Showing posts with label economic policy. Show all posts
Showing posts with label economic policy. Show all posts

Friday, November 2, 2018

የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ አስፈላጊነት በኢትዮፒያ

የምጣኔ ሃብት ማሻሻያን የማድረግ አስፈላጊነት " ፦

የፋይናንስ ዘርፉ ለኢኖቬሽን (ለስራና አዳዲስ ቴክኖሎጂ ፈጠራ) እንቅፋት መሆኑ ተገለፀ።  የሃገራችን የፋይናንስ (በተለይም የባንክ፥የኢንሹራንስ) ዘርፍ በአፍሪካ አቅም እንኩዋን ተወዳዳሪ አይዶለም። ቅርባችንን ኬንያን ብንወስድ እንኩዋን ያደገ የፋይናንስ ዘርፍ ያላት ሲሆን ያደገ ያክስዮን ገበያ እንዲሁም የሃገሪቱ ባንኮችና ኢንሹራንስ ድርጅቶች በአፍሪካ ተወዳዳሪ ሲሆኑ በምስራቅ አፍሪካ ደቡብ ሱዳንና ኡጋንዳ ድረስ ሄደው መስራት የሚሉ ባንኮች እና የፋይናንስ ተቁዋማት ባለቤት ነች። ብድር ማግኘትም የኛን ሃገር ያህል ከባድ አይደለም በሞባይል ስልኮች የባንክ ብድርን መጨረስ እሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅም አላቸው። በሃገራችን GDP የኬንያን ያለፈ ሲሆን በውጭ ኢንቨስትመንት በመሳብ ኢትዮፒያ ኬንያን አልፋለች። ይህ ሁሉ ግን ተወዳዳሪ የሆነ የባንክ ስርአትን ይፈልጋል። ይሁንና ገዥው ፓርቲ የዚህን ዘርፍ ክፍት ለማድረግ ፈቃደኛ ካለመሆኑም በላይ ሃገሪቱ የWTO ያለም የንግድ ድርጅት አባል እንዳትሆን እንቅፋት ሆኖአል።
በርካታ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ባገሪቱ ተከፍተዋል እነርሱም ያገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ያካባቢውንና ያለም አቀፍ ገበያን ይፈልጋሉ ምርቶቻቸውን ለመሸጥ። የWTO አባል መሆን ኢንዱስትሪዎቹ በቀላሉ የአለም አቀፍ ገበያ ውስጥ እንድትገባና በከፍተኛ የውጭ ብድር የተሰሩት ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመጠቀም ሃገሪቱ ብድራን እንድትከፍል ያስችላታል። ነገር ግን ፓርኩን መስራት ብቻ ሳይሆን ማሻሻያዎችን በማድረግ ፓርኮቹና ምርቶቻቸው በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስችላቸዋል ።