Tuesday, March 12, 2013

መሪዎች ሲባል እነማን ናቸዉ?



መሪዎች ሲባል በርካታ ሰዎችን ያጠቃልላል ። በአብዛኛው የተማሩና ሀላፊነት ላይ ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃልል ቢመስልም ከስልጣን ውጪ ያሉና ህብረተሰቡ እንደ መሪዎቹ ከፍ አድርጎ የሚመለከታቸውን የሀይማኖት ሰዎችንም ይጨምራል ።

አርቲስቶችና ሌሎችም ታላላቅ ሰዎች አወቁም አላወቁም የማህበረተሰቡ መሪዎች ናቸው ። የሀይማኖት ሰዎች ፣ ፖለቲከኞችንም ይጨምራል፣ በተለይ አርቲስቶች የሚሰሩት ስራ ዘመን ተሻጋሪ መሆኑን ማወቅ  አለባቸው ። ማንኛውም ህብረተሰቡ በየትኛውም ዘርፍ እሚከተለው ፣ እሚሰማው ሰው ይፋዊ ሶስልጣን ባይኖረውም እንደ መሪ ሊታይ ይችላል ። ለምሳሌ አርቲስቶችን ብንወስድ በይፋ የተሰጣቸው ሹመት ባይበኖራቸውንም ማህወበረሰቡ እንደ መሪው የሚያያቸው ናቸው ። ስራቸውም የማህበረሰቡን ፍላጎትና እምነትን ማንፀባረቅ ይጠበቅበታል ። ያንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ተቀባይነታቸው እየቀነሰ ፣ የሚያሳድሩት ተፅእኖ እየላላ ይመጣና የሚረሱና እንደሌሉ የመቆጠሩ ይሆናሉ ።

አንድ መንግስት ከሱ በታች ያሉ የበለጠ ጉልበት ሊኖራቸዉ አይገባም ወይንም የዛ መንግስት ሀላፊዎች እንደዛ እንዲሆን መፍቀድ የለባቸዉም ።ይህ የዲሞክራሲን ሲፈታተን የህግ የበላይነትንም ይፈታተናል ። ይህም በተደጋጋሚ ዲሞክራሲ አድጎባቸዋል በሚባሉ ሀገራትም ጭምር ታይቷል ።

በኛ ሀገር እያንዳንዱ ሰው በራሱ መሪ መሆኑን አለመረዳቱ በርካታ ችግሮችን ለመፍታትና ፣ ብዙ ሀሳቦችን ለማፍለቅና ለመሰስራት የነበረውን እድል አጥቦታል ። ሁሉም ሰው በየራሱ መንገድ መሪ ሲሆን ፣ እያንዳንዱ ግለሰብ ከቤተሰቤና ከአካባቢው ጀምሮ እንደ መሪ ሊቆጠር የሚችል ነው ።

መሪዎች የግድ የስልጣን ማእረግ ያላቸው ላይሆኑም ይችላሉ ። ምንም አይነት ይፋዊ ማእረግ ባይኖራቸውም ነገር ግን እንደ መሪ የሚቆጠሩ አሉ ። እንደውም ከዋናዎቹ መሪዎች የበለጠ ማህበረሰቡ እንደ መሪም የሚያያቸው ሰዎች በየትኛውም ማህበረሰብ እንዳሉም  ይታወቃል ።

አንድ መሪ ታሪክንና ነገን ተከትሎ ሊመጣ የሚችልን ተጠያቂነትን መፍራት አለበት ። የሚያደርጋቸዉን ነገሮች የነገን ዉጤትም አበክሮ መገንዘብ አለበት ። በአለም ላይ በተራ ወንጀለኞች ከተፈፀሙ ወንጀሎች ይልቅ በስልጣን ላይ ባሉ ሰዎች የተፈፀሙ ወንጀሎች ይበልጣሉ ። ለዚህም ከጀርመን ናዚዎች እንኳን ብንጀምር እና ሌሎችንም በታሪክ ተነሱ አጥፍዎችን መመልከት ይቻላል ።


No comments:

Post a Comment