Friday, February 6, 2015

Human Psycholgy ማመዛዘንና ማነፃጸር



የስነ - አእምሮና የስነ - ማህበረሰብ ጥናት ባለሙያዎች እንዳረጋገጡት የሰው ልጅ አእምሮ ነገሮችን በማመዛዘንና በማነፃፀር እንደሚሰራ ተረጋግጧል ፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት የመኪና መንዳት ልምምድ ያስተምረን በክፍል ውስጥ ያስተምረን የነበረ ሰው ከፊት ለፊቴ አንድ ሰው መጥቶ ቢገባብኝና እርሱን ለማዳን ስል ፍሬን ብይዝ መኪናው ተግልብጦ በውስጡ የጫንኳቸው ሰዎች የሚያልቁብኝ ከሆነ ሰውዬው ላይ ወጥቼበት መኪናው እንዳይገለበጥ አድርጌ የጫንኳቸውን ሰዎች ማዳን እርምጃን ነው እምወስደው ብሎ ሲያስተምር ትዝ ይለኛል ፡፡
እንዲሁም በጦርነት ወቅት ሰዎች የቀለለውን ምርጫ ይወስዳሉ ፡፡ ለምሳሌ አሜሪካኖች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓን ላይ የአቶሚክ ቦምብን ሲጥሉና የወታደሮቻችንን መስዋእትነት ለመቀነስ በሚል ቢሆንም በርካታ የታሪክ ሰዎች እንደሚስማበት ግን አሜሪካ ጃፓን ላይ እያለቀ በነበረና ጃፓን ሽንፈቷ በታወቀበት ጦርነት ላይ ያንን አውዳሚ ቦምብ የጣሉበት ምክንያት ግን የቀድሞዋን ሶቭየት ህብረትን ለማስፈራራት እንደሆነና መጪዋ ተፎካካሪያቸው ልትሆን የምትችለው እርሷ መሆኗን በማመን ያንን ለመግታት መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ የወታደሮቻችንን መስዋእትነትን ለመቀነስ ነው በሚለው ብንሄድም ይሄም በራሱ ማነፃፀር ነው ማለት ነው ፡፡ ለዚህም መሪዎቹ ያነፃፀሩትንና ያመዛዘኑትን መገመት ይቻላል ፡፡
አእምሮው በማመዛዘንና በማነፃፀር መስራቱ የሰውን ልጅ በምድር ላይ ካለ ከየትኛውም እንሰሳ የበለጠ አደገኛ ፍጡር ያደርገዋል ፡፡ ፈረንጆች አስቸጋሪ ሁኔታ ሲገጥማቸው ከሁለት ክፋቶች ያነሰውን መምረጥ ‹‹The lesser of two evils›› የሚሉት አባል አለ ፡፡ የሰው ልጅ አእምሮ በስሌት የሚመራ ስለሚሆን ለሌላው ባለማሰብ ለራሱ ይጠቅመኛል ብቻ የሚለውን ብቻ እንዲያደርግና ፣ በራሱ ጥቅም አንፃር ብቻ የሚንቀሳቀስ ይሆናል ፡፡ ለማህበረሰቡ ጥቅም ግዴለሽ በመሆን የሚሄድ ይሆናል በዓለም ላይ በአሁኑ ወቅት የምናያቸው ችግሮች እንደ የአየር ንብረት ለውጥ ፣ በዓለም ላይ አገራት እጅግ ሀብታም ሲሆን የተቀሩት ደግሞ እጅግ ደሀ ሆነዋል ፡፡ የሰው ልጅ እርስ በእርሱ ላይ ያደረሰው ጉዳትና ክፋትም እንዲሁ በታሪክ በርካታ ሲሆን አንዱ ሀገር ዘመናዊ የጦር መሳሪያን በታጠቀበት ወቅት ዘመናዊ መሳሪያ የሌለውን አገር በባርነትና በቅኝ ሲገዛና ሲበዘብዝ ኖሯል ፡፡  
የሰው ልጅ አእምሮ ‹‹180 ቢሊየን ህዋሳት አሉት ፣ከእነዚህም ውስጥ 80 ቢሊዮን የሚሆኑት በአእምሯችን ውስጥ የሚካሄዱ ሂደቶችን የሚያንቀሳቅሱ ናቸው ፡፡ ቀሪዎቹ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችንን የሚቆጣጠሩ ናቸው፡፡ይህ በዚህ እንዳለ እያንዳንዷ የአእምሮ ህዋስ ወደ 1000 ከሚሆኑ ሌሎች ህዋሳት ጋር መረጃዎችን ይቀባበላሉ ፡፡ በሁለት መረጃ በሚቀባበሉ ህዋሳት መሀከልም የትየለሌ የሆኑ ክፍተቶች አሉ ይህም ማለት አንድ ህዋስ መረጃዎችን ከተለያዩ ህዋሳት ያገኛል፣ ያገኘውንም መረጃ ለብዙ ህዋሳት ያስተላልፋል ፡፡ ስለሆነም ነው እንግዲህ ሁለቱም የፍሰት ሂደቶች የሚያስልጉን››[1]
የዚህ እጅግ የተወሳሰበ የአእምሯችን አሰራር አደጋም አለው ይሄውም መረጃዎች ሊደበላለቁና ፣ መረጃውን በአንድ ቦታ የሚያስቆመው ሃይል ከሌለ መረጃው ዝም ብሎ ከአንዱ ህዋስ ወደ ሌላው ዝም ብሎ ሊፈስና ግንዛቤያችንን ሊያምታታና ሊያደበላልቀው ይችላል ፡፡እነኚህ መረጃዎች ከኬሚካል ሃይልነት ወደ ወደ ኤሌክትሪክ ፍሰት ተቀይረው ነገሮችን ለመረዳት የሚያስችሉን ናቸው ፡፡ ስለሆነም የመስኩ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት የመረጃዎችን ፍሰት የሚገድብ ወይም የሚያስቆም ነገር ያስፈልጋል የሚሉት፡፡ ያለበለዚያ አስፈላጊ ያልሆነና የተሳሳተ መረጃ ሊፈስና ሰውየውን በማደናበር ወደ ተሳሳተ ውሳኔና አቅጣጫ ሊያመራው ይችላል ፡፡
ለዚህም አይነተኛው ምሳሌ ሰዎች አንድን ነገር በተሳሳተ መንገድ ሲተረጉሙት ፣ማየት ከዚሁ ከአእምሯችን አሰራር የሚመነጭ ነው ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ነገሮችን በተሳሳተ መንገድ በመረዳት ወንጀልን ሲፈጽሙ ፣ ሰው ሲገድሉ ጥቃት ሊሰነዘርበት በማይገባው ነገር ላይ ጥቃትን ሲፈፅሙ እናያለን እንሰማለን ፡፡

ሰውና ስራው

ስራን መስራት ህይወትን በአግባቡ ከመምራት ለብዙ ሰዎች የቀለለ ነው ፤ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ሰዎች የሚሰሩት ስራ ስለሚስትለው ውጤትን ብዙም አይጨነቁም ፣ ነገር ግን  ለምሳሌ በናዚ የማጎርያ ካምፕ ውስጥ የነበሩ እስረኞች ሃላፊዎች ያሰሯቸው ሰዎች በጣም ዝቅተኛ ስራን ማፅዳትን ፣ ጥበቃን የመሳሰሉ ስራዎችን የሚሰሩ ቢሆንም ያሰሯቸውን ታላላቅ አይሁዳውያን የባንክ ፕሬዝደንት የነበሩ ፣ የስነ አእምሮ (Psychiatry) ሀኪሞች ፣ የዩንቨርስቲ ፕሮፌሰሮችና የመሳሰሉ አሉ የተባሉ ሰዎች ቢሆኑም ነገር ግን የሚጠብቋቸው ግን ከእስረኞች የበለጠ በራስ የመተማመመን ስሜትንና ስራን ሰራን ብለው ወደ ቤታቸው ይሄዱ እንደነበረ በፃፈው መፅሀፍ  ጠቅሶ ፅፏል ፡፡ 
ኤክሀርት ቶሌ የተባለው የዘመናችን ረቂቅ መንፈሳዊ አዋቂ እንደሚለው በሰው ልጅ እድገት ውስጥ የምንሰራው ስራ አይደለም ዋናው ነገር ፣ እርሱ ሁለተኛ ነገር ግን ግንዛቤያችን ማደጉ ነው ዋናው›› ይለናል ፡፡ አብዛኛው ግን ሰው ስለሚሰራው ስራ በመጨነቅ ስለ ውጤቱ ፣ ማሰብን ባለመፈለግ ወይንም ውጤቱን ባለማወቅ ተደጋጋሚና አሰልቺ የሆነውን ስራ በመስራት አብዛኛውን የህይወት ዘመናቸውን ያሳልፋሉ ፡፡ ስራ ዘመናቸው አብቅቶ በጡረታ ቢገለሉም ከስራቸው መገለላቸው ሲያስቆጫቸው በቀድሞው ሰራተኛ የነበሩበትን ዘመን በመናፈቅ እና በማሰላሰል ያሳልፋሉ ፡፡ በእርግጥ ስራን መስራት ለአንድ ሰው የሚሰጠው ልዩ ክብርና መደነቅ (Privilage & Status) መወደድ እና አስተማማኝ ገቢ ባለቤት መሆን የመሳሰሉት የሚታዩም  ሆነ የማይታዩ ጥቅሞች ነገሮች አሉት ፡፡
ሰው ብዙውን ጊዜ በራሱ ማንነት መተማመን ስለማይሰማው ፣ በተፈጥሮው ስማይረካ ማህበረሰቡ የሚሰጠውን ሌላ ማንነትን ይፈልጋል ፡፡ ይህም ማንነት ለራሱ ያለውን ስሜት ‹‹ኢጎ›› ከፍ የሚያደርግና በማህበረሰቡ ዘንድ አክብሮትን የሚያጎናፅፈውን ነው የሚሻለው ፡፡ ይህንንም  አንድ ሰው የሚሰራውን ስራ በማየት የሰውየውን ማንነት መናገር ይቻላል ፡፡
ይሁን እንጂ ሰው ለራሱ ያለውን ስሜት ከፍ ያደርግልኛል ብሎ እሚያስበው የሚሰራው ነገር ለእርሱ ሳይሆን ከእርሱ በኋላ ለሚመጣው ወራሹ ነው እንጂ ለእርሱ አይደለም ፡፡ በመጽሀፈ መክብብ ምእራፍ 2 ፣ ቁጥር 20 - 23 ላይ ‹‹ሰው በጥበብና በእውቀት ፣ በብልሃትም ከደከመ በኋላ ለሌላ ላልደከመበት ሰው ያወርሰዋልና ይህም ደግሞ ከንቱ ትልቅም መከራ ነው፡፡ ከፀሃይ በታች በደከመበት ድካም ሁሉና በልቡ አሳብ የሰው ጥቅም ምንድር ነው ? ዘመኑ ሁሉ ሃዘን ፣ ጥረትም ትካዜ ነው ፣ልቡም በሌሊት አይተኛም ይህም ደግሞ ከንቱ ነው››፡፡
ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚሰሩበት መስሪያ ቤት ፣ ያላቸው ሃላፊነት ወይንም ስልጣን የመሳሰለው የበለጠ ስሜትንና ለራሳች የሚሰጡትን ክብርና ስሜት ከፍ ያደርግላቸዋል፡፡ ከቀድሞ ባልደረቦች ጋራ ስነጋገር የት ነው ያለኸው የሚል ጥያቄ መስማት የተለመደ ሲሆን የት ነው የምትሰራው ? የመሳሰሉት ናቸው ፡፡ እነኚህ ጉዳዮች አንድን ሰው ስለራሱ ለጊዜው የገዘፈ ማንነትን የሚሰጡትና የእኔነት ስሜቱን የሚያሳድጉለት ናቸው ፡፡ ነገር ግን እነኚህ ሰው ከጀርባው እንዲኖረው የሚፈልጋቸው ማእረጎችና ስሞች የክብር ስሞች ለተወሰነ ገዚያት የሚቆዩ ናው አቸው ፡፡ ጡረታ ሲወጣ ፣ ከስራ ሲባረር ወዘተ እነኚህ ነገሮች አይሩም ፡፡
አንድ የባንክን ፕሬዝደንት ለምሳሌ የሚሰጠው ክብርና መደነቅ ከፍተኛ ነው ፡፡ አንድ የሀገር መሪ ወይንም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣንም እንዲሁ የሚደረግለት ክብርና አድናቆት የሚዲያ ሽፋን የመሳሰሉት ነገሮች ለራሱ ያልሆነውን ነገር የሚጨምርለት ነው ፡፡ 
አንደ አንድ መሀንዲስ አንድ ህንፃን ሲገነባ ህንፃው የሚያርፍበት ቦታ ላይ ያሉ ዛፎችን ቆርጦ ፣ ሳሮችም ካሉ አጥፍቶ ነው ፡፡ መንገድም ሲሰራ አንደዚያው በአካባቢው ላይ ባሉ የተፈጥሮ ሀብቶች ላይ ጉዳት ደርሶ ቢሆንም ፡፡ እንደዛው ሁሉ አንድ የማእድን ማውጫም እንዲሁ ማእድንን ለማውጣት በርካታ አካባቢዎችን መርዞ ፣ ጭስ ለቅቆ ፣ ወንዞችን በክሎ መሆኑ ነው ፣ ነገር ግን እኛ ሰዎች ስራን መስራታችንን እንጂ ስራው የሚስከትለውን ጉዳት ብዙዎቻችን ፈጽሞ አናስበውም ማለት ይቻላል ፡፡ 
መፅሀፍ መክብብ ላይ ምእራፍ 1፣1-8 ላይ ‹‹ሰባኪው ፡- ከንቱ ፣ከንቱ ፣ የከንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል ፡፡ ከጸሀይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድነው? ትውልድ ይሄዳል ትውልድ ይመጣል ፣ ምድር ግን ለዘልአለም ነው ፡፡ ጸሀይ ትወጣለች ፣ ጸሀይም ትገባለች ፣ ወደምትወጣትበት ስፍራ ትቸኩላለች ፡፡ንፋስ ወደ ደቡብ ይሄዳል ፣ ወደ ሰሜንም ይዞራል ዘወትር በዙረቱ ይዞራል ፣ነፋስም ይመለሳል፡፡ፈሳሾች ሁሉ ወደ ባህር ይሄዳሉ ፣ ባህሩ ግን አይሞላም ፈሳሾች ወደሚሄዱበት ስፍራ እንደ ገና ወደዚያ ይመለሳሉ፡፡ ነገር ሁሉ ያደክማል ሰው ይናገረው ዘንድ አይችልም ዓይን ከማየት አይጠግብም ፣ ጆሮም ከመስማት አይሞላም ››  
‹‹እጄ የሰራቻትን ስራዬን ሁሉ የደከምሁበትን ድካሜን ሁሉ ተመለከትኩ ፣እነሆ ሁሉ ከንቱ ንፋስንም እንደመከተል ነበረ ፣ ከፀሀይ በታችም ትርፍ አልነበረም›› መክበብብ 2፣11 ጠቢቡ ሰለሞን ይህን ሲል ሰራ አይጠቅምም ማለቱም ወይም አይደለም ወይንም ስንፍናን ማበረታታቱ አይደለም ፡፡ ‹‹ሰነፍ እጁን ኮርትሞ ይቀመጣል፣ የገዛ ስጋውንም ይበላል›› ምእራፍ 4 ቁ፣6 ፡፡ ከአንድ ይልቅ ሁለት እንደሚሻል የአንዱ ሰው ብልሃትና ስራ ለሌላው ቅንአትን ሲያስከትል እንደታዘበና ይህ ደግሞ ከንቱ ንፋስን እንደ መከተል ነው ይላል ፡፡ መተባበርን ሲያሰምርበት ‹‹ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውም ያሳነሳዋልና ፣አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ግዜ ግን የሚያሳው ሁለተኛው የለውምና ወዮለት››

ስነ - ልቦናዊ የስብእና ዝንፈቶች (Psychological Disorders)

በርካታ የሆኑ የስብእና ቀውሶች እንዳሉ የስነ - ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡ በመስኩ ባለሙያዎች በርካታ አይነት የስበአብና ቀውሶች ሲኖሩ ተለይተው የታወቁት ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው ፡፡
ሲበዛ ጠራጣሪ ስብእና ባለቤቶች (Paranoid Personality Disorder) ፤ የዚህ የስብእና ቀውስ ባለቤት የሆኑ ሰዎች እጅግ ሲበዛ ተጠራጣሪዎች ሲሆኑ ሁሉንም ሰውና ማንኛውንም ነገር የሚጠራጠሩ ናቸው ፡፡
schetypal personality disorder በመተት የሚያምኑ ናቸው ፡፡ መተትም ጥንቆላንና አጉል እምነትን መሰረት ያደረጉና በዚህም ህይታቸውን ለመምራት የሚሞክሩ ናቸው ፡፡
ፀረ - ማህበረሰብ ስብእና (Anti -Social Behaviour ) ባህሪያት የሚያሳዩ የዚህ ዝንፈት ተጠቂዎች ለህብረተሰቡ ባህል የማይገዙ ፣ የሌሎችን መብት የሚጋፉ ፣ መደባደብን የሚመርጡ ፣ ህግና ስርአት ተጋፊ የሆኑ ሰዎች ከስነ - ስርአት ውጪ የሆኑ እውነትና ውሸትን ልዩነት የማያውቁ፣ ውሸታሞች ሲሆኑ ሁሉን ነገር በስሜት ለማሟላት የሚሞክሩ (Impulsive) በቅሚያ ፣ በአስገድዶ መድፈር የሚታወቁ ፡፡ ለትዳር ጓደኛቸው ፣ለልጆቻቸውና ለቤተሰቦቻቸው ፍቅር የማይሰጡ ፣ ፀፀት የማያውቁና የማይታይባቸው ስሜታቸውን መቆጣጠር የማይችሉ ሲሆን ግልፍተኝነት ፣ በስሜታቸው የሚገፋፉና ድርጊታቸውንና ስሜታቸውን የማይቆጣጠሩ ሲሆን ችኩልነት ፣ ውሳኔ ለመውስድ የሚጣደፉና ፀረ - ማህበረሰብ ውጪ የሆኑ ባህርያትን የሚያሳዩና በሌሎች ስቃይ የሚደሰቱ (Sadists) እና ንኮች (Psychopath) ‹‹ሳይኮፓዝ››  ናቸው ፡፡
ለ) የሚያንቀዠቅዥ ስብእና ባለቤቶች ደግሞ ያላቸው ማህበራዊ ተግባቦት ያልተስተካከለ ፣ ከአንድ ሰው ብዙም ሳይቆዩ የሚሄዱ ወረተኞች ፣ መጠጥና ጫት እና ሌላም ሱስ የሚያዘወትሩ ሲጠጡ በቀላሉ የማይሰበሩ ወይም የማይመለሱ ፣ ቁማር የሚወዱ ፣ በሰዎች ላይ ያላግባብ የሚደነፉ ፣ የሚጮሁ ፣ ስሜታቸው በቀላሉ የሚቀያየር ፣ ጥቃቅን የሆኑ ነገሮችን ካለልክ የሚካብዱ ፣ ራሴን አጠፋለሁ ብለው (Suicidal Attempt) የሚያስፈራሩ ራሳቸውንም ለማጥፋት የማይመለሱ ፣ የማይጨበጥ ተቀያያሪ ባህሪ ያላቸው ናቸው ፡፡
የልታይ ልታይ ባህሪ ያለባቸው (Hysteria) የሌላውን ቀልብ ለመሳብ ፣ ቃላትን መጎተት ፣ሴሰኝነት፣ ትኩረትን የሚስብ ነገርን የሚፈልጉ በአብዛኛው የዚህ ባህሪ ባለቤቶች ሴቶች ሲሆኑ አማላይ ባህሪ ያላቸውና ጥቅም ፈላጊዎች በሃገርኛው አባባል ጭራ ቀረሽ የሚባሉ አይነቶች ናቸው ፡፡
ሐ) ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚደርጉ ‹ናርሲስቲክ› (Narcissistic Personality Disorder) ስብእና ባለቤቶች ደግሞ የዚህ የስብእና ቀውስ ባለቤቶች ራሳቸውን ከሌላው አስበልጠው የማየት ፣ ራሳቸውን አዋቂ አድርገው ማየት ፣ እነሱ ብቻ ቆንጆና መልከ መልካም እንደሆኑ አድርገው ማሰብ፤ ከራሳቸው በስተቀር ሌሎች ከኛ ያነሱ ናቸው ብለው ማሰብ ይቺ ለኔ ምንድነች የማለት ሙገሳንና ክብርን አብዝተው መውደድ ካብ ካብ የሚያደርግ የሌሎችን አትኩሮትን መፈለግ ፣ ሌላው ከእነርሱ በልጦ ጎልቶ እንታይ አለመፈለግ እንዲሁም አለቃ ከሆኑ ይበልጡኛል ለሚሏቸው መልካም ስሜት አለመኖር ፡፡ በሚሰሩበት አካባቢ እነርሱ ከሌሉ መ/ቤቱ ድርጅቱ ህልውና የማይኖር የሚመስላቸው ለሌላው ምንም ርህራሄም ሆነ ሃዘኔታ የላቸውም ፡፡ ከፍ ከፍ ካሉ ሰዎች ጋር መዋል ይፈልጋሉ እከሌን አውቀዋለሁ ጉዳይህን አስፈፅምልሃለሁ የሚሉ ናቸው ፡፡ 
መ) የተረበሹና ፣ የደነገጡና በስጋት ውስጥ የሚኖሩ ራሳቸውን አሳንሰው የሚያዩ ፣ ከዚህ ጋር የሚገናኘው ፍፁም ለየት ያለ ባህሪ በከፍተኛ ጭንቀት ፣ ፍርሃትና ስጋትና ድንጋጤ ውስጥ የሚኖሩ ደግሞ የመሸሽና (Avoidant Personality Disorder ) ባህሪ ያላቸው ሲሆኑ ወንዶችም ሴቶችም በእኩል የዚህ ዝንፈት ተጠቂዎች ናቸው ፤ ሃላፊነትን የሚሸሹ ፣ በራሳቸው የማይተማመኑ ፣ ከሰዎች አንሳለሁ የሚል ጥቅልቅ ስሜት የሚሰማቸው ፣ የሃፍረትና የመሸማቀቀቅ ስሜት የሚሰማቸው ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር በጉትጎታ ካልሆነ በስተቀር የማይቀላቀሉ እና ራሳቸውን ዋጋ ቢስ አድርገው የሚያዩ ናቸው ፡፡ 
ሠ) የጥገኝነት ባህሪ ዝንፈት የተጠናወታቸው (Dependency Personality Disorder) ‹‹ዲፖፔንደንሲ ፐርሰናሊቲ ዲሰኦርደር›› ደግሞ ሁልግዜ የሌሎች ሰዎችን የሃሳብና የስሜት ድጋፍን የሚፈልጉ ያለሌሎች ድጋፍ በራሳቸው ተንቀሳቅሰው አንድን ነገር መወሰን የማይችሉ ፤ አንድን ግንኙነት ሲያቋርጡ ያለግንኙነት መኖት ስለማይችሉ ወዲያውኑ ከሌሎች ጋር ግንኙነትን መመስረት የሚፈልጉ እና ሁልግዜ ከሌሎች አይዞህ ባይነትን የሚፈልጉ ናቸው ፡፡    
ረ ) አንድን ነገር አለመሰልቸት መደጋገምና በትክክል ተደርጎ እንደሆነ ያለማመን (Obsessive Compulsive Disorder) እነኚህ የሃሳብና የድርጊት ድግግሞሽ የሚታይባቸው ናቸው ፡፡ ሃሳባቸውና ድርጊታቸው የማይገታ ሲሆን ፣ ለጥቃቅን ነገሮ ሁሉ ትልቅና ልዩ የሆነ ትኩረትን የሚሰጡ ሲሆን ለዝርዝርና የራሳቸውን ስርአት የሚጠብቁና ከራስ ፀጉራቸው እስከ እግር ጥፍራቸው ድረስ እንከን የሌለው ፍፁማዊ ስብእና ሰፊ ጊዜን ሰጥተው በስራቸው የሚያሳልፉ ናቸው ፡፡ ለምሳሌ የቤታቸው ቁልፍ ተቆልፎ እንደሆነ ደግመው ደጋግመው የሚረጋግጡ ሲሆን መዘጋቱን ባለማመን ደግመው ደጋግመው ይሞክራሉ ፡፡ (Busy without Work) የሚባሉና ለጓደኛና ለቤተሰብ ጊዜን የማይሰጡና ኮስተር ያሉና ሃሳበ ግትር ሲሆኑ ይሁን እንጂ የሚመጡት ውጤት ያን ያህል አይደለም ፡፡
የተዛነፉ ስብእናዎች በህክምና መስተካከል የሚችሉ ሲሆን ስብእናን ለመቀየርና ለማሻሻል ሁለት ነገሮች አስፈላጊ ናቸው ፡፡ አንደኛው ራሱ ወይም ራሷ ግለሰቡ ወይም ግለሱቡ የስብእና ችግር እንዳለበት በህክምና ባለሙያ ቀርቦ ለማነጋገር ፈቃደኛ መሆንና በባለሙያ ሲነገረው ውስጡ መቀበልና ለመለወጥም ተነሳሽ መሆን መቻል አለበት ፡፡ ሁለተኛው ነገር ደግሞ ብዙውን ጊዜ ሰዎች ስብእናቸው የውስጣዊ ድብቅ ፍላጎታቸው ጭምር ማርኪያ ስለሆነ እንደ ችግር አይተው ለመቀየር ተነሣሽ አይሆኑም ፡፡  
አንድ ስብእና ሲቀረፅ በረጅም ጊዜ ስለሆነ ለማስተካከልም ልክ እንደዛው የረጅም ጊዜ የአእምሮ ህክምናንና ክትትልን ይፈልጋል ፡፡ የስብእና ዝንፈት በመድሀኒት የሚታከም አይደለም ፡፡ ቤተሰብ የማንኛውም ህብረተሰብ አስኳል መሰረት ሲሆን በማህበረሰብ ውስጥ ተገፊ ድጋፍ መኖር ወሳኝ ነው ፡፡ በወላጆችና በልጆች መሃከል የተበላሸ ግንኙነት መኖር በልጅነት የሚፈፀም አካላዊ ድብደባ ፣ አስገድዶ መደፈር ፣ በአሳዳጊ ወይም በቤተሰብ የሚፈለገውን ነገር አለማሟላት ወሲባዊ ጥቃት የመሳሰሉት በልጅነት ወራት ስብእና በሚቀረጽበት ወቅት በእጅጉ ስብእና ላይ የራሳቸውን አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ተፅእኖ የሚያሳርፉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡        

    ምድርና የሰማይ

ምንም እንኳን ሳይንስ ከሃይማኖት በእጅጉ ያነሰ ቢሆንምና ሀይማኖትን ለመገዳደር መነሳት ያልነበረበት ቢሆንም በአሁኑ ዘመን ግን ሳይንስ የሃይማኖትን ቦታ በመቀማት የዓለምን የሁሉንም ነገር ሚስጥር ሳይንስ መፍታት እንደሚችል አድርጎ ራሱን አስቀምጧል ፡፡
ይህን እንጂ ሳይንስ የፈለገ ብዙ ምርምርን አድርጌአለሁ ቢልም እና ለብዙ ምድራዊ ነገሮች መልሱን አዘጋጅቻለሁ ቢልም ይሄ ሁሉ ሃይማኖት ከሚያቀርባቸው ምላሾች የበለጠ ምላሽን ማቅረብ እንዳልቻለ ግን ግልፅ ነው ፡፡ በቀድሞው ዘመን በመካለኛው ዘመን ሀይማኖት በሁሉም መስክ የበላይነቱን ጨብጦ የነበረ ቢሆንም እንዲሁም በአውሮፓ የመካከለኛውን ዘመን ሳይንሳዊ ምርምሮች ይደረጉ ስላልነበረ የ ‹‹ጨለማው ዘመን›› (The Dark Age) ተብሎ ቢሰየምም ነገር ግን ሃይማኖት የበላይነት የነበረበት ዘመን ነበረ ፡፡ ጨለማው ዘመን ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ሰዎች ለምር ኑሯቸው ፀጠቃሚ የሚሆኑ ምርመርሮችን ሃይማኖትን መመርመር ነው ፣ እግዝአብሄርን መፈታተን ነው በሚሉ አጉል ምክንያቶች ሰበብ ምርምሮች እንዳይደረጉ በአውሮፓ ንጉስም ፣ ዳኛም ፣ መስፍንም ጳጳስም የነበሩት ነገስታት ይከላከሉ ስለነበረ ነው ፡፡ ገዢዎቹ ይህን ያደርጉ የነበረበት ምክንያት ከስነ - መለኮት ጋር በተገናኘ ሳይሆን ነገር ግን የምድር ስልጣናችንን እንነጠቃለን ፣ ንብረት ርስታችንና ክብራችን አደጋ ውስጥ ይገባል በሚል ሰማያዊ ሳይሆን ምድራዊ ሰበብ ነው አንጂ ጉዳዩ ከሃይማኖታዊ ሆኖ ስነ መለኮትን የሚፃር ሆኖ ወይም ከእምነት ጋር ተገናኝቶ አልነበረም ፡፡   
ጋሊሊዮ ጋሊሊ ምንም እንኳን ምድር የምትገኝበት ስርአተ ማእከሉ ፀሀይ ነች ቢልም ይህ ከስነ - መለኮት ጋር ግጭት ያልነበረው ቢሆንም በዘመኑ የነበሩ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን መሪዎችን ግን ሊያስቆጣና ጋሊሊዮ ሀይማኖትን የናደ አስተሳሰብን ያራመደ ነው በማለት በሽምግልና ዘመኑ እስር ቤት ሊጎተት፣ ሊወገዝና ሊከሰሰስ በቅቷል ፡፡ ነገር ግን የጨለማው ዘመን የበዛ አዲስ አስተሳሰብ እንዳይፈጠር ተከላካይት ለሰው ከልጅ ምድራዊ ኑሮውን የሚቆረቁር ማድረጉ እርግጥ ነው ፡፡ የምድራዊ ህይወት ማመር ሃይማኖትን ይፃረራል ወይ የሚለው አከራካሪ ነው ፡፡ የምድር ህይወትን በምቾት የተሟላ ማድረግና በሃይማኖት መሀከል ያለውን ፣ሚዛን የመጠበቅ ጉዳይ ነው ጉዳዩ ፡፡
ፅሃፍ ቅደሱ ፤ላይ ‹‹ነገ ለራ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ ፣ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል›› ማቴ ም 6 ፣ 34 ይላል ፡፡ ክርስቶስ ሲያሰስተም ምን እንበላለን ምን እንጠጣለን ብላችሁ አትጨነቁ ፣ ለሁለት በጌቶች ማለትም ለገንዘብና ለእግዝአብሄር መገዛት አትችሉም ብሎ አስተምሯል ፡፡  
በቀደምቶቹ የግሪክ ፈላስፎች ማለትም በአሪስቶትልና በፕሌቶ መሀከል የነበረው አንዱ ልዩነት የነበረው አሪስቶትል እውነትም ሁሉም ነገር ያለው በዚህ ምድር ነው ሲል አንፃሩ ፕሌቶ በበኩሉ ደግሞ በሰማይ ወይም እላይ ነው የሚል አቋም እንዳላቸው ይታወቃል ፡፡ የክርስትና ሃይማኖት በርካታ የፕሌቶ ሃሳቦችን ሲወስድና ሲጠቀምባቸው በአንፃሩ የአሪስቶትል አስተሳሰቦች ለበርካታ ክፍለ ዘመናት በጥርጣሬ ሲታዩ ቆይተው ከጊዜ በኋላ ነው የተወሰነ ተቀባይትን ሊያገኙ የበቁት ፡፡ ይሁን እንጂ ምንም እንኳን የፕሌቶ አስተሳሰቦች ከአሪስቶትል ይልቅ የረቀቁና ለመረዳት እጅግ ውስብስብ ቢሆኑም ከአሪስቶትል ይልቅ የፕሌቶ አስተሳሰቦች የበለጠ ሀያልና መንፈሰዊም ጭምር ናቸው ማለት ይቻላል ፡፡
ቁሳዊው ወይንም በሃዋርያው ጳውሎስ አጠራር ‹‹ፍጥረታዊው›› ወይንም ቁሳዊው ዓለም የሚጨበጥና የሚታይ ቢሆንም ዘላቂ ግን አይደለም ፡፡ ፕሌቶ ግን በአንፃሩ ፍልስፍናውን መሰረት ያደረገው በማይታየው ዓለም ላይ ሲሆን ሃዋርያው ጳውሎስ ከፕሌቶ ጋር የሚስማማ ሲሆን ሃዋርያው ጳውሎስ ‹‹ፍጥረታዊው ሰው መንፈሳዊውን ዓለም አይረዳውም›› ሲል ገልፆታል ፡፡ የፕሌቶ ፍልስፍና ይህንን የላይኛውን መንፈሳዊውን ዓለም በመረዳት ላይ ያተኮረ ነው ፡፡
ሶስቱ ህልውናን መሰረት ያደረጉና (Existential) ‹‹ኤክዝቴንሽያል›› የሆኑ ጥያቄዎች ስለ ህልውና የሚያነሱ ጥያቄዎች አንደኛው ከየት ነው የመጣነው? ወዴትስ ነው የምንሄደው ? በዚህ ምድር ላይ ምንድነው የምንሰራው ወይም ምንድነው የምናደርገው ? የሚሉት ሶስቱ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው ፡፡
ሃይማኖት ሶስቱንም ጥያቄዎች መመለስ ሲችል በአንፃሩ ግን ሳይንስ ከየት እንደመጣን መላምት ነው እንጂ ቁልጭ ያለ ምላሽ የለውም ፣ወዴት ነው የምንሄደው የሚለውን የጥያቄን በተመለከተም እንዲሁ ሳይንስ የሚያውቀው ነገር የለም ማለት ይቻላል ፡፡ የነፍስን ህልውና ጨርሶ በማይቀበለው በሳይንስ አባባል አንድ ሰው ሲሞት ልክ እንደማንኛውም እንሰሳ ስጋው ይበሰብሳል ፣ የፈራርሳል ከማለት ውጪ ሌላ መልስ የለውም በአንፃሩ ግን ሃይማኖት ለዚህ ምላሽ አለው ይህም መልካም ከሰራ ወደ ገነት ሲገባ መጥፎ ከሰራ ደግሞ ወደ ሲኦል ይገባል ፣ በክርስትና ሃይማኖት እንዲሁ እየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር በሚመጣበት ወቅት አብረን ከክርስቶስ ጋር እንነሳለን ከእርሱም ጋራ ለዘልአለም በገነት እንኖራለን የሚል ምላሽ አለው ፡፡
የሩቅ ምስራቅ እምነቶችም በዚሁ ከሞት በኋላ ስላለው ዳግም መወለድ ሪኢንካሪኔሽን ብለው ሲጠሩት ማለትም ለምሳሌ በቲቤት ቡድሂዝም አንድ ሰው ሞቶ ከተቀበረ በኋላ ከ49 ቀናት በኋላ ተመልሶ ሌላ እንሰሳንም ሆነ ንፋስን ወይም አየርን ማንኛውንም መልክንና ገጽታን ይዞ ዳግም ይወለዳል ፡፡ ቤድሂዝምም እንዲሁ አንድ ሰው ከመቶ በኋላ ዳግም ሲወለድ ሃጢአተኛ ከሆነ ሰው ሳይሆን ሌላ ፍጥረትን ይዞ ይወለዳል ይላል ፡፡
በአንፃሩ ሳይንስ አንድ ምላሽን የሚሰጠው በዚህ ምድር ላይ ምንድነው የምንሰራው የሚለውን ብቻ ነው ፣ ይህም ስራ በመስራት በሳይንሳዊ እውቀት ማደግን መማርን ቴክኖሎጂ መፍጠርን እና በዚህ ምድር ላይ ያለንን ኑሮ ጣፋጭ ማደግን በሚሉት ጉዳዮች ላይ ሳይንስ ከሃይማኖት ይልቅ የተሻለ ምላሽ አለው ፡፡ ነገር ግን ይህንም ቢሆን ለአጭር ጊዜ ነው ምክንያቱም እርሱም ቢሆን ማለትም የአንድ ሰውን ኑሮ በምቾት የተሞላ ማድረግም ቢሆን ከሰውየው እድሜ ጋር የአጭር ጊዜ ቆይታ ያለው ስለሆነ ነው ፡፡
በመካለኛው ዘመን በአውሮፓ የነበረው ትግል ይሄ ነበረ ፡፡ በዘመኑ የነበሩ አሳብያንና ሳይንቲስቶች እግዝአብሄር የካዱ ባይሆኑም ነገር ግን ሃይማኖት ቁጥጥሩ ጠንካራ ስለነበረ ምንም አይነት ምርምርም ሆነ ሳይንሳዊ መፈላሰፍ እንዲኖር አይፈቅድም ነበረ ፡፡
የሳይንቲስቶቹ ዓላማ እንደ አሁኑ ሰብአያን ‹‹ሂውማስት›› (Humanist) ፈላስፋዎች ሃይማኖትን ለመናድ ባይሆንም ነገር ግን የሰውን ልጅ ከምድራዊ ድንቁርና ነፃ ለማውጣትና ሰው በዚህ ምድር ላይ የተሻለ ጤናው ተጠብቆ ፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆንና ስለ አፅናፈ - ዓለም ያለው አመለካከት የተሻለ እንዲሆንና በዙሪያው ያለውን ተፈጥሮን እንዲቆጣጠር ለማስቻል ነበረ እንጂ ሀይማኖት ድረስ ተንጠራርተው የሃይማኖትን መሰረት ለመናድ አልነረበም ፡፡ ዛሬ ቀላል የሆኑና በአንድ መርፌ የሚድኑ ህመሞች አውሮፓ ውስጥ በዚያን በጨለማ ዘመን ሚሊየኖችን ሲጨርሱ ፣ እንደ ጥቁሩ ሞት፣ ጨብጥና ቂጠኝን እና ኢንፍሉዌንዛን የመሳሰሉ በሽታዎች በቀላሉ ብዙዎችን አካለ ስንኩልና ሙት ሲያደርጉ ኖረዋል ፡፡ ይህንንም በማስተዋል ከአጉል አመለካከቶች ነፃ በማውጣትና የሰው ልጅ አሁን ላለበት አንፃራዊ ለሆነ በምቾት የተሞላበት ኑሮ የሳይንቲስቶች አበርክቶ ቀላል አይደለም ፡፡ 
አሁን በዘመናችንም በኢንተርኔት በስማርት ስልኮች ፣ በናኖ ቴክኖሎጂ ፣ በባዮቴክኖሎጂ ፣ በኮምፒውተር ሳይንስ በህክምናው፣ በጠፈር ምርምር ፣በመሳሰለው ዘርፍ ከፍተኛ ምርምሮችና ውጤቶች እየተመዘገቡ ሲሆን እነኚህ ሁሉ ምርምሮችና ውጤቶቻቸው የሰውን ልጅ በዚህ ምድር ላይ ላለው ቆይታ ምቾትንና ረጅም እድሜን እያጎናፀፉ ያሉ ናቸው ፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን የሳይንስ ማደግና አድጎ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ሃይማኖትን ሊገዳደርም ሆነ የሃይማኖትን ቦታ ሊተካ የሚያስችለው አይደለም ፡፡
ለምሳሌ ሰው ሰራሽ ኢንተሊጀንስ (Artificial Intelligence) ወይንም ብንወስድ ሮቦቶች በራሱ በሰው ልጅ የተሰሩ ቢሆንም ስቴፋን ሀውኪንግስ የተባለው ታዋቂው እንግሊዛዊው ሳይንቲስት በሰጠው አስተያየት ግን ሰው ሰራሽ (Artificial Intelligence) ኢንተሊጀንስ ወይንም ሮቦት የሰውን ልጅ ህልውና ስጋት ውስጥ ሊከትና በሰው የተሰራ ሮቦት ራሱን የሰውን ልጅ ከምድረ ገፅ ሊያጠፋ እንደሚችል ስጋቱን ገልጧል ፡፡ ይህ የሚያሳየው የሰው ልጅ በራሱ እውቀት የተፈጠረን ነገር እንኳን መቆጣጠር መቻሉ አጠራጣሪ የሆነ  ፍጡር መሆኑን ነው ፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን በምድር ላይ እየደረሰ ያለው የአካባወቢ የአየር ንብረት ለውጥና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በምድር ላይ ያለው እንሰሳም ሆኑ እፅዋት ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቁ እንዲሁም በሰው የተሰሩ እጅግ አደገኛና አውዳሚ የሆኑ የአቶሚክ ፣ የባዮሎጂካልና የኬሚካል የጦር መሳሪያዎች በዚህ ምድር ላይ ላለ ህይወት ስጋትን መደቀናቸው በየቀኑ የሚታይ ሀቅ ነው ፡፡   
በአሁኑ ዘመናዊ ዓለም ከመካከለኛው ዘመን የሚለይበት ነጥብ አለ ፡፡ ይሄውም በቀድሞው ዘመን ሀይማኖት የሁሉም ነገር መልስ እንዳለውና ስለ ተፈጥሮም ሆነ ስለ ማንኛውም ነገር ምርምርን ማድረግ ሃይማትን እንደመፈታተን ተደርጎ ይወሰድ ነበረ ፡፡ በዚህም በመካለኛው መዘን የጨለማ ዘመን ተብሎ ሊጠራና ሰው ከሃይማኖት በስተቀረ ስለሌላ ስለምንም ነገር እውቀት እንዳይኖረውና እውቀቱንም እንዳያሰፋ ሃይማኖቶት ገድበውት ኖረዋል ፡፡ በመካለኛው ፣ ዘመን ድረስ የነበረው አስተሳሰብ ወደ መንፈሳዊው ዓለም በማድላቱ ምክንያት የሰው ልጅ ሳይንሳዊ እድገት ተጓትቶ ቆይቷል ፡፡ የአሁኑ ዘመን ድግሞ ከዚህ ተቃራኒ በሆነ አቅጣጫ በመሄድ ወደ ሳይንስ እጅግ ያደላ ሲሆን ሁሉም ትኩረት ሳይንስ ላይ ነው ያለው በዚህም ምክንያት ቁሳዊው ነገርን በመፍጠርና በሚታየው ዓለም ላይ ማተኮር የሚታይ ሀቅ ነው ፡፡ 
በዚህም ምክንያት ምድራዊው ህይወቱ በአጉል እምነቶች ፣ እውነት ባልሆኑ ልማዳዊ አስተሳሰቦችና ድርጊቶች ተከብቦ የምድር ህይወቱ ጉስቁልና የበዛበትና በቀላሉ በሚድኑ ህመሞች በሚሊዮኖች ሲያልቅ ፣ አካሉ ሲጎድል ፣ የመኖር አማካይ እድሜው አጭር ሲሆንና በተፈጥሮ አደጋዎች ሲያልቅ ኖሯል ፡፡ ነገር ግን ሳይንስ ከዚህ ሁሉ የሰውን ልጅ ለመጠበቅ ረድቷል፡፡ በአንድ ወቅት ፖርቱጋል ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም የሮማው ካቶሊክ ፖፕ ይህ አደጋ የደረሰባቸው በሰሩት ሀጢአት ምክንያት ነው በማለታቸወስ ምክንያት በዘመኑ የነበሩ የአውሮፓ ፀሀፍት ትችት ተሰንዝሮባቸዋል እንደ ቮልቴርን በመሳሰሉ ፖፑ ተተችተዋል ፡፡ አደጋዎች እግዝአብሄር ህዝቡን ለመቅጣት የሚያመጣው ነው መባሉ ራሱ የሃይማኖት መሪዎችን ምክንያታዊ አስተሳሰብ ካላቸው ፈላፎች ጋር ሲያወዛግብ ኖሯል ፡፡
ለምሳሌ በዛሬው ዘመን የእሳተ ጎመራ በአንድ አካባቢ ሊነሳ ቢል  ወይም የመሬት መንቀጥቀጥ ሊነሳ ሲል ሳይንሳዊ መሳሪያዎች መጠቆም ሲቻል ፣ ዘመናዊ የኢንጂነሪንግ ጥበብን በመጠቀም በመሬት መንቀጥቀጥ በቀላሉ የማይናድ ህንፃዎችን ማነፅ ተችሏል በዚህም ጃፓናውያን አይነተኛ ተጠቃሽ ናቸው ፣ እንዲህም ከባድ አውሎ ነፋስ ቶርኔዶም ይሁን ሁሪኬን አንድን አገር ሊመታ ሲል በቀላሉ እንደ (NASA) ናሳ ባሉ ዓለም አቀፍ የጠፈር ምርምር ተቋማት ከሳተላይት በሚያነሷቸው ፎቶግራፎች በማየት ከአካባዎቹ  በመሸሽ ህይወትን ከጥፋት ማዳን የሚቻልበት ደረጃም ተደርሷል - እነኚህ ሁሉ የሚሊዮኖችን ህይወት የሚታደጉ የሳይንስ ትሩፋቶች ናቸው ፡፡  
በጥንት ዘመን ስነ - መለኮት ‹‹የጥበቦች ሁሉ ንግስት›› (Queen of the Arts) ትባል የነበረ ቢሆንም ፣ በአሁኑ ዘመን ግን ሳይንስ ቦታውን ወስዷል ፡፡ ነገር ግን ሳይንስ በስነ - መለኮት ስር መሆን ሲገባው ከራሱ ተነጥሎ በመውጣቱ ምክንያት የሳይንስና ሀይማኖት ልዩነት እየሰፋና ከመቼውም ይልቅ ሊታረቁ የማይችሉ እየሆኑ ነው ፡፡ ነገር ግን ሳይንስ አዳዲስ ምርምሮችን ባደረገ ቁጥር አዳዲስ ግኝቶችንም ባገኘ ቁጥር የበለጠ ጉልበት ያገኘ ስለሚመስለው ከሃይማኖት እየራቀ እየራቀ በመሄድ ላይ ነው ፡፡
ሩዶልፍ ስቴነር የተባለው ኦከልቲስት እንደሚለው (Evolution) ዝግመተ - ለውጥ ‹‹ኢቮሉሽን›› ምንም እንኳን ሳይንሳዊ መሰረት ቢኖረውም አዝጋሚ ለውጥ የሰውን ልጅ ራሱን ያልፈዋል ይላል ፡፡ የሰው ልጅ ዓለምን መረዳት ከፈለገ ከዝግመተ - ለውጥ ንድፈ ሃሳቦች ማለፍ አለበት ፡፡ እንጂ እዚያው ዝግመተ - ለውጥ ምክንያተዊ በሚመስሉ አስተሳሰቦች ውስጥ ከቀረ ስለ ዓለምም ሆነ ስለ ራሱ ሊያውቅ የሚገባውን ሳያውቅ ይቀራል ፡፡ ሳይንስ መሰረታዊ የሆኑትን ጥያቄዎችን መመለስ ስለማይችል የሃይማኖትን ስፍራ መረከብ መቻሉ አጠራጣሪ ነው ፡፡ 
ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹ምድር የሰው ስትሆን ፣ ሰማይ የእግዝአብሄር ነው ››
ቆላ 3፣3-4 ‹‹ ››
በሰማይ መዝገብህን ሰብስብ እብራውያን በላከው መልእክት ላይ ምእራፍ 10 ላይ ‹‹ለሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በእስራቴ ራራችሁልኝ›› ይህን ሲል የፅድቅ ምንዛሬ ፣ ለዘወትር የሚኖር ፡፡ በዚህ ምድር ላይ ሆኘ በበሰማይ ሂሳብ አለኝ ፡፡



[1] ሜዲካል መፅሄት ፤ቅፅ 1 ፣ ቁጥር 9 ፣ ታህሳስ 2007 ዓ.ም.

No comments:

Post a Comment