Tuesday, April 2, 2013

የስልጣኔዎች አወዳደቅ



ብዙዎቹ ማለት ይቻላል መሰረታዊ የጂኦሜትሪ ህግጋትን ደርሰውባቸው ነበረ ማለት ይቻላል ፣ ማያዎች እንኳን ከሌላው አህጉር ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው ከግብፃውያን ፒራሚድ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ፒራሚዶችን ማነፅ ችለዋል ። ዳር ዳሩ ማእዘኑ ላይ ደረጃ የወጣለት ከመሆኑ በስተቀር የማያዎች ፒራሚድ ከግብፃውያኑ ጋር በቅርፅም ሆነ በመልክ ተመሳሳይ ነው ፣ በእኛም ሀገር አክሱማውያን በተመሳሳይ መንገድ ቀጥ ያሉ ሀውልቶችን ሲገነቡ በእነኚሁ መሰረታዊ የጂኦሜትሪና የሂሳብ ህግጋት እየተመሩ እንደሆነ ግልፅ ነው ።

አንድ ሰው የጥንቶቹን ስልጣኔ ባለቤቶችን በኮኮብ ቆጠራ ማመናቸውን አለማወቅና የዋህነት ነው ሊል ይችላል ፣ ነገር ግን የጥንቶቹ ሰዎች አላዋቂዎች እልነበሩም ፣ ነገር ግን ታላላቅ ፒራሚዶችን ከሰሜን አፊረካ ፣ ምስራቅ አፍሪካ አሜሪካ ድረስ የገነቡ ነበሩ ። የሂሳብን ፣ የፊዚክስን እንዲሁም የጂኦሜትሪን ህግጋትን በራሳቸው ጊዜና መንገድ ድረሰውባቸዋል ።

ለምሳሌ ከጥንት ስልጣኔ ባለቤቶች ዋነኞቹ የነበሩትን የጥንት ግባብፃውያንን ብንወስድ  ስልጣኔአቸው ለሶስት ሺ ዘመናት ዘልቋል ። በሺ ለሚቆጠሩ ዘመናት የዘለቀው የጥንታዊ ግብፃውያን ስልጣኔ በመንፈስ በኩል እንዲሁም በሀይማኖትና በሂሳብ በሳይንስ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሰው የነበሩ ሀያላን ነበሩ ።

በአለም ላይ በርካታ ስልጣኔዎች ውድቀታቸው ከምን የመነጨ ነው ? ብዙዎቹ ስልጣኔ ዎች መሰረታቸው በተቃርኖ ላይ ነው ። ይህም ለኋላ ኋላ ውድቀታቸው በርን የሚከፍት  ሲሆን ፣ በተፈጥሮ አደጋ ከጠፉት የሰው ልጅ ስልጣኔዎች በስተቀር ፣ማለትም በመሬት መንቀጥቀጥ ፣ በእሳተ-ገሞራ ፣ በሱናሚ ከመሳሰለው ባልተጠበቀ የተፈጥሮ አደጋ ከጠፉት ውጪ ብዙዎቹ ስልጣኔዎች የራሳቸውን መቃብር ራሳቸው ቆፍረው ሊሆን ይችላል ተብሎ ይገመታል ።

No comments:

Post a Comment