Friday, March 15, 2013

የነፍስያ ሚስጥር




ነፍስ ምንድነች ? የሚለው ፕሌቶ ልክፍት ይዞት ነበረ ። ፕሌቶ ስለ ነፍስ ብዙ ጥናትን አድርጓል ። ፕሌቶ ሰዎችን በሙያቸው አይነት ሲከፋፍል ለመከፋፈሉ መሰረቱ የነፍስ ጥናት ነው ። የፕሌቶ ክፍፍል ፈላስፋው ንጉስ መሆን አለበት ፣ ጦርነት ወዳዱ ወታደር መሆን አለበት ፣ ወዘተ እያለ ከፋፍሏል ። ሂንዱዎች በተመሳሳይም ብራህሚን ወይም የሂንዱ ቀሳውስት እያሉ ይከፋፍላሉ ። የህንዶች ክፍፍል ግን የተወሰኑ ሰዎችን ዝቅ የሚያደርግ ነው በተለይም አይነኬ በሚል የተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ዝቅ የሚያደርግ በመሆኑ ከህንድ የዲሞክራሲ ስርአት ጋር አብሮ ሊሄድ አልቻለም ።


ነፍስያ ማንኛውንም ሰው የሚገልፅ ነገር ነው ። የጥንት ግብፃውያን «የሙታን መንፈስ» «The Book of the Dead» በተሰኘ እጅግ ታዋቂ በሆነ መፅሀፋቸው ስለ ነፍስ እጅግ ብዙ ብዙ ብለዋል ። ሁሉም ስለ ነፍስ የተፃፉ ድርሳናት እንደሚያመለክቱት ነፍስ የማትሞት እና ዘላለማዊ የሆነች ነገር ነች ። አንዳንድ የዝግመተ-ለውጥ ሳይንቲስቶች ግን ነፍስ የለችም የሚል አቋም አላቸው ። ለምሳሌ ዳውኪንግስ የተባለው እንግሊዛዊ ሳይንቲስት ነፍስ የለችም ብሎ ያምናል ።

የሰውን ልጅ በርካታ ሚስጥሮችን በውስጧ የያዘችው የነፍስ ስትሆን ። በርካታ የአለማችን ሀይማኖቶች የየራሳቸው መንፈሳዊ አዋቂዎች «ሚስቲክስ» አሏቸው ። የነፍስን ምንነት ለመረዳት የረቂቅ መንፈሳዊነት «ሚስቲሲዝም» እውቀትን ይጠይቃል ።  ረቂቅ መንፈሳዊነት «ሚስቲስዝም» የበርካታ ሀይማኖቶች መሰረት ነው ።