የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር በድረ-ገፁ ባሠራጨዉ መግለጫ እንደሚለዉ ሶስቱ መንግሥታት በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል የተጀመረዉን የሠላም ሒደት-በተለይ፣ የአፍሪቃ ቀንድን ባጠቃላይ ለማተራመስ እያሴሩ ነዉ። መግለጫዉ «እርባና ቢስ» ያላቸዉ እርምጃዎች ካታር በመደበችዉ ገንዘብና የዘመቻ አገልግሎት የሚቀነባበሩ ናቸዉ።
የባህር በር አልባ #Landlocked አገር መሆን አንዱ ጥቅም አለው ከተባለ ይኽው ከሀያላኑ ፍጥጫ ነጻ መሆን ነው። በዚህ የሀብታም ዓረብ አገራትና የሀያላኑ ሽኩቻ መድረክ ከመሆን እነ ጅቡቲና ኤርትራ ፤ ሱዳን፤ ሶማልያ አላመለጡም። በአንጻሩ ኢትዮጵያ ይህ ከመጋረጃው በስተጀርባ የቀይ ባህርን የመቆጣጠር ወይም የአረብ ባህር የማድረግ ውዝግብ ወይም ትግል አይመለከታትም ።
በቅርቡ ኤርትራ የቀይ ባህርን ጠረፍ ለመቆጣጠር የሚደረግ ያለችውን «የጥፋት መልዕክተኞች» ያለቻቸዉን ቱርክን፣ ቀጠርንና ሱዳንን አውግዛለች።
የቱርክ መንግሥት፤ በጎርጎሪያኑ 2019 መጀመሪያ ላይ ለማይታወቀዉ «የኤርትራ ሙስሊም ሊግ» ሊቀመንበር፣ የኤርትራ ዑለማ ሊግ/የኤርትራ ራቢጣ-አይ ዑለማ በሚል ሽፋን ፅሕፈት ቤት መክፈቱን ይጠቅሳል። መግለጫዉ እንደሚለዉ ከጥቂት ቀናት በፊት ካርቱም፣ ሱዳን በተደረገ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ «ጥፋት አራማጅ» ሰዎችም በኤርትራና በኢትዮጵያ ላይ የጠብ አጫሪነት መልዕክት አስተላልፈዋል። ቀጠር የኤርትራ የቅርብ ወዳጅ፣ የኤርትራና የጅቡቲ ሸምጋይም ነበረች።የቀይ ባህርን የዓረብ ባህር ለማድረግ በሳዑዲ አረቢያ የሚመሩት የዓረብ መንግሥታት ከካታር ጋር ዉዝግብ ከገጠሙ ወዲሕ ግን ኤርትራ ካታርን ትታ ከሳዑዲ አረቢያ ጎን መቆሟን አስታዉቃለች። ቱርክ ባንፃሩ ቀጥር ዉስጥ ያላትን ጦር ሠፈር አጠናክራለች።
No comments:
Post a Comment