በሀገራችን ደራስያን መፅሀፍ በሚፅፉበት ወቅት ግን ምንጭንና ዋቢ
መፅሀፍትን የማይጠቅሱ ሲሆን ቀደምት ደራስያን ስራዎቻውን ልክ ራሳቸው እንደ ወጥ በሆነ ሁኔታ እንደፃፉት አድርገው ይፅፉታል በዚህም
ምንም አይት ዋቢ መፅፍ የሌላቸው ሲሆን የአውሮፓውያንን ታሪክ ሲፅፉ ያገኙባቸውን የታሪክ ምንጮችን አይጠቅሱም ፍልስፍናም ሲሆን
እንዲሁ የዋናውን መፅሀፍ ምንጭ የማይጠቅሱ ሲሆን ይህም የሀገራችንን
ጸሀፍት የራሳቸው ያልሆነውን ሰራ የራሳቸው አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው ያስወቅሳቸዋል እንጂ አያስመሰግናቸውም ፡፡
ለምሳሌ ክቡር ከበደ ሚካኤል በፃፏዋቸው ታላላቅ ሰዎች በተሰኘው
መፅሀፍ ላይ ምንም አይነት ምንጭንም ሆነ የታሪክም ሆነ የፍልስፍና መፅሀፍን ያልጠቀሱ ሲሆን ነገር ግን በመፅሀፉ ውስጥ የተጠቀሰው
ግን ታሪክና ፍልስፍና ነክ ነገር እንደ መሆኑ ምንጮቹን እና የተጠቀሙባቸውን የማመሳከሪያ መፅሀፍቱ ሊጠቀሱ ይገባ ነበረ ፡፡
በሃገራችን የአድዋ ጦርነት የኢትዮጲያ ብቻ ሳይሂን የአፍሪካና የመላው አለም
የነፃነት ተምሳሌትነ የጭቁን ህዝች የነፃነት መሰረት የሆነ ድል መሆኑ አያከራክርም ፡፡ የአድዋን ጦነት አባቶቻችን ያሸነፉት በነበራቸው
የጋለ የሀገር ፍቅርና ለሃገራቸው በነበራቸው ተቆርቋሪነት በባዶ እጃቸው በኢንዱስትሪ አብዮት ከተደራጀና ዘመናዊ የጦር መሳሪያን
መድፍንና መትረየስን ከታጠቀ ዘመናዊ አውሮፓዊ ሃይል ጋር ነው ፡፡
ይህ በጦር ሜዳ ድል የተገኘ ነፃነት በእውቀት ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ በአጠቃላይ
በእውቀት ታግዞ ልማትንና እድገትን ካላመጣ የሃገሪቱ ህልውና አሁንም አደጋ ውስጥ ሊወድቅ እንደሚችል በዘመኑ የነበሩ ምሁራኖች በተለያየ
መንገድ መንገድ ሃሳባቸውን ገልጸዋል ፡፡
በሀገራችን እውቀትን መደበቅና ለራስ ብቻ ማወቅ መፈለግ የተለመደ ሲሆን አዲስ
አበባ ዩንቨርሰቲ በነበርኩበት ወቅት አንዳንድ ጠቃሚ የሆኑ መፅሀፍት ያውም በፈተና ሰሞን ይደበቁ የነበረ ሲሆን ከውስጣቸውም ገፃቸው
እየተቀደደና እየተቦጨቀ ይወሰድ ነበረ ፡፡
በሃገራችን አዲስ ሃሳብን ለመቀበል ደካሞች ስንሆን አዳዲስ አስተሳሰቦችን
እንፈራለን ፣ እንጠራጠራለን ፡፡ አዲስ ሃሳብን ያፈለቀ ሰውን የተወገዘ አድርገን የማየትና ምንም እንኳን ሰውየው ያለው ትክክል
ቢሆንም ያንን ለማየትና ለመረዳት ረጅም ጊዜን ይወስድብናል ፡፡ በዚህም በዚያ አዲስ ሃሳብ ለመጠቀም ያለንን እድል ሲያጠብብን ከዚያም
ባለፈ ግን ለየት ያለ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች ሃሳባቸውን በአደባባይ እንዳይገልፁና እንዲፈሩ ያደርጋል ፡፡
ቅናትም እንዲሁ በሰፊው በመሀከላችን የሚታይ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ዋናው
የእውቀት ምንጭ የሆነው የንባብ ባህላችን ደካማ ነው ፡፡ ከየትኛውም ሚዲንያን ከመከታተል ፣ ወይንም ቴሌቪዥን ከማየትና ሬዲዮ ከመስማት
በበለጠ ከማንበብ የበለጠ እውቀት የሚገኝ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የመደማመጥ ባህላችን ራሱ በትኩረት ሊቃኝ የሚገባ ሲሆን የተለያየ
አቋም በሚያጋጥም ጊዜ አንዱ ለአንዱ የሚለውን ለማዳመጥ እንኳን እግስት አናሳይም ፡፡
ወጣትነት በዘመን እይታ
ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ አዲስ
አድማስ ጋዜጣ ላይ በታህሳስ 4 ቅፅ 13 ቁጥር 778፣ 2007 ዓ.ም. ከወጣው ያነበብኩት ፅሁፍ ሲሆን አስረስ አያሌው የተባሉ
ፀሀፊ ‹‹ወጣቱን
በቅኔ›› በሚል ርእስ ያቀረቡትን ጽሁፍ በማየት ነው ፀሀፊው እንዲህ ይላሉ ፤
‹‹የኛ ትውልድ ግራ የተጋባ ነው፡፡ እንደ አያቶቹ አርበኛ
፣ እንደ አባቶቹ ደግሞ አብዮተኛ አይደለም ፡፡ ልግመኛ ነው፡፡ ልግመኛ የሆነው ግን ወዶ አይደለም ፡፡ የሚያግዘው አጥቶ ነው ››
የድሮዎቹ አባቶቻችን ድንበርን በማስከበር
፣ ጦርነት ወራሪን በመከላከል በመሳሰለው የአርበኝነት ጀብድና ገድል
ዘመናቸውን ሲያሳልፉ ፣ ከእነሱ በኋላ የመጣው ዘመናዊ ትምህርትን የቀሰመው አብዮተኛው ትውልድ በበኩሉ ደግሞ እነርሱ ለዘመናት ይዘውት
የቆዩትና ሊለውጡት ፈቃደኛ ያልነበሩትን ስርአት ለወደፊቱ አገራችን አይበጅም በሚል ስሜት አብዮትን አስነስቶ የአባቶቹን ስርአት
ያፈራረሰና ከዚያም የራሱን ይጠቅማል ያለውን ስርአት ለመተካትና ተግባራዊ ለማድረግ እርሱ በእርሱ በመጫረስም ጭምር መስዋእትነትን
የከፈለ ነው ፡፡
ለለውጥና አገርን በአዲስ አስተሳሰብና
ስርአት ለመቃኘት መነሳሳት በዓለም አገራት ታሪክ ውስጥ ያለና የተለመደ ነገር ነው ፡፡ ለምሳሌ በአውሮፓ የቡርዧ ስርአት የመጣው
የፊውዳል ስርአትን በማፈራረስ ነው ፡፡ ነገር ግን ይህ የሆነው በጣም ስር ነቀል አብዮትን በማካሄድ ሳይሆን ዘመናት የፈጀ ጥገናዊ
ለውጥን በማካሄድና ወቅቱ ሲደርስም መለወጥ ያለበትን በመለወጥ ነው፡፡ የኢኮኖሚው መሰረት ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ሲቀየር እና
የኢንዱስትሪ አብዮት ስር ከሰደደ በኋላ የፖለቲካ ስርአቱንም መለወጥ አስፈላጊነቱን ተረዳው ገዢ መደብ ራሱን ቀስ በቀስ ወደ ቡርዧ
ስርአት ማሸጋገር ችሏል ፡፡
አሜሪካንንም ብንወስድ አሜሪካኖች
ምንም እንኳን የባርያ አሳዳሪውን ስርአት ለማፈራረስ የተነሱት የኢንዱስትሪው አብዮት በአሜሪካ ሲካሄድ በፋብሪካዎቻው አማካይነት
ርካሽ በሆነ ሁኔታ ማምረት ስለሚቻል ያንን የሰው ሃይል ያነሰ ምርታማ በሆነው ግብርናው ዘርፍ ከማሰማራት ይልቅ በኢንዱስትሪው ውስጥ
ማሰማራት የበለጠ ትርፍማ በመሆኑና ለዚህ ደግሞ የሚያስፈልገው የሰው ሃይል ያለው ግብርናው ውስጥ በመሆኑ የባርያ አሳዳሪው ስርአት
መፈራረስ ነበረበት እንጂ ነጭ አሜሪካውያን ለጥቁሮች አዝነው ወይንም የባርያ አሳዳሪው ስርአት ስነ - ምግባራዊ ስላልሆነ ብለው
እንዳልነበረ በርካታ የታሪክና የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይስማማሉ ፡፡ በዚያም አለ በዚህ ግን ስርአቱን መለወጥ አስፈላጊ የእርስ
በእርስ ጦርነት ጭምር አካሂደው ለውጠውታል ፡፡
በአንፃሩ በኢትዮጲያ የተካሄደው አብዮትና ተከትሎት የመጣው እልቂት ወጣቱንና የተማረውን ሀይል ሙልጭ አድርጎ ያጠፋ መሆኑንና
አይደለም በአፍሪካ በአለም ደረጃ እንኳን የዚህ አይነት ጥፋትን ያስከተሉ አብዮቶች ቁጥራቸው እምብዛም እንዳልሆኑ ስለ አብዮቶች
ያጠኑ የአፍሪካ ምሁራን ጭምር ይመሰክራሉ ፡፡ የኢትዮጲያ አብዮት ውጤት እጅግ የመረረ የሆነበት ምክንያት የሃገሪቱ የምጣኔ - ሃብትና
የፖለቲካ ስርአት ለክፍለ ዘመናት ለውጥንና ማሻሻያን ይፈልግ የነበረ በመሆኑና ይህ ግን በገዢዎቹ ታፍኖና ተገቢው ትኩረት ሳይሰጠው
ሁኔታው ገነፍሎ ከቁጥጥር ውጪ በመውጣቱ ነው ፡፡ ለምሳሌ እጅግ ኋላ ቀር የነበረውና ከዘመኑ ጋር ፈጽሞ የማይሄደው የመሬት ስሪት
ስርአቱ ተጠቃሽ ነው ፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ጸሀፊው ልግመኛ ያሉት ትውልድ በራሱ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በሱስ የተጠመደ
መሆኑን ፣ ስለ አገሩ ደንታ ቢስና ግዴለሽ መሆኑን ነገር ግን ተጠያቂ እንዳይሆን ወዶ አይደለም ፣ የሚያግዘው አጥቶ ነው ብለዋል
፡፡ ካለፉት ትውልዶች የደረሰው እልቂት በተለይም በቀይና በነጭ ሽብር የደረሰው እልቂት መሀል ላይ የሚሸጋግር የትውልድ ማለትም
በታላቅየው ወይም በአባትየው ትውልድ እና በታናሽየው ልጅ ትውልዶች መሀል ክፍተት መፍጠሩን በርካታ የስነ - ማህበረሰብ ወይም ሶሺዎሎጂ
ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡ አዲሱ ትውልድ ‹‹እርስ
በእርሱ የተገዳደለ ትውልድ›› የሚለው የቀድሞው አብዮተኛው ትውልድ የበዛ መስዋእትነትን በመክፈሉ ምክንያት
ከመጪው ትውልል ጋር የሚያገናኘው ጠንካራ ድልድይ እንዳይኖር ቢያደርግም ፣ ይህ መሀል ላይ የተፈጠረ ክፍተት አዲሱ ትውልድ እንደ
ታላቅ የሚያየውና የሚያከብረው እንዲሁም እንደ አርአያ የሚቆጥረው ትውልድ እንዳይኖርና ነገሮችን በራሱ መንገድ ብቻ እንዲረዳና እንዲተረጉም
ለቀድሞው ትውልድ መልካም ተግባራት ጭምር እውቅናን እንዳይሰጥና ከዚያም ተጠቃሚ እንዳይሆን እድሉን ዘግቶበታል ፡፡
የአሁኑ ትውልድ ግን ሀብትን በማከማቸት ፣ ገንዘብን በመሰብሰብ
ሲጠመድ ማየትና መስማት የተለመደ ነው ፡፡ ይህም የዘመኑ ትውልድና የቀድሞው ትውልድ ምን ያህል የተራራቀ የአስተሳሰብ አድማስ እንደነበራቸው
የሚያሳይ ነው ፡፡ የዘመኑ ትውልድ ቁጥርና ስታትስቲክስ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ላይ ሲያተኩር የቀድሞው ትውልድ ፖለቲካና ህግ ላይ
ትኩረትን ያደርጋል ፡፡ የአሁኑ ትውልድ ገንዘብና ገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ የበለጠ እውቀት ሲኖረው የቀድሞው ትውልድ ስለ ገንዘብም
ሆነ ስለ ምጣኔ ሀብት የነበረው እውቀት ከአሁኑ ጋር የሚወዳደር አይደለም ፡፡ የቀድሞው ትውልድ ለአገሩ ቀናኢ በመሆን የአካልና
የህይወት መስዋእትነትን በመክፈል አገሩንና ዳር ድንበሩን አስከብሮ አለፈ እንጂ በአብዛኛው በነበረው
ሀብት የተጠቀመ እና በድሎት ተንደላቆ የኖረ አይደለም ፡፡ በአንፃሩ የአሁኑ ትውልድ ከአባቶቹ በወረሰው ድህነት እጅግ መማረሩ ለገንዘብ
ከፍተኛ ፍቅር እንዲያድርበት ዋነኛ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ፡፡ ወደ ውጪ አገር በህጋዊም ሆነ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እሚሰደደው
በአብዛኛው ወጣት በኢኮኖሚ ምክንያት ሲሆን በሚችለውም ይህንን ነባራዊ ሁኔታ ለመለወጥ በትግል ላይ ይገኛል ፡፡
ሁሉም ነገር ድሮ
ቀረ ማለት በተለመደበት ባህል ውስጥ ሁልግዜ የድሮውን ናፋቂ
መሆን ከስህተት ላይ እንዳይጥለንና የራሳችንን ዘመን ታሪክ ሳናደንቅም ሆነ በራሳችን ዘመን ታሪክ ተሳታፊ እንዳንሆን እንዳያደርገን
መጠንቀቅ አለብን ፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን በመጽፈ መክብብ ላይ ምእራፍ 7፣ቁጥር 10 ላይ ‹‹ከዚህ ዘመን ይልቅ ያለፈው ዘመን ለምን ተሻለ? ብለህ አትናገር ፣ የዚህን ነገር በጥበብ አትጠይቅምና
››፡፡
ስነ - ጥበብና አገራችን
ከጣልያን ጦርነት ከማይጨው ጦርነት ከተመለሱ
ወዲህ ንጉሰ ነገስቱ ፣ ምንም እንኳ ጣሊያን ትቷቸው የሄዳቸው ጥቂት የመሰረተ ልማቶችና መንገዶች ህንፃዎች ቢኖሩም ሃገሩ ግን በጦርነት
መፈራረሱ ግልጽ ነበረ ፡፡ እንደ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ የጀመሩት የሀገራዊ ስሜትን የሚቀሰቅስ እንቅስቃሴ ነበረ ያም በኋላ መኮንን ሀብተወልድ
ይዘውት በሀገር ፍቅር ትያትር ተቋማዊ አደረጃጀትን ይዞ ሲቀጥል ፡፡ በ1950ዎቹ አካባቢ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች ይታያሉ በ1960
ዎቹ እነ ዮሀንስ አድማሱ ፣ ዮናስ አድማሱ እና የመሳሰሉትም እንዲሁ የተለያየ ድርሰቶችን በመስራት አገራዊ ስሜትን ለማነቃቃትና
ህብረተሰቡን ለማንቃት ጥረት የተደረገበት ነበረ ፡፡ ገብረ ክርስቶስ ሀዲስ አለማየሁ አፈወርቅ ተክሌን የመሳሰሉ ሽልማት በመስጠትና
ለማነቃቃት ጥረት ተደርጓል ፡፡
አብዮቱ ከፈነዳና 1970ዎቹ ወደ ቀበሌ
ኪነት ኪነ ጥበብ ሲሰራ ይህ ህዝቡ ለመድረስ ሲያስችል ቀድሞ የነበረው ምሁራዊ የነበረው አቅምና ደረጃ የነበረው ባይሆንም ወደ ህዝብ
ግን በቅርበት መድረስ የቻለና በርካታ አቀንቃኞችና ተዋንያን በኋላ ላይ ከቀበሌ ኪነት ታዋቂ ሆነው የወጡበት ነበረ ፡፡ አብዮቱ
ሲመጣ ቀድሞ የነበረው የአርቲስቶች ስብስብ ግን አንዳንዶች በሞት ፣ ከአገር በመውጣት ሲበተኑ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ከአገር ሰለሞን
ደሬሳ ሲወጡ ጸጋዬ ገ/መድህን ፣ መንግስቱ ለማ ፣ተስፋዬ ገሰሰን፣ አባተ መኩሪያን የመሳሰሉት ቀጥለዋል ፡፡
የአገራን ደራሲዎች በራሳቸው በአማርኛ
ቋንቋ ሲፅፉ ይህ ህዝባዊ ተቀባይትን በአለም ለማግኘት አስቻጋሪ ሲያደርገው ሌሎች የአፍሪካ አገራት ግን በፈረንሳይኛና በእንግሊዝኛ ሲፅፉ
የአገራቸውን ስነ - ፅሁፍ ለአለም ለማስተዋወቅ ረድቷል ፡፡
የሼክስፒር ስራዎች በ17ኛው ክ / ዘመን
የተሰሩ ቢሆንም አሁንም እንደ አዲስ በየመድረኩ ይሰራሉ በየትያትር ቤቶች በተመሳሳይም የሃራችን ስራዎች ከአሁኑ ሁኔታ ጋር ሊተረጎምና
ከአሁኑ ጋር ካለው ሁኔታ ጋር በዛሬ ሁኔታ ላይ ቆመን ስንመለከተው ስለአሁኑ የሚነግረን ይኖራል ፡፡ አውሮፓውያን ከቀድሞው ስራዎቻቸው
ብዙ ብዙ ለዘመኑ አንዳመቻቸው ይወስዳሉ ፡፡
በአገራችን ግን በዚህ አይነት መንገድ
ደራሲዎቻችንን ፣ ሰአሊዎችቻችንን ዋጋ የተረዳን አይመስልም ፡፡ በአሉ ግርማ እንዴት እንደሞተ የማይታወቅ ሲሆን እንደ አቤ ጉበኛ
፣ ገብረህይወት ባይከዳኝና ዮፍታሄ ንገሱ እንዴት እንደሞቱ እንኳ
አይታወቅም ፡፡
ባህላችንና ታሪካችን ግለሰባዊነትን የሚበረታታ
አይደለም ፡፡ ሁሉንም ነገገር ለንጉሰ ለጳጳሱ ወይም ለገዢው ነው የምንሰጠው ፡፡ በዚያ ውስጥ ግን እጅግ በርካታ ባለሙያዎች ሰዎች
ያሉ ሲሆን ስለ እነሱ ምንም የሚባል ነረገር የለም ፡፡ ሰአሊዎች በቤተክርስትያን የሚስሉትን ስእሎችን ስንመለከት ንጉሱን ዛፍ አሳክለው
ሲስሉ ሌሎቹን ሰዎች ደቃቃ እና ከአይን የማይገቡ አድርገው ነው የሚስሉት ፡፡ የሁሉንም ነገር ማእከልም ፣ መጨረሻውም መጀመሪያው
ንጉሱ ወይንም ጳጳሱ አድርገው ነው ፡፡
አውሮፓዊያን በህዳሴው ዘመን ያንሰራሩበት
አንዱና ዋናው ምክንያት ቀድሞ የሁሉም ነገር ማእከል የነበረውን መለኮት ላይ ተንጠልጥሎ የነበረውን ወደ ግለሰብ ትይዩ ማለትም ወደ
ሰው ደረጃ በማውረዳቸው ነው ፡፡ ለምሳሌ የማክያቬሊ አስተሳሰብ ከህዳሴው ዘመን ዋናው ተደርጎ የሚወሰድበት ምክንያት ቀድሞ ሁሉም
ነገር በመለኮት መሪነትና ፈቃጅነት ይደረግ የነበረውንና ከላይ (ቨርቲካል) ከመለኮት ወደ ታች ማለትም ወደ ሰው ይወርድ የነበረውን
ግንኙነት ወደ ጎን ማለትም ወደ ሰውና ሰው ፣ ሰውና መለኮት የትይዩ (ሆሪዞንታል) ግንኙነት እንዲኖር ፈርን የቀደደ በመሆኑ ነው
፡፡
አንድን ስነ የጥበብ ተረድቶና ለማስቀመጥም
የመካከለኛው መደብ ያስፈልጋል፡፡ ኢትየጲያ ውስጥ ስእሎችን የመግዛት ነገር አሁን አሁን የሚታይ ነው ፡፡ ብሄራዊ የሳይንስ አካዳሚና
ብሄራዊ ሙዚየም ስነ - ጥበብ የሚደግፉና በክብር የሚያስቀምጡ ተቋማት ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment