Tuesday, November 20, 2018

ኣንድ ጥያቄ ኣለኝ ጉዋዶች ! ?

“የኢትዮጵያ መንግስት በሙስናና የሰብኣዊ መብቶች ጥሰት ስም የጀመረው እንቅስቃሴ ኣቅጣጫውን ስቶ የትግራይ ህዝብ ለማንበርከክ የሚደረግ ጥረት ስለሆነ አንቀበለውም። ከዚህ በተጨማሪም የውጭ ጣልቃ ገብነት አለው ብለን እናምናለን። ”

Ethiopia: Debretsion Gebremichael claimed that the anti-corruption and human rights campaign have gone astray. Source TPLF

ኣንድ ኣጠራጣሪ ነገር ዶ/ር ኣብይን የኢህአዴግ ሊቀመንበር ኣድርገው ሲመርጡ እነ ዶ/ር ደብረጽዮን በሰብአዊ ምብት ጥሰትና በግዙፍ ሙስና grand corruption  የተጠረጠሩትን ለፍርድ ላለማቅረብ ተስማምተው ነው ወይ ? በዚህ ጉዳይ ላይስ በድርጅቱ ውስጥ ተነጋግረውበታል ወይ ? ሌላው ደግሞ በሰብአዊ መብት ጥሰት ምህረትም ሆን ይቅርታ ኣይደረግለትም ይላል ህገመንግስቱ ኣንቀጽ 28።  አሁን ኣቃቤ ህግ በዚህ አንቀጽ መሠረት ነው ስራውን እየሰራ ያለው። ያም ሆነ ይህ " ህግን ኣለማወቅ ከተጠያቂነት ኣያድንም " ይላል የወንጀለኛም ሆነ የፍትሃ ብሄር ህጉ ። ይህን እነ ዶ/ር ደብረጽዮን እንዴት ኣዩት ጎበዝ ? ሁለት ክፍተቶች ይታያሉ ፦

1 )ባንድ በኩል ምህረትና ይቅርታ ይደረጋል ሲባል እነማንን ያካትታል እነማንን ኣያካትምም እሚለውን በግልጽ ጊዜ ወስደው ዶ/ር ኣብይ ከመመረጣቸው በፊት ኣለመወያየት
2) ሌላው የፖለቲካ ስልጣንን ሥለታማ ባህሪን ከመሳት የመጣ ነው። "ለሁሉም።ምህረት የተሰጠ ነው የመሰለን " የሚለው ኣባባል የዋህነትን naivity ከማሳየት ውጭ የሚያዋጣ ኣይመስልም።

የዶ/ር ኣብይ መንግስት ህዝባዊ ድጋፉ ሲያቆለቁልበት የህዝብ ድጋፍን ለማግኘት ሲል ይህን የተዘጋ የመሰለውን ግን ኣቆይቶት የነበረውን ዶሴ ሊከፍት ይችላል።ሌላው ለጠ /ሚሩ መንግስት ይህን ግዙፍ ሰብአዊ መብት ጥሰትን በዝምታ ቢያልፍ ለራሱ ለመንግስቱ ህልውናም ጭምር እሚበጀው ኣይዶለም። ያገራችን ፖለቲካ በፊትም ቢሆን በህግና በመርህ ተመርቶ ኣያውቅም። ስለዚህ ኣሁን ድንገት ደርሶ በመርህና በህግ ይመራ ቢባል በፊት እነደጺ ራሳቸው በህግና በመርህ ተመርተው ያውቃሉ ወይ ?

No comments:

Post a Comment