ? ተብላ ግጥም ተገጥሞባላታል ፥ ዜማ ተዚሞባታል።
ቦብ ጌልዶፍ #Bob Geldof  በ77ዓ.ም.ረሃብ ለችግረኞች ተቆርቁዋሪ መሥሎ ራሡን ዝነኛ ኣድርጎበታል። አሁን እርሱ ቢጠሩት እምስይሠማ ቱጃር ሆኖአል ኣሉ ። ይህን ሻለቃ ዳዊት ከጋዜጠኛ መአዛ ጋር በሸገር 102 FM ያደገውን ቃለ መጠይቅ አድምጡ ።

Friday, March 29, 2019

ከንቱ ነው

‹‹ኒዕመቱ ዱኒያ በይነል ፈኺዘይን ››
(አሌክስ አብርሃም )

ብየሽ የነበረው ማግባት ምናባቱ
ብየሽ የነበረው ትዳር ማለት ከንቱ
ኡመቱ ለዱኒያ ሲሻኮት ሲለፋ
አለች ያልናት አለም ከጃችን ስጠፋ ….

አንድ ነገር ገባኝ ሹክ አለኝ መለይካው
በነብስህ እልፍኝ ውስጥ ከንቱ ነው ፍራንካው !
ከንቱ ነው ጭብጨባው
ከንቱ ነው ጉልበቱ
ከንቱ ነው ስልጣኑ
ከንቱ ነው ወረቱ !
እዛም እዛም አትጫር
ከንቱ ነው እሳቱ !
የመምጫ መሄጃው
ፍጥረተ ኡመቱ …..
አንድ ነገር ገባኝ
እኔ ያንች ገልቱ …..

ፍቅር በሌለበት ዱኒያ ማለት ጤዛ
አቅልን ስቶ መሮጥ መዋከብ ወ….ደዛ !
የምን መንጀላጀል የምን ነገ ዛሬ
ጥቅልል ከመሻትሽ ኒካየን አስሬ
ፍቅር አንችን ብቻ
ውድድድ አይንሽን
ፍቅር አፍንጫሽን
እብድ ለከንፈርሽ
መልመድ ከጠረንሽ
ለ…..ሽ ከደረተሸ
ጡትሽን መከዳ …
ኧረ እ……..ዳ !

ከዛ …..
እንደሰማይ መብረቅ
ካየር እንደጣሉት ጋን የሚያህል ፈንጅ

ተምዘግዝጌ …. የሳት ከተማሽ ውስጥ እልም ነው እንጅ !

የኔ የሰማይ መና ሃላል የነብስ ሃቄ
ቤቴን በፈገግታሽ ቤትሽን በሳቄ
‹‹ኒዕመቱ ዱኒያ በይነል ፈኺዘይን ››
በፍቅርሽ ሰክሬ በጆሮሽ የምለው
ለካስ ጀነት ያለው በሃቂቃ ሚስቴ ጭኖች መካከል ነው !!

Wednesday, March 13, 2019

የዘርአያቆብ ፍልስፍና ሃቲት

ፈላስፋው ዘርአያቆብ "እስራኤላውያን በእግዝአብሄር የተመረጡ ሕዝቦች ናቸው የሚለውን" የሙሴን መሠረታዊ አስተምህሮን አይስማማበትም ። መናፍቁ እና ጠርጣራው #Heretic Philosopher ፈላስፋው ዘርአያቆብ የሙሴን መሰረታዊ አስተምህሮቶችን ይጠራጠራል ።

ዘርአያቆብ እግዝአብሄር ለአህዛብ ሚስጥሩን መችልም አይገልጥላቸውም የሚለውን በሙሴ የተጻፈውን የመዝሙረ ዳዊትን ጥቅሥ አይስማማበትም ። ይሁን እንጂ ጸሀፊው የካቶሊክ ቄስ ከሆነ ለአይሁድ ባላቸው ጥላቻን ማንጸባረቁ ሊሆን ይችላል ።

በመዠመር ያዘርአያቆብ ማነው ? ትውልዱስ እንፍራንዜ (ጎንደሬ) ወይስ የአክሱሜ ? ወይስ የካቶሊክ ካህን ?  ። ይሄ መታወቅ አለበት። ማንነቱን ማወቅ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ጸሐፊው ኢትዮጲያዊ ላይሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ ስላለ ነው። 

ፕሮፌሰር ጌታቸው በጻፉት መጽሀፍ እንፍራንዜ ሲያደርጉት ሌሎች በተረጎሙት ደግሞ በወቅቱ በነበረው በካቶሊኮችና ኦርቶዶክሶች የሃይማኖት ውዝግብ ከአክሱም በሃይማኖት ክፍፍል ምክንያት ሸሽቶ ወደ ጎንደር የተሰደደ ትግሬ ያደርጉታል ።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለ ዘርአያቆ ትውልድ ስፍራ የትውልድ ስፍራ የራሱን ሃሳብ ሲገልጽ ፦

" የዘርአ ያእቆብ የዓለም ስሙ ‹ወርቄ› ነው፡፡ ‹ወርቄ፣ ብርቄ፣ ድንቄ› የሚሉ የስም አወጣጦች በአማራው አካባቢ እንጂ በአኩስም አካባቢ የተለመዱ ስሞች አይደሉም፡፡ ኡርቢኖ በደብረ ታቦር አካባቢ ሲኖር የሰማውን ስም መሆን አለበት የተጠቀመው፡፡" ይላል በዳንኤል ክብረት እይታ ዘርአያቆብ የጎንደሬ ስም ነው የተጠቀመው ።

ዲያቆን ዳንኤል ሲጠቅሥ " እንዲያውም ‹እንደዚህ ከሀገር ወደ ሀገር ስሄድ ወደ አኩስም እመለስ ዘንደ አልፈቀድኩም፤ የካህኖቿን ክፋት ዐውቅ ነበርና›(ያሬድ፣25) ይላል፡፡ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት እይታ "ዘርአ ያእቆብ በምንም መልኩ አኩስማዊ አይደለም ፡፡ አክሱምን በዚህ መጠን የሚጠላ አኩስማዊም ሊኖር አይችልም፡ በምክንያት የሚያምን ሰው ለዚህ ጥላቻው በቂ ምክንያት አላቀረበም፡፡ ዋና ማዕከላቸውን በአድዋ አድርገው ለነበሩት ካቶሊካውያን አኩስማውያን ቦታ ሊሰጧቸው አልፈቀዱም ነበር፡፡ የካቶሊክ ሚስዮናውያን መሠረት ሊጥሉ የፈለጉት በአኩስም ነበር፡፡ነገር ግን የአኩስም ካህናት አልፈቀዱም፡፡ይህንን ጥላቻ ነው ኡርቢኖ ያንጸባረቀው፡፡" ይላል።

ሌላው አብዛኛው ዘርአያቆብ እሚጠቅሳቸው ጥቅሦች ከመዝሙረ ዳዊት የተወሰዱ መሆናቸው ሌሎቹን የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎችን በጥልቀት ያውቃል ወይ ሊያስብል ይችላል።

ዘርአ ያእቆብ ሙሴን ሲወቅስ ‹ወሙሴሰ ይቤ ኩሉ ሩካቤ ርኩስ ውእቱ - ሙሴም ሩካቤ ሁሉ ርኩስ ነው አለ› ይላል(215,9a)፡፡ ነቢዩ ሙሴ ራሱ በጋብቻ ጸንቶ የኖረ ነቢይ ነው፡፡ በምን መልኩ ይህንን ሊል አይችልም፡፡ ሙሴ ይህንን ነገር ለመናገሩ መጽሐፋዊም ትውፊታዊም ማስረጃ የለም፡፡ ዘርአ ያዕቆብ ዳዊት ከማወቅ (እርሱንም ሲደበቅ ደጋግሞ በማንበቡ)፣ ሐዲስን ከማንበብ የዘለለ የብሉይ ትምህርት የለውም ይላል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡፡

ከሙሴ ይልቅ ግን ሐዋርያው ጳውሎስን በዚህ ጉዳይ ቢጠቅሥ ይመረጥ ነበረ ልምን ቢባል ጳውሎስ ከቻላችሁ እንደኔ አታግቡ ማለቱ በመልእክቶቹ የሚታወቅ ሲሆን ሐዋርያውም ራሱ ግን በዚህ ሊወቀስ የሚችል አይደለም ይህን ያለው ራሳቸውን በቅድስና ለሚለዩቱ ቅዱሳን ነው ፥ ምክንያቱም እርሱም ቢሆንም ግን የጋብቻን ክቡርነትንና የትውልድ መቀጠልን ነው ያስተማረው። ጌታ እየሱስም ጭምር "አንድ ሴት ለአንድ ወንድ" ብሎ ነው ያስተማረው። ጋብቻ ከሌለ ትውልድ ሊቀጥል እንደማይችል በጥንት ዘመንም የሚታወቅ ቀላል እውነት መሆኑ ይታወቃል ። ስለዚህ ዘርአያቆብ የቱ ቦታ ላይ ነው ሙሴ ሩካቤ ሁሉ እርኩስ እንዳለ ምንጩን አይጠቅሥም። በሙሴ ግዜ እንደውም እስራኤላውያን ህዝቡም ሆነ ነገስታቱ በርካታ ሚስቶችን ያገቡ ነበረ። ሙሴ ለነገስታቶች በሰጠው ምክር "ንጉሡ ሚስቶችን አያብዛ " የሚል ነው። በሃዲስ ኪዳን በአንድ ስለመወሰን ከመደንገጉ በስተቀር በብሉይ ዘመን ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እንደሚቻል ከብሉይ መጽፍሐት መረዳት ይቻላል ። በሙሴ ህግ የሚመሩት የእስራኤል ነገስታት ከአንድ በላይ ሚስቶችን አግብተው በርካታ ልጆችን እንደወለዱ መጽሐፈ ነገስት ያትታል ። ለምሳሌ።ንጉስ ዳትዊንስ የንጉስ ሰለሞን ልጅ ኢዮርብአም በርካታ ሚስቶች እንደነበሩዋቸው ማንበብ ይቻላል ።

ዘርአያቆብ መዝሙረ ዳዊት ላይ ብቻ ትኩረትን ስላደረገ ከብሔረ ኦሪት አሟልቶ መጥቀስ አልቻለም፡፡ የካቶሊክ ሚስዮናውያን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ቤተ ክርስቲያኒቱን የከሰሱበት አንዱ ክስ ‹ኦሪታዊት ናት› የሚል ነው፡፡ ለእነርሱ በንጉሥ ገላውዴዎስ ዘመን የነበሩት ሊቃውንት መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ዘርአ ያእቆብ የእነርሱ ወገን ካልሆነ በቀር ሙሴን በዚህ መልኩ አይጠቅሰውም፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዘርአያቂብ ማለት ኡርቢኖ የተባለ የካቶሊክ መነኩሴ ነው።

ሌላው ዘርአያቆብ ስለ ንጉሥ ፋሲለደስ ያለው አመለካከት ነው ። "በዐመሉና በደም ማፍሰስ ጸና፣በጎ ላደረጉለት፣ ቤተ መንግሥትንና ያማሩ ቤቶችን ለሠሩለት፣ በጥበብ ነገር ሁሉም መንግሥቱን ላሣመሩለት ፈረንጆችን ጠላቸው› ይላል " ፋሲለደስ ቤቶችን ይወርስ ነበረ ሴቶችን አብሮአቸው ካደረ በሁዋላ ይገድላቸው ነበረ ሲል ንጉስ ፋሲልን ግፈኛ አድርጎ ያቀርበዋል።

በራሱ አንደበት እንዲህ ይላል " ፋሲለደስ ክፉን ነገር የሚሠራ ሆነ፡፡ ሰዎችን ያለ ፍርድ ይገድል ነበር፡፡ አመንዝራነትም ያበዛ ነበር፡፡ ሴቶችንም ከእነርሱ ጋር ካመነዘረ በኋላ ይገድላቸው ነበር፡፡ ዐመጻን የሚያደርጉ ሠራዊትንም ልኮ የድኾችን ሀገሮችና ቤቶች እንዲቀሙ ያደርግ ነበር፡፡

እግዚአብሔር ለክፉዎች ሕዝቦች ክፉውን ንጉሥ ሰጥቷቸው ነበርና፡፡ ስለ ንጉሡና ስለ ሕዝቡም ኃጢአት ረሀብና መቅሰፍት መጣ፡፡ ከረሃብ በኋላም ቸነፈር ሆነ፡፡ ብዙዎችም ሞቱ፡፡ ሌሎችም ፈሩ፡፡" ዘርአያቆብ በወቅቱ ለነበረው ማህበረሰብ በጎ አመለካከት አልነበረውም የህዝቡ ክፋት ፋሲለደስ የተባለ ክፉ ንጉስ እንደሰጣቸው አፍርጎ ነው የተረዳው።

ይሁንና ግን ፋሲለደስ በአጼ ሱስንዮስ ዘመን የነበረውን የሃይማኖት ውዝግብን ያስቆመና ፤ግራኝ አህመድን ወረራ ለመመከት መጥተው ነገር ግን ከግራኝ ሽንፈት በሁዋላ የኦርቶዶክስ እምነትን ወደ ካቶሊክ ለመለወጥ የሞከሩትን ፖርቱጋሎችን ያስወጣ ነው።

china port

Marine Gen. Thomas Waldhauser, the top U.S. military officer for Africa, told a congressional hearing last year that the U.S. military could face significant consequences if China took the port in Djibouti.

Tuesday, March 12, 2019

ከተማና ድንኩዋን የትም ይተከላል

ህንድ፥ ግብጽ፥ ሳኡዲ ፥እንዲሁም ቻይና አዳዲስ ከተሞችን እየገነቡ ይገኛሉ ። ሳኡዲ ከአፍሪካ ጋር በድልድይ የሚገናኝ ቀይ ባህር ጠረፍ ላይ ከጆርዳንና ግብጽ ቅርበት ባለው ስፍራ ግዙፍ ከተማን እየገነባች ነው።

ቻይና እየገነባች ያለችው ከተማ የ #USA ውን ኒው ዮርክ ሲቲን በግዝፈት የሚያስንቅ ሲሆን ከሆንግ ኮንግ ጋር በትላልቅ ድልድዮች እያገናኘችው ነው።

ጎረቤት ኬንያ እንኩዋን 6 የተለያዩ ግልጋሎት እሚውሉ ከተሞችን ልትገነባ ነው።  ለስፖርት ፥ ለቴክኖሎጂ ፥ ለህክምና ፥ ለመዝናኛ ...ወዘተ እሚውሉ ሲሆን በርካታ የዓለማችን ሀገርስት አዳዲስ ከተሞችን ከስክራች #Scratch እየገነቡ ይገኛሉ። ህንድ 12 አዳዲስ ትላልቅ ከተሞችን እየገነባች ትገኛለች ። ቻይናም ኒው ዮርክ ሲቲን እሚያስንቅ ከሆንግ ኮንግ ጋር እሚገናኝ ግዙፍ ከተማን እየገነባች ትገኛለች ።

እንዲሁም ቱጃሩ ቢል ጌትስ በአሪዞና በረሐ ውስጥ የቴክኖሎጂ የዘመነ ከተማን እያስገነባ ነው። ይህ ከተማ ያለ ሹፌር እሚነዱ መኪኖችን በአውራ ጎዳናዎቹ ላይ ይሽከረከራሉ። ይህ ከተማ ተሰርቶ ሲያልቅ 182 ሺህ ህዝብ መኖርያ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል .።

አሁን በአለም ዙሪያ እየተቆረቆሩ ያሉ ከተሞች በብዙ ነገራቸው ዘመናዊና የተራቀቁ ናቸው።

እኛ ግን አዲስ ከመፍጠር ይልቅ፥ የተፈጠረው ላይ ስለምናተኩር ነው እንጂ "ከተማ እና ድንኩዋን የትም ይተከላል" የሚለው ይትበሀል ረስተናል።

Monday, March 4, 2019

የዘርአያቆብ ፍልስፍና ሃቲት

ፈላስፋው ዘርአያቆብ "እስራኤላውያን በእግዝአብሄር የተመረጡ ሕዝቦች ናቸው የሚለውን" የሙሴን መሠረታዊ አስተምህሮን አይስማማበትም ። መናፍቁ እና ጠርጣራው #Heretic Philosopher ፈላስፋው ዘርአያቆብ የሙሴን መሰረታዊ አስተምህሮቶችን ይጠራጠራል ።

ዘርአያቆብ እግዝአብሄር ለአህዛብ ሚስጥሩን መችልም አይገልጥላቸውም የሚለውን በሙሴ የተጻፈውን የመዝሙረ ዳዊትን ጥቅሥ አይስማማበትም ። ይሁን እንጂ ጸሀፊው የካቶሊክ ቄስ ከሆነ ለአይሁድ ባላቸው ጥላቻን ማንጸባረቁ ሊሆን ይችላል ።

በመዠመር ያዘርአያቆብ ማነው ? ትውልዱስ እንፍራንዜ (ጎንደሬ) ወይስ የአክሱሜ ? ወይስ የካቶሊክ ካህን ?  ። ይሄ መታወቅ አለበት። ማንነቱን ማወቅ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ጸሐፊው ኢትዮጲያዊ ላይሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ ስላለ ነው። 

ፕሮፌሰር ጌታቸው በጻፉት መጽሀፍ እንፍራንዜ ሲያደርጉት ሌሎች በተረጎሙት ደግሞ በወቅቱ በነበረው በካቶሊኮችና ኦርቶዶክሶች የሃይማኖት ውዝግብ ከአክሱም በሃይማኖት ክፍፍል ምክንያት ሸሽቶ ወደ ጎንደር የተሰደደ ትግሬ ያደርጉታል ።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለ ዘርአያቆ ትውልድ ስፍራ የትውልድ ስፍራ የራሱን ሃሳብ ሲገልጽ ፦

" የዘርአ ያእቆብ የዓለም ስሙ ‹ወርቄ› ነው፡፡ ‹ወርቄ፣ ብርቄ፣ ድንቄ› የሚሉ የስም አወጣጦች በአማራው አካባቢ እንጂ በአኩስም አካባቢ የተለመዱ ስሞች አይደሉም፡፡ ኡርቢኖ በደብረ ታቦር አካባቢ ሲኖር የሰማውን ስም መሆን አለበት የተጠቀመው፡፡" ይላል በዳንኤል ክብረት እይታ ዘርአያቆብ የጎንደሬ ስም ነው የተጠቀመው ።

ዲያቆን ዳንኤል ሲጠቅሥ " እንዲያውም ‹እንደዚህ ከሀገር ወደ ሀገር ስሄድ ወደ አኩስም እመለስ ዘንደ አልፈቀድኩም፤ የካህኖቿን ክፋት ዐውቅ ነበርና›(ያሬድ፣25) ይላል፡፡ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት እይታ "ዘርአ ያእቆብ በምንም መልኩ አኩስማዊ አይደለም ፡፡ አክሱምን በዚህ መጠን የሚጠላ አኩስማዊም ሊኖር አይችልም፡ በምክንያት የሚያምን ሰው ለዚህ ጥላቻው በቂ ምክንያት አላቀረበም፡፡ ዋና ማዕከላቸውን በአድዋ አድርገው ለነበሩት ካቶሊካውያን አኩስማውያን ቦታ ሊሰጧቸው አልፈቀዱም ነበር፡፡ የካቶሊክ ሚስዮናውያን መሠረት ሊጥሉ የፈለጉት በአኩስም ነበር፡፡ነገር ግን የአኩስም ካህናት አልፈቀዱም፡፡ይህንን ጥላቻ ነው ኡርቢኖ ያንጸባረቀው፡፡" ይላል።

ሌላው አብዛኛው ዘርአያቆብ እሚጠቅሳቸው ጥቅሦች ከመዝሙረ ዳዊት የተወሰዱ መሆናቸው ሌሎቹን የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎችን በጥልቀት ያውቃል ወይ ሊያስብል ይችላል።

ዘርአ ያእቆብ ሙሴን ሲወቅስ ‹ወሙሴሰ ይቤ ኩሉ ሩካቤ ርኩስ ውእቱ - ሙሴም ሩካቤ ሁሉ ርኩስ ነው አለ› ይላል(215,9a)፡፡ ነቢዩ ሙሴ ራሱ በጋብቻ ጸንቶ የኖረ ነቢይ ነው፡፡ በምን መልኩ ይህንን ሊል አይችልም፡፡ ሙሴ ይህንን ነገር ለመናገሩ መጽሐፋዊም ትውፊታዊም ማስረጃ የለም፡፡ ዘርአ ያዕቆብ ዳዊት ከማወቅ (እርሱንም ሲደበቅ ደጋግሞ በማንበቡ)፣ ሐዲስን ከማንበብ የዘለለ የብሉይ ትምህርት የለውም ይላል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡፡

ከሙሴ ይልቅ ግን ሐዋርያው ጳውሎስን በዚህ ጉዳይ ቢጠቅሥ ይመረጥ ነበረ ልምን ቢባል ጳውሎስ ከቻላችሁ እንደኔ አታግቡ ማለቱ በመልእክቶቹ የሚታወቅ ሲሆን ሐዋርያውም ራሱ ግን በዚህ ሊወቀስ የሚችል አይደለም ይህን ያለው ራሳቸውን በቅድስና ለሚለዩቱ ቅዱሳን ነው ፥ ምክንያቱም እርሱም ቢሆንም ግን የጋብቻን ክቡርነትንና የትውልድ መቀጠልን ነው ያስተማረው። ጌታ እየሱስም ጭምር "አንድ ሴት ለአንድ ወንድ" ብሎ ነው ያስተማረው። ጋብቻ ከሌለ ትውልድ ሊቀጥል እንደማይችል በጥንት ዘመንም የሚታወቅ ቀላል እውነት መሆኑ ይታወቃል ። ስለዚህ ዘርአያቆብ የቱ ቦታ ላይ ነው ሙሴ ሩካቤ ሁሉ እርኩስ እንዳለ ምንጩን አይጠቅሥም። በሙሴ ግዜ እንደውም እስራኤላውያን ህዝቡም ሆነ ነገስታቱ በርካታ ሚስቶችን ያገቡ ነበረ። ሙሴ ለነገስታቶች በሰጠው ምክር "ንጉሡ ሚስቶችን አያብዛ " የሚል ነው። በሃዲስ ኪዳን በአንድ ስለመወሰን ከመደንገጉ በስተቀር በብሉይ ዘመን ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እንደሚቻል ከብሉይ መጽፍሐት መረዳት ይቻላል ። በሙሴ ህግ የሚመሩት የእስራኤል ነገስታት ከአንድ በላይ ሚስቶችን አግብተው በርካታ ልጆችን እንደወለዱ መጽሐፈ ነገስት ያትታል ። ለምሳሌ።ንጉስ ዳትዊንስ የንጉስ ሰለሞን ልጅ ኢዮርብአም በርካታ ሚስቶች እንደነበሩዋቸው ማንበብ ይቻላል ።

ዘርአያቆብ መዝሙረ ዳዊት ላይ ብቻ ትኩረትን ስላደረገ ከብሔረ ኦሪት አሟልቶ መጥቀስ አልቻለም፡፡ የካቶሊክ ሚስዮናውያን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ቤተ ክርስቲያኒቱን የከሰሱበት አንዱ ክስ ‹ኦሪታዊት ናት› የሚል ነው፡፡ ለእነርሱ በንጉሥ ገላውዴዎስ ዘመን የነበሩት ሊቃውንት መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ዘርአ ያእቆብ የእነርሱ ወገን ካልሆነ በቀር ሙሴን በዚህ መልኩ አይጠቅሰውም፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዘርአያቂብ ማለት ኡርቢኖ የተባለ የካቶሊክ መነኩሴ ነው።

ሌላው ዘርአያቆብ ስለ ንጉሥ ፋሲለደስ ያለው አመለካከት ነው ። "በዐመሉና በደም ማፍሰስ ጸና፣በጎ ላደረጉለት፣ ቤተ መንግሥትንና ያማሩ ቤቶችን ለሠሩለት፣ በጥበብ ነገር ሁሉም መንግሥቱን ላሣመሩለት ፈረንጆችን ጠላቸው› ይላል " ፋሲለደስ ቤቶችን ይወርስ ነበረ ሴቶችን አብሮአቸው ካደረ በሁዋላ ይገድላቸው ነበረ ሲል ንጉስ ፋሲልን ግፈኛ አድርጎ ያቀርበዋል።

በራሱ አንደበት እንዲህ ይላል " ፋሲለደስ ክፉን ነገር የሚሠራ ሆነ፡፡ ሰዎችን ያለ ፍርድ ይገድል ነበር፡፡ አመንዝራነትም ያበዛ ነበር፡፡ ሴቶችንም ከእነርሱ ጋር ካመነዘረ በኋላ ይገድላቸው ነበር፡፡ ዐመጻን የሚያደርጉ ሠራዊትንም ልኮ የድኾችን ሀገሮችና ቤቶች እንዲቀሙ ያደርግ ነበር፡፡

እግዚአብሔር ለክፉዎች ሕዝቦች ክፉውን ንጉሥ ሰጥቷቸው ነበርና፡፡ ስለ ንጉሡና ስለ ሕዝቡም ኃጢአት ረሀብና መቅሰፍት መጣ፡፡ ከረሃብ በኋላም ቸነፈር ሆነ፡፡ ብዙዎችም ሞቱ፡፡ ሌሎችም ፈሩ፡፡" ዘርአያቆብ በወቅቱ ለነበረው ማህበረሰብ በጎ አመለካከት አልነበረውም የህዝቡ ክፋት ፋሲለደስ የተባለ ክፉ ንጉስ እንደሰጣቸው አፍርጎ ነው የተረዳው።

ይሁንና ግን ፋሲለደስ በአጼ ሱስንዮስ ዘመን የነበረውን የሃይማኖት ውዝግብን ያስቆመና ፤ግራኝ አህመድን ወረራ ለመመከት መጥተው ነገር ግን ከግራኝ ሽንፈት በሁዋላ የኦርቶዶክስ እምነትን ወደ ካቶሊክ ለመለወጥ የሞከሩትን ፖርቱጋሎችን ያስወጣ ነው።

Ethiopia Debt Sustainability

የገንዘብ ስርአት ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል። ከለውጡ በፊት በኢትዮፒያ በኢትዮፒያ ልማት ባንክ በኩል ብድር ቢመቻችም ብድሩ ሳይመለስ #npl ማለትም #የማይመለሱ ብድሮች ይፋዊ በሆነው መረጃ #Non_Performing_Loans #NPL ወደ 40 በመቶ ከፍ ቢልም እስከ 70 በመቶ ይደርሳል በዘርፉ ባለሙያዎች ግምት።ለዚህ ምሳሌ እሚሆነው #Aika_Addis የተባለው የ#ቱርክ #ኩባንያ #አይካ_አዲስ በ8 ቢሊየን እዳ እሳቅፈው ሲሄዱ 29 ሚሊየን ዶላር ማሽን ቢያመጣም 150 ሚሊየን ዶላር እንዳመጣ ተደርጎ ብድር ከልማት ባንክ ተለቆለታል ። ይህም።ልማት ባንኩን አክስሮአል ።
አሁን ግን በዚህ አይነት መንገድ በተለይም ግብርና ዘርፍ እንሰማራለን ብለው ከልማት ባንክ ብድር ወስደው ያልከፈሉ በህግ እንደሚጠየቁ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ጠቁመዋል ።

#small & medium eneterprisrs አነስተኛና መካከለኛ ተቁዋማት አበዳሪ
ያጡት በዚህ ምክንያት ነው ።
እሚያበድራቸው የለም ፥ ወጣቱ ስራ ያጣው በዚህ ምክንያት ነው።
አሁን ያለው ለውጥ መደገፍ የምንችለው በኢኮኖሚ ስልት ነው ስራ እድል ለወጣቱ መፈጠር እና ኤክስፖርት #import_Export_Trade #ወጪና_ገቢ_ንግድ መንቀሳቀስ አለበት ፥ ለዚህ ደግሞ መንግስት #ፕላን ማውጣት አለበት። የሀገሪቱ የውጭ ብድርን ጫና የመሸከም አቅም #Debt Sustainability መፈተሽ አለበት።  ከአቅም በላይ ብድርና ክፍያ የውጭ ምንዛሪውን ጠራርጎ እየወሰደው ነው። ሃገሪቱ ብድር ለመክፈል አጠራጣሪ ሁኔታ ውስጥ ልትገባ እንደነበረ ወይም #Default ልታደርግ እንደነበረ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ጠቆም አድርገዋል በቅርቡ በሰጡት ቃለ ምልልስ።

Sunday, March 3, 2019

Zar’a Ya’aqob Ethiopian philosopher

Zar’a Ya’aqob is not Ethiopian or there was no such philosopher called Zar’a Ya’aqob. The one known as Zara Ya’aqob was a pseudonym used by a 19th Century Freemason European — who penned the treatises as better known as the Hatetas.

Thursday, February 28, 2019

ህገ_መንግስት ኢንሹራንስ ሰምተው ያውቃሉ

ሕገ መንግሥት ተርጓሚው አካል ከዚህ መሠረታዊ የፍትሕና ርትዕ መርህ በመነሳት፣ ለየትኛውም ወገን ባለማድላት ተጥሰዋል ተብሎ የቀረበለትን የሕገ መንግሥት መርሆዎች ለማፅናትና ለማስከበር ገለልተኛ መሆን ይገባዋል፤ በዚህ መርህ መሠረትም ተርጓሚው አካል እጅግ ወሳኝ ሚና የሚጫወት መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊው ነው፡፡

ሌላው ሕገ መንግሥትን ከመተርጎም አንፃር አዲስ ክስተት ወይም ጽንሰ ሐሳብ የሆነው የሕገ መንግሥት ኢንሹራንስ የሚለውንም አስፈላጊነትን ማንሳት ያሻል፡፡ ሕገ መንግሥት ተርጓሚው አካል በተለይ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት በሚከተሉ አገሮች ውስጥ፣ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ዋስትና የሚሰጥ አካል እንደሚሆን ይታወቃል።፡

‹‹የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት የሚከተል የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፓርቲዎች ይቀያየራሉ፡፡ ስለሆነም አንድ ፓርቲ ከሥልጣን ከወረደ በኋላ ምንም አድልኦ በሌለበት ሁኔታ በሚቀጥለው ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳና ዘመቻ አድርጎ ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ዋስትና ያስፈልገዋል፡፡

አማርኛ የAU የስራ ቁዋንቁዋ ሆነ

የአውሮፓ ህብረት #EU ከአስር በላይ የስራ ቁዋንቁዋዎች ሲኖሩት፥ የአፍሪካ ህብረትም አማርኛ ከአረብኛ ከእንግሊዝኛ ከስዋሂሊና ከፖርቱጋል እና ከፈረንሳይኛ ቀጥሎ 6ኛ የስራ ቁዋንቁዋ ይሆን ዘንድ አማርኛ ቁዋንቁዋን ሰይሞአል።  ከአስሩ አፍሪካውያን አንዱ ኢትዮጲያዊ ሲሆን የህዝብ ብዛቱዋ ከአፍሪካ 2ኛ የሆነ ህዝብ መግባቢያ ቁዋንቁዋ የሆነው አማርኛ ቁዋንቁዋ የAU one of the official languages of AU መሆኑ አኩሪ ሲሆን የጠ/ሚሩ ድል ነው።
ይህም ለበርካታ ኢትዮጲያውያን የስራ እድልን ሲፈጥር የኢትዮጲያውያን ደራሲዎች በአማርኛ ብቻ ነው እሚጽፉት በአውሮፓውያን ቁዋንቁዋ እንደ ኬንያ ጋና ወይም እንደ ናይጄሪያና ደቡብ አፍሪካ ደራስያን  በእንግሊዝኛ ቁዋንቁዋ ቢጽፉ ኖሮ አለም ኣቀፍ እውቅናን ይጎናጸፉ ነበር ለሚለው ምላሽን የሚሰጥ ነው። ምክንያቱም በርካታ ኣፍሪካውያን የአማርኛ ቁዋንቁዋን እሚማሩ ከሆነ የኢትዮጲያ ቁዋንቁዋ ፥ ስነ-ጽሁፍና ባህል ሰፊ የመተዋወቅ እድልን ያገኛክ።

Wednesday, February 6, 2019

trade war USA Vs China

የአሜሪካና የቻይና የንግድ ጦርነት #Trade war ወደ ገንዘብ ምንዛሪ ጦርነት # Currency war ይቀየራል ተብሎ ተሰግቶአል። ይህ ደግሞ የሌላውን አገር ሆነ ብሎ# የገንዘብ ምንዛሪን ከፍና ዝቅ እንዲል በማድረግ የዝያን ሃገር ገንዘብ #ማክሰርና ዋጋ ማሳጣት ማለት ሲሆን ይህ በትራምፕ የተቀሰቀሰው የንግድ ጦርነት አለምን በተለይም ታዳጊ ሃገራትን ክፉኛ ሊጎዳ ይችላል። እልኽኛው #Stubbourn ግትሩ # ፕሬዝደንት ትራምፕ ገና ከዚህ የባሰ #ማዕቀብን #በቻይና ላይ ለመጣል እየተዘጋጁ ነው።
አሜሪካ ከዚህ ቀደም ባላንጣ ያለቻቸውን ቱርክንና ሩስያን ገንዘብ ምንዛሪን ዋጋ በማሳጣት የስራ አጥ Unemployment rate #ቁጥሩ እንዲጨምር ፥ #ኤክስፖርት እንዲቀንስና ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስን እሚያስከትልና መንግስታትን እሚያናጋ ነው። ቻይናም የስራ አጥ ቁጥሩዋ እየወነሰ ሲገኝ ይህን የንግድ #ጦርነትን ተከትሎ ለመጀመርያ ግዜ #በ30 አመታት ውስጥ የኢኮኖሚ #እድገትዋ #ቀንሶአል።

Sunday, January 27, 2019

ፋሪድ ዘካራይ ማነው ?

#ፋሪድ_ዘካራይ ማነው ?
በአለም ኢኮኖሚ ፎረም የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም #Word_Economic_Forum
ላይ ተገኝቶ ከጠ/ሚር ዶ/አብይ አህመድ ጋር ሲነጋገር በዚህ ፎቶ የምናየው ጋዜጠኛና የፖለቲካ ሳይንቲስት ሲሆን# ፓኪስታን አሜሪካዊ ሲሆን በ#newsweek መጽሄት ላይ ቁዋሚ #ኣምደኛ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን የCNN tv #GPS የተሰኘ ስለ አለማችን ወቅታዊ ሁኔታ የተለያዩ መሪዎችን የሚያወያይ ዝግጅት አዘጋጅና አቅራቢ #host ሆኖ ይሰራል። በርካታ መጽሐፍትን የጻፈ ሢሆን በፖለቲካ ትንተና ክህሎቱ የተመሰከረለት ነው። የአለማችን ታላላቅ መሪዎች በእርሱ ኢንተርቪው #interview ላይ መገኘት አጥብቀው ይፈልጉታል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፥ የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም #Word_Economic_Forum
የ2020 ስብሰባ በኢትዮጲያ እንዲካሄድ ተወስኖአል። 

Monday, January 21, 2019

የነዳጅ እጥረትና መፍትሄው

የሰሞኑ የነዳጅ መጥፋት የነዳጅ አከፋፋዮች የትርፍ ህዳግ (#profit_margin ) ሲበዛ ማነሱ ዋነኛ ምክንያት ሁኖ ተጠቅሶአል። ይህ የትርፍ ህዳግ ከፍ ይበል ተብሎ በተደጋጋሚ ተጠይቆ የነበረ ቢሆንም ምላሹ ዘግይቶአል። የዶላር ምንዛሬ ሲጨምር የነዳጅ ዋጋ ግን አልጨመረም በአቶ ሃይለማርያም ግዜ ። ይህም በሌሎች ሸቀጦችና ኣገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ወዲያውኑ #Instantly የኑሮ ውድነትን ያስከትላል ይህ ደግሞ በፈንታው የፖለቲካ ኣለመረጋጋትን ሊያስከትል ይችላል። በኣሁኑ ወቅት በሱዳንና ዚምባብዌ የሚታይርው ህዝባዊ ኣመጽ ሰበቡ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ ነው። ነዳጅ ማደያዎች ማደያውን ህንጻ እየገነቡበት ነው ተብሎአል ትርፉ በጣም ትንሽ ስለሆነና አዋጭ ሥላልሆነ ህንጻ ሰርቶ ማከራየትን የቀለለ ሁኖ ኣግኝተውታል። ከዚህም።በላይ ደግሞ ነዳጅ አከፋፋዮችም በዱቤ የወሰዱትን በቢሊየን ዱቤ እየከፈሉ አለመሆኑ ታውቆአል።

የኣጼ።ምንሊክና የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ታሪክ

#አጼ #(እምዬ) #ምኒልክ እና ፊት አውራሪ #ሀብተ_ጊዮርጊስ ዲነግዴ እጅግ የልብ ወዳጅ ሲሆኑ እንዲሁም ለዘመናዊቱዋ #ኢትዮጵያ ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረጉም ናቸው።
#እምዬ ምኒልክ በአንዱ ወገን እምዬ የሚል የእናትነት ስያሜ #ሲሰጣቸው በሌላው ሲቀጥል ደግሞ የነጭ ወራሪን ከባህረ ነጋሽ (ኤርትራ) ጨርሰው ማስወጣት ነበረባቸው ይላሉ። #አጼ ምኒሊክ #አባታቸው# ከሞቱ ቡኃላ #አጼ ቴዎድሮስ #ተማርከው በ11 ዓመታቸው ተወስደው በቴዎድሮስ ቤተ መንግስት ለተወሰነ ዓመታት #ከቆዩ ቡኃላ #ሸሽተው ወደ #ሸዋ ገብተው በአባታቸው #ሃይለ #መለኮት #ዙፋን ነግሰዋል። ሙሉ ለሙሉ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ከጀመሩ ቡኃላም #ለዘመናዊቱዋ #ኢትዮጵያ መሠረት ጥለዋል ። #የነጭ ወራሪንም #ዋጋውን ሰጥተው አባረዉታል። 
#ሀብተ ጊዮርጊስ #ዲነግዴ #በጦረኝነታቸው ወደር #ከሌላቸው ወድ ኢትዮጵያዊ ጀግኞች መካከል ናቸው። #በአድዋ #የጦርነት ውሎ በርከት ያለ ሰራዊት ይዘው #ጉልህ #የጀግንነት ተጋድሎ አድርገዋል።# ሀብተ ጊዮርጊስ በፍርድ አዋቂነታቸው ስማቸውም #ሀብቴ አባ መላ ይሉዋቸዋል። አባ #መላ #አጼ (እምዬ) ምኒልክ ካረፉ ቡኃላ የስልጣን #ሽኩቻ እንዳይነሳ በማለት አገሪቱዋ በማረጋጋት #ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

የአጼው እና የአባ መላ ሞት አስገራሚ የሚያደርግው #ነገር ቢኖር #እምዬ በ1906ዓም ታህሳስ 03 ቀን #እለተ አርብ በስድሳ #ዘጠኝ (69) #አመታቸው አረፉ ።# እምዬ ባረፉ በ13ኛው ዓመት #ታህሳስ 03 /1919ዓም# ሀብተ #ጊዮርጊስ #ዲነግዴ #አረፉ ።
ሌላው ደግሞ #ሞታቸውን# አስገራሚ የሚያደርገው #ሁለቱም #በዕለተ #አርብ ማረፋቸው ነው። አባ መላ ሞቴን# በጌታዬ በምኒልክ ቀን አድርግልኝ ብለው #መጸለያቸውና #ያሉትም መሆኑ #አስዳናቂ ነው።

Sunday, January 20, 2019

የነዳጅ እጥረትና መፍትሄው

የሰሞኑ የነዳጅ መጥፋት የነዳጅ አከፋፋዮች የትርፍ ህዳግ (#profit_margin ) ሲበዛ ማነሱ ዋነኛ ምክንያት ሁኖ ተጠቅሶአል። ይህ የትርፍ ህዳግ ከፍ ይበል ተብሎ በተደጋጋሚ ተጠይቆ የነበረ ቢሆንም ምላሹ ዘግይቶአል። የዶላር ምንዛሬ ሲጨምር የነዳጅ ዋጋ ግን አልጨመረም በአቶ ሃይለማርያም ግዜ ። ይህም በሌሎች ሸቀጦችና ኣገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ወዲያውኑ #Instantly የኑሮ ውድነትን ያስከትላል ይህ ደግሞ በፈንታው የፖለቲካ ኣለመረጋጋትን ሊያስከትል ይችላል። በኣሁኑ ወቅት በሱዳንና ዚምባብዌ የሚታይርው ህዝባዊ ኣመጽ ሰበቡ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ ነው። ነዳጅ ማደያዎች ማደያውን ህንጻ እየገነቡበት ነው ተብሎአል ትርፉ በጣም ትንሽ ስለሆነና አዋጭ ሥላልሆነ ህንጻ ሰርቶ ማከራየትን የቀለለ ሁኖ ኣግኝተውታል። ከዚህም።በላይ ደግሞ ነዳጅ አከፋፋዮችም በዱቤ የወሰዱትን በቢሊየን ዱቤ እየከፈሉ አለመሆኑ ታውቆአል።

Friday, January 11, 2019

ጥቂት ስለ ቡልጋ

ጥቂት ስለ ቡልጋ ቡልጋ ሰሜን ሸዋ ከሚገኙ ታሪካዊ ጠቅላይ ግዛቶች አንዱ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ፣ የመካከለኛው ዘመን አምሓራ ነገሥታት ይነግሡበት ከነበረው ከተጉለት ጋር እጅግ የተሳሰረ በመሆኑ አብሮ ተጉለትና ቡልጋ ሲባል ይታወቃል። መልክዓምድራዊ ገጽታው ወይና ደጋ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ዋንኛ ከሚባሉ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ቦታዎች አንዱ ነው። ታላላቅ ቅዱሳን የወጡበትም ቦታ ነው። ለምሳሌ አፄ ይኩኖ አምላክን ያነገሡት ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የቡልጋ ተወላጆች ነበሩ። የአፄ ምኒልክ የአማራ ጦር ብዙው ከተጉለትና ቡልጋ እንደነበር አንዳንድ የታሪክ ጽሐፊያን ጽፈዋል። የምኒልክ ምሽግና የጦር ግምጃ ቤት የሚገኘውም ቡልጋ ነው። በኢትዮጵያ ብዙ ታላላቅ የሚባሉ የእውቀትና የሃይማኖት መጻሕፍት የጻፉ ሊቃውንት ከቡልጋ የወጡ ነበሩ። ለምሳሌ በማንኛውም የግዕዝና የተለያዩ ሰነዶች ላይ ዘብሔረ ቡልጋ የሚል ካለ ደራሲው ቡልጌ ናቸው። የሸዋ አምሓራ መንግሥት ዋና ዋና ሊቃውንት የሚፈልቁበት ቦታም ነበር። አፄ ፋሲል የተወለዱበት መገዘዝ የሚባለው ተራራ የሚገኘው ቡልጋ ነው። ታዋቂ ከሆኑ ሌሎች ከቡልጋ ተወላጆች መካከል ጽሓፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሐብተወልድ፣ ጽሓፌ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሓንስ፣ ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድሕን፣ ብላቴን ጌታ ማሕተመሥላሴ ወልደመስቀል፣ ተስፋ ገብረሥላሴ፣ ተክለጻዲቅ መኩሪያ፣ ደጃዝማች ሐብተሥላሴ በላይነህ ይገኙበታል። የኔም አባት ሎሬት ዶክተር መላኩ ወረደም እንዲሁ። ፎቶው ላይ ያለው አፄ ፋሲል ተወለዱበት የሚባለውና ቡልጋ የሚገኘው መገዘዝ ተራራ ነው
1-2 minutes

ጥቂት ስለ ቡልጋ

ቡልጋ ሰሜን ሸዋ ከሚገኙ ታሪካዊ ጠቅላይ ግዛቶች አንዱ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ፣ የመካከለኛው ዘመን አምሓራ ነገሥታት ይነግሡበት ከነበረው ከተጉለት ጋር እጅግ የተሳሰረ በመሆኑ አብሮ ተጉለትና ቡልጋ ሲባል ይታወቃል። መልክዓምድራዊ ገጽታው ወይና ደጋ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ዋንኛ ከሚባሉ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ቦታዎች አንዱ ነው። ታላላቅ ቅዱሳን የወጡበትም ቦታ ነው። ለምሳሌ አፄ ይኩኖ አምላክን ያነገሡት ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የቡልጋ ተወላጆች ነበሩ። የአፄ ምኒልክ የአማራ ጦር ብዙው ከተጉለትና ቡልጋ እንደነበር አንዳንድ የታሪክ ጽሐፊያን ጽፈዋል። የምኒልክ ምሽግና የጦር ግምጃ ቤት የሚገኘውም ቡልጋ ነው። በኢትዮጵያ ብዙ ታላላቅ የሚባሉ የእውቀትና የሃይማኖት መጻሕፍት የጻፉ ሊቃውንት ከቡልጋ የወጡ ነበሩ። ለምሳሌ በማንኛውም የግዕዝና የተለያዩ ሰነዶች ላይ ዘብሔረ ቡልጋ የሚል ካለ ደራሲው ቡልጌ ናቸው። የሸዋ አምሓራ መንግሥት ዋና ዋና ሊቃውንት የሚፈልቁበት ቦታም ነበር። አፄ ፋሲል የተወለዱበት መገዘዝ የሚባለው ተራራ የሚገኘው ቡልጋ ነው። ታዋቂ ከሆኑ ሌሎች ከቡልጋ ተወላጆች መካከል ጽሓፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሐብተወልድ፣ ጽሓፌ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሓንስ፣ ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድሕን፣ ብላቴን ጌታ ማሕተመሥላሴ ወልደመስቀል፣ ተስፋ ገብረሥላሴ፣ ተክለጻዲቅ መኩሪያ፣ ደጃዝማች ሐብተሥላሴ በላይነህ ይገኙበታል። የኔም አባት ሎሬት ዶክተር መላኩ ወረደም እንዲሁ።

ፎቶው ላይ ያለው አፄ ፋሲል ተወለዱበት የሚባለውና ቡልጋ የሚገኘው መገዘዝ ተራራ ነው