የአውሮፓ ህብረት #EU ከአስር በላይ የስራ ቁዋንቁዋዎች ሲኖሩት፥ የአፍሪካ ህብረትም አማርኛ ከአረብኛ ከእንግሊዝኛ ከስዋሂሊና ከፖርቱጋል እና ከፈረንሳይኛ ቀጥሎ 6ኛ የስራ ቁዋንቁዋ ይሆን ዘንድ አማርኛ ቁዋንቁዋን ሰይሞአል። ከአስሩ አፍሪካውያን አንዱ ኢትዮጲያዊ ሲሆን የህዝብ ብዛቱዋ ከአፍሪካ 2ኛ የሆነ ህዝብ መግባቢያ ቁዋንቁዋ የሆነው አማርኛ ቁዋንቁዋ የAU one of the official languages of AU መሆኑ አኩሪ ሲሆን የጠ/ሚሩ ድል ነው።
ይህም ለበርካታ ኢትዮጲያውያን የስራ እድልን ሲፈጥር የኢትዮጲያውያን ደራሲዎች በአማርኛ ብቻ ነው እሚጽፉት በአውሮፓውያን ቁዋንቁዋ እንደ ኬንያ ጋና ወይም እንደ ናይጄሪያና ደቡብ አፍሪካ ደራስያን በእንግሊዝኛ ቁዋንቁዋ ቢጽፉ ኖሮ አለም ኣቀፍ እውቅናን ይጎናጸፉ ነበር ለሚለው ምላሽን የሚሰጥ ነው። ምክንያቱም በርካታ ኣፍሪካውያን የአማርኛ ቁዋንቁዋን እሚማሩ ከሆነ የኢትዮጲያ ቁዋንቁዋ ፥ ስነ-ጽሁፍና ባህል ሰፊ የመተዋወቅ እድልን ያገኛክ።
Thursday, February 28, 2019
አማርኛ የAU የስራ ቁዋንቁዋ ሆነ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment