Showing posts with label ethiopian constitution amendement or rsform. Show all posts
Showing posts with label ethiopian constitution amendement or rsform. Show all posts

Sunday, November 11, 2018

ህገ መንግስት ማሻሻል አስፈላጊነት Ethiopian constitution reform or Amendment

የህገ መንግስት (constitution ) ማሻሻያ ፦

በመጀመርያ የህገ ምንግስት ስለሚሻሻልበት እሚደነግገው አንቀጽ መሻሻል አለበት።   ከዚህም ሌላ የህገ መንግስታዊ ፍ/ቤት ማቃዋቃዋም አስፈላጊ ነው።  ለምሳሌ ህገ መንግስት ተርጉዋሚ ነው የተባለው የፌ/ምቤት ክህግ ባለሙያዎች ይልቅ በፖለቲከኞች የተሞላ ስለሆነ በራያ ወልቃይት ወዘተ... የተነሱትን የማንነት ጥያቄዎች ምላሽ ሳያገኙ ለአመታት ሲዳፈኑና ሲጉዋተቱ ወደ አመፅ ተቀየረ ጥያቄው። ህገ ምንግስታዊ ፍርድ ቤት ቢሆን ግን ጉዳዩን ከፖለቲካ ገለልተኝነት ውሳኔን ያሳልፍበት ነበረ። 

አንዳንድ ከሰብአዊ መብት አንፃር የተቀመጡት የህገ ምንግስቱ ኣንቀፆች advanced ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ ከዘመኑ አንጻር ታይተው ሊሻሻሉ የሚገባቸው ናቸው።
የምርጫ ህጉ ለምሳሌ በ (majority vote) ብቻ አሸናፊው የሚለይበት ሲሆን ይህ የምርጫ ህግ ወደ ተመጣጣኝ ውክልና (proportional voting system )እና ወደ የሁለቱም ድብልቅ የምርጫ ውጤት አሰጣጥ ሊሻሻል ይገባል ተብሎ በአቶ ሃይለማርያም ዘመን ተጀምሮ የነበረ ነው። ግን ይህ ህግ በተቃዋሚዎች የሚጠበቅና መጭው ምርጫ በተሻለ ፍትሃዊ ሊያደርግ ቢችልም አልተሻሻለም።
ህገ ምንግስቱ ውስጥ ገብተው መታሰር ያልነበረባቸው ማለትም የሊዝ ህጉና የምርጫ ህጉ ህገ ምንግስቱ ውስጥ ገብተው ሊቆለፍባቸው አይገባም ነበረ። flexibility የሚጠይቁ ስለሆነ እነኝህ ሁለት ጉዳዮች እንዳስፈላጊነቱ የተወካዮች ም/ቤት እና የክልል ም/ቤቶች አዋጅ እያወጣ ሊያሻሽላቸው የሚገቡ ነበረ።

የፍትህ ስርአቱ ልምሳሌ ህግ ተርጉዋሚው አካል ዳኞችን ፍ/ቤቶች ብቻ መሆን አለባቸው። ይህ የፍትህ አተረጋጎም እስካልተሻሻለ ድረስ የፍትህ ስርአቱን ሪፎርም ተደርጎአል ማለት አይቻልም የፌደራል ስርአቱ ለገባበት አጣብቂኝ አንዱ መፍትሄው የህግ ምንግስታዊ ፍ /ቤት ማቁዋቁዋም ነው። 

የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ ፦

ሕገ መንግሥት አንቀጽ 47 መሠረት ማንኛውም በአገሪቱብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ የራሱን ክልል የመመሥረት መብት አለው፡፡ በዚህ አንቀጽ መሠረት ይህ መብት ተግባራዊ የሚሆነው የክልል መመሥረት ጥያቄው በብሔሩ፣ ብሔረሰቡ፣ ወይም ሕዝቡ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ማግኘቱ ሲረጋገጥና ጥያቄው በጽሑፍ ለክልል ምክር ቤት ሲቀርብ፣ ጥያቄው የቀረበለት ምክር ቤት ጥያቄውን በደረሰው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለጠየቀው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ ሲያደራጅ፣ ክልል የመመሥረት ጥያቄው በብሔሩ፣ ብሔረሰቡ ወይም ሕዝቡ ሕዝበ ውሳኔ በአብላጫ ድምፅ ሲደገፍና የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣኑን ለጠየቀው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ሲያስረክብ እንደሆነና ይህ አዲሱ ክልል የፌዴራል መንግሥቱ አባል እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡

የበርካታ ዞኖች ክልል የመሆን ጥያቄ ምላሽን ይጠይቃል ። ይህ ግን የተዘጋውን pandora box መክፈት ይሆናል። ይሁንና ማንም በቀላሉ እንደሚረዳው የ87 ኣ.ም. ህገ መንግስት ሲፀድቅ ህዝብ ተወያይቶበት ስላልነበረና በርካታ የአተረጉዋጎም  ክፍተቶችና ብዙም የማያራምዱ አንቀፆች የበዙበት ስለሆነ ዶ/ር አብይን ጨምሮ ፖለቲከኞቹም ይህን የፓንዶራ ሳጥን ከፍተው ራሳቸውን ጣጣ ውስጥ መጨመር አይፈልጉም።
ሲጀመርም ያለበቂ የህዝብና የምሁራን ክርክር ያልተደረገበት ከሰብአዊ መብቶች መከበር እውቅና ከመስጠቱ ውጭ አንቀፅ 39ን ጨምሮ አወዛጋቢ በሆኑ አንቀፆች የተሞላ እንደመሆኑ በስልጣን ላይ ያሉ ይህን ህገ መንግስት መነካካት አይፈልጉም። ይሁንና ባገር ደረጃ ግን ህገ መንግስት ማሻሻያን እሚፈልጉ ጉዳዮች ካልተሻሻሉ በስተቀረ የማያባራ ግጭትንና ውዝግብን ሲፈጥሩ መኖራቸው አይቀርም። ለምሳሌ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ብሐዋሳ ከተማ ተደጋጋሚ ረብሻ ሲፈጠር በመጨረሻ ሲዳማ ዞን የክልልነት መብትን እንዲጠይቅ ፈቃድ ሰጠ ። የቱሪስት መስህብ የሆነችው ውቢቱዋ ሐዋሳ ስትረበሽ ፥ቱሪስት መቅረት ሲጀምር በተደጋጋሚ ጉዳዩ ፌደራል መንግስቱን ሲያስጨንቅ ሆነ የክልሉን መንግስት እንዳሳሰበ ግልፅ ነው።