Thursday, November 22, 2018

reform & Revolution in Ethiopia

ሪፎርምና ሪቮሊሽን ፦

#revolution Vs # reform

#Revolution or # Evolution ? 
ይሻላል ወይስ ኣዝጋሚ ለውጥ ተሃድሶ ይሻላል ?

አብዮት ማለት ስር ነቀል ለውጥ ወይም radical ለውጥ ሲሆን ባብዮት ወቅት" ኣብዮት ልጆችዋን ትበላለች " ይባላል ባብዮት ወቅት ኣብዮተኞቹ የገደሉትን ገድለው ያሰሩትን ኣስረው ተጠያቂነቱን ለታሪክ ነው እሚተውት ። # በኢትዮፒያ በተካሄደው የ#66ቱ ኣ.ም. #የኢትዮፒያ ኣብዮት ወቅት እጅ በማውጣት ብቻ መንጌና መሰል የደርግ ኣባላት ባንዲት ሌሊት ኣለቆቻቸው የነበሩትንና በእድሜ የገፉትንና በርካታ ታላላቅ ስራዎችን የሰሩትን እነ # ኣክሊሉ ሃብተወልድንና ሌሎቹን ባንድ ሌሊት እንደዋዛ # 60 ሰዎችን ኣውጥተው ገድለዋል ወይም በእነሱ ኣነጋገር " ረሽነዋል "  ፥ እነኝህም በተለምዶ "60ዎቹ"  የሚባሉት ናቸው።

ቀጥላም ኣብዮት የራስዋን ልጆችንም ኣትምርም። እንደ ድመት የራስዋን ልጆችንም ቅርጥፍ ኣድርጋ ትበላ ነበረ ኣሉ። የቀድሞዎቹ ሶሻሊስቶች በዚህ ይታወቃሉ።

ጥገናዊ ለውጥ (reform )ግዜን የሚፈልግ ሲሆን እንደ ኣብዮት ባንድ ምሽት ሁሉም ነገር እሚለወጥበት ኣይዶለም። ትእግስትን የሚያጡ ወደ # ደቦ ፍርድ ፥ ረብሻ ብጥብጥ እሚታይበት ምክንያት ይኽው ብዙ በደል ስለተፈጸመ በዚህች ኣገር ላይ ፍርድ ዘገየ ብሎ የሚይስቡ በራሳቸው ፍትህን ለማስፈንና #የመንጋ ፍርድ እዚህም እዚያም እሚታይበት ይኽው የተሐድሶን ባህሪ ካለመረዳትና ይኽን ክፍተት መጠቀም የሚፈልጉና ያልታወቀ ኣላማን ያነገቡ ሃይሎችም ግጭቶችን በማባባሳቸው ነው ።

No comments:

Post a Comment