Thursday, August 15, 2013

የአፍሪካ ህዳሴ


በዓለም ላይ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዘመኑ ወደ አፍሪካ ያዘመመ ሆኖ መታየት ጀምሯል ። ለአንዱ ሲዘንብ ለሌላው ያካፋል እንዲሉ ለቻይናና ለሌሎች የደቡብ መስራቅ እስያ ያካፈው የስልጣኔና የምጣኔ-ሐብት ብልፅግና ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካም ማካ ፋት ጀምሯል ።
      ለአፍሪካ አህጉር ድህነት ብቸኛው ዋና ምክንያት ባይሆንም አንዱ ምክንያት በርካታ የአፍሪካ አገራት በባርነት ፣ ከዚያም በቅኝ ግዛት አገዛዝ ስር መውደቃቸው ለአህጉሩ መደህየት አንዱ ምክንያት መሆኑ አያጠራጥርም ። አፍሪካ ነፃነቷን ካገኘች በኋላም ቢሆን በአብዛኛው ስለ ፖለቲካ ፣ አስተዳደርና ስለ ምጣኔ-ሀብት ስለ መሳሰለው ጉዳይ እውቀት ባልነበራቸው ወታደራዊ መሪዎች እጅ ስልጣኑ በመግባቱ ምክንያት ከ1960ዎቹ ጀምሮ እስከ 2000ዎቹ ጅማሮ ድረስ ብዙዎቹ አፍሪካ አገራት ጉዞ የኋሊት ሆኖ ቆይቷል ።
      ነገር ግን የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት ማንሰራራት ከጀመሩ ወዲህ ከእድገቱ ፀበል ለአፍሪካ አገራት መድረስ ጀምሯል ። የምጣኔ-ሐብት እድገት ለአንድ አገር ጅማሮ ሲሆን ለዛ ሀገር ወደፊት በሌሎች ዘርፍ ለሚያስመዘግበው እድገት መደላድሉ የምጣኔ-ሐብት እድገቱ ነው ። ለአንድ ስልጣኔ ኢኮኖሚ መሰረት ሲሆን ከኢኮኖሚ እድገት ብቻ ግን እድገት ያበቃል ማለት አይደለም ።  በብዙዎቹ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ካለፉት ስህተቶቻቸው በመማር ከመቼውም ጊዜ በተሻለ አመራርን መስጠታቸው መታዘብ ይቻላል ።
      የአፍሪካ አገራት ለዚህ አስፈጊውን ስልጣኔ መሰረት በመጣል ላይ መሆናቸው መልካም  ዜና ነው ። ነገር ግን እንደሚታወቀው አንድ ስልጣኔ በኢኮኖሚ እድገት ብቻ አያበቃም ከዚያ ይልቅ አንድ ጊዜ የሰዎች መሰረታዊ ፍላጎቶች ከተሟሉ በኋላ ግን መንፈሳዊ ፣ ስነ-ልቦናዊ ባህላዊ ሀይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ እና ሀሳብን የመግለፅ ነፃነቶቻቸውን የመሳሰሉ ከፍ ያሉ ፍላጎቶቻችቸውን ወደ ማሟላት መሄዳቸው አይቀርም ።
ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ የምትሆነው ቻይና ስትሆን ይህቺ ሀገር ምጣኔ ሀብቷን በአስደናቂ ፍጥነት በሀያና ሰላሳ አመታት ውስጥ ወደ ግዙፉ ምጣኔ ሀብት ስትቀይር በአንፃሩ የፖለቲካ አድተዳደሯ ግን በአንድ ፓርቲ ላይ የተመሰረተ ሆኖ መቀጠሉ ለወደፊት መረጋጋቷ ስጋትን መደቀኑ አይቀርም ። ነገር ግን በርካታ ተመልካቾች እንደሚገምቱት የመካከለኛው መደብ በቁጥና ፣በሀብት እየበረከተ ሲሄድ ተጨማሪ የፖለቲካ መብቱን መጠየቁ አይቀርም ። ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆን ወጣት ትውልዷን እ.አ.አ. በ1989 ዓ.ም. በታይናሚን አደባባይ ባደረጉት የተቃውሞ አመፅ የፈጀችው ቻይና እየበለፀገ ያለው ወጣት ህዝቧ የበለጠ የመናገር ነፃነትን ፣ የመምረጥ ሀሳብን የመግለፅ የመሳሰሉ ዲሞክራሲያዊ መብቶቹ በበለጠ እንዲከበሩለት መጠየቁ አይቀርም ።  
      ምእራባውያን ከላይ ከላይ ሲታይ ስልጣኔአቸው በቁሳዊ ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት ላይ የተመሰረተ ቢመስልንም ወደ ውስጡ ሲገባ ግን ስልጣኔቸው የተመሰረተው በጣም መሰረታዊ በሆኑ ፍልስፍናዎች አስተሳሰቦችና አስተምህሮቶች ላይ ነው ። ከእነኚህ መሰረታዊ ከሆኑ የፖለቲካን ሆነ የህግ የምጣኔ ሀብት አስተምህሮዎቻቸው ዝንፍ የማይሉ ሲሆን ችግር ቢያጋጥማቸው እንኳን ጊዜ ሰጥተው መልሰው ነገሮችን ወደ ነበሩበት ያስተካክሉታል ።
      ምንም አስንኳን በ20ኛው ክፍል ዘመን ላይ የአለም ሀያሏ አገር አሜሪካ ብትሆንም አሜሪካንን የመሰረቱ መስራች አባቶቿ ግን ያቺን አገር መሰረት የጣሉት በአውሮፓውያን ፈላስፎች አስተረምህሮና ፍልስፍና ላይ ነው ። እንደ ጆን ሎኬና ፣ሩሶን በመሳሰሉ የእንግሊዝና ፈረንሳይ ፈላስፎች አስተምህሮዎች ላይ ነው ። በአብርሆት ዘመን ከአውሮፓ እንደ ዋና አሳብያንና ፈላስፎች ይቆጠሩ የነበሩት በተለይም የፈረንሳይ እንግሊዝ ፈላስፎችና ፀሀፍት ነበሩ ። አሜሪካ በምትመሰረትበት ወቅት በአለም ላይ ተሰሚነት የነበራቸው የአውሮፓውያን አሳብያን ነበሩ ። በመሆኑም አሜሪካ የእነሱን አስተምህሮ በመውስድ ራሷን እንደ አገር በሁለት እግሯ መቆም ችላለች ።

No comments:

Post a Comment