ምእራባውያን
ራሳቸው አልፎ አልፎ ቢደነቃቀፉም ቢሉም ብዙ ጊዜ ግን መርሆቻቸውና ፍልስፍናዎቻቸው ሰርተውላቸዋል - በመርህ የሚመሩ መሆናቸውም
በእጅጉ ሳይጠቅማቸው አልቀረም ። ለመርህ ተገዢ መሆን ለጊዜው ችግር ቢያጋጥም እንኳንካለው ችግር አንፃርከመርህ ለመውጣት ሊፈታተን
ቢችልም ፤ በረጅም ጊዜ ግን በመርህ ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ አሸናፊና ጠንካራ ሆኖ ይወጣል ።.
በተለይም ከዲሞክራሲ ፣ ከሰብአዊ መብት ጋር በተያያዘ ከሌሎች ሀገራት በተሻለ
የነሱ መርሆዎች በበለጠ የሚሰሩ ሆነው ተገኝተዋል ። ነገር ግን እነሱም በቀላሉ እዚህ ደረጃ አልደረሱም በርካታ ስህተቶችን ሰርተው
ነው ። በባሪያ ንግድ እና በግኝ ግዛት ዘመን በሌሎች ህዝቦች ላይ ካደረሷቸው ሰቆቃዎች፣ ከአንደኛውና ከሁለተኛው የአለም ጦርነቶች
፣ በየሀገሮቻቸው ከነበሩ የመብት ትግሎች ለምሳሌ ጥቁሮች በአሜሪካን አገር የሰብአዊ መብታቸውን ለማስከበር ካደረጓቸው ትግሎች እና
ከሌሎችም ብዙ ትምህርቶችን ቀስመው ነው እዚህ አሁን ለደረሱበት የሰብአዊ መብትን ማክበርና ወደ የዲሞክራሲ ደረጃ የደረሱት ።
ከቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ጋር ባደረጉት ትግል የቀዝቃዛው ጦርነት ፣ ሶቭየት ህብረትም ከአሜሪካ ጋር ተመጣጣኝ የጦር መሳሪያ እና
ወታደራዊ አቅም የነበራት ሀገር ነበረች ። ይሁን እንጂ በ1963 ተከስቶ የነበረው የኩባው የሚሳይል ቀውስ አደገኛ ሁኔታን ለአለም
ከመፍጠሩ የተነሳ ፣ ቀውሱ በሰላም ባይፈታ ኖሮ አለማችን የዛሬዋን አለማችንን አትሆንም ነበረ ።በአለም ላይ አሁን ባለው የሰው
ልጅ በታጠቀው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ፊት ለፊት ሊደረጉ የሚችሉ ጦርነቶች አለማችንን አንዴ ብቻ ሳይሆን ደግመው ደጋግመው ማጥፋት
እሚችሉበት የቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ ተደርሷል ።
ይህን
የተረዱት አሜሪካኖች ግን የሶቭየት ህብረትን ግዙፍ አቅም በአመታት ውድድር በማድረግ ፣ ያንን ውድድር መቋቋም ሲያቅተው ራሱ ስርአቱ
ከውስጡ ሊፈራርስ ችሏል ። የኮኮቦች ጦርነት(Star Wars) የተሰኘው አሜሪካን የጀመረችው ሶቭየት ህብረት ከነበራት የገንዘብም
ሆነ የቴክኖሎጂ አቅም አንፃር በአጠቃላይ ከአሜሪካንም ሆነ ከምእራብ አውሮፓውያን ጋር መወዳደር ባለመቻሏ ልትፈራርስ በቅታለች ።
ይህ ብቻ ሳይሆን የሶሻሊስት ስርአት እንደ ዲሞክራሲያዊ ስርአት መሪዎችን እየቀያየረ ፣ የፖሊሲ ለውጥ እያደረገ የመሄድ አቅምና
ብቃትም ስላልነበረው መሪዎቹ በእድሜ እያረጁና አንዳንዶቹም እየሞቱ የነበሩትየሶቭየት መሪዎችን ውስጥ ችግሮቻቸውን በተለይም የኢኮኖሚ
ችግሮችን ለመፍታት ሳይችሉ ቀርተዋል ። ይባስ ብሎም በወቅቱ የገቡበት የአፍጋኒስታን የጦርነት ክፉኛ ጎድቷቸዋል ። ሌላው ደግሞ
የሶቭየት ስርአት ከፍተኛ አመራሩ ተቋማዊ ሳይሆን መቅረቱ ለውድቀቱ ትልቅ አስተዋፅኦን አድርጓል ።
የቻይና የኮሚኒስት ፓርቲን ብንወስድ ለማኦ ሞት በኋላ በቶሎየአመራር ስፍራውን ወደ ተቋማዊነት አደረጃጀት ስለቀየሩት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የሶሻሊዝምን ውድቀት መትረፍ ችሏል ። ይህንም በመሆኑ ምጣኔ - ሀብታዊ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግናስላስቻለው በሌሎች የኮሚኒስት ስርአቶች ያጋጠመው መፈራርረስ ሳያጋጥመው ቀርቷል ። ወደ ተቋማዊ አደረጃጀት መቀየር አንድ ስርአት ለዘብ «flexible» ለዘብ እንዲሆን ያስችለዋል ።በአመራሩ ላይ የሚመጡ የተለያዩ ሰዎች ስለሚኖሩ የተቋማዊ ፣የተለያዩ የአመራር ስልቶች ስራ ላይ የመዋልና አስፈላጊ የሆኑ የፖሊሲ ለውጦችን ለማድረግ እድልን ይሰጣል ።
በወቅቱ
የሶቭየት ህብረት መሪ የነበሩት ሚካኤል ጎርባቾቭ ፔሬስትሮይካና ግላስኖት በተባሉት የግልፅነትና የሶቭየት ህብረትን ስርአት ለማሻሻል
ነው እንጂ ስርአቱን ለማፍረስ አልነበረም አላማቸው ። ይሁን እንጂ ነገሮች ተቀያይረው ባልተጠበቀ ሁኔታ ስርአቱ ፍርስርሱ ወጥቷል
። ምእራባውያን ከ20ኛው ክ/ዘመን ታላላቅ ሰዎች አንዱ ናቸው እሚሏቸው ጎርባቾቭን ሲሆን እንደ ተወዳጅ ታዋቂ ሰው አድርገው ነው
እሚወስዷቸው - ያንን ያስፈራቸው የነበረን ግዙፍ ስርአት ስላፈራረሱላቸው ሊሆን ይችላል ። ይሁን እንጂ ትልቁ ነገር የምእራባውያን ትእግስትና ፣ ፊት ለፊት በወታደራዊ
ጉልበት ለመጋፈጥ አስቸጋሪ የሆነን ስርአት ለመጣል የተጠቀሙበት ስልት ግን እሚደነቅ ነው ።
አንዱ
የምእራባውያን የጥንካሬ የዲሞክራሲ ስርአት ሲሆን የፖለቲካ አመራራቸው ተቋማዊ ሲሆን ፣ የምጣኔ - ሀብት አስተዳደራቸውም ተከታታይነት
ባለው እቅድ የሚመራ ነው ። የማእከላዊ ባንኮችን ብንወስድ ነፃና በራሱ የምጣኔ - ሀብትን ማለትም የገንዘብ ፖሊሲዎችን መውስድ
የሚችል ሲሆን ከፖለቲከኞች ቀጥታ ስልጣን እና ቁጥጥር ውጪ ነው ። በነገራችን ላይ ነፃ የሆነ የማእከላዊ ባንክ ምጣኔ - ሀብት
ሲያድግ የሚሆን ሲሆን እንግሊዝ እንኳን በቅርቡ ነው ባንክ (Bank of England) ነፃ ያደረገችው ። ስለዚህ ነፃና ከፖለቲካ
አመራሩ ገለልተኛ የሆነ ማእከላዊ ባንክ እንዲኖር ያደረገ እንደ ቅድመ ሁኔታ የገንዘብና የአክስዮን ገበያዎች መኖር አለባቸው ።
ይሁን
እንጂ ምእራባውያን ሁልግዜ መርሆዎቻቸው ይሰሩላቸዋል ማለት አይደለም ። ምእራባውያን ከተደነጋገሩባቸው «ስታምብል» ካደረጉባቸው
የኢራቅና የአፍጋኒስታን ጦርነቶች ምሳሌዎች ናቸው ። አሜሪካን ውስጥ ጦርነት ሲመጣነው ጂኦግራፊን የሚማሩት ይባላል።
እንጂ ከዛ በፊት ወጣቶቹ ስለአለም በሚገባ እውቀትን ይዘው አለማደጋቸው በፖለቲከኞቹም ላይ የሚንፀባረቅ ነው ። ከዚህ ቀደም አሜሪካ ራሷን እንደ አለም ማእከል አድርጋ ትወስድ የነበረ
ቢሆንም አሁን ግን ያንን በመረዳት አለምንም ራሳቸውንም በተለየ መንገድ ማየት ጀምዋል ።በታወጀው በሽብር ላይ ጦርነት (War
on Terror) ከጓናታናሞ ቤይ በፊት ሽብርተኝነትን በአሜሪካ ላይ በፈፀሙ ላይ በመደበኛ ፍርድ ቤት ታይቶ ለምሳሌ አይነስውሩ
ግብፃዊ ላይ ጨምሮ ፍትህ የተሰጠ ቢሆንም ሆንም በቡሽ ዘመን ግን ጓንታናሞ ቤይን በመክፈት የሰብአዊ መብትን የሚጥስ ፍርድ ቤትን
ለመክፍትና በአለም አቀፍ ደረጃም ስለሰብአዊ መብት የነበራትን መልካም ስም ለማጉደፍ በቅታለች ። ይህ ብቻ ሳይሆን ለፕሬዝዳንትነት
የሚወዳደሩ በርካታ ፖለቲከኞቿ የቀድሞውን ትንሹ ቡሽን ጨምሮ በቂ የአለም አቀፍ እውቀት እንደሌላቸውና ፣ በርካታ ስህተቶችን ሲሰሩ
ታይተዋል ። አንድን የአለም ሀያል የሆነ አገርን የሚመሩ የፖለቲካ ሰዎች ስለአለም አቀፋዊ እውነታዎች በቂ ግንዛቤና እውቀት ሊኖራቸው
እንደሚገባ ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው ።