Tuesday, March 12, 2013

የመሪው ችግር ፈቺነት



አንድ መሪ ችግርን የሚፈታ መሆን አለበት አስፈላጊ ከሆኑት ክህሎቶች ዋነኛው ነው ወደ ድርድር ፅንሰ - ሀሳብ ያመራል። ይህም የዲፕሎማሲ ጥበብን የሚጠይቅና ሰፊ ትእግስትን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው በድርድር ወቅት ሁለት አይነት ሰዎች ሲኖሩ አንደኛው ሱቅ ጠባቂ ባለ ሱቆች የሚባሉት ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ተጋፊ ተዋጊዎች የሚባሉት ናቸው ሌላው ደግሞ ተኩሰህ ተደራደር ወይንም ወደ ፊት እየገፋህ ተደራደር (Negotiate While Advancing) በሚለው መርህ መሰረት ነው ይህም የአውሮፓ ነገስታት እና መኳንንቶች እየተንገታገተ የነበረውን የዘውዳዊ ስርአታቸውን እድሜ ለማራዘም  ይጠቀሙበት የነበረ ሲሆን በዚህ እንዲሁም አውሮፓውያን ለግዛትና ለመሬት ብለው የእርስ በእርስ ትግል ውስጥ ገብተው በነበረበት እስከ 17 ኛው 18 ኛው ክፍለ ዘመናት ድረስ በስፋት ይሰራበት የነበረ ነው (የጦርነት ስትራቴጂ ተመልከት»

ለዚህም የሚጠቀሰው ኦስትሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረው ልኡል መተርኒሽ ሲሆን እንደ ናፖሌዎችን ያለ ሀያልን ለማንበርከክ ተጠቅሞበታል በእርግጥ በድርድር ወቅት አንዳንድ ለድርድር ሊቀርቡ የማይችሉ (Uncompromisable) የሆኑና ለድርድር ሊቀርቡና በድርድር መቀራረብ እና መግባባት ሊፈጠርባቸው የሚችሉ ሀሳቦች አሉ
 
አንዳንድ ጊዜ አለቅጥ ፍትሀዊ (Fair) ለመሆን ስንሞክር መሞከር ፣መሪዎችን ከጥሩ አላማ በመነሳት ብለው የሚያደርጉት ነገር ወደ ስህተት ወይንም እንደ ሞኝ የሚያስቆጥር ነገሮችን እንዲሰሩ አድርጎ ፍትሀዊነቱ ወደ ተዛባ ድርጊትን እንዲያደርጉ ሲያደርጋቸው ይስተዋላል ለምሳሌ አንድ መንግስት ፍትሀዊነት የዩንቨርስቲ ስርጭትን ለመጠበቅ በሚል በርካታ ዩንቨርስቲዎችን በተለያዩ የአገሪቱ ክልል ቢከፍት ነገር ግን ለጥራት ትኩረትን ካልሰጠ ምንም እንኳን ዩንቨርስቲዎች ስርጭታቸው ፍትሀዊ ነው ቢባልም ጥራታቸውን የጠበቁ ካልሆኑ ግን የታለመለትን የፍትሀዊነትን ግብ ሳይመታ ይቀራል ይህ ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ዩንቨርስቲዎችን ከመክፈት ይልቅ እየተዳከመ ያለውን የትምህርት ቤቶችን ማጠናከር የበለጠ አስፈላጊ ሆኖ ሊገኝ  ይችላል አሁንም በተደጋጋሚ እንደምንሰማው የፍትህ መስፈን መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እንደ አንድ መሰረታዊ አስፈላጊ ጉዳይ ተደርጎ ይወሰዳል


የፀና የፍትሀዊነት ስሜት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት አስፈላጊና ቁልፍ ጉዳይ ነው ታላቁ የምእራቡ አለም ፍልስፍና መስራች ፕሌቶ ዋናው የፍልስፍናው እንብርት የነበረው ጉዳይ ፍትህ ነው ይህም እንደ ፕሌቶ እምነት የፖለቲካ ፍልስፍና ዋና አላማው ፍትህን ማስፍን ሲሆን ነገር ግን የፍትህ መስፈን በቀላሉ የሚመጣ አይሆንም ፍትህ በተለያዩ ምክንያቶች ላይሰፍን ይችላል ፍትህን ያሰፈነ መሪ ዋናውን ተግባሩን እንደተወጣ ይቆጠራል ።ነገር ግን ታሪክ በአሸናፊዎች እንደሚቀረፀውና እንደሚፃፈው ሁሉ ፍትህም በአሸናፊዎች አማካይነት የሚተገበር ነገር ነው ፍትህን የሚተረጉሙትና ተግባር ላይ የሚያውሉት አሸናፊ የሆኑ ወይንም ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ቢሆኑም ነገር ግን መሰረታዊ በሆነ ሁኔታ ግን የማይጣሱ መርሆዎች አሉት የሀራችን ፍትሀ - ነገስት ስጋዌና መንፈሳዊ የፍትህ አሰራሮችንና አካሄዶችን ይዘረዝራል የስጋዌ የፍትህ ዝርዝራሩ የሀገራችን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት እንደሆነ ይታወቃል


ሌሎችን ለመረዳት መሞከር እንዲሁም (Compassionate) መሆን ለመሪዎች አስፈላጊ ክህሎት ነው ተብሎ ይታመናል ይህም ግን በሀይማኖት መሪዎች ዘንድ በተደጋጋሚ የሚነሳ ጉዳይ ነው ታላላቆቹ የአለማችን ሀይማኖቶች ከተመሰረቱባቸው አስተምህሮቶች አንዱና ዋነኛው ይሄው የእዝነት ወይንም እራሮት ጉዳይ ነው ነገር ግን እዝነት ማለት መሪው ጥፋትን እያየ ይለፍ እንዲሁም ትክክል ያልሆነ ነገርግን ለሌሎች ለማዘን ሲል ብቻ ያድረግ ማለት አይደለም እንደውም እንደዛ ካደረገ ስራ የማይሰራበት ሁኔታን ይፈጥራል እንዲሁም መዝረክረክንና የመሪው አመራር በመላሸትን ይፈጥራል


ለዳኝነት አንድ ሰው እድሜው እየገፋ ሲሄድ ለተዛቡ አመለካከቶች (Prejudice) ይጋለጣል የሚል ግምት አለ ከዚህ ይልቅ ዳኝነት መካከለኛ እድሜ ላይ ያሉ ሰዎች የተሻለ ዳኝነትን ሊሰጡ ይችላሉ ለምሳሌ በቤተሰብ ውስጥ ያለ ችግርን መፍታትና በአንድ የቢሮክራሲ መዋቅር ውስጥ ያለ ችግርን መፍታት የየራሳቸው የሆነ አቀራረብንና መፍትሄን እና አካሄድን ይጠይቃሉ

No comments:

Post a Comment