Friday, February 6, 2015

የክስ አቀራረብና ስነ - ስርአት



አንድ ሰው ፍርድ ቤት ሲሄድ በክስ ማመልከቻው ላይ በሚያቀርብበት ወቅት በግልፅ ችሎቱ የማየት ስልጣን አለው ስለዚህም ፣ ይፈረድብኝ ወይንም ይፈረድልኝ ብሎ ምሎ ነው ፡፡ የክስ ማመልከቻውን በሚያቀርብበትም ጊዜ መጀመሪያ የሚለው ይህ ፍርድ ቤት ጉዳዩን የማየት ስልጣን አለው በሚል አረፍተ ነገር ነው ፡፡ ይህን አካሄድ ሳይከተልም ማንኛውንም ክስም ሆነ አቤቱታን ማቅረብ አይቻልም ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ህግ ሲወጣ ወይም አንድ አዋጅ ሲታወጅ ሆነ ተብሎ የሚተው ክፍተት እና አሻሚ የሆኑ ቃላቶች ስራ ላይ ሊውሉ ይችላሉ ፤ ይሄውም በተከራካሪ ወገኖች ብርታት እንዲሞላና አንደኛው ተከራካሪ ወገን ሌላ ወገን ተከራካሪ ወገን በማይኖርበት ወይንም ጠያቂ የማይኖርበት ሁኔታ በሚፈጠርበት ወቅት ያለውን ክፍተት እንዲጠቀምበት እና ጉዳዮችና እና ንብረቶች ባለቤቶች እንዲኖራቸው ለማስቻል ነው ፡፡ ባለቤት የሌላቸው ንብረቶች እንዳይፈጠሩ ለማድረግ አንድ ንብረት ሌላ ተከራካሪ ከሌለው የኔ ነው ለሚል ወገን ሊፈረድለት ይችላል ፡፡
ሌላው በወንጀል ህጉም ሆነ በፍትሐ ብሄር የስነ ስርአት ህጉ ላይ በግልፅ አስን እንደተነደነገገው ፅጥቅነሙን ለማስከበር ክዶ መከራከር ይችላል ፡፡ ነገር ግን ከሳሽ ወይም ተከሳሽ ሳይሆን በሐሰት ለሌላ ሰው ጥቅምን ለማስገኘት ወይንም ሌላውን ሰው ለማሳሰር ቢዋሽ ወይንም በሀሰት መረጃ ቢያቀርብ ግን በህግ ተጠያቂ እደሚሆን በግልፅ ተደንግጓል ፤ አንዳንድ ሰዎች ከሳሽ ወይንም ተከሳሽ በሚሆኑበት ወቅት ክዶ መከራከር ጥቅማቸውን ሎያስከብር እንደሚችል ከፍ ግምት ውስጥ ባለማስገባት ወይም ባለማወቅ ወይንም የህግ አማካሪን ባለመያዝ ሲጎዱና በባላጋራቸው የበለጠ ጉዳት ሲደርስባቸው ይስተዋላል ፡፡ ራሱ ሰበር ሰሚው በወሰናቸው ውሳኔዎች ላይም በግልፅ እንደሚተነትነው ተክዶ ቢከራከሩ ኖሮ እንደዚህ ይሆን ነበረ ነገር ግን ስላልተካደ እሚወሰነው እንደዚህ ነው በማለት ትንታኔ ሲሰጥ ይስተዋላል ፡፡  
በአንድ የሰበር መዝገብ ላይ በተደረገ ክርክር የቤት ሽያጩ መደረጉ ሳይካድ ነገር ግን የአፃፃፍ ፎርሙን አልጠበቀም በሚል ሽያጩ ይፍረስልኝ የሚል ክስ ተቀባይነት እንደሌለው ሰበር በሰጠው ውሳኔ ላይ ማየት ይቻላል ፡፡ በማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ጋር በተገናኘ ውል መኖሩን በማመን ነገር ግን ውሉ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1723 መሰረት የተከናወነ አይደለም በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይት የሌለው ስለመሆኑ እንዲሁም 1723 (1) መሰረት የሚደረግ ምዝገባ ዓማላማ በተዋዋይ ወገኖች መሀከል ውል መኖሩን ለማስረዳት መሆኑን በፍ/ብ/ቁ 1723 (1) ፣ እና በፍ/ብ/ህ/ ቁ 2878 መሰረት አድርጎ በ13ኛው ቅፅ 2004 ዓ.ም. በሰ/መ/ ቁጥር 36887 ላይ ትንታኔን ሰጥቶበታል ፡፡
  ዞሮ ዞሮ በቃልም ይሁን በፅሁፍ ይደረግ ሁለቱ ወገኖች ውል አለን ብለው እስካመኑ ድረስ ውሉ የሚፀና ነው የሚሆነው ውል የለንም ብለው ሁለቱም ወይም አንደኛው እስካልካደ ድረስ ፣ የውል አፃፃፍ ፎርሙን አልጠበቀም በሚል ብቻ የታመነ ውል ሊፈርስ እንደማይችል መረዳት ይቻላል ፡፡ አንዱ ውል አለን ቢልና አንደኛው ቢክድ እንኳን በውልና ማስረጃ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፊት የተረደረገ ውል እስከሌላቸው ድረስ አንደኛው ወገን  ያልተረጋገጠን ወይንም በማስረጃ ሊረጋገጥ የማይችልን ውል እንዲፈፅም አይገደድም ፡፡   
በወንጀል ህጉ አንቀፅ 252 ላይ እንደተመለከተው በቁጥ 1 እስከ 3 ላይ ሲመለከት ሐሰተኛ ቃል ቢሰጥ እንዲሁም ፣ ዳኝነት ነክ ስልጣን ባለው አካል ፊት ቀርቦ በሚወሰን ጭብጥ ላይ እያወቀ አግባብነት ያላቸውን ፍሬ ነገሮችን እያወቀ ሐሰተኛ ቃሉን የሰጠ እንደሆነ ከ3 እስ 5 አመት ሊደርስ በሚችል ፅኑ እስራት ሊቀጣ እንደሚችል ሲደነግግ በዚሁ አንቀፅ በቁጥር 3 ላይ ግን ይህንን ያደረገው ተከተራካሪው ወገን ጥቅሙን ለማስከበር ሲል ለሚያቀርበው ትክክኛ ያልሆነ ከክርክር እነዚህ ከላይ የተመለከቱት አንቀፆች ተፈፃሚ እንደማይሆኑ ይደነግጋል ፡፡
በተመሳሳይም በ1958 ዓ.ም. የወጣው የፍትሀ ብሄር የስነ - ስርአት ህጉ አንደውም ተከራካሪው ወገን ሊክድ የፈለገውን ግልጥ አድርጎ መካድ እንዳለበት ይደነግጋል ፡፡ በስ/ስ/ቁጥር 83 ላይ ተከሳሹ የቀረቡትን ነገሮች ሁሉ በዝርዝር እና በግልፅ ክዶ በመቃወም ነው ፡፡ እንደዚሁም ከሳሹ ተሰከሳሽ ሆኖ መልስ በሚሰጥበት ጊዜ የቀረበበትን ክስ በዝርዝርና በግልፅ መካድ አለበት ፡፡ ስለ ካሳ ጥያቄ የቀረበውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ ካልሆነ በስተቀር በክሱ ላይ የቀረበውን ነገር በግልፅና በዝርዝር ያለመካድ ያልተካደውን ነገር በከፊል ሆነ በሙሉ አምኖ እንደመቀበል ያስቆጥራል ይላል ፡፡

No comments:

Post a Comment