Tuesday, March 12, 2013

የመግባባት (Communication Skill) ችሎታ





የመግባባት ችሎታ ለመሪነት ብቻም ሳይሆን ለአንድ ሰው የህይወት ስኬት እጅግ ቁልፍ ከሆኑ ክህሎቶች አንዱና ዋነኛው ነው ። እንኳን መሪ ይቅርና አንድ ሰው በህይወት ውስጥ የሚፈልገውን ማንኛውንም ነገር በቀላሉ ሊያገኝና በሚፈልገው መንገድ ለመኖር የመግባባት ክህሎት አስፈላጊ ነው ።

የስነ - ልቦና ባለሙያዎች እንዳረጋገጡት የመግባባት ችሎታ ለመሪው እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ችሎታዎች አንዱ ሲሆን ተግባቦት (Communication) የሚባለው ነገር 64 በመቶው በአካላዊ እንቅስቃሴ መግባባት የሚካሄድበት ሲሆን የተቀረው 36 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በንግግር ፣ በፅሁፍና በስእል መግባባት የሚደረግበት ነው ። መሪም እነኚህን የመግባባት መንገዶችን ጠንቅቆ ማወቅ ሲኖርበት ፣ ይህንን የመግባባት ችሎታን ያልተረዳ መሪ ግን ሊያስተላልፍ የሚፈልገውን መልእክት ሳያስተላልፍ ይቀራል ። መልእክቱን በአግባቡ ካላስተላለፈ ደግሞ ለመምራት ያለውን እድል ይቀንሰዋል ።

አንድ መሪ በአራትና በአምስት አቅጣጫ መግባባት መቻል አለበት ። ከበታቾቹ ጋር ፣ ከእርሱ ትይዩ ካሉ እኩዮቹ ጋ ፣ እንዲሁም ከበላዮቹ ጋርና እንዲሁም ከደንበኞቹ እንዱሁም በአጠቃላይ ከሚያገለግለው ህዝብ ጋር ፣ ሌላው ቀርቶ አንድ መሪ ከጋዜጠኞች ጋር ያለው ግንኙነት ሁሉ ለስኬቱ ወሳኝነት አለው ። በተለይም በእንዲህ አይነቱ ግንኙነት ወቅት ከአለባበሱና ከአነጋገሩ ጀምሮ ስነ - ስርአትን በጠበቀ መልኩ ግንኙነትን መፍጠር አለበት ። ከስርአት ውስጪ የሆኑ ባህሪያቶችን ማስወገድ አለበት ይህም በሌሎች ሰዎች ዘንድ ቅሬታን ሊፈጥር ስለሚችል ሌሎችን እንደናቃቸውና ዝቅ እንዳደረጋቸው አሰድርገው እንዳይወስዱት ያደርገዋል ።

ከዚህም በተጨማሪ ስኬታማ ለሆነ የቡድን ስራ ተግባቦት እጅግ አስፈላጊ ነው ። በቂ ተግባቦት የሌለባቸው የስራ ከባቢዎችመግባባት ከማጣት የታወኩና ውስጥ ውስጡን የማያቋርጥ የእርስ በእርስ ሽኩቻ የሚደረግባቸው ናቸው ።

ለጥሩ ተግባቦች መሪው ራሱን በቅጡ ማወቁ እጅግ አስፈላጊ ነው ። ለምሳሌ መሪው የራሱን እሴቶችን ፣ አስተሳሰቦችን እውነት ብሎ የያዛቸውን ሀቆችን ፣ እንዲሁም የራሱን የተዛቡ አስተሳሰቦችንም  ጭምር የሚያውቅ መሪ ከሌሎችን ጋር በቀላሉ መግባባት ይችላል ። ራሱን በሌሎች ሰዎች ቦታ አድርጎ የመመልከት ልማድ መሪው የሌሎችን ፍላጎትና አላማና ችግር በቀላሉ ለመረዳት ያስቸግረዋል ።ሌሎችንም እንዲሁ ማወቅ አስፈላጊ ነው ። የሌሎችን ስሜት ፣ ፍላጎት ፣ ሀሳብ መረዳትም እንዲሁ ለተሳካ ተግባቦት አስተዋፅኦን ያደርጋል ።

መሪዎች አወዛጋቢ ከሆኑ የስልጣን እድሜአቸውን ያሳጥራል ። አወዛጋቢ መሪዎች በስልጣን የመቆየት እድሜቸው አጭር ነው ። መሪዎች አወዛጋቢ ከሆኑ ብዙ ተቃዋሚዎችን ስለሚያፈሩ ሌሎች ሰዎች በዚያ ስልጣን ሊያቸው አይፈልጉም ፣ ብዙውንም ጊዜ ለሀላፊነታቸው እንዲለቁ ግፊት ይደረግባቸዋል ። መቼ ነው ከስልጣን የሚለቁት የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄም ይቀርብላቸዋል ። በእርግጥ ሁሉም ጠላታቸው ይሆናል ማለት ባይሆንም ፣ ነገር ግን ለስራቸው መቃናት ግን እንቅፋትን ይፈጥርባቸዋል ።

No comments:

Post a Comment