Thursday, August 15, 2013

Jews and the Bible


ጦርነት የሌለበት ስርአትን ለማሰብ አዲሱን የአለም ስርአትን ማሰብ ሳይቀል አይቀርም ። በአለም ላይ ሀገራት እስካሉ ድረስና ሀገራት በድንበር ፣ በሀይማኖት በርእዮተ-ዓለም ፣ በኢኮኖሚና በብሄራዊ ጥቅም እስከተለያዩ ድረስ በአለም ላይ የጦርነት ስጋት መኖሩ አይቀሬ ሆኖ ይታያል ።
በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ከ188 ያላነሱ ሴቶች መጠቀሳቸውን የመፅሀፍ ቅዱስ ምሁራን ይገልፃሉ ። መፅሀፍ ቅዱስ አፈንጋጭ ለሆኑ ሴቶች የተደረገባቸውንነም ቅጣትንም ይገልፃል ። ለምሳሌ መግደላዊት ማርያም ከአሮን ጋር ሆና ሙሴ ኢትዮጲያዊቷን በማግባቱ ምክንያት ሙሴን በመናገሯ ምክንያት እግዝአብሄር እጅግ ተቆጥቶ እንዴት ባሪያዬን ሙሴን ትናገሪያለሽ በማለት መግደላዊት ማርያም በመጨረሻም በምድረ በዳ እንደሞተች እንዲሁም እግዝአብሄር በሷ ምክንያት ለሰባት ቀናት እስራኤላውያን ጉዟቸውን እንዳዘገዩም መፅሀፍ ቅዱስ ይገልፃል ።
እንዲሁም ኤዛቤል የተባለች እንዲሁ ባእድ አምልኮን በመከተል ፣ በማምለክና በክፋት የምትታወቅ ሴት በመጨረሻ አስከሬኗን ውሻ እንደበላው ይገልፃል ። በእርግጥ ኤዛቤል የእስራኤል አምሳያ ነች ጣኦትን ማምለክ የጀመረችውና ለእግዝአብሄር አልታዘዝ ያለችውን እየሩሳሌምን ይወክላል ። እስራኤልም ሩትና ሁለት ሴቶች እስራኤል የመሰረቱት ናቸው ። እብራውያን ምእራፍ 12 ቁጥር 22 ።
መፅሀፍ ቅዱስ በተመለከት ቮልቴር አይሁዳውያንን ሲተች «እውራን ተርጓሚዎች» ይላቸዋል ፣ ቮልቴር እንደሚለው እኛ አውሮፓውያን ስናቃጥላቸውና በተገኘው ምክንያት ሁሉ ጥፋተኛ አድርገን ስንቀጣቸው የነበሩት አይሁዳውያን የእግዝአብሄር በእነርሱ በኩል መገለጡ ያስገርመዋል ።
ይህ ብቻም ሳይሆን ቮልቴር አዲስ ኪዳን እርስ በእርሱ የሚጋጭ ስለሆነ የትኛውን እንዳለብን ግልፅ አይደለም ይላል ። ለቮልቴር ሀይማኖተኛና ስነ-መለኮተኛ የተለያዩ ናቸው ። እንደ ቮልቴር አገላለፅ ለአለም በሀይማኖት የተነሳ ለተከሰቱ ግጭቶች ተጠያቂዎቹ ስነ- መለኮተኞች ስለሆኑ ነው የሚል አቋም አለው  ። ሀይማኖተኛ ጦርን አይመዝነም ማለቱ ነው በተዘዋዋሪ መንገድ ። ለቮልቴር በአለም ላይ ያሉ ካህናት ፣ ሰባኪዎች ፣ ፓስተሮች ወዘተ ሰነ- መለኮታውያን ናቸው እንጂ ሀይማኖተኞች አይደሉም ። ለቮልቱር ስነ - መለኮታውያን ማለት ልክ እንደ አንድ ርእዮተ አለም አራማጅ ማለት ነው ። በአለም ላይ በአሜሪካን በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ፣ በአሜሪካና በኮሚኒስት ቻይና መሀከል እንዳለው አይነት የአስተሳሰብ ወይም የአስተምህሮ «የዶክትሪን» እና የቀኖና «ዶግማ» ልዩነት የሚንፀባረቀው የአለምን ሀይማኖት የሚመሩት ስነ-መለኮታውያን ስለሆኑ ነው ባይ ነው ። 

ሀዋርያው ጳውሎስ ትኩረቱን የደረገው በእምነት ዙሪያ ሲሆን በህግ አልታሰርንም ፣ በህግ አልተፈረደብንም የሚል አስተምህሮዎቹን ለበርካታ በግሪክ ዙሪያ ለነበሩ ህዝቦች፣ እንዲሁም ለጣሊያንና ለስፔንም ጭምር በላካቸው መልእክቶቹ ላይ አስርፍሮ ልኳል ። አይሁዳውያን የሙሴን ህግጋት አጥብቀው የሚከተሉ ሲሆን በዋነኛው መፅሀፋቸውም በታልሙድም ጭምር የአይሁድ እምነትን የማይከተሉትን ሁሉ እንደ ዝቅተኛ ሰው ዘር አድርጎ የሚቆጥር ነው ። ጳውሎስም በመልእክቱ በረከት የመጣው በአይሀዳውያን ስለሆነ አይሁዳውያንን እነዲ ንዲባርኩ ለተከታዮቹ ክርስትያኖች በመልእክቱ አስተላልፎ ነበበረ ።

No comments:

Post a Comment