Friday, January 11, 2019

ጥቂት ስለ ቡልጋ

ጥቂት ስለ ቡልጋ ቡልጋ ሰሜን ሸዋ ከሚገኙ ታሪካዊ ጠቅላይ ግዛቶች አንዱ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ፣ የመካከለኛው ዘመን አምሓራ ነገሥታት ይነግሡበት ከነበረው ከተጉለት ጋር እጅግ የተሳሰረ በመሆኑ አብሮ ተጉለትና ቡልጋ ሲባል ይታወቃል። መልክዓምድራዊ ገጽታው ወይና ደጋ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ዋንኛ ከሚባሉ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ቦታዎች አንዱ ነው። ታላላቅ ቅዱሳን የወጡበትም ቦታ ነው። ለምሳሌ አፄ ይኩኖ አምላክን ያነገሡት ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የቡልጋ ተወላጆች ነበሩ። የአፄ ምኒልክ የአማራ ጦር ብዙው ከተጉለትና ቡልጋ እንደነበር አንዳንድ የታሪክ ጽሐፊያን ጽፈዋል። የምኒልክ ምሽግና የጦር ግምጃ ቤት የሚገኘውም ቡልጋ ነው። በኢትዮጵያ ብዙ ታላላቅ የሚባሉ የእውቀትና የሃይማኖት መጻሕፍት የጻፉ ሊቃውንት ከቡልጋ የወጡ ነበሩ። ለምሳሌ በማንኛውም የግዕዝና የተለያዩ ሰነዶች ላይ ዘብሔረ ቡልጋ የሚል ካለ ደራሲው ቡልጌ ናቸው። የሸዋ አምሓራ መንግሥት ዋና ዋና ሊቃውንት የሚፈልቁበት ቦታም ነበር። አፄ ፋሲል የተወለዱበት መገዘዝ የሚባለው ተራራ የሚገኘው ቡልጋ ነው። ታዋቂ ከሆኑ ሌሎች ከቡልጋ ተወላጆች መካከል ጽሓፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሐብተወልድ፣ ጽሓፌ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሓንስ፣ ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድሕን፣ ብላቴን ጌታ ማሕተመሥላሴ ወልደመስቀል፣ ተስፋ ገብረሥላሴ፣ ተክለጻዲቅ መኩሪያ፣ ደጃዝማች ሐብተሥላሴ በላይነህ ይገኙበታል። የኔም አባት ሎሬት ዶክተር መላኩ ወረደም እንዲሁ። ፎቶው ላይ ያለው አፄ ፋሲል ተወለዱበት የሚባለውና ቡልጋ የሚገኘው መገዘዝ ተራራ ነው
1-2 minutes

ጥቂት ስለ ቡልጋ

ቡልጋ ሰሜን ሸዋ ከሚገኙ ታሪካዊ ጠቅላይ ግዛቶች አንዱ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ፣ የመካከለኛው ዘመን አምሓራ ነገሥታት ይነግሡበት ከነበረው ከተጉለት ጋር እጅግ የተሳሰረ በመሆኑ አብሮ ተጉለትና ቡልጋ ሲባል ይታወቃል። መልክዓምድራዊ ገጽታው ወይና ደጋ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ዋንኛ ከሚባሉ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ቦታዎች አንዱ ነው። ታላላቅ ቅዱሳን የወጡበትም ቦታ ነው። ለምሳሌ አፄ ይኩኖ አምላክን ያነገሡት ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የቡልጋ ተወላጆች ነበሩ። የአፄ ምኒልክ የአማራ ጦር ብዙው ከተጉለትና ቡልጋ እንደነበር አንዳንድ የታሪክ ጽሐፊያን ጽፈዋል። የምኒልክ ምሽግና የጦር ግምጃ ቤት የሚገኘውም ቡልጋ ነው። በኢትዮጵያ ብዙ ታላላቅ የሚባሉ የእውቀትና የሃይማኖት መጻሕፍት የጻፉ ሊቃውንት ከቡልጋ የወጡ ነበሩ። ለምሳሌ በማንኛውም የግዕዝና የተለያዩ ሰነዶች ላይ ዘብሔረ ቡልጋ የሚል ካለ ደራሲው ቡልጌ ናቸው። የሸዋ አምሓራ መንግሥት ዋና ዋና ሊቃውንት የሚፈልቁበት ቦታም ነበር። አፄ ፋሲል የተወለዱበት መገዘዝ የሚባለው ተራራ የሚገኘው ቡልጋ ነው። ታዋቂ ከሆኑ ሌሎች ከቡልጋ ተወላጆች መካከል ጽሓፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሐብተወልድ፣ ጽሓፌ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሓንስ፣ ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድሕን፣ ብላቴን ጌታ ማሕተመሥላሴ ወልደመስቀል፣ ተስፋ ገብረሥላሴ፣ ተክለጻዲቅ መኩሪያ፣ ደጃዝማች ሐብተሥላሴ በላይነህ ይገኙበታል። የኔም አባት ሎሬት ዶክተር መላኩ ወረደም እንዲሁ።

ፎቶው ላይ ያለው አፄ ፋሲል ተወለዱበት የሚባለውና ቡልጋ የሚገኘው መገዘዝ ተራራ ነው

No comments:

Post a Comment