አንድ መሪ ተከታዮቹን መውደድ ሲኖርበት የመሪነት እና የመምራት እድሉን ስለሰጡትም ለተከታዮቹ አክብሮት ሊኖረው ሲገባ
። የዚህ ስሜት የሌለው ከሆነ ግን እነሱን እሱን መተካት ሲችሉ ተከታዮቹ ግን እሱን በሌላ መሪ ሊተኩት ይችላሉ - የሱ ቦታ በቀላሉ
በሌላ ሰው ሊተካ ይችላል፤ በተለይም የሀገር መሪ ከሆነ ። ስለዚህ
ራሱን ከተከታዮቹ አስበልጦ መውደድ የለበትም ። ታላላቅ የነበሩ መሪዎች እንኳን ሁሉ በታሪክ ውስጥ ከነሱ በተሻሉ ፣ ባነሱ ወይም
ባልተሻሉ መሪዎች ተተክተዋል ። ስለዚህ ለራሱ እጅግ የበዛ ወይም የተጋነነ ቦታን መስጠት የለበትም ። ችግሮችን ከሚገባው በላይ
አሳንሶ ማየት ወይንም ቸል ማለት አንድ መሪ ሊፈፅማቸው ከሚችላቸው ስህተቶች አንዱ ነው ።
የአይበገሬነት እና አይሳሳቴነት (Invincibility &Infallibility)
ስሜት
በሰው ልጅ ታሪክ እንደታየው በአለም ህዝቦችም ሆነ ኩባንያዎች አመራር ታሪክ ውስጥ በጣም አንፀባራቂ ፣ ዳግመኛ አይፈጠሩም
የሚባሉ ሰዎች ተከስተዋል ። ነገር ግን ሁሉም እንደ ሰው የእድሜ ዘመናቸውን ጨርሰው አልፈዋል ። መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የጠቢቡ ንጉስ
ሰለሞንን ያህል ግርማ ሞገስና ፣ ክ ብር እና እውቀት የነበረው ንጉስ በታሪክ እንዳልተከሰተ ይነግረናል ። ነገር ግን ጠቢቡ ሰለሞን
ምንም እንኳን እጅግ ብልህ እና አዋቂ ቢሆንም መጨረሻ ላይ በሰራቸው ስህተቶች ክብሩ ዝቅ እንዳለና በመጨረሻም እንደማንኛውም መሪ
እንዳለፈ በታሪክ የሚታወቅ ነገር ነው ። ከዘመናዊውም አለም የሚጠቀሱ በርካታ መሪዎች ተፈጥረዋል ። ስለዚህ መሪዎች የፈለገ ሀያል
፣ ገናና አዋቂ ቢሆኑም ያለው ትውልድ ስርአትንና ህግን ጠብቆ መኖር ስለሚፈልግ እነሱ ካለፉ ፣ በሌላ ተተክተው ኑሮ መቀጠሉ አይቀሬ
ነው ።
አንድ መሪ ራሴን አይተኬ አድርጎ ከወሰደ (Indispensable) ነኝ ብሎ ካሰበ ፣ የማደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው ወደሚል አስተሳሰብ ያመራል ። ይህም የሚያደርጋቸው ነገሮች
ውጤታቸውን በአግባብና በቅጡ ሳያመዛዝን እንዲወስንና እንዲፈፅም ሲያደርገው ውሎ አድደሮም ከሚመራው ተቋም ወይም ሀገር ጥቅም አንፃር
እሚፃረሩ ውሳኔዎችን እንዲወስንና ፣ ብሎም ከራሱ ጥቅም አንፃር ብቻ እንዲንቀሳቀስ ሊያደርገው ይችላል ። ይህ መሪዎች ሊፈፅሙት
ከሚችሏቸው ስህተቶች ትልቁን ቦታ ይይዛል ። ለምሳሌ አንዳንድ አምባገነናዊ አገዛዝ በሚገዙ ሀገራት ውስጥ መሪዎች ለራሳቸው ትልቅ
ስፍራን በመስጠት ከሀገርና ከሚመሯቸው ተቋማት በላይ በማሰብ ብዙ ስህተትን እንዱሰሩና ተቃውሞ እያቆጠቆጠባቸው እንዲሄድ ያደርጋል
።
እነኚህ ስሜቶች አንድ መሪን አደጋ ውስጥ ሊከቱ የሚችሉ ናቸው ፣አንድ ማንኛውም ሰው እንደ ሰው የሚቆጠር ነው ። የሰው
ባህርያቶችንም የያዘ ነው ። እንደሰው ይታመማል ፣ ያረጃል ፣ ይሳሳታል ወዘተ … ሰውለሆነም አንድ ሰው ራሱን ከሌሎች የተለየና
ሌሎችን የሚጣያጋጥሙ ችግሮች እርሱን እንደማይመለከቱት አድርጎ ማሰብ የለበትም ። አንድ መሪ ተከታዮቹ በሱ አመራር እምንትን በሚያጡበት
ጊዜ ውሳኔዎቹ እማይተገበሩ ሲሆን ፣ ትእዛዞቹም ተፈፃሚነታቸው እየቀረ ይሄዳል ። ይህን ሁሉ መሪው ራሱ ወዲያውኑ ላያውቀው ይችላል
። ውሎ አድሮ ሊረዳው ይችላል ። እዚህ ደረጃ ከደረሰ የመሪነቱን ወይም የአመራሩን ውድቀትደረጃ እሚያሳይ ነው ።
ዳዊት በመዝሙሩ «ንጉስን የሰራዊት ብዛት አያድነውም
» ይላል ። ይህም አግባብ የሆነውን ነገር ከማድረግ ይልቅ ባለው ነገር መመካትና ምንም አልሆንም ብሎ ማሰብ የለበትም ።
ግትርነት ወይም ችኮነት (Stubbornness)
ሌላው
ደግሞ ለአንድ መሪ ወቅቱን ከመረዳት ጎን ለጎን ራሱን ከሁኔታዎች ጋር ማስማማትና ማዛመድ ያስፈልገዋል ፤ ራሱን ማስማማት ፣ ማዛመድ
(Flexibie) መሆን
አለበት ፣ ነገር ግን ከእውነታው ውጪ ግትር ከሆነ ግን ራሱን ማዛመድና ማስማማት (Adapt) የማድረግ ብቃቱን ይቀንስበታል በተከታዮቹም
ሀፖነ በሌሎች ተመልካቾች ዘንድ እንደ የለውጥ እንቅፋት ተደርጎም ሊቆጠር ይችላል ። ግትርነት ለህመም እንደሚዳርግም በሀኪሞች የታወቀ
ነገር ነው ።
ከልክ ያለፈ ጥርጣሬ (Paranoia)
ጤነኛ የሆነ ጥርጣሬ አንድን መሪ ሊመጡ ከሚችሉ አደጋዎች ይጠብቀዋል ። ነገር ግን ጥርጣሬ በመሪው ቁጥጥር ስር ያለ
ነገር መሆን አለበት ። ከልክ ያለፈ ጥርጣሬ አንድ መሪን ትክክል በሆነውና ባልሆነው፣ መጥፎ በሆነውና ባልሆነው፣መሆን ባለበትና
መሆን በሌለበት ፣በወዳጆችና በተቀናቃቀኞች መሀከል ያለውን ልዩነት እንዳይረዳ ያደርገዋል ። ሁሉንም ነገር በመጥፎ ብቻ እንዲያይና
አላስፈላጊ እርምጃዎችን እንዲወስድ ያደርገዋል ። በአጭሩ ካለው እውነታ ውጪ የሆነ አስተሳስብን እንዲይዝ ያደርገዋል ።
ለዚህ ብዙ ጊዜ በምሳሌነት የሚጠቀሰው የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት መሪ ለዚህ ብዙ ጊዜ በምሳሌነት የሚጠቀሰው የቀድሞዋ
ሶቭየት ህብረት መሪ የነበረው ጆሴፍ ስታሊን ነው ። በጥርጣሬ ብቻ በርካቶችን ለሞት የዳረገው ስታሊን አሁን አሁን እየወጡ ያሉ
የህክምና መረጃዎች የሚያሳዩት የአእምሮውን ጤነኛነት የጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ የህክምና መረጃዎች እየወጡ ነው ። ሀኪሞቹ እንደሚሉት
የዛን ጊዜዋ ሀያል ሀገርጤንነቱ አጠያያቂ በነበረ ሰው እጅ እንደነበረች ነው ። ብዙውን ጊዜ አምባገነናዊ የሆኑ መሪዎች በዚህ አጉል
ጥርጣሬ ተጠቂዎች ናቸው ።
No comments:
Post a Comment