Friday, March 22, 2013

የጎንደሩ ስብሰባ

ኢሱ በኢትዮፒያ የውስጥ ጉዳይ ይመለከተዋል ወይ ? ወያኔ ክስልጣን መውረድ አለበት የማለትስ መብት አለው ወይ ?
ይህ ሁሉ ሽብረብ ደፂን ከበባ ውስጥ ለመክተት እንደሆነ መገመት ይቻላል። ደፂን ለመክበብ ባይሆን ኖሮ ሱዳን በጎንደሩ ስብሰባ ላይ ትጠራ ነበረ። 

Friday, March 15, 2013

የነፍስያ ሚስጥር




ነፍስ ምንድነች ? የሚለው ፕሌቶ ልክፍት ይዞት ነበረ ። ፕሌቶ ስለ ነፍስ ብዙ ጥናትን አድርጓል ። ፕሌቶ ሰዎችን በሙያቸው አይነት ሲከፋፍል ለመከፋፈሉ መሰረቱ የነፍስ ጥናት ነው ። የፕሌቶ ክፍፍል ፈላስፋው ንጉስ መሆን አለበት ፣ ጦርነት ወዳዱ ወታደር መሆን አለበት ፣ ወዘተ እያለ ከፋፍሏል ። ሂንዱዎች በተመሳሳይም ብራህሚን ወይም የሂንዱ ቀሳውስት እያሉ ይከፋፍላሉ ። የህንዶች ክፍፍል ግን የተወሰኑ ሰዎችን ዝቅ የሚያደርግ ነው በተለይም አይነኬ በሚል የተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ዝቅ የሚያደርግ በመሆኑ ከህንድ የዲሞክራሲ ስርአት ጋር አብሮ ሊሄድ አልቻለም ።


ነፍስያ ማንኛውንም ሰው የሚገልፅ ነገር ነው ። የጥንት ግብፃውያን «የሙታን መንፈስ» «The Book of the Dead» በተሰኘ እጅግ ታዋቂ በሆነ መፅሀፋቸው ስለ ነፍስ እጅግ ብዙ ብዙ ብለዋል ። ሁሉም ስለ ነፍስ የተፃፉ ድርሳናት እንደሚያመለክቱት ነፍስ የማትሞት እና ዘላለማዊ የሆነች ነገር ነች ። አንዳንድ የዝግመተ-ለውጥ ሳይንቲስቶች ግን ነፍስ የለችም የሚል አቋም አላቸው ። ለምሳሌ ዳውኪንግስ የተባለው እንግሊዛዊ ሳይንቲስት ነፍስ የለችም ብሎ ያምናል ።

የሰውን ልጅ በርካታ ሚስጥሮችን በውስጧ የያዘችው የነፍስ ስትሆን ። በርካታ የአለማችን ሀይማኖቶች የየራሳቸው መንፈሳዊ አዋቂዎች «ሚስቲክስ» አሏቸው ። የነፍስን ምንነት ለመረዳት የረቂቅ መንፈሳዊነት «ሚስቲሲዝም» እውቀትን ይጠይቃል ።  ረቂቅ መንፈሳዊነት «ሚስቲስዝም» የበርካታ ሀይማኖቶች መሰረት ነው ። 

Thursday, March 14, 2013

የምእራባውያን ማቆልቆል



ምእራባውያን በየቀኑ በመገናኛ ብዙሀን በምንሰማቸው ዘገባዎች ቀድሞ የነበራቸውን ተፈሪነት፣ ሀይል ሀብትና አቅም እያጡ እንደመጡ የሚያመለክቱ ናቸው ። የኩባንያዎቻቸውና የባንኮቻቸውና ሌሎች የገንዘብ ተቋማቶቻቸው መክሰር ፣ የአንዳንዶቹም በመንግስት ድጋፍ ህልውናቸው መቆሙ እና ሰራተኛ ማሰናበታቸው ሁሉ  ለምእራባውያን ጤና እንደማይሰጥ ግልፅ ነው ።

Wednesday, March 13, 2013

የመሪዎች ተጠያቂነትና ሀላፊነት

በታሪክ ወደ ኋላ መለስ ብለን ብንመለከት የጥንት ነገስታት የአሁኑን አይነት ተጠያቂነት አልነበረባቸውም ። ሰዎችንና አውሬዎችን በማደባደብ በምትታወቀው በጥንታዊቷሮም ፣ የሮማውያን ነገስታት ካሊጉላንና ኔሮን ብንወስድ ካሊጉላ ሮም ከተማን እናቃጥላትና እስኪ ምን እንደምትመስል እንመልከታት ይል እንደነበርናአቃጥሏትም ያለቅስ እንደነበረ ይነገራል ። ካሊጉላ በዚህ ብቻም ሳይወሰን ፈረሱን ለሴኔቱ ምክር ቤት ለማስመረጥም በቅቷል ። ኔሮም እንዲሁ በርካታ ሮማውያንን የገደለ ሲሆን በእርሱም እንደ አንዳንድ የታሪክ ፀሀፊዎች አባባል አእምሮው አብዶ ነበረ እስከማለት ደርሰዋል ። ይህም በጥንት ዘመን የነበረውን እጅግ የላላ ወይንም ጨርሶ ያልነበረን የተጠያቂነት ስሜት ጨርሶ አለመኖርን የሚያሳይ እና ነገስታት የሚመሩትን ህዝብ እንደፈለጋቸው ይጨፈጭፉ እንደነበረ የሚያሳይ ሲሆን ባስ ካለም የተጠያቂነትና የሀላፊነት ስሜት የማይሰማቸው ነገስታትም የሚያደርሱት ጉዳት እጅግ ከፍተኛ ነው ። 


እንደዛ እንደዛ እያልን ቀረብ ካሉትም ብንወስድ በታሪክ የተፈፀሙ ዘግናኝ የዘር ማጥፋቶች ፣ ጭፍጨፋዎች የመሳሰሉት የተጠያቂነት ስሜት ከመጥፋትና ካለመኖር (Impunity) እና ከእብሪተኝነት ስሜት የመጡ ናቸው ፤ ለምሳሌ ናዚዎች በአይሁዳውያን ላይ ያደረሱት ፍጅት ከዚሁ ተጠያቂነት ካለመኖር ስሜት የመነጨ ነው ፣ ከዛ ወዲህም በአለም ላይ የተከሰቱ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋዎች ከዚሁ ስሜት የተፈፀሙ ናቸው ። አሁን ባለንበት ዘመን ግን ከቀድሞው ዘመናት በአንፃራዊነት የተሻለ ተጠያቂነት የሰፈነበት ዘመን ሲሆን ። አሁን ያለንበት ዘመን ግን መሪዎች በከፍተኛ ደረጃ ተጠያቂነት ሀላፊነት የሚጠየቁበት ዘመን ነው ። የኩባንያ መሪዎችን ብንወስድ የምእራቡ አለም ግዙፍ ኩባንያ ስራ አስኪያጆች ግዙፍ ቦነስ ለራሳቸው እንደሚወስዱ ይታወቃል ። ነገር ግን በቅርቡ ግን የባለአክስዮኖች አመፅና ተቃውሞን (Share Holder Revolt) በማድረግ የኩባንያ መሪዎች የሚወስዱት ቦነስ እንዲቀነስ ማድረግ ችለዋል ። በአሁኑ ወቅት የኩባንያ ሀላፊዎች ጭምር የሚመሩትን ኩባንያ ወደ አላግባብ ወደ ሆነ ችግር ውስጥ ሲከቱና ፣ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በኮንግሬስና በፓርላማ ጭምር ሀላፊዎቹ ተጠርተው እስከመጠየቅ ደርሰዋል ።

በአሁኑ ወቅት በምእራቡ አለም የግዙፍ ኩባንያ መሪዎች ኩባንያቸውን ችግር ውስጥ በሚጨምሩበት ወቅት ወይም ፣ የማጭበርበር ድርጊቶች በሚፈፀሙበት ወቅት ስራ አስኪያጆቹ ወደ ፓርላማና ኮንግሬስ ተጠርተው እንዲጠየቁ ሲደረግ ፣ ከባድ የቅጣት ከገንዘብ እንዲከፍሉና ባስ ካለም ሀላፊነታቸውን እንዲያጡ ፣ በፍርድ ቤት ጭምር ተጠያቂ እንዲደረጉ መደረግ ተጀምሯል ። ለዚህም ምክንያቱ የአንድ ኩባንያ ኪሳራ ምን ያህል ለአለም የሚተርፍ የምጣኔ - ሀብት ቀውስን እንደሚያስከትል ካለፉት ልምዶች በመረዳት ሲሆን ለምሳሌ በ2008 ለአለም የገንዘብ ቀውስ መንስኤ የሆነው ሊማን ብራዘርስ (Lehman Brothers) የተሰኘው የአሜሪካ አራተኛው ግዙፍ ባንክ ጨርሶ መክሰር ሲሆን ፣ የሱን መውደቅ ተከትሎም ከ1930ዎቹ ወዲህ ለመጀመረያ ጊዜ ለአለም ከባድ የምጣኔ - ሀብት ቀውስን ያስከተለው የ2008 የገንዘብ ቀውስ ተከትሎ ለአመታት የምእራብ ሀገራትን ችግር ላይ ጥሎ ቆይቷል ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ተጠያቂነት የሌለበት የኮርፖሬሽን አመራር (Corporate Governance) የሚፈጥረውን ኪሳራ በማወቅ ነው ። በአብዛኛው የኩባንያዎቹ ቦርዶች ውስጣዊ የአመራር ችግሮችን በመሸፋፈን ስለሚያልፉ በዛም ላይ አምነት ካለመኖሩ ልክ የፖለቲካ መሪዎች በቀጥታ ለህዝብ ተጠያቂ እንደሆኑት ሁሉ ፤ በርካታ የአገርን ሀብት የሚያንቀሳቅሱትና ለብዙ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥሩና ብሎም የሀገር ምጣኔ - ሀብት የተመሰረባቸው ኩባንያዎችን ከውድቀት ለማዳንና ግልፅነት የሰፈነባቸው ለማድረግ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ተገኝቷል ። 


በአገር ደረጃ በከፍተኛ የአመራር እርከን የሚቀመጡ መሪዎች ብዙውን ግዜ የህግ ከለላን (Immunity) የሚኖራቸው ሲሆን ይህ ከለላ ግን ሰውየውን ወይንም ግለሰቡን ለመከላከል ሳይሆን መሪው ተግባሩን ያለስጋት በሙሉ የራስ መተማመን መንፈስ እንዲወጣና ስራውን በመስራቱ ወይንም ሀላፊነቱን በመወጣቱ በግል ይመጣብኛል የሚል ስጋት ሳያድርበት ስራውን እንዲሰራ ለማስቻል ነው እንጂ አለአግባብ አንድ ነገርን እንዲያደርግ ወይምን ጥፋትና ወንጀልን እንዲሰራና ከህግ በላይ እንዲሆን ለማበረታትና መሪው እንደ ግለሰብ ራሱን ከህግ በላይ አድርጎ እንዲቆጥር አይደለም ። በእርግጥ በሀገራችን ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ የሚል ይትበሀል አለ ፣ ነገር ግን ይህ በአሁኑ ተጠያቂነት በስፋት እየሰፈነ ባለበት አለም ውስጥ የሚሰራ አይደለም ።

የስነ - ህዝብ ለውጦች

በአለም ላይ በስነ-ህዝብ በኩል መሰረታዊ ለውጦች በመታየት ላይ ይገኛሉ ። በአንድ በኩል የምእራባውያን ህዝብ በእድሜ መግፋትና ማርጀት ብሎም ፣ በእድሜ ለገፉት የሚደረግ የህክምና እና ፣ የጡረታ ወጪዎች ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ የወጣት ቁጥር መመናመን በተለይም በአውሮፓና በጃፓን ይህ በስፋት ተስተውሏል ። አውሮፓውያን እያነሰ የመጣውን ህዝባቸውን ቁጥር ከፍ ለማድረግ የሰራተኛ ሀይል ለማግኘት የግድ ከጎረቤት አገራት የውጭ አገር ዜጎችን ወዳገራቸው ማስገባት ግዴታቸው ነው ፣ በተለይም በህክምናው ዘርፍ እንደ ነርስ የመሳሰሉት ሙያዎች በርካታ ወጣቶችን የሚጠይቁ ናቸው ።


በሌላ በኩል ደግሞ የእስያ ሀገራት እንደ ቻይናና ህንድ ያሉት ደግሞ የስነ - ህዝብ ስብጥር «ዲሞግራፊ» እና የፆታ ቁጥር መዛባት ተስተውሏል ። ቻይና ለአመታት በተከተለችው አንድ ልጅ የመውለድ «One Child Policy» የስነ-ህዝብ ፖሊሲ ምክንያት ወላጆች ለሚወልዱት ልጅ አንድ ልጅ ወንድ ልጆችን በመምረጣቸው ምክንያት የወንዶቹ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ በአንፃሩ ደግሞ የሴቶች ቁጥር መመናመንንና ፣ ወንዶች ለትዳር በሚደርሱበት ወቅት በቂ የሴቶች ቁጥር የማይኖርበት ሁኔታ ሲፈጠር ፣ ቻይናውያን እንደ ፊሊፒንስ ካሉ የጎረቤት አገራት የትዳር አጋር እስከ መፈለግ ደረጃ ደርሰዋል ።


በህንድና በቻይና የፅንሱን ፆታ በመለየት ሴት ከሆነች የማስወረድ ድርጊት ስለሚፈፀም በአስር እና ሀያ አመታት ውስጥ በእነኚህ ሀገራት የስነ-ህዝብ ስብጥሩ እንዲዛባ ምክንያት ሆኗል ። በህንድም እንዲሁ በሴቶች ላይ ለሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶች አንዱ መነሾ ተደርጎ የተወሰደው ነገር ይሄው የሴቶች ቁጥር ከወንዶቹ ጋር ተመጣጣኝ አለመሆን ነው ።

በአንፃሩ አህጉረ አፍሪካ ወጣት የሆነ እና ብዛት ያለው የሰራተኛ ሀይል ያለው ሲሆን ፣ የበርካታ ሀገራት ህዝብ ብዛትም እየጨመረ እንደሚሄድ ይገመታል ። ይህም ለአህጉሪቱ እድልን እና ፈተናዎችን ይዞ እንደሚመጣም ይጠበቃል ። እድሎቹ ሰፊ ገበያ ፣ በቂ ሰራተኛ ሀይል ሲሆኑ ፣ ፈተናዎቹ ደግሞ ባልተሟላ መሰረተ ልማት ላይ የተመሰረተ መሆኑ ለአገራቱ ኢኮኖሚ ፈተና ሊጋርጥ ይችላል ።

Tuesday, March 12, 2013

መሪዎች ሲባል እነማን ናቸዉ?



መሪዎች ሲባል በርካታ ሰዎችን ያጠቃልላል ። በአብዛኛው የተማሩና ሀላፊነት ላይ ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃልል ቢመስልም ከስልጣን ውጪ ያሉና ህብረተሰቡ እንደ መሪዎቹ ከፍ አድርጎ የሚመለከታቸውን የሀይማኖት ሰዎችንም ይጨምራል ።

አርቲስቶችና ሌሎችም ታላላቅ ሰዎች አወቁም አላወቁም የማህበረተሰቡ መሪዎች ናቸው ። የሀይማኖት ሰዎች ፣ ፖለቲከኞችንም ይጨምራል፣ በተለይ አርቲስቶች የሚሰሩት ስራ ዘመን ተሻጋሪ መሆኑን ማወቅ  አለባቸው ። ማንኛውም ህብረተሰቡ በየትኛውም ዘርፍ እሚከተለው ፣ እሚሰማው ሰው ይፋዊ ሶስልጣን ባይኖረውም እንደ መሪ ሊታይ ይችላል ። ለምሳሌ አርቲስቶችን ብንወስድ በይፋ የተሰጣቸው ሹመት ባይበኖራቸውንም ማህወበረሰቡ እንደ መሪው የሚያያቸው ናቸው ። ስራቸውም የማህበረሰቡን ፍላጎትና እምነትን ማንፀባረቅ ይጠበቅበታል ። ያንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ተቀባይነታቸው እየቀነሰ ፣ የሚያሳድሩት ተፅእኖ እየላላ ይመጣና የሚረሱና እንደሌሉ የመቆጠሩ ይሆናሉ ።

አንድ መንግስት ከሱ በታች ያሉ የበለጠ ጉልበት ሊኖራቸዉ አይገባም ወይንም የዛ መንግስት ሀላፊዎች እንደዛ እንዲሆን መፍቀድ የለባቸዉም ።ይህ የዲሞክራሲን ሲፈታተን የህግ የበላይነትንም ይፈታተናል ። ይህም በተደጋጋሚ ዲሞክራሲ አድጎባቸዋል በሚባሉ ሀገራትም ጭምር ታይቷል ።

በኛ ሀገር እያንዳንዱ ሰው በራሱ መሪ መሆኑን አለመረዳቱ በርካታ ችግሮችን ለመፍታትና ፣ ብዙ ሀሳቦችን ለማፍለቅና ለመሰስራት የነበረውን እድል አጥቦታል ። ሁሉም ሰው በየራሱ መንገድ መሪ ሲሆን ፣ እያንዳንዱ ግለሰብ ከቤተሰቤና ከአካባቢው ጀምሮ እንደ መሪ ሊቆጠር የሚችል ነው ።

መሪዎች የግድ የስልጣን ማእረግ ያላቸው ላይሆኑም ይችላሉ ። ምንም አይነት ይፋዊ ማእረግ ባይኖራቸውም ነገር ግን እንደ መሪ የሚቆጠሩ አሉ ። እንደውም ከዋናዎቹ መሪዎች የበለጠ ማህበረሰቡ እንደ መሪም የሚያያቸው ሰዎች በየትኛውም ማህበረሰብ እንዳሉም  ይታወቃል ።

አንድ መሪ ታሪክንና ነገን ተከትሎ ሊመጣ የሚችልን ተጠያቂነትን መፍራት አለበት ። የሚያደርጋቸዉን ነገሮች የነገን ዉጤትም አበክሮ መገንዘብ አለበት ። በአለም ላይ በተራ ወንጀለኞች ከተፈፀሙ ወንጀሎች ይልቅ በስልጣን ላይ ባሉ ሰዎች የተፈፀሙ ወንጀሎች ይበልጣሉ ። ለዚህም ከጀርመን ናዚዎች እንኳን ብንጀምር እና ሌሎችንም በታሪክ ተነሱ አጥፍዎችን መመልከት ይቻላል ።


የመሪነት ድክመቶች



አንድ መሪ ተከታዮቹን መውደድ ሲኖርበት የመሪነት እና የመምራት እድሉን ስለሰጡትም ለተከታዮቹ አክብሮት ሊኖረው ሲገባ ። የዚህ ስሜት የሌለው ከሆነ ግን እነሱን እሱን መተካት ሲችሉ ተከታዮቹ ግን እሱን በሌላ መሪ ሊተኩት ይችላሉ - የሱ ቦታ በቀላሉ በሌላ ሰው ሊተካ ይችላል፤ በተለይም የሀገር መሪ ከሆነ  ። ስለዚህ ራሱን ከተከታዮቹ አስበልጦ መውደድ የለበትም ። ታላላቅ የነበሩ መሪዎች እንኳን ሁሉ በታሪክ ውስጥ ከነሱ በተሻሉ ፣ ባነሱ ወይም ባልተሻሉ መሪዎች ተተክተዋል ። ስለዚህ ለራሱ እጅግ የበዛ ወይም የተጋነነ ቦታን መስጠት የለበትም ። ችግሮችን ከሚገባው በላይ አሳንሶ ማየት ወይንም ቸል ማለት አንድ መሪ ሊፈፅማቸው ከሚችላቸው ስህተቶች አንዱ ነው ።


የአይበገሬነት እና አይሳሳቴነት (Invincibility &Infallibility) ስሜት

በሰው ልጅ ታሪክ እንደታየው በአለም ህዝቦችም ሆነ ኩባንያዎች አመራር ታሪክ ውስጥ በጣም አንፀባራቂ ፣ ዳግመኛ አይፈጠሩም የሚባሉ ሰዎች ተከስተዋል ። ነገር ግን ሁሉም እንደ ሰው የእድሜ ዘመናቸውን ጨርሰው አልፈዋል ። መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የጠቢቡ ንጉስ ሰለሞንን ያህል ግርማ ሞገስና ፣ ክ ብር እና እውቀት የነበረው ንጉስ በታሪክ እንዳልተከሰተ ይነግረናል ። ነገር ግን ጠቢቡ ሰለሞን ምንም እንኳን እጅግ ብልህ እና አዋቂ ቢሆንም መጨረሻ ላይ በሰራቸው ስህተቶች ክብሩ ዝቅ እንዳለና በመጨረሻም እንደማንኛውም መሪ እንዳለፈ በታሪክ የሚታወቅ ነገር ነው ። ከዘመናዊውም አለም የሚጠቀሱ በርካታ መሪዎች ተፈጥረዋል ። ስለዚህ መሪዎች የፈለገ ሀያል ፣ ገናና አዋቂ ቢሆኑም ያለው ትውልድ ስርአትንና ህግን ጠብቆ መኖር ስለሚፈልግ እነሱ ካለፉ ፣ በሌላ ተተክተው ኑሮ መቀጠሉ አይቀሬ ነው ።


አንድ መሪ ራሴን አይተኬ አድርጎ ከወሰደ (Indispensable) ነኝ ብሎ ካሰበ ፣ የማደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው ወደሚል አስተሳሰብ ያመራል ። ይህም የሚያደርጋቸው ነገሮች ውጤታቸውን በአግባብና በቅጡ ሳያመዛዝን እንዲወስንና እንዲፈፅም ሲያደርገው ውሎ አድደሮም ከሚመራው ተቋም ወይም ሀገር ጥቅም አንፃር እሚፃረሩ ውሳኔዎችን እንዲወስንና ፣ ብሎም ከራሱ ጥቅም አንፃር ብቻ እንዲንቀሳቀስ ሊያደርገው ይችላል ። ይህ መሪዎች ሊፈፅሙት ከሚችሏቸው ስህተቶች ትልቁን ቦታ ይይዛል ። ለምሳሌ አንዳንድ አምባገነናዊ አገዛዝ በሚገዙ ሀገራት ውስጥ መሪዎች ለራሳቸው ትልቅ ስፍራን በመስጠት ከሀገርና ከሚመሯቸው ተቋማት በላይ በማሰብ ብዙ ስህተትን እንዱሰሩና ተቃውሞ እያቆጠቆጠባቸው እንዲሄድ ያደርጋል ። 



እነኚህ ስሜቶች አንድ መሪን አደጋ ውስጥ ሊከቱ የሚችሉ ናቸው ፣አንድ ማንኛውም ሰው እንደ ሰው የሚቆጠር ነው ። የሰው ባህርያቶችንም የያዘ ነው ። እንደሰው ይታመማል ፣ ያረጃል ፣ ይሳሳታል ወዘተ … ሰውለሆነም አንድ ሰው ራሱን ከሌሎች የተለየና ሌሎችን የሚጣያጋጥሙ ችግሮች እርሱን እንደማይመለከቱት አድርጎ ማሰብ የለበትም ። አንድ መሪ ተከታዮቹ በሱ አመራር እምንትን በሚያጡበት ጊዜ ውሳኔዎቹ እማይተገበሩ ሲሆን ፣ ትእዛዞቹም ተፈፃሚነታቸው እየቀረ ይሄዳል ። ይህን ሁሉ መሪው ራሱ ወዲያውኑ ላያውቀው ይችላል ። ውሎ አድሮ ሊረዳው ይችላል ። እዚህ ደረጃ ከደረሰ የመሪነቱን ወይም የአመራሩን ውድቀትደረጃ እሚያሳይ ነው ።
ዳዊት በመዝሙሩ «ንጉስን የሰራዊት ብዛት  አያድነውም » ይላል ። ይህም አግባብ የሆነውን ነገር ከማድረግ ይልቅ ባለው ነገር መመካትና ምንም አልሆንም ብሎ ማሰብ የለበትም ።


ግትርነት ወይም ችኮነት (Stubbornness)

ሌላው ደግሞ ለአንድ መሪ ወቅቱን ከመረዳት ጎን ለጎን ራሱን ከሁኔታዎች ጋር ማስማማትና ማዛመድ ያስፈልገዋል ፤ ራሱን ማስማማት ፣ ማዛመድ (Flexibie) መሆን አለበት ፣ ነገር ግን ከእውነታው ውጪ ግትር ከሆነ ግን ራሱን ማዛመድና ማስማማት (Adapt) የማድረግ ብቃቱን ይቀንስበታል በተከታዮቹም ሀፖነ በሌሎች ተመልካቾች ዘንድ እንደ የለውጥ እንቅፋት ተደርጎም ሊቆጠር ይችላል ። ግትርነት ለህመም እንደሚዳርግም በሀኪሞች የታወቀ ነገር ነው ።


ከልክ ያለፈ ጥርጣሬ (Paranoia)

ጤነኛ የሆነ ጥርጣሬ አንድን መሪ ሊመጡ ከሚችሉ አደጋዎች ይጠብቀዋል ። ነገር ግን ጥርጣሬ በመሪው ቁጥጥር ስር ያለ ነገር መሆን አለበት ። ከልክ ያለፈ ጥርጣሬ አንድ መሪን ትክክል በሆነውና ባልሆነው፣ መጥፎ በሆነውና ባልሆነው፣መሆን ባለበትና መሆን በሌለበት ፣በወዳጆችና በተቀናቃቀኞች መሀከል ያለውን ልዩነት እንዳይረዳ ያደርገዋል ። ሁሉንም ነገር በመጥፎ ብቻ እንዲያይና አላስፈላጊ እርምጃዎችን እንዲወስድ ያደርገዋል ። በአጭሩ ካለው እውነታ ውጪ የሆነ አስተሳስብን እንዲይዝ ያደርገዋል ።


ለዚህ ብዙ ጊዜ በምሳሌነት የሚጠቀሰው የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት መሪ ለዚህ ብዙ ጊዜ በምሳሌነት የሚጠቀሰው የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት መሪ የነበረው ጆሴፍ ስታሊን ነው ። በጥርጣሬ ብቻ በርካቶችን ለሞት የዳረገው ስታሊን አሁን አሁን እየወጡ ያሉ የህክምና መረጃዎች የሚያሳዩት የአእምሮውን ጤነኛነት የጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ የህክምና መረጃዎች እየወጡ ነው ። ሀኪሞቹ እንደሚሉት የዛን ጊዜዋ ሀያል ሀገርጤንነቱ አጠያያቂ በነበረ ሰው እጅ እንደነበረች ነው ። ብዙውን ጊዜ አምባገነናዊ የሆኑ መሪዎች በዚህ አጉል ጥርጣሬ ተጠቂዎች ናቸው ።