Tuesday, August 20, 2019

ጣይቱ ብጡል ሃይለማርያም ብርሃን ዘኢትዬጵያ (ከ ነሐሴ 12: 1832 - የካቲት 4: 1910)

በአመራር ጥበባቸው አቻ ያልተገኘላቸው ንግስት
በሃገራችን የመጀመሪያው ባንክ # Bank of Abyssinia የተቋቋመው
በእንግሊዞች ነበር። ባንኩ ለስራ ማስኬጃ የተበደሩ ደንበኞች ብድራቸውን
መክፈል ሳይችሉ ሲቀሩ ንብረታቸውን ይወርሳል ከዚያም ይከሳል አልፎ ተርፎ
ተበዳሪወቹም ለእስር ይዳረጋሉ።
ታዲያ ይሄ ጉዳይ እቴጌ ጣይቱን እጂጉን ያሳስባቸው ነበርና
አንድ ቀን አፄ ሚኒሊክ እና ሹማምንቱ በቤተ መንግስቱ እልፍኝ ተሰብስበው
ስለ ባንኮ ኦፍ አቢሲኒያ ሲወያዩ እቴጌ ጣይቱ ሃሳብ አቀረቡ
"በመናገሻ ከተማችን ህዝባችንን እስር ቤት አዘጋጂቶ አይናችን እያየ
ጆሮአችን እየሰማ የእንግሊዝ መንግስት ያሻውን እንዲህ ሲሰራ ይሄ ህዝብ
ምኑን የእኛ ነው ማለት ይቻላል? ግብርስ መከፈሉ ፋይዳው ምንድን ነው?
እነዚህ ባለእዳ ተብለው በገዛ አገራቸው ፍዳቸውን ለሚያዩት # ሰወቻችን
እዳቸውን የሚከፍሉበት መፍትሄ ልናበጅላቸው አይገባምን?" ብለው ጠየቁ
እና እቴጌም ባንክ እንዲቋቋም መፍትሄ አቀረቡ ሹማምንቱም በእቴጌ ሃሳብ
ተስማሙ ተፈቀደላቸውም።
ባንክ በሚል ስያሜ # የእቴጌ_ጣይቱ_የእርሻና_ንግድ_ማስፋፊያ_ማህበር
ተቋቋመ ==>> የአሁኑ የ # ልማት_ባንክ መሰረት የተጣለው ያኔ በእቴጌይቱ
ነበር
- የመጀመሪያውን 100,000 ብር እቴጌ ጣይቱ
- ከመንግስት ግምጃ 200,000 ብር
ሌላውን አክሲዬን ደግሞ
- ንጉስ ወልደ ጊወርጊስ
- ራስ ተሰማ ናደው
- ንጉስ አባ ጂፋር
- እና ሌሎች የመንግስት ሹማምንት
- እና ታዋቂ የሮዝንደር ነጋዴወች እንዲያወጡ አደረጉ
ቀሪውን አክሲዬን ደግሞ
- ህዝቡና መሳፍንቱ ገዛ::
በመስከርም 2 /1909 ዓም ባንኩ ስራ ጀመረ።
ባንኩ ስራ እንደጀመረ ባንክ ኦፍ አቢሲንያ ላሰራቸው ሰወች በማበደር ከእዳ
እና እስራት ነፃ አደረገ።
ለንግድና እርሻ ማስፋፊያ የሚሆን ብድር በመስጠት የህዝቡን የኢኮኖሚ
እድገት ማበልፀግ ተቻለ።
በእቴጌ ጣይቱ የተሾሙ የበንኩ ስራ አስኪያጂ
~ የመጀመሪያው ነጋድራስ በሃብቴ
~ ቀጥሎ አቶ ምትኬ
~ ለጥቆ አቶ ይታጠቁ ነበሩ

No comments:

Post a Comment