Friday, December 14, 2018

professor mesfin w/mariam

#መስፍን #ወ/ማርያም ምን እያሉን ነው? | በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስኃጽዮን

በርግጥ በዘመናዊው ዓለም አንድ ሰው ከአካዳሚክ ተቋማት ከወጣ በኋላ #ፕሮፌሰር አይባልም፡፡ጡረተኛ የሚል ቃል ይጨመርበታል፡፡ጡረተኛ #ፕሮፌሰር ተብሎም ይጠራል፡፡እኛ ጋር ግን ልማድ ሆኖብን ማዕረግ ከሰጠን አናወርድም፡፡ለዚህ #መስፍን ወልደማርያም ማሳያ ናቸው፡፡እኒህ ታዋቂ ፖለቲከኛ፣ከአካዳሚክ ተቋም ከወጡ 26 ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ግን ፕሮፌሰር እያልን እንጠራቸዋለን፡፡ ይህም ሳይበቃ እርሳቸው በቀጥታ ከማስተርስ ወደ ፕሮፌሰርነት፣ በሴኔት ውሳኔ እንዳደጉ እየታወቀ ጉዳዩ አይነሳም፡፡

ለማንኛውም የዚህ ጽሁፍ ዓላማ፣ የፕሮፌሰሩን #የትምህርት እና የማዕረግ ጉዳይ መሞገት አይደለም፡፡ አጀንዳው ሰሞኑን እርሳቸው #በኢትዮጲስ ጋዜጣ ላይ የፃፉትን ሐሳብ ይመለከታል፡፡ እኔም ስለለመደብኝ ወይም አድናቂዎቻቸው እንዳይቀየሙኝ ፕሮፌሰር መስፍን እያልኩ ልቀጥል፡፡

#መስፍንፕሮፌሰር # ከላይ በጠቀስሁት #ጋዜጣ ላይ፣ #ፕሬዚዳንት #ሳህለወርቅን የተመለከተ ጽሁፍ ጽፈዋል፡፡ የጽሁፍ ጭምቅ ሐሳብ፣‹‹#ሶስት ሥርዓትን ያገለገለች #ሴት እንዴት #ፕሬዚዳንት ተደርጋ ትሾማለች›› የሚል ብስጭት የወለደው ነው፡፡በፕሬዚዳንቷ መሾም የተደሰተውን የሕብረተሰብ ክፍልም ዱላ ቀረሽ ስድብ አውርደውበታል፡፡

ይህን የእርሳቸውን አቋም ምን ያህል ሰው እንደሚስማማበት አላውቅም፡፡ #ግን ከራሳቸው ከፕሮፌሰሩ ሕይወትና ተፈጥሮ ጋር የሚቃረን ለመሆኑ አያከራክርም፡፡ #እርስበርሳቸው የሚጣረሱ ብዙ ሐሳቦችንም ይዟል፡፡ ከመሠረታዊ ሎጂክ ጋርም ይጣረሳል፡፡

ፕሮፌሰሩ ፕሬዚዳንቷን ከተቹበት መከራከሪያ ጋር እራሳቸውን እናነፃፅር፡፡ ወ/ሮ ሳህለወርቅን በፕሮፌሰሩ ያስተቻቸው ነገር ‹‹ #ሶስት አምባገነን #ሥርዓቶችን አጎብድዳ፣ አገልግላለች›› የሚለው #ክርክር ነው፡፡

እንግዲህ በጥቅሉ ሲታይ #ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ #የመንግሥት ሠራተኛ ናቸው፡፡ የመንግሥት ሠራተኛ ደግሞ መንግሥቱ ያወጣውን ፖሊሲና የሚከተለውን ርዕዮት ተከትሎ ይሠራል፡፡በዚህ ሂደት ውስጥም ፕሮፌሰር መስፍን አልፈዋል፡፡
©
#በጃንሆይም ሆነ #በደርግ እንዲሁም በኢሕአዴግ ውስጥ ፕሮፌሰሩ የመንግሥት ሠራተኛ ነበሩ፡፡ በበፊቱ #ቀዳማዊ #ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ፣ በአሁኑ #የአዲስ አበባ #ዩኒቨርሲቲ ወገባቸውን አጥብቀው አስተምረዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን የሚቀጥረው #ት/ት ሚኒስቴር መሆኑ ይታወቃል፡፡ #ት/ት ሚኒስቴር ደግሞ #የአገሪቱ #የካቢኔ አባልና ትልቁ #የፖሊሲና የርዕዮተዓለም #ማዕከል ነው፡፡

ታዲያ ፕሮፌሰር መስፍን #ሶስት #አምባገነን ሥርዓቶችን በማገልገል ረገድ ከወ/ሮ ሳህለወርቅ በምን አነሱ?…#ፕሬዚዳንቷ #ለውጭ #ጉዳይሚኒስቴር፣ ፕሮፌሰሩ #ለት/ት ሚኒስቴር ተቀጥረው ሶስት ሥርዓቶችን አገልግለዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ ያወጡት #ፎርሙላ ለራሳቸው አይሰራም ካልተባለ በቀር፡፡

አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት እንደውም እንደ ፕሮፌሰር መስፍን አምባገነኖችን የማገልገል ፍላጎት ያለው ሰው የለም፡፡#በጃንሆይ ዘመን የአውራጃ አስተዳዳሪ እስከመሆን የደረሱት እኒህ ታዋቂ ሰው፣ #ደርግ ጊዜም #የመርማሪ #ኮሚሽን አባል ነበሩ፡፡በዚህ #የኮሚሽን #አባልነታቸውም #ስድሳዎቹ ‹‹የአጼ ኃይለሥላሴ ባለሥልጣናት›› እንዲገደሉ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው እራሳቸው #ኮሎኔል #መንግሥቱ #ኃይለማርያም ተናግረዋል፡፡

ኮሎኔል መንግሥቱን ማመን ይከብዳል ቢባል እንኳ ከዋናዋናዎቹ #ባለሥልጣናት ቀጥሎ ያሉትን ሹማምንት ለማጣራት በዚሁ #ሥልጣን ደርግን ሁለት ዓመት አገልግለዋል፡፡ #አክሊሉ #ሀብተወልድን የሚያህል የሀገር አድባር #ትክክለኛ ፍትህ እንዳያገኙ #ጂኦግራፊ #መምህሩ #መስፍን #ወልደማርያም ምክንያት መሆናቸውን ብዙ ሰው ውስጥውስጡን ሲያወራው የቆየ ጉዳይ ሲሆን፣ እርሳቸውም አልፎ አልፎ ማስተባበያ ሲሰጡበት የኖረ ነገር ነው፡፡

#አክሊሉ #ሐብተወልድ #ቃልህን #በጽሁፍ አቅርብ ተብለው #ስንት መቶ #ገጽ ጽፈው ካመጡ በኋላ #‹‹ይህንን ለመስማት ጊዜ የለንም›› ብለው ውድቅ ያደረጉባቸው መስፍን ወልደማርያም #ከሻዕቢያው ሰላይ #በረከት ሀብተሥላሴ #ጋር ሆነው ነው፡ ፡ (ይህ ጽሁፍ #የአክሊሉ #ማስታወሻ በሚል ርዕስ ታትሞ የሚገኘው መጽሐፍ ነው) ይህም ገና ከመጣ ጀምሮ በሕዝብ የተጠላውን #ደርግን ሥርዓት ለማገልገል #ቆርጠው #መነሳታቸውን ^የሚያሳይ ነው፡፡  ከዚህ በላይስ #አምባገነንን ማገልገል ከወዴት አለ…? ከዚህ በላይ #ስለሥልጣን #ጅራትን መቁላት ከወዴት ይገኛል…?

ፕሮፌሰር መስፍን #ሀገሪቱን #ቀይ #ሽብርና #ነጭ - ሽብር ባስጨነቋት፣ #የእርስበርስ ጦርነት በወጠራት ጊዜ ፕሮፌሰር መስፍን ትንፍሽ ብለው አያውቁም፡፡ እርሳቸው መናገር የጀመሩት ኢሕአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ ነው፡፡ ከአቶ መለስ እና ከሌሎች ሁለት ሰዎች ጋር ባደረጉት #የ1983 ዓ.ም. ^ውይይት #‹‹አማራ የሚባል #ብሔር የለም›› የሚል አቋም ያንጸባረቁበት ንግግራቸው የመጀመሪያ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ እስከዛሬ ድረስ በቤታቸው #ከአዛውንት የኢሕአዴግ #ባለሥልጣናት ጋር ውስኪ #ችርስ እንደሚሉ ይታወቃል፡፡

እነዚህ አዛውንት #ባለሥልጣናት #ከፕሮፌሰሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ ለምን #ኢሕአዴግን ሌት ከቀን እንደሚሳደቡ ሲጠይቋቸው #‹‹ጃንሆይም፣ ደርግም #አቅርበውኝ ነበር፡፡ #እንዳማክራቸውም አድርገውኛል፡፡ #እናንተ ግን ናቃችሁኝ፤ይልቁንም ከሥራዬ አባረራችሁኝ›› ብለው #እንደመለሱላቸው #የኢሕአዴግ ሹመኞች ለዚህ ጸሐፊ ነግረውታል፡፡

የሆነው ሆኖ #ፕሮፌሰር #መስፍን በ90 ዓመታቸውም ሰውን ከመዘርጠጥ አልተመለሱም ያስባላቸውን ነገር ሰሞኑን ጽፈዋል፡፡

ሰው በቀድሞው ሥርዓት ውስጥ አገልግሏል ተብሎ አቅም ቢኖረው #የጠገበ ልምድ ቢያካብትም እንኳ በአገሩ መሥራት የለበትም ብለዋል #ፕሮፌሰሩ፡፡ #ስለዚህ ወታደራዊውን መንግሥት በመምህርነት አገልግለሃል በሚል #ከዩኒቨርሲቲ ተባርሬያለሁ የሚሉት እኒህ ሰው መባረራቸው ተገቢ ነው ማለት ይሆናል፡፡

በቀድሞ ሥርዓት ያገለገለ በሙሉ #በአዲሱ አስተዳደር ውስጥ መግባት የለበትም የሚለው ትርክት ተገቢነት ካለው #ፕሮፌሰሩ #ከአዲስ አበባ #ዩኒቨርሲቲ #መባረር የነበረባቸው #ደርግ ሥልጣን በያዘ #ዕለት ነበር #ማለት ይሆናል፡፡

ፕሮፌሰር #መሥፍን አንዳንዶች እንደሚሏቸው መቃወምን የሕይወት #መርሃቸው አድርገው ይዘውታል፡፡ፕሮፌሰር መስፍን #ደግፈውታል የሚባል አሰራር፣ #ርዕዮት፣ #ፖለቲካና ሥርዓት ተሰምቶ አይታወቅም፡፡#እርሳቸው የመሠረቷቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች ሳይቀር #ተቃውመዋል፡፡ #ቅንጅት ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ እርሳቸው ከሌሎች ጋር ከመሠረቱት በኋላ #ቅንጅትን በመቃወም የመጀመሪያ ሰው ሆነው የቀረቡት እርሳቸው ነበሩ፡፡ #ምናልባትም ከኢሕአዴግ #ቀጥሎ የቅንጅት #ተቃዋሚ #ፕሮፌሰር መስፍን ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡

ደጋግመው በመጽሐፋቸው ሁሉንም #ሥርዓቶች ሲቃወሙ እናገኛቸዋለን፡፡ #ፊውዳላዊውን ሥርዓትም፣ ወታደራዊውን አስተዳደርም፣#ፌደራላዊውን አወቃቀርም፣#ኮሙዩኒዝሙንም፣ #ካፒታሊዝሙንም፣ ሁሉንም #አስተዳደር ተቃውመዋል፡፡

መንግሥታትንም #ተቃዋሚዎቹንም እንደሚቃወሙ የሚገልጹት #ፕሮፌሰሩ አቋማቸው ከመቃወም ውጭ ምን እንደሆነ #አይታወቅም፡፡ አንዳንድ በእርሳቸው ሥራዎች ላይ ምርምር ያደረጉ ሰዎች (#ሐብታሙ- አለባቸው፤#2010) #የኢትዮጵያን #የብሔረ-መንግሥት-#Nation Building ግንባታ ካዘገዩ ግንባር ቀደም #ልሂቃን አንዱና ዋነኛው ያደርጓቸዋል፡፡ #ሌሎች ደግሞ እንደ ፕሮፌሰር መስፍን አምባገነን የለም ይላሉ፡፡ ላለፉት ብዙ ዓመታት (መስፍን ኢሕአዴግ ከገባ በኋላእንጂ ከዚያ በፊት የሰደቡት የደርግ ባለሥልጣንም ሆነ ድርጅት የለም) ባለሥልጣናትንም ሆነ ሌሎች ግለሰቦችን ሙልጭ አድርገው እየተሳደቡ፣ ሌሎች ግን በእርሳቸው ሥራ ላይ #አስተያየት ከሰጡ የስድብ ናዳ ይወርድባቸዋል፡፡ #ዲያቆን- ዳንኤል -ክብረት ላይ የደረሰውን የምናስታውሰው ነው፡፡

እርሳቸው ፕሮፌሰር #እየተባሉ ባለፉት 27 ዓመታት ፕሮፌሰርነታቸውን የሚመጥን #የምርምር ሥራ ሲሰሩ ታይተው አይታወቅም፡፡ቁ ጭ ብለው የሚሰራን ሰው ሲሳደቡ ነው የሚታወቁት፡፡ #ለሀገር አንድነትና ፍቅር ምንም እርባና የሌላቸውን #መፃሕፍት እየፃፉ የሞቱትንም #የቆሙትንም ሰዎች ሲዘነጥሉ ነው የነኖሩት፡፡#መቃወም፣#መሳደብ፣#ማዋረድ ዓመላቸው ይመስላል፡፡

#ፕሬዚዳንት #ሳህለወርቅን #የተቃወሙትም በዚህ የመቃወምና #የማዋረድ #ልማዳቸው ተነሳስተው ይመስላል፡፡

No comments:

Post a Comment