#ኢትዮ_ቴሌኮም የዋጋ #ቅናሽ ቢያደርግም ነገር ግን ይህ ዘርፍ ሌላ #ተወዳዳሪ ያስፈልገዋል። ኢትዮ-ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ለማዛወር ቢወሰንም ሃገሪቱ የበለጠ ተጠቃሚ እምትሆነው ይህ ፈጣን የቴክኖሎጂ እድገት የሚታይበት ዘርፍ ላይ የግል #ባለሃብቶች ሲሳተፉበት ነው።
የቴሌኮም ማጭበርበር #እየቀነሰ ሳይሆን እየባሰበት ነው የሄደው። ይህ ዘርፍ ከነ-ሞኖፖሊ መብቱ ወደ ግል ከመዛወሩ በፊት የግል ባለሃብቲች በራሳቸው ካፒታል አዲስ ኩባንያ ይዘው ለመቀላቀል እሚያስችላቸው አዋጅ መጽደቅ አለበት ማጭበርበሩ ( #Telecom_Fraud) እየባሰበት ሄዶአል።
ለሕገወጥ የቴሌኮም አገልግሎት መስፋፋት የተለያዩ ምክንያቶች ተጠቅሰዋል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም ለዓለም አቀፍ ሥራ ትኩረት አለመስጠቱ፣ የውጭ ጥሪዎች ለመቀበል የሚያስከፍለው ክፍያም ከፍተኛ መሆን፣ የዓለም አቀፍ ጥሪ ዋጋ በየጊዜው አለመከለሱና በሕገወጥ ቴሌኮም አገልግሎት የተሰማሩ ግለሰቦችን ተከታትሎ ለሕግ የማቅረብ ሥራ በበቂ መጠን አለመከናወን እንደ ድክመት ተዘርዝረዋል፡፡
ለዚህም መንግስት የግል ባለሃብቶችን ለማሳተፍ የህግ ማዕቀፍ እያዘጋጀ እንደሆነ ተገልጾዓል። #ኢትዮ_ቴሌኮም #ethio_telecom በላከው መግለጫ በአዲስ አበባና #በጅማ ዞን በቴሌኮም ማጭበርበር ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች ከነመሣሪያዎቻቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታወቀ፡፡
ከተለያዩ #የፌዴራልና የክልል #ፀጥታ #አካላት ጋር በጋራ በተደረገ ክትትል #በአዲስ አበባ 34፣ በጅማ ዞን ደግሞ 32 #ሲም ቦክሶች መገኘታቸውንም ጠቁሟል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ ጊዜያት በቴሌኮም ማጭበርበር ምክንያት በርካታ ገንዘብ እንደሚያጣ ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን፣ በተለይም ከዓለም አቀፍ ጥሪዎች የሚያገኘው ገቢ በእጅጉ እንደቀነሰበት ሲያስታውቅ ቆይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት፣የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬ ሕይወት ታምሩ በሰጡት መግለጫ በሕገወጦች ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀው ነበር፡፡
No comments:
Post a Comment