Tuesday, August 20, 2019

የዓለም የሕዝብ ቁጥር

መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ፒው የጥናት ማዕከል ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚጠቁመው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በጎርጎሮሳዊው 2100 ዓ.ም. 294 ሚሊዮን ይደርሳል ,

በተጠቀሰው ጊዜ 527 ሚሊዮን ዜጎች የሚኖሯት ናይጄሪያ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ ትሆናለች። ከአፍሪካ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ታንዛኒያ፣ አንጎላ፣ ኒጀር፣ ግብፅ እና ሱዳን የሕዝብ ቁጥራቸው በከፍተኛ ፍጥነት ከሚያድግባቸው ሃገራት መካከል ቀዳሚ ናቸው።

በመረጃው መሠረት የምሥራቅ አውሮጳ ሃገራት የሕዝብ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል። አልባኒያ፣ ሰርቢያ፣ ሞልዶቫ እና ቦስኒያ ሔርዝጎቪና በ2100 ዓ.ም. የሕዝብ ቁጥራቸው በከፍተኛ ደረጃ ከሚቀንስባቸው መካከል ይገኙበታል።

የዓለም ስነ-ሕዝብ ቀን በዛሬው ዕለት ሲከበር የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሕዝብ ብዛት መጨመር በሰው ልጅ አኗኗር እና በልማት እቅዶች ላይ ስለሚኖረው ጫና ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይሠራሉ።

የተፈጥሮ ሐብት መመናመን፣ የሐብት ክፍፍል መዛባት፣ መሠረታዊ ግልጋሎቶች አለመሟላትን የመሳሰሉ ቀውሶች በሕዝብ ቁጥር መብዛት የበለጠ እንደሚጠናከሩ የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ይጠቁማል።

No comments:

Post a Comment