Wednesday, December 26, 2018

የጥንቱዋ ኢትዮጵያ ታሪክ

#የጥንቱዋ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ታሪክ_#የሱባ ቋንቋ መዝገበ ቃላት_#መጽሃፈ ብሩክ_ዣንሹዋ
#መጽሐፈ ክቡር #መጽሐፈ_ፈውስ #የእውነትን ህይወት_ወደዱ #አፍሪካ_ሁኑ #ጥበብ_ከዕውቀት_ ትምህረት_ከልጅነት #የልቤ_ ወዳጅ_የሰው_ዘር_ልጅ #ምክር_ከእኔ_ስማ_አንተ_ወገኔ ስል የተሰኙትን መጽሐፍት ጨምሮ 24 የሚደርሱ መጻህፍትን ጽፌአለሁ። አብዛኛው ጹሁፎቼ  ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ ስለ ዓለም ስልጣኔ ብሎም በጥልቅ ስለማይታወቀው ስላልተመረመሩት
ለሎች ዓለማት ጨምሮ የሚያወሳ ነው።
  #መሪ ራስ ዓማን በላይ ነኝ
መጽሐፎቼን የምጽፋቸው ለህትመት ይበቁልኛል ብዬ ሳይሆን የኢትዮጵያ ታሪክ ትውልድ ሳያውቀው ተከድኖ በመኖሩ ይቆጨኝ ስለነበር ነው። አንድ አንዶች የኢትዮጵያ ታሪክ እንዲሁም መሰረት የሌለው የሚመስላቸው አሉ እንደዚህ አይነት እሳቤዎች በእርግጥም የተሳሳቱ ናቸው። ምክኒያቱም ኢትዮጵያ እነሱን ጨምሮ የእነሱን ዘር ማን ዘር ከመፈጠራቸው በፊት የነበረች ሃገር ናት ። ነጮች ልብስ መልበስ ሳያውቁ በፊት ኢትዮጵያውያን በስልጣኔ በአመራር ጥበብ በህክምና በምህንድስና ሳይቀር ትልቅ ቦታ የነበራቸው ህዝቦች ነበሩ። በነዚህ ጉዳዮችም በተለያዮ መጽሐፍቶቼ ላይ ያካተትኩ ሲሆን ወደ ሃያ አራት (24) የሚደርሱ መጽሐፍቶችን መሳተም ችያለሁ። ሆኖም ለህትመት ያልበቁ ሌሎች ስራዎች አሉኝ። ይህን ሃሳብ ይዤ ነው እንግዲህ የጥንታዊቱዋ #ኢትዮጵያ ትንሳኤ ታሪክ የሚለውን መጽሐፍ የጻፍኩት ። በዚህ መጽሐፍ ውስጥም ማንም ከዚህ ቀደም ስለ ኢትዮጵያ  የማያውቃቸውን ለማመን የሚፈታተኑ ታሪኮች አሰባስቤ የጻፍኩት። እውነት ግን መጪውም ሆነ አሁን ያለው ትውልድ ያሳዝነኛል። እኛ ቀደምቶቹም ብንሆን እውነተኛ ታሪክ ባለማወቅ እውነተኛ ማንነቱ ጠፍቶበት በየሄደበት ታሪኩን ለማግኘት የሚናውዝ በስጋው በነፍሱ የማንነቱ ገናናነት እየታወቀው ዓለም  ሳያውቀው በመቅረቱ ሲያሳንሰው ተደቁሶ  የሚኖር እንደ ግማሽ እብድ የሚያደርገው ስለ ታሪኩ ገናናነት ሲገልጽ ሲሞክር በውስጡ ያለውን አውጥቶ መናገር መግለጽ ስለሚሳነው ዓይኖቹን በማፍጠጥ በቁጣ መንፈስ የሚጋጭ የገዛ ወንድሙን ኢትዮጵያን አገሬን  እንደኔ አታውቃትም አትወዳትም ብሎ የሚደነፋ ነበር። #አሁን ያለው #የማንነት ግራ መጋባት ያናወዘው ነው። የሃገራችን ታሪክ መዛባት ና መጥፋት መነቀፍ የጀመረው ደግሞ ከእኛ ዘመን ቡኃላ በመጣው ትውልድ ነው።
    #የትውልድ ቦታዬም ሆነ ዕድገቴ #ጎንደር_በለሳ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ነው። ገና በልጅነቴ ለትምህርት በሰጠሁት ቦታ ትኩረት ከፍተኛ ነበር። የትምህርት ጥማት ስለነበረብኝ ገና በልጅነቴ ከቤተሰቦቼ ተለይቼ ለዕረጅም ዓመታት ከደብር ደብር እየዘዋወርኩ የቤተክርስቲያን ትምህርት ልቅም አድርጌ ተማርኩ ቤተሰቦቼ ለዘመናት ስለጠፋሁባቸው ጫካ ለጫካ ስሔድ አውሬ በልቶት ይሆናል ብለው እርግጠኛ በመሆን እርማቸውን በለቅሶ ካወጡ ከሰላሳ ከ(30) ዓመት ቡኃላ በህይወት እንዳለሁ አወቁ ። በህይወት አጋጣሚ ብዙ ሃገር ዞሬአለሁ ። በተለይም የማረሳውና ወደ ጥልቅ ጥናት እንዳመራ መንገድ የከፈተልኝን ምስጢር ያገኘሁት ከዛሬ 45 ዓመት በፊት በ19 ዓመቴ ወደ #ሱዳን ኑቢያ ሔጄ በነበረበት ወቅት ነው።  በአንድ ቤተክርስቲያን ግቢ በነበረ የድንጋይ ሳጥን ውስጥ የተገኙ በርካታ የብራና መጻህፍትና ለሃገራችን ታሪካዊ ጥናት አዲስ የምርምር ዕይታ የከፈቱልኝ ነበሩ። በወቅቱ በገዳሙ ውስጥ የነበረኝ ቆይታ እንደ ማንኛውም የሃይማኖት አካልና ተማሪ ነበረ ።
ይሄ ወቅት 1950ዎቹ መጨረሻ የጥንቱዋ ኑቢያ ከነበሩ የጥንት ቤተክርስቲያኖች ፍርስራሽ ውስጥ #የብራና መጻህፍት ማግኘት ችዬ ነበር።
ወደ #ኢትዮጵያ እንደተመለስኩ ብራናዎቹን ለቀዳማዊ አጼ #ኃይለ ስላሴ አሳየዋቸው አጼውም ብራናዋቹን ተመልክተው በጊዜው ለነበሩት የትምህርት ምኒስትር ላኩዋቸው #ምኒስትሩም ብራናዋቹን ተመልክተው አሁን ይህን አሳትመህ ብታቀር  የሚያምንህ የለም።
ዝም ብለህ ጹሁፎቹን እያጠናህ እየተረጎምክ ቆይ ከዛ አመቺ ጊዜ ሲገኝ አሳትመን ለዓለም እናቀርባለን። አሉኝ።   ምክኒያቱን ባላውቀውም የተባለው ቃል ሳይፈጸም ቀረ  ለብቻዬ ሆኜ ከብዙ አመታትና ልፋት ቡኃላ #ብራናዋቹን መተርጎም ቻልኩ።

ጹሁፎቹ የተጻፍት በጥንቱ #ሱባ ቋንቋና በጥንቱ የመሮ ፊደላት እናም በግዕዝ ልሳናት ነበረ። እነዚህን ለመተርጎም እረጅም ጊዜ ፈጀብኝ ሁለቱን ቋንቋዎች ለመተርጎም በቂ እውቀት ያለው ሰው ማግኘትና እንዲመጥን አድርጎ መተርጎም ከባድና ፈታኝ ነበር። በተጨማሪም ስለ ኢትዮጵያ ያልተነገሩ  ሚስጥራትን ለማወቅ ከጠቅላይ ግዛት ወደ ጠቅላይ ግዛት እየተዛወርኩ  #ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት ጋር እየተገኛኘሁ ስለ #ኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ መመራመርና ማወቅ ችያለሁ። የተለያዩ ቦታዎች  ያሉትንም ብርቅ መጻሕፍት ለማወቅ ዕድል አግኝቻለሁ ።   እነዚህን መጻህፍት አሰባስቤ መጻህፈ_ሱባዔ የተባለውን የመጽሐፉን ንድፍ ጽፌ ለወዳጆቼ ሳሳያቸው ከዛም አማን_በላይ ብለው በስሜ የባለቤትነት መብት አያይዘው ይሰጡኛል። ከዛም በጣም በረጃጅም ዐርፍተ ነገር የጻፍኳቸውን ጹሁፍ ሳላስተካክል የላኩላቸውን እነሱ በበኩላቸው ለአንባቢ እንዳያሰለች በአጭር በአጭሩ እየከፋፈሉ እንዲመች አድርገው እያዘጋጁ ያስደስቱኝ ነበር።

በዚህ መልኩ ያሰባሰብኩዋቸውን ጹፎች ወደ መጻህፍት መቀየር ብዙ አላስቸገሩኝም ነበር።
እንደ ነገርኳቹ አብዛኛው የምጽፋቸው ጹሁፎች  በሰው ልጅ በጥልቀት ስላልተዳሰሱ ስለ ዓለማት ሚስጥር ነው። በተለይም መጻህፈ_ብሩክ_ዣንሽዋ መጻህፈ_ክቡር የተባሉ መጻህፍቶቼ ከኢትዮጵያ በአሳሹ ጀምስ_ብሩስ ተሰርቀው ከወጡት ታላላቅ የሚስጢራት  አንዱ በሆነው መጻህፈ_ሄኖክ ዙሪያና አልበርት_አንስታይን ሳይቀር ተመራምሮ ሊፈታቸው ስላልቻለው ስለ ሌሎቹ ዓለማት ሚስጢራትና እኛ ስለምንኖርባት ምድር ትልቅ ሚስጢሮች ነው። እኔም ኢትዮጵያን የእነዚህን ድንቅ ሚስጥራት የያዙ
መጻህፍት ባለቤት እንደመሆናችን  የማወቅ መብት አላቸው ብዬ ስለማምን ሁሉንም ሳይሆን ለንባብ ይመጥናሉ ያልኳቸውን ለንባብ ።

No comments:

Post a Comment