ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በሚኒስቴሩ ስር የሚገኙ 15 ተጠሪ ተቋማት በቦሌ ለሚና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሐምሌ 15/2011 የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡
ከ3,800 በላይ ሠራተኞች በተሳተፉበት በዚህ የችግኝ ተከላ ከ22,000 በላይ ችግኞችን በቦሌ ለሚና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመትከል ተችሏል፡፡
በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በነበረው የቸችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተሳተፉት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረየሱስ እንደገለፁት ይህ የችግኝ ተከላ መርሃግብር በዋናነት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ አቅም መፍጠሪያና በሐምሌ 22/2011 የሚካሄደው ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ቀን መንደርደሪያ ነው ብለዋል፡፡
ሐምሌ 22 ለሚካሄደው ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ሁሉንም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞችን ማሳተፍ እንዲቻል የቅድመዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን አውስተው በእለቱም በኦሮሚያ ክልል በፍቼ ከተማ አካባቢ 80,000 ችግኞች እንደሚተከሉ ገልፀዋል፡፡
በችግኝ ተከላው የተሳተፉ ሠራተኞች እንደገለፁት በዚህ ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ቀን ላይ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ በመቻላቸው የተሠማቸውን ደስታ ገልፀው በሀገራዊው የሠላም፣ የዴሞክራሲና የልማት እንቅስቃሴም ውስት ሁሉም በላፊነት የየግሉት አስተዋፅኦ በማድረግ የተጀመረውን ሀገራዊ መግባባት ማሳደግ እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment