Thursday, November 22, 2018

ሪፎርምና ኣብዮት በኢትዮፒያ

ሪፎርምና ሪቮሊሽን ፦
#revolution Vs # reform

አብዮት ማለት ስር ነቀል ለውጥ ወይም radical ለውጥ ሲሆን ባብዮት ወቅት" ኣብዮት ልጆችዋን ትበላለች " ይባላል ባብዮት ወቅት ኣብዮተኞቹ የገደሉትን ገድለው ያሰሩትን ኣስረው ተጠያቂነቱን ለታሪክ ነው እሚተውት።# በኢትዮፒያ በተካሄደው የ#66ቱ ኣ.ም. #የኢትዮፒያ ኣብዮት ወቅት እጅ በማውጣት ብቻ መንጌም ባንዲት ሌሊት በእድሜ የገፉትንና በርካታ ታላላቅ ስራዎችን የሰሩትን እነ # ኣክሊሉ ሃብተወልድንና ሌሎቹን ባንድ ሌሊት # 60 ሰዎችን ኣውጥተው ገድለዋል።

ኣብዮት የራስዋን ልጆችንም ኣትምርም። እንደ ድመት የራስዋን ልጆችንም ቅርጥፍ ኣድርጋ ትበላ ነበረ ኣሉ።የቀድሞዎቹ ሶሻሊስቶች በዚህ ይታወቃሉ።

ጥገናዊ ለውጥ ግዜን የሚፈልግ ሲሆን እንደ ኣብዮት ባንድ ምሽት ሁሉም ነገር እሚለወጥበት ኣይዶለም። ትእግስትን የሚያጡ ወደ # ደቦ ፍርድ ፥ ረብሻ ብጥብጥ እሚታይበት ምክንያት ይኽው ብዙ በደል ስለተፈጸመ ፍርድ ዘገየ ብሎ የሚይስቡ በራሳቸው #የመንጋ ፍርድ እዚህም እዚያም እሚታይበት ይኽው የተሐድሶን ባህሪ ካለመረዳትና ይኽን ክፍተት መጠቀም የሚፈልጉ ሃይሎችም ግጭቶችን በማባባሳቸው ነው ።

No comments:

Post a Comment