ፕሬዝዳንት ኦባማ በ2014ዓ.ም.
በተደረገው የህዝብ አስተያየት መለኪያዎችን እንደሚያመለክቱት እ.ኤ.አ ከ1940ዎቹ ወዲህ የመጀመሪያው ዝቅተኛው የህዝብ ድጋፍ ያላቸው
ፕሬዝዳንት ሊሆኑ በቅተዋል ፡፡ ውሳኔን ለማሳለፍ ጥንቃቄን በማብዛታቸው በተለይም ሪፐብሊካን ዘመም የሆኑ በርካታ አሜሪካውያንን
ያበገኑት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ኦባማ በ2014 ጥቅምት ወር ላይ በተደረገው የመካከለኛው ዘመን (Mid Term) ምርጫ ወቅት የዲሞክራቲክ
ፓርቲው ክፉኛ በተሸነፈበት ወቅት ይህንንም በማየት የራሳቸው የዲሞክራቲክ ፓርቲው አባላት ጭምር ለመጪው ምርጫ አይረዳንም በማለት
ራሳቸውን ከኦባማ ሲያርቁ ተስተውለዋል ፡፡ ይህን ተከትሎም ‹‹ሰምቻችኋለሁ››፤
‹‹አድምጫችኋለሁ›› ቢሉም
ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ ሆኖባቸዋል ፤ የስልጣን ዘመናቸው እያበቃ በሄደበትና ኮንግሬሱና ሴኔቱ በሪፐብሊካን እጅ በወደቀበት እና አብዛኛውን
የስልጣን ዘመናቸውን ባገባደዱበት ሁኔታ ‹‹አድምጫችኋለሁ
፣ ሰምቻችኋለሁ ›› ማለት እምብዛም የሚያመጣው ለውጥ የለም ፡፡
ኦባማ በኢሚግሬሽን ላይ የያዙት አቋም
፣ ከቻይና ጋር የአየር ንብረትን ለውጥን በተመለከተ የያዙት አቋምና ከሀዲ ያስባላቸውን በኩባ ላይ የያዙትን አቋም ከሀዲ እስከመባል
ድረስ አድርሷቸዋል ፡፡ በእነኚህ አቋሞቻቸው ከሁለቱም ከዲሞክራትም ከሪፐብሊካንም ፓርቲዎች ትችት አዝንቦባቸዋል፡፡ በተለይ በኩባ
ላይ ማእቀቡን ለማንሳት መወሰናቸው ሪፐብሊካኖችን ሲያበሳጭ ፣ ከቻይና ጋር የአየር ንብረትን በተመለከተ የያዙት አቋም ደግሞ ዲሞክራቶችንም
ጭምር አበሰጭቷል፡፡
በእርሳቸው የፕሬዝዳንትነት ዘመን የቀድሞው የሲ አይ ኤው ዳይሬክተርና የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ሊዎን
ፓኔታ እንዳሉት ፕሬዝዳንት ኦባማ ከነገሮች ሸሽተዋል (Disengaged) ወይንም ከእውነታው ራሳቸውን አርቀዋል ብለዋል ፣ ማለትም አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ፣
በቶሎ መወሰንና የአሜሪካን ጥቅም በሚስጠብቅ መልኩ መሳተፍ ሲገባቸው ነገር ግን ጦርነትን በመፍራትና ፣ ምጣኔ ሀብቱ ላይ ጉዳት
ይደርሳል በሚል እንዲሁም የአገር ውስጥ የህዝብ ድጋፍ አይኖርም በሚል ፍራቻ አሜሪካንን ቁልፍ ከሆኑ ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ላይ እንድትገለልና
ተሰሚነቷ እንዲቀንስ አድርገዋል ፡፡ የፕሬዝዳንት አሳድ መንግስት በራሱ ህዝብ ላይ የኬሚካል የጦር መሳሪያ በተጠቀመበት ወቅት በአውሮፕላን
እንዲደበደብ ወስነው ሲያበቁ እንደገና ውሳኔያቸውን አጥፈውታል ፡፡ የህዝብ አስተያየት መለኪያዎችም ያመለከቱት እርምጃ እንዳይወሰድ
ቢሆንም ፣ ከአሳድ መንግስት ጋራ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ያላቸው የሩስያው ፕሬዝዳንት ጭምር አየር ድብደባቸውን በመቃወም በኒውዮርክ
ታይምስ (New York Times) ጋዜጣ ላይ ተቃውሞ እስከመፃፍ ሲደርሱ ኦባማ ውሳኔያቸውን ትተውታል ፡፡ የኦባማ አሜሪካንን ከዋና
የዓለም ዓቀፍ ፖለቲካ ተሳታፊነት ውጪ ማድረጋቸው የፈጠረው የሀይል ክፍተት በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ በግልፅ የታየ ነው ፡፡
ፕሬዝዳንት ኦባማ
ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በአሜሪካውያን መሀከል ያለው የዘር ግንኙነት የተበላሸበትና የበለጠ የዘር ውጥረት የሰፈነበት መሆኑ አስገራሚ
ነው ፡፡ በዚህም በርካታ ጥቁሮች በፖሊሶች የተገደሉበትና ይህንንም በመቃወም ሰላማዊ ሰልፎችና በየከተሞቹም ረብሻዎች የታዩበት ሆኗል
፡፡ እነኚህ ጉዳዮች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ያስብላሉ ወይስ አያስብሉም በሚል በፍ/ቤቶች ጭምር ቢታዩም ገዳዮቹን ተጠያቂ ባለማድረጋቸው
ምክንያት የአፍሪካ አሜሪካውያንን ቁጣ አባብሷል፡፡
ፕሬዝዳንት ኦባማ
አሜሪካን ለመወጥ ‹‹ለውጥ›› በሚል መፈክር ወደ ስልጣን ቢመጡም ወደ ስልጣን ቢመጡም ራሷ አሜሪካ
ነች ፕሬዝዳንቱን የለወጠችው ሲሉ የኦባማን የስልጣን ዘመን የተከታተሉ አስተያት ሰጪዎች ይናገራሉ ፡፡
ይህን ተከትሎም በአካባቢው የሀይል
ክፍተት መፈጠሩን የተጠቀመው ISIS አይ ኤስ አይ ኤስ የተሰኘው የመካከለኛው ምስራቅ ሶሪያንና ኢራቅን በከፊል የተቆጣጥሮ እያመሰ
ያለውን ዓለም ዓቀፍ ታጣቂ እስላማዊ ድርጅት መግታት አልቻሉም ፣ እንዲሁም የሶርያው ጦርነት አውዳሚና አጥፊ ሲሆን እና ወደ ኢራቅ
ሲዛመት፣ሊባኖስን ሲከፋፍልና ስጋት ሲደቅን እርምጃን ሳይወስዱ ቀርዋል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አይ ኤስ አይ ኤስ ላይ እርምጃን ለመውሰድ
ኮንግሬስ ድጋፉን ይግለፅልኝ ማለታቸውም እንዲሁ ወሳኝ እርምጃን ለመውሰድ ቁርጠኝነቱ እንደሚያንሳቸው አመላክቷል ፡፡ እንዲሁም በአለም
ላይ የኢቦላ በሽታ በአደገኛ ሁኔታ ሲዛመት ተገቢውን ፈጣን እርምጃ መውሰድ አልቻሉም ተብለው ተነቅፈዋል ፡፡
ከዚህ ይልቅ ለኢራኑ ፕሬዝዳንት የሚስጥር
ደብዳቤ መፃፋቸው ኢራን የኒውክሊየር መሳሪያን በተመለከተ ከምእራባውያን ጋር በቶሎ መስማማት ከቻለች አሜሪካ ከኢራን ጋር አይ ኤስ
አይ ኤስን በመግታት በኩል ለኢራንም ሆነ ለአሜሪካ ጠላት የሆነውን (ISIS) አይ ኤስ አይኤስን ለመግታ አብረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል
፡፡ ይሁን እንጂ ኦባማ በዚህ በኩል ስሌት ስህተት የሰሩ ይመስላል ለዚህም ምክንያቱ በአካባቢው ለምእራባውያንም ሆነ ለእስራኤል
በረጅም ጊዜ አስጊ የምትሆነው ኒውክሊየር ልትታጠቅ የምትችልና የበለጠ ጠንካራ የሆነችዋ ኢራን ነች እንጂ (ISIS) አይ ኤስ አይ
ኤስ አይደለም ፡፡ እርግጥ ነው ለዚህም ዋናው ምክንያት አይ ኤስ አይ ኤስ ምንም
እንኴን የአልቃኢዳ አምሳያ ቢሆንም ውሎ አድሮ ግን (ISIS)
አይ ኤስ አይ ኤስ ተሸናፊ መሆኑ የማይቀር ሲሆን ጠንካራዋንና ኒውክየር ለመታጠቅ
የምትንደረደረው ኢራን ግን የበለጠ አደገኛ መሆኗ ለምእራባውያን የማይጠፋቸው ሀቅ ነው ፡፡ ከታሊባንና ከናይጄሪያው ቦኮሀራም ጋራ
ተመሳሳይ የሆነው (ISIS) አይ ኤስ አይ ኤስ ህልውናው የረጅም ጊዜ እንደማይሆን መገመት ይቻላል ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዝዳንት
ኦባማ የስደተኞች ጉዳይን ለብዙ ወራት ኮንግሬሱ እንዲያፀድቁ ሲማጠኑ
የነበረ ቢሆንም ኮንግሬሱ ግን የኦባማን ፖሊሲን ለማፈን በሚመስል ሁኔታ አላፀድቅም
ብሎ አንጀታቸውን ሲያሳርረው ከቆየ በኋላ ከሚድ ተርም ምርጫ በኋላ ግን ራሳቸው ፕሬዝዳንታዊ ትእዛዝን በማውጣት ለእነኚህ ቁጥራቸው
ከአምስት ሚሊዮን በላይ ይገመታል ለሚባሉ በህገ ወጥ መንገድ አሜሪካ ይገኛሉ ለተባሉ ሰዎች ምህረትንና ጊዜያዊ የስራና የመኖሪያ
ፈቃድን ለመስጠት መወሰናቸው በአለም ዙሪያ በተለይም እንደ ሜክሲኮ ፣ፔሩ ባሉ አገራት ከፕሬዝዳንቶቻቸው ጭምር ይበል የሚያሰኝ ድጋፍን
ቢያሰጣቸውም የራሳቸው ኮንግሬስ ግን እከሳቸዋለሁ እስከማለት ደርሷል ፡፡
በህገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካን ሃገር
ገብተው ከአምስት አመታት በላይ ለኖተሩትና ለክልጆች ላላቸው ከነልጆቻው ለጊዜውም ቢሆን ምህረትን የሚደርገው የኦባማን ኢምግሬሽን
አዋጅ እንዲያፀድቀው የተጠየቀው ኮንግሬስ በዝምታ አመታትን በማስቆጠሩ ፕሬዝዳንታዊ ስልጣናቸውን በመጠቀም ለእነኚህ ሰዎች እፎይታን
ያመጣ አዋጅን ማፅደቃቸው በአብዛኛው በተለይም ከላቲን አሜሪካ አገራት በርካቶቹ ስደተኞች ከሚገኙበት ድጋፍን ሲያስገኝላቸው የራሳቸው
አገር በተለይም የሪፐብሊካን ፓርቲ ምክር ቤት አባላትን በእጅጉ አንጨርጭሯል ፡፡
በዚህ ፖሊሲ የምክር ቤት አባላቱ
ሃሳብ ከተግባር የራቀ ነው ለምን ቢባል አሜሪካ አምስት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ከአገር አባርራለሁ ብላ ብትነሳ በዓለም ውግዘትን
የሚያተርፍላት ነው የሚሆነው እንጂ አያስመሰግናትም ስለዚህ የኦባማ ሃሳብ ከተጨባጭ እውነታው ጋር ቅርብ ነው ማለት ይቻላል ፣ ሪፐብሊካን
የሆኑ የኮንግሬስ አባላትም ቢሆኑ እነኚህን ሰዎች ሊያባርሩ አይነሱም ፣ነገር ግን እንዲሁ ሰዎቹ ያለ ህጋዊ መኖሪያና ስራ ፈቃድ
ሲታሹ ይኖራሉ እንጂ ጉዳዩ ውሳኔን አያገኝም ነበረ፡፡
እዚህ ላይ የኦባማ ውሳኔ ስሌትን
የያዘ ይመስላል ፣ ለምን ቢባል ፓርቲአቸው በሚድ- ተርም ክፉኛ ስለተሸነፈ ፣ የዚህን ሽንፈት ለመበቀልና ለመጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ
የላቲኖችን ድምፅ ሰጪዎችን ድጋፍ ለፓርቲአቸው ለማስገኘት መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ ለመጪው እ.ኤ.አ በ2017 ለሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ
ምርጫ ለዲሞክራቶች ይህ ወቅታዊ ውሳኔ የበለጠ ጉልበትን የሚሰጥ መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ ለዚህም በመጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ይወዳደራሉ
ተብለው የሚጠበቁት ሚስ ሂላሪ ክሊንተን በትዊተር ገፃቸው ላይ ድጋፍ መስጠታቸው ነው ፡፡ በ2017 ዓ.ም. ለመመረጥ እድላቸው ጠቦ
የነበረው ዲሞክራቶች ለመጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የቀራቸውን የመጨረሻውን ካርድ ማለትም የኢምግሬሽንን ካርድ መምዘዛቸው መሆኑ ግልፅ
ነው ፡፡
ከኢምግሬሽን (Emigration)
በተጨማሪም ኦባማ በኩባ ላይ በተናጠል የአስፈፃነት ስልጣናቸውን በመጠቀም በኩባ ላይ የተጣለውን ማእቀብ አንስተውታል ፡፡ ፕሬዝዳንት
ኦባማ ኪዩባ ላይ የነበረውን በ እ.ኤኤ ከ 1954 ጀምሮ ተጥሎ የነበረውንንና በኩባ ላይ 1.1 ትሪሊየን ዶላር ኪሳራ ያደረሰውን
ማእቀብ ማንሳታቸው ከላቲን አሜሪካን አገራትና ከራሳቸው የአሜሪካ ህዝብም ጭምር እና ከአለም ህዝብም ጭምርን ድጋፍን ሲያስገኝላቸው
፣ አሜሪካ ከሩስያ ጋራ ባለባት ውዝግብ ኩባን እንደ ቀድሞ እንደ ኬኔዲ ጊዜ ወደ ሩስያ እቅፍ እንዳትገባ ነው ፣ ሲሉ አጥባቂ ሪፐብሊካኖች
የሰማቸው የለም ፣ እንጂ በኩባ ላይ የተጣለው ማእቀብ መነሳት ያለበት በኩባ ዲሞክራሲ ሲሰፍን መሆን አለበት ብለው ተከራክረዋል
፡፡
ኦባማ በኩባ ላይ የተጣለውን ማእቀብ
ዘመን ያለፈበትና አላፈላጊ ነው በማለት ማእቀቡ እንዲነሳ አዘዋል ፡፡ በሃምሳ አመታት ውስጥ በጣም አስፈላጊው ለውጥ ነው ሲሉ ነገር
ግን ይህ በኮንግሬስ መጽደቅ ያበት ቢሆንም ይሁን እንጂ ኦባማ በኩባ ላይ የተጣለውን ማእቀብ ማንሳታቸው አንድ ትልቅ የፕሬዝዳንትነታቸው
መልካም ውጤት ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን አሁን ባይሆን ፕሬዝዳንት
ኦባማ በታሪክ የሚሰጣቸው ስፍራ ወደፊት ከአሁኑ የተሻለ እንደሚሆን መገመት ይቻላል ፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያቱ የአሜሪካንን ምጣኔ
ሀብት ከወደቀበት ማንሳታቸው እንዲሁም እርሳቸው ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሶ ከነበረበት ወቅት አንስተው
የተሻለ ማድረጋቸው ፣ የስራ አጥ ቁጥሩን ከመጡ በኋላ በእጅጉ እንዲቀንስ ማድረጋቸው ፣ እንዲሁም ከብዙ ትግልና ውዝግብ በኋላ የአሜሪካውያንን
የጤና መድህን ሽፋን ለመጀመሪያ ጊዜ ፖሊሲ ማውጣታቸው ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ አዋጁ በርካታ ድክመቶች ቢኖሩትም እነኚህ ተጠቃሽ
የሆኑ የኦባማ የአስተዳዳር ውጤቶች ናቸው ፡፡
የአሜሪካ ምጣኔ ሐብት
የአሜሪካ ምጣኔ ሀብት ችግር ያለበት
የተወሳሰበ ችግር ያለበት ሲሆን ከ1970 ዎቹ ወዲህህ አሜሪካ ኢንዱስትሪዎቿ ከጃፓን ኢንዱስትሪዎች ጋር መወዳደር እያቃታት ወዲህ
ችግሩ በጊዜ በውስጥ እየተባባሰ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ጃፓን ብቻ ሳትሆን የጃፓን ጎረቤት የሆኑ የእስያ ሀገራት እንደ ደቡብ ኮርያ
፣ ታይዋንና ግዙፏ ቻይናም ጭምር የአሜሪካንን ኢንዱስትሪዎች የመወዳደር አቅም በእጅጉ እየፈተኑ ይገኛሉ ፡፡
ይህ ብቻ ሳይሆን አሜሪካ ከመስረም
11ዱ የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ በኢራቅና በአፍጋኒስታን የገባቻቻው ጦርነቶች ትሪሊዮኖች ዶላሮቿን እሳት ያየው ቅቤ ሲያደርግ ፣ሀገሪቱ
በእዳ መዘፈቋ ሳያንስ ጦርነቱ ይባስ ብሎ አገሪቱን አክስሯል ፡፡
ኩባ ላይ የተጣለው የ54 አመት ማእቀብ መነሳት
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ኦባማ ከኮንግረስ
ጋር አብረው በመስራት ኩባ ላይ የተጣለውን ማእቀብ እንዲነሳ እንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡ ዲፕሎማሲ ግንኙነትን እንደሚመሰርቱ ፣ ኢምባሲ እንደሚከፍቱ እና የጉዞ ማእቀብን እንሚያላሉ ተናግረተዋል ፡፡ ኩባ በቀድሞው
በቻቬዝ ቬንዙዌላ ትደገፍ የነበረ ቢሆንም ቬንዙዌላ ኢኮኖሚዋ ሲቀዘቅዝ ወደ አሜሪካ ማእቀቡ መላላቱ ለኩባ ጠቃሚ ነው ፡፡ ሪፐብሊካን
ሴናተሮች የቬንዙዌላ ኢኮኖሚ በቀዘቀዘበት በአሁኑ ወቅት ቬንዙዌላ ኩባን መደገፍ በተሳናት በዚህ ወሳኝ ወቅት ማእቀቡ መነሳት የኩባን
አምባገነናዊ መንግስት እጅግ ይጠቅመዋል ብለው ተከራክረዋል ፡፡
ኩባ ኢንተርኔትን መጠቀም ስትጀምር ፣ እንዲሁም የተባበሩት
ምግስትታትና ከቀይ መስቀል ጋር ግንኙነቷን አሻሽላለች ፡፡ የሮማው ካቶሊክ ፖፕ ሸመገሉት በተባለው በዚህ የማእቀብ መላላት ኩባም
ወዲያው አንድ አሜሪካዊ እስረኛን በመልቀቅ ደስታዋን ስትገልፅ በአሜሪካ ያሉ ኩባውያንም ደስታቸውን ገልፀዋል ፡፡ ቀጥሎም ኩባ ወደ
53 የሚሆኑ አሜሪካ የፖለቲካ እስረተኛ ስትል ትጠራቸው የነበሩ እስረኞችን ለቃለች ፡፡
በኩባ ላይ የተጣለውን ማእቀብ ለማንሳት የኮንግሬሱን ድጋፍ
የሚጠይቅ ሲሆን ኤምባሲ መክፈትና ግንኙነትን ማሻሻል ፣ የጉዞ እገዳዎችን ማላላት የመሳሰለው ፕሬዝዳንቱ በስልጣናቸው ሊያደርጉት
ሲችሉ የኢኮኖሚ ማእቀብ ማንሳት ግን የኮንግሬሱን ድጋፍ ካልታከለበት ውጤት አይኖረውም ፡፡
የቀዝቃዛው ጦርነት ካበቃ ወዲህ ፕሬዝዳንትት ሬገንና እሳቸውን
ተከትለው የመጡ የአሜሪካ መንግስታት ለሶቭየት ህብትረት ማእቀብን ሲያላሉና ሲያነሱ በኩባ ላይ ግን በተከታታይ ወደ ስልጣን የመጡ
ፕሬዝዳንቶች እንኳን ማእቀብ ሊያነሱ ቀርቶ በኩባ ላይ ጥርሳቸውን ነክሰው ቆይተዋል ፡፡ የአሜሪካ ጠላቶችን በተመለከተ በወጣው አዋጅ
መሰረት (America Enemies Act) በሚለው ድንጋጌ መሰረት አሜሪካውያን ኩባን ረግጠው ቢመጡ እና ፓስፖርታቸው ላይ የኩባ
ቪዛ የተመታበት ማህተም ቢታይባቸው እስከ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ቅጣትና እስር ይጠብቃቸው ነበረ፡፡
ሪፐብሊካን የፕሬዝዳንቱ ተቺዎች በበኩላቸው እንደሚሉት
ፕሬዝዳንቱ ብዙ ሰጥተው ምንም አላገኙም በሚል ተችተዋቸዋል፡፡ የሰብአዊ መብትን ለሚጥስ መንግስት ሽልማት እንደመስጠት ነው ብለዋል
፡፡ አንዳንድ ኩባ አሜሪካውያን ሲደግፉ ሌሎች ተቃውመዋል ፡፡ ራሳቸው ኩባ አሜሪካውያን በከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኙ ሪፐብሊካኖቹም
ሆኑ ዲሞክራቶቹ ውሳኔውን ሲነቅፉ ተስተውለዋል ፡፡ ፕሬዝዳንቱ ንግድንና ጉዞን ኢንቨስመንትን ከሰብአዊ መብት አስበልጠዋል ተብለው
ሲተቹ ፡፡ ሽብርተኝነትን ከሚደግፉ አገራት መዝገብ ዝርዝር ውስጥም አሜሪካ ኩባን መሰረዝ ይጠበቅባታል ፡፡
ኩባ እዳ በመክፈል 173ኛዋ ሃገር ስትሆን ከሰሜን ኮርያ
በአንድ ደረጃ ከፍ በማለት በዚህ ደረጃ የምትገኘው ኩባ እዳዋን በማትከፍለው በዚህች አገር ብድር የማግኘት እድሏ ጠባብ ነው ፡፡
አሁን ይህ ማእቀብ ሊነሳ የተፈለገበት ምክንያት በኩባ
የደም መፋሰስንና አብዮትን ለመከላከል ነው ፣ የተገለሉት ጄኔራሎች እንዲሁም የኩባ ኢኮኖሚ በመውደቁ ኩባን በነዳጅ አቅርቦት በመሳሰለው
ኩባን ስታግዝ የነበረችው ከቬንዙዌላ ኢኮኖሚ መንኮታኮት ወዲህ በኩባ የዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲኖር በሚል ሊሆን ይችላል ፡፡ ሰላማዊ
ሽግግር እንዲኖርና የኩባ ጄኔራሎች ጥቂት ኦክስጅንን ወደ ኩባ ለመልቀቅ ነው ፡፡
አሜሪካ በኩባ ላይ ማእቀብን ያነሳችበት ምክንያት ኩባ
ወደ ሩስያ እንዳትሄድ ነው ቢባልም ነገር ግን በላቲን አሜሪካ ለአሜሪካ ጥቅም ጠንካታራ ባላጋራ የሆነችው ቬንዙዌላ ነች እንጂ ኩባ
አለመሆኗ አሜሪካ አታጣውም ፡፡ ትልቋና የነዳጅ ዘይንት የበለፀገችው ሃብታሟ ቬንዙዌላ በድፍረት የአሜሪካንን ጥቅም በአለካባቢው
ስትቃረን በመቆየተዋ ሲሆን ቬንዙዌላ ኩባን በነዳጅ አቅርቦትና በገንዘብ ድጋፍ ስትደግፋት ቆይታለች ፡፡ ይን እንጂ ሁጎ ቻቬዝ ከሞቱና
ከቅርበ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የነዳጅ ዋጋ ከተንኮታኮተ ወዲህ ከነዳጅ የምታገኘው ገቢ የቀነሰባት ቬንዙዌላ በሃገራ የዋጋ ንረት በማሻቀቡ
የምጣኔ ሃብት አቅሟ ሲዳከም እንደ ቀድሞው ኩባን ለመደገፍ አቅም እያነሳት መሄዱ ግልፅ ነው ፡፡ አሜሪካ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም
ኩባን ከቬንዙዌላ ወደ ራሷ ለማምጣት ተጠቅማበታለች ፡፡
አሜሪካንና የፑቲንና ሩስያ
የሩስያው
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለምእራባውያን የማይጨበጥ የጋለ ፍም ብረት ሆነውባቸዋል ፡፡ ምንም እንኳን ምእራባውያንና ዓልም አቀፍ
የሚዲያ ተቋማቶቻቸው በፑቲን ላይ በርካታ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን ቢያደርጉም ፑቲን በሙስና የተዘፈቀች ሩስያን ነው እሚመሩት ፣
ራሳቸው ፑቲን ወደ 40 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የደለበ ሃብትን አካብተዋል ፣ የሚሉና ለሌሎቸ በአንድ ወቅት በአንድ ከተማ የቼቼኒያ
አማፅያን እንዳደረጉት በማስመሰል ፈንጂ እንዲፈነዳ በማድረጋቸው የህዝብ ቁጣ በቺቺኒያ አማፅያን ላይ ያን ተከትለው ዘመቻን አካሂደዋል
የመሳሰሉት ክሶችን ሃሳቦችን አቀውርበዋል ፡፡
ፒቢ ኤስ የተሰኘው የአሜሪካ የቴሌቪዥን
ማሰራጫ ተቋም በፑቲን ላይ በሰሯቸው ጥናታዊ የዘገባ ፊልሞች ላይ የፑቲንን አነሳስ ሲዘረዝር እንዲሁም ፑቲን አርባ ቢሊዮን ዶላር
ሃብት አካብተዋል ሲል ባደረኩት ምርመራ ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡
ይሁንና ፑቲን ይህ ሁሉ እርሳቸው
ቢባልም በሩስያ ጥቅም ላይ የሚደራደሩ አለመሆናቸውና በአገራቸው ጥቅም ለመደራደርም ፈቃደኛ አለመሆናቸው ግን ምእራባውያኑን ያሳርራል
፡፡ ፑቲን ሩስያ ሶርያ አሳድ የኬሚካል ጋዝን በዝህዝቧ ላይ በተጠቀመችበት ወቅት አአሜሪካኖች ሶርያን ሊደበድቡ በነበረበት ወቅት
ፑተን በመከላከላቸውና በኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ድብደባውን በመቃወም ፅሁፍን ማውጣታቸው በአሜሪካኖችና በሱኒ አረብ መንግስታት
ጥርስ አስነክሶባቸዋል ፡፡
ሩስያ አስገራሚ በሆነ ሁኔታ ኢኮኖሚዋን
ከቀዝቃዛው ጦነት ወዲህ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣበት ባለማድረጓ ለተደጋጋሚ የምእራባውያን የፋይናንስና የምጣኔ ሃብት ማእቀብ ተጋላጭ
አድርጓታል ፡፡ ይህም በተፈጥሮ ማእድናት የበለፀገችው ሩስያ ከአውሮፓ ሃገራት ርካሽ የፋይናንስ አቅርቦትንና ብድርን የምታገኝ ሲሆን
አውሮፓውያንም የሩስያን ማእድናትና ነዳጅ ዘይነትና የተፈጥሮ ሃብትን በኢንዱስትሪ ላይ የተመሰረተው ኢኮኖሚያቸው ሲሉ ይፈልጉታል
፡፡
በዚህም ምክንያት በዩክሬይን ምክንያት
ምእራባውያን በሩስያ ላይ በጣሉት ማእቀብ የተነሳ ሩስያ በትቂ ጥቂት ወራት ውስጥ መንኮታኮቷ ራሳቸውን አውሮፓውያኑን ጭምር አስደንግጧል
፣ ይህም ሩስያ የምጣኔ ሃብትንና የማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ከገባች ዳፋው ለአውሮፓም ይተርፋል የሩስያ መንኮታኮት ለአውሮፓም ጭምር
ስጋትን ሊደቅን ይችላል በሚል ሰስጋት ሲገባቸው በአንፃሩ አሜሪካኖች ግን ሩስያ በደንብ እንድትቀጣላቸው ነው እሚፈልጉት ፡፡
ከቻይናም ሆነ ከሌሎች የብሪክስ አገራት
በተለየ ሁኔታ ሩስያ ከውጭ እንደምትታየው ውስጣዊ ጥንካሬ ያላት አገር አይደለችም ፡፡ የሩስያ ፖለቲካ በሙስና የተዘፈቀና ግልፅነት
የሌለው ሲሆን ኩባንያዎቿም እንዲሁ በሙስና የተዘፈቁ ሲሆን የቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃትን ተከትሎም ወደ ግል ሲዛወሩ አብዛኞቹ በጥቂት
ኦሊጋርኮች ቁጥጥር ስር ውለዋል ፡፡ ክሌፕቶክራሲና ክሮኒዝም የተንሰራፋባችት ሩስያ አስፈሪ አገር ነች ሲሉ የምእራባውያን መዋእለ
ንዋይ አፍሳሾች የሚፈሯት ሃገር ሰትሆን በአንፃሩም የሩስያ ገዢ መደብ ‹‹ኤሊት›› ሃገራቸውን ለመጪው ውድድር አለማዘጋጀታቸው ፣
የሃገራቸውን የተፈጥሮ ሃብት በመላክ ያገኙትን ገንዘብ ወደ ውጪ ሃገራት ባንኮች ማሸሻቸው ሳቢያ በምእራባውያን ላይ የበዛ የምጣኔ
ሀብት ጥገኝነት ላይ የተመሰረተው በመሆኑ የሩስያ ኢኮኖሚ ምንም እንኳን እውሮፓውያኑ ራሳቸው በማእቀቡ ሳቢያ ጉዳት ቢደርስባቸውም
የበለጠ ግን ሩስያ ተጎጂ ነች ፡፡
አውሮፓ በቆዳ ስፋት ጠባብ ሲሆን
በአንፃሩ ሩስያ ግን እጅግ ሰፊ የሆነ መሬት ባለቤት ስትሆን በመሬቷ ውስጥ ያሉት ማእድናትን እንደ አልሙኒየም ፣ ኮባልት ፣ ኮፐርና
ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ እና የሌሎችንም የበርካታ ማእድናት የደለበ ሃብት ባለቤት ነች ፡፡ ሩሥያ ይህ ብቻም ሳይሆን በሳይቤሪያ
እና በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ አካባባ ከሚገኘው ግዛቷ ሰፊ የማእድናት ክምችት ያላት አገር ነች ፡፡ አውሮፓ ጠባብ አህጉር ቢሆንም
ለክፍለ ዘመናት ያደገ ኢንዱስትሪ ባለቤት ሲሆን ሩስያኖች ይህንን የአውሮፓውያንን ፍላጎት እምብዛም አይረዱትም ፡፡
ምእራባውያን በብዛት የሩስያ የፖለቲካ
ስርአት ተመችቷቸው አያውቁም ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡ ምእራባውያን የሩስያን የፊውዳሉን ዘመን ደራሲያንና ፀሀፍትን አብዘተው
የሚያደንቁ ሲሆን ከዚያ ውጪ ብዙም ሩስያን በደግ አያነሱም ፡፡ አውሮፓውያን ሩስያን ለማስገበር በርካታ ግዜ ሞክረዋል ለምሳሌ የፈረንሳዩ
ጀብደኛው ንጉሰ ነገስት ናፖሌዎን ቦናፖርቴ ሩስያን የወረረ ሲሆን በከባዱ የክረምት ‹ዊንተር› በረዶ አብዛኛው ሰራዊቱ በአርበኞቹ
ሩስያውያን ተመቶ አልቆበት ሩስያን ለቆ ወጥቷል ፡፡ የጀርመኑ የናዚዎች መሪ አዶልፍ ሂትለርም ሩስያን ወሯል ነገር ግን እርሱም
ሰራዊቱ ተመቶ አልቆበት በሽንፈት ተመልሷል ፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን በቀዝቃዛውም ጦርነት ዘመን ጭምር ምእራባውያን ሩስያን በቀጥታ
መውረር አደጋ እንዳለው በመረዳት በኦኮኖሚ መክበብ ፣ ተደጋጋሚ ማእቀብ መጣል ፣ በኔቶ መስፋፋት ሩስያን አጣብቂኝ ውስጥ መክተትን
አማራጭ አድርውት ቆይተዋል ፡፡ በቀዝቃዛው ጦርነት ሩስያ የተሸነፈችው በኢኮኖሚ ከምእራቡ ዓለም ጋር መወዳደር ባለመቻሏ ሲሆን እንኳን
ከአሜሪካ ይቅርና ከአውሮፓውያኑ ጋር እንኳን የሚወዳደር የኢንዱስትሪም ሆነ የፋይናንስ አቅም ስላልነበራት ከሰባ አመታት በኋላ እጅ
ለመስጠት ተገዳለች ፡፡
No comments:
Post a Comment