ሕገ መንግሥት ተርጓሚው አካል ከዚህ መሠረታዊ የፍትሕና ርትዕ መርህ በመነሳት፣ ለየትኛውም ወገን ባለማድላት ተጥሰዋል ተብሎ የቀረበለትን የሕገ መንግሥት መርሆዎች ለማፅናትና ለማስከበር ገለልተኛ መሆን ይገባዋል፤ በዚህ መርህ መሠረትም ተርጓሚው አካል እጅግ ወሳኝ ሚና የሚጫወት መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊው ነው፡፡
ሌላው ሕገ መንግሥትን ከመተርጎም አንፃር አዲስ ክስተት ወይም ጽንሰ ሐሳብ የሆነው የሕገ መንግሥት ኢንሹራንስ የሚለውንም አስፈላጊነትን ማንሳት ያሻል፡፡ ሕገ መንግሥት ተርጓሚው አካል በተለይ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት በሚከተሉ አገሮች ውስጥ፣ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ዋስትና የሚሰጥ አካል እንደሚሆን ይታወቃል።፡
‹‹የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት የሚከተል የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፓርቲዎች ይቀያየራሉ፡፡ ስለሆነም አንድ ፓርቲ ከሥልጣን ከወረደ በኋላ ምንም አድልኦ በሌለበት ሁኔታ በሚቀጥለው ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳና ዘመቻ አድርጎ ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ዋስትና ያስፈልገዋል፡፡
No comments:
Post a Comment