Thursday, August 15, 2013

የመንፈስ ህልውና


በሚሊየን አመታት ውጥ የሰው ዘር ራሱ ህልውናውን ሊያጣ ይችላል ። በዚህ ምድር ላይ የምናየው ነገር በጊዜ ውስጥ ሊፈራርስና ሊጠፋ እንደሚችል መገመት ይቻላል ።
በምእራባውያን የስልጣኔ አስተሳሰብ መሰረት ስልጣኔ ከተጀመረ ቢበዛ አስር ሺህ አመታት አይበልጥም ። የምስራቁ ቅድመ-ታሪክ የሚባለውን የሚያጠቃልል ሲሆን በአንፃሩ የምእራበውባውያን ስልጣነቤ ኔም ሆነ አስተሳሰብ ከዘመናዊው ውምን ወይንም በስነ-ሰብ «አንትሮፖሎጂስቶች» ተመራማሪዎች  ከተደረሰበት የምርምር ውጤት አያልፍም ። ይህም ማለት በአብዛኛው የሰው ልጅ እርሻን ጀምሮ የቤት እንሰሳትን አርብቶ መኖር ከጀመረበት ዘመን የሚጀምር ነው ። ነገር ግን ቅድመ-ታሪክ ከዚያም ያለፈ ሲሆን በመቶ ሺዎች አመታት የሚ ቆጠር እድሜን ያስቆጠረ ነው ።  
መንፈስን በተመለከተ አይሁዳውያን ፣ ኢራናውያን (ፐርሺያኖች) እና አረቦች እና ህንዶችናቸው ሊቃውንቱ ። በአብዛኛው ምእራባውያን ቁሳዊ ነገርን በመፍጠር ረገድ ተወዳዳሪ የላቸውም ። ምእራባውያና ባሏቸው ወፈ - ሰማይ ኩባንያዎቻቸውና ኮርፖሬሽኖቻቸው አማካይነት በአለም ላይ ግዙፍ ምጣኔ-ሐብት እንቅስቃሴ ባለቤቶች ሲሆኑ በአንፃሩ መንፈሳዊ ነገርን በተመለከተ ግን ከምስራቅ ሰዎች ብዙ የሚማሩት ነገር አለ  
በአንፃሩ ቁሳዊ ነገርን በመፍጠር ረገድ ግን ምስራቆቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከምእራባውያን በመማር ምጣኔ-ሀብታቸውን ማሳደግ እና በኢንዱስትሪ መበልፀግ የጀመሩት አሁን በቅርብ ነው ማለት ይቻላል ። ለዚህም በአንድ በኩል ቀድመው በሳይንስና ቴክኖሎጂ የበለፀጉት ምእራባውያን ቀድሞ አፍሪካውያንን በባርነት ፣ በኋላም አፍሪካንና እስያን በቅኝ ግዛት በመ  ግዛት ለመቶዎች አመታት ወደ ኋላ እንዳያድጉ ማነቆ ስለሆኗቸው ሲሆን ፣ በኋላ ላይም ቢሆን እነኚህ በምእራባውያን አጠራር «ሶስተኛው ዓለም» በመባል ሲጠሩ የነበሩት መጀመሪያ ለይ ላይ የአገሮቻቸውን አስተዳደሮች ከቅኝ ገዢዎች በተረከቡባቸው ወቅቶች ካለማወቅና ብሄራዊ ስሜታቸውን ለማነቃቃት በአንዛኛው ትክክለኛውን የእድገትና የልማት ጎዳናን ሳይከተሉ በመቅረታቸው ምክንያት ከምእራባውያን አይነት የዳበረ እድገትን ለአስርት አመታት መፍጠር አቅቷቸው ቆይተዋል ።
ሀያልና ግዙፍ ኢኮኖሚን በሀያና በሰላሳ አመታት ውስጥ የገነባችና ቻይናን  ብንወስድ ቻይና በማኦ የአገዛዝ ዘመን በባህል አብዮት እድገት ገጠር ነው ያለከው በሚል የተማረውን ሀይሏን ወደ ገጠር በመላክ በሚሊዮን ዜጎቿን ለእልቂት ስትዳርግ ምጣኔ ሀብቷም የሶስተኛው አለም ከሚባሉት ሆኖ ቀርቶ ቆይቷል ። ቻይና ከማኦ ህልፍት በኋላ በዴንግ ዚያዎ ፔንግ ዘመን «ድመቷ ጥቁት ወይም በነጭ መሆኗ ሳይሆን ፣ ድመት መያዝ መቻሏ ነው» በሚል አለመካከት ካፒታሊዝምም ሆነ ሶሻሊዝም ዋናው ምጣኔ ሀብቱን ማሳደጉና የህዝብን የኢኮኖሚ ጥያቄን መመለሱ ነው በሚል ተግባራዊ «ፕራግማቲክ» በሆነ አስተሳሰብ ወደ ካፒታሊዝም የኢኮኖሞ ስርአት በመግባት ምእራባውያን ለመድረስ በርካታ መቶ አመታት የፈጀባቸውን በሀያና ሰላሳ አመታት ውስጥ ማሳካሰት የቻለችው ። ቀድሞ ታዳጊ ይባሉ የነበሩት አገራት ወደ ቁሳዊ እድገት ፈጠራ ከገቡ ምእተራባውያንን በቀላሉ ማለፍ እንደሚችሉ ቻይናና ሌሎቹንም ተመሳሳይ የእድገት ጎዳና  ውስጥ የገቡት «ብሪክስ» በመባል የሚታወቁት አገራት አይነተኛ ምስክሮች ናቸው ።      
ብላስቶቭስኪ የተባለችው የአዲሱ ዘመን እንቅስቃሴ መስራች ራሺያዊት እንደምትለው ምእራባውያን ለህንዳውያን መፋንፈሳውያን የበላይነትን መቀለበል አለባቸው ።
በነገራችን ላይ አፍሪካውያንና እስያውያን ከተፈጥሮ ጋር ያላቸው ትስስር እጅግ ጠንካራ ነው ። ለምሳሌ በቻይና አንድ ቤሄረሰብ አንድ ልጅ ሲወለድ አንድ ዛፍ የተ ይተከልለታል ፣ ልክ ያ ሰው ሲሞት ሲወለድ የተተከለለት ዛፍ ተቆርጦ የአስከሬን ሳጥን ይሰራበትና ይቀበርበታል ። ዛፉም ለዛ ሰው የተተከለ እንደመሆኑ ማንም ሰው አይቆርጠውም ። ለደኑ በየጊዜው የአምልኮ ስርአትን የሚያደርጉለት ሲሆን አካባቢውም በደንና በጫካ የተሸፈነ ሲሆን ደናማው አካባቢ በመባል በቻይና ይጠራል ። አፍሪካውያንም ተፈጥሮን የማይነኩ ሲሆኑ ከሚበሉትና ከሚጠጡት ውጪ ደኑን የማይነኩትና ጉዳትን የነማያደርሱበት ሲሆን ጥቅጥቅ ካለው ደን ጋር ጎን ለጎን በሰላም ለዘመናት ሲኖሩ ቆይተዋል ። በአማዞንም ደኖችም ውስጥ እንዲሁ ጥንታዊና ቀደምት የሆኑት የአማዞን ነዋሪዎች ከተፈጥሮ ጋር ለሺዎች አመታት በሰላምና ተፈጥሮውን ሳይነኩት ኖረዋል ።
አንድ ሰው እነኚህን ሰዎች ባእድ አምላኪዎች ናቸው ሊል ይችላል ፣ ነገር ግን ከተፈጥሮ ጋር ተግባብተው ለሺዎች አመታት መኖር መቻላቸውን ማየት ይገባል ። በአሁኑ  ዘመን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባደገ ቁጥር በተፈጥሮ ላይ የሚደርሰው ጉዳትም እያየለ ሲሄድ በተለያዩ አገራት የሙቀት መጨመር ፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ ፣ የዓለም ሙቀት መጨመር ፣ የአካባቢ መጎዳት ፣ የአፈር አሲዳማ መሆን ፣ የአሲዳማ ዝናብ መጣል፣የውቅያኖስና የውሀ አካላት መጠን መጨመርና በሰሜንና በደቡብ ዋልታዎችና በተራራዎች አናት ላይ ያለ በረዶ መቅለጥ እየታየ ነው ። ይህም ዘመናዊው ሰው በእውቀቱ ተፈጥሮን በመቃረኑ የተከተለ መሆኑ አያሻማም ። የሰው ልጅ በገዛ ራሱ አስቦና ተጨንቆ የፈጠረው እውቀቱ ጠላቱ ሊሆን እንደሚችል ለመረዳት በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በማየት በቀላሉ መረዳት ይቻላል ።    
         

No comments:

Post a Comment