Friday, February 6, 2015

ፊሜኒዝምና ሊበራሊዝም



ከምእራባውያን ፍልስፍና ውስጥ ‹‹ፊሜኒዝም›› (Femenism) እንዲሁም ሊበራሊዝም (Liberalism) ተፈጥሮን በመቃረን ይታወቃሉ ፡፡ ፊሜኒዝምን ብንወስድ ወደ ፅንፍ ይህ ፍልስፍና ሲሄድ ተፈጥሮን የሚቃረን ነው ፣ ሊበራሊዝም የመጀመሪያው የዚህን ፍልስፍና አባት ተደርጎ የሚወሰደው ቶማስ ሆብስ ሲሆን ይህንን እንጂ ፊሜኒዝም ከመስመር ሲያልፍ ሴትን ከተፈጥሮዋ ውጪ በሚያደርግበት ወቅት ሴቷዋን ከራሷና ከማህበረቧ ፣ ከቤተሰቧ ጋር ሊያጋጫት የሚችል ነው ፡፡
ምእራባውያን በሊበራሊዝም ስም የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን መፍቀድ መጀመራቸው ተፈጥሮን መቃረናቸውን እንዲሁም ሰው ከመሰሉ ፆታ ጋራ እርስ በእርሱ መጋባትና መኖር ከጀመረ የሚቀጥለው አዲሱ ትውልድ እንዴት ሊወለድና ሊተካ እንደሚችል ግልፅ አይደለም ፡፡  የሰው ልጅ የመኖር አላማው ወሲባዊ ስሜቱን ከተመሳሳይ ፆታም ጋር ጭምር ከቁጥጥር ውጪ መረን የወጣ ወሲባዊ ስሜቱን ማርካት አለበት ፣ ለወሲብ ብቻ ነው ወይ የተፈጠረው? ያስብላል ፡፡ ይሁን እንጂ ይህን አስተሳሰብ በምእራቡ ዓለም የሚገፉት እነማን እንደሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ዓላማው ከወሲባዊ ጉዳዮች አልፎ ሀይማኖታዊና ፖለቲካዊም ጭምር ነው ፡፡ 
አንድ የፈረንጆች አባባል እንደሚለው ከሆነ አንዲት ሴት ‹‹እንደ ልጃገረድ ሆና መታየት ሲኖርባት፣ ስራዋ እንደ ሴት ወይዘሮ ፣ እንዲሁም እንደ ወንድ ማሰብ እና እንደ ውሻ ለፍታ መስራት ይገባታል›› Look like a girl, act like a lady, think like a man and work like a dog
አንድ ሴት የምትሰራው ስራ ህፃናትን መውለድና ተንከባክቦ ማሳደግ ፣ ቤት ውስጥ ስራና የመሳሰለው ሁሉ በአጠቃላይ አገራዊ ምርትም ውስጥም ጨርሶ የማይገባ ሲሆን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የሴትን ያህል የተበዘበዘ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡  እንደ ጃፓን ባሉ አገራትን ጭምር የሴቶች በቤት ውስጥ የሚሰሩት ልጅን በማሳደግ ፣ ቤትን በማፅዳት ልብስንና ቤትን በማፅዳት ምግብ በማዘጋጀት በመሳሰለው የሚደርጉት የጉልበት ሴቷን ተዋፅኦ ጨርሶ በአገራዊ ምረት ውስጥ ባለመካተቱ ነው ፡፡
ለምሳሌ የወሊድ ፈቃድን ብንወስድ የወሊድ ፈቃድ ከተወሰነ በላይ ቢያድግ ሴቶች ቀጣሪ አያገኙም የሚል ስጋት አለ ፡፡ ራሳቸው ሴቶቹ በዚህ ገፍተው አይሄዱም ምክንያቱም ይህ ሴቶችን ይስ የስራ የመያዝ መብትን ያጣብባል በሚል ነው ፡፡
ለምሳሌ እየሱስ ክርስቶስ ከቀራጮች ጋር ሲመገብ ሲያዩ ክርስቶስ የስነ - ምግባር ደረጃን ዝቅ እንዳደረገው አድርገው ተቃዋሚዎቺ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ተችተውት የነበረ ቢሆንም ገምተው ነበረ ይሁን እንጂ በአለም ላይ ካሉ ሃይማኖቶች ከአንድ ሴት በላይ አታግባ ፣ አታመንዝር፣ቀኝ አይንህ ብታሰናክል አውጥተህ ጣላት የመሳሰሉት የእየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮዎች ክርስትናን ሃይማኖት የስነ - ምግባር ወይም የሞራል ደረጃ እጅግ ከፍ ያደርጉታል ፡፡
ሃዋርያው ጳውሎስ አይሁድን ከክርሰትና ለማስታረቅ ‹‹ስር ቅርንጫፍን ይሸከማል እንጂ ፣ ቅርንጫፍ ስርን አይሸከምም›› ብሏል ፡፡
ውስጣዊ ፃድቅነት ፣ እንዲሁም ክርስቶስ የሙሴን ህግጋት ሊያፀና እንጂ ሊሽር እንዳልመጣም ተናግሯል ፡፡ ፈሪሳውያን ግን ስህተትን በመፈለግ እስቲ የሙሴን ህግ ተቃርኖ ይፈርድ ይሆን በሚል የሙሴን ህግ ይቃረን ይችላል ብለው የሚገምቷቸውን ነገሮች እያመጡ ዳኝቱን ጠይቀውታል ፡፡ ለምሳሌ በዝሙት የተያዘች ነች ያሏትን ሴት ፊቱ በማምጣት እስቲ በድንጋይ ተወግራ ትገደል ብሎ ይፈርድ እንደሆነ ፈትነውታል ፡፡ ነገር ግን እነሱ በባልጠበቁት ሁኔታ ከመሀከላችሁ ሃጢአት የሌለበት እስቲ ይውገራት ፣ ሲል አንዳቸውም በድንጋይ ለመውገር ሳይደፍሩ ጥለው ሄደዋል ፡፡ በተመሳሳይም እንዴት በሰንብት ይፈውሳል በማለት ሲፈትኑነት እንዴት ከቀራጮች ጋር ይበላል ፣በማት ሲያጉረመርሙበት ቆይተዋል ፡፡ 

No comments:

Post a Comment