Saturday, December 22, 2018

ፌዴሬሽን ም/ቤትና የማንነት ጥያቄ

"የማንንነት እና የወሰን ጥያቄ ኮሚሽን ህገ መንግስታዊ ነው ወይስ አይደለም? " እሚለው ሳይሆን የኮሚሽኑ #ገለልተኝነት ላይ ትኩረት ቢደረግ ይሻላል። #ኮሚሽኑ አሁንም ቢሆን አጣርቶ #ለፌዴሬሽን ም /ቤት ያቀርባል እንጂ ወሳኝ አይደለም። ስለዚህ #unconstitutional አይደለም። #በህገ መንግስቱ መሰረት አንድ #አዋጅ# ህገ_መንግስታዊ ነው ወይስ አይደለም ብሎ እሚያጣራ #ተቁዋም #የለም #ፍ/ቤቶችም ይህ ስልጣን የላቸውም #ህገ_መንግስታዊ ፍ/ቤትም አልተቁዋቁዋመም #ህገ መንግስቱም ይህን አይፈቅድም። ለዚህ ኮሚሽን መቁዋቁዋም ብቸኛው ባይሆንም ግን  አንዱ ምክንያት የፌዴሬሽን ም/ቤት ወቅታዊ ምላሽን መስጠት አለመቻል ነው።
#የምክር ቤቱ #አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ #ኬሪያ_ኢብራሂም እንደገለጹት፤#" የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ምላሽ አሰጣጥ ውስንነት ነበረው።

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በማንነት ጥያቄዎች ላይ የማይመለከታቸው አካላት እጃቸውን በማስገባት ግጭት እንዲፈጠር እያደረጉ መሆኑን" ገልጸዋል።

”ህገ-መንግስታዊ ስርዓት እንዲሰፍንና የህግ የበላይነት እንዲከበር በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 62 በተሰጠን ስልጣን መሰረት ለጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን” ብለዋል።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት እስካሁን 76 ብሔሮች ዕውቅና ያገኙ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ ኬርያ በቀጣይ የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ምላሽ እንደሚያገኙ" አረጋግጠዋል። ይኽ ከሆነ ዘንዳ የኮሚሽኑ የአስፈጻሚው አካል እንደመሆኑ  ተጠሪነቱ ለጠ/ሚሩ ነው እንጂ እንደ #ፌዴሬሽን ም/ቤት የህግ ተርጉዋሚነትን ስፍራ ስላልወሰደ ህገ መንግስቱን ይጣረሳል #unconstitutional ነው ለማለት አያስደፍርም። ይህ ኮሚሽን የሚያቀርበው ሃሳብ በጠ/ሚሩ ይሁንታን ካገኘ በሁዋላ ለፌዴሬሽን ም/ቤት ይቀርባል ማለት ነው።

No comments:

Post a Comment