# የደሕንነት አዋጅ ቁ 804/2005 ★★★★★★
የፌድራል ዓቃቢ ሕግ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይፋ ሲያደርግ ፥የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያፀደቀውና ሐምሌ 16/2005 ዓ.ም በነጋሪት ጋዜጣ “የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የተደነገገው” አዋጅ ቁጥር 804/2005 ስለሕግ ከለላና ስላለመገደድ (Immunity and Non–compellability) በሚያትተው አንቀፅ 20(1) ሥር፡– “ማንኛውም የአገልግሎት #ኃላፊ ወይም ሰራተኛ #ከስራ_ሲሰናበት ወይም ወደ ሌላ ቦታ ስራ ሲዘዋወር በአገልግሎት ተመድቦ በሚሰራበት ወቅት ከተልዕኮው ጋር ተያይዞ ስላወቃቸው መረጃዎች ወይም በእጁ ስለገቡ ሰነዶች ለፍርድ ቤት ወይም አጣሪ ኮሚቴ ወይም ለሌላ አካል እንዲገልጽ ወይም እንዲያቀርብ አይገደድም’ ሲል ያትታል። በዚህ መሰረት የፌድራል ዓቃቢ ሕግ ለፍርድ ቢያቀርባቸውና የአዋጁን አንቀፅ ጠቅሰው #መረጃ_አልሰጥም ቢሉ #ዓቃቢ_ ሕግ በምን መስፈርት ጥፋተኛ ናቸው ወይም ጥፋተኛ አይደሉም የሚል ውሳኔ ሊያሳልፍ ይቻለዋል? የሰራተኛው ተጠሪነት ለ#ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመሆኑ የቀድሞው ጠቅላይ ሚ/ር ስራቸውን በአግባቡ ባለመምራታቸው ተጠያቂ ሊሆኑ አይገባምን? …ወዘተረፈ ** አንድ አዋጅ ሲወጣ ከህገ መንግስቱ ጋር መጣረስ የለበትም ነገርር ግብ ግን ከፍተኛው ተስልጣን አካል የህዝብ ተወካዮች ም /ቤት ስለሆነ ይህ ያወጣው ህግ ማለትም በህገ መንግስቱ መሰረት ሰብአዊ መብትን የጣሰ ይቅርታ ወይም ምህረት አይርረግለትም ሥለሚል ይህ የደህንነት መስርያ ቤትን እሚምመለከት አዋጅ ከህገ መንግስቱ ጋር ይጣረስ አይጣረስ ያየው የለም። ለሰብአዊ መብት ጥሰት መንስኤ የሆነው የጸረ_ሽብር አዋጁም ከህገ_መንግስቱ አንጻር የፈተሸው የለም። “ማንኛውም የአገልግሎት #ኃላፊ ወይም ሰራተኛ #ከስራ_ሲሰናበት ወይም ወደ ሌላ ቦታ ስራ ሲዘዋወር በአገልግሎት ተመድቦ በሚሰራበት ወቅት ከተልዕኮው ጋር ተያይዞ ስላወቃቸው መረጃዎች ወይም በእጁ ስለገቡ ሰነዶች ለፍርድ ቤት ወይም አጣሪ ኮሚቴ ወይም ለሌላ አካል እንዲገልጽ ወይም እንዲያቀርብ አይገደድም’ ሲል ያትታል።" ይህ ማለት ለህዝብ ተወካዮች ም /ቤት በተቁዋቁዋመ ኮሚቴ ፊትም ጭምር ያወቀውን መረጃ እንዲሰጥ አይገደድም። የደህንነት ተቁዋሙ የአስፈጻሚው አካል እንደመሆኑ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው። ከም /ቤቱ እሚደበቅ ሚስጥርም ሊኖር አይገባውም። ለተወካዮች ም / ቤት ሪፖርት ሢያቀርብም አልተሰማም። ይህ የደህንነት መ/ቤትን በአግባቡ መቆጣጠር አለመቻል አሜሪካኖችን ጭምር የደህንነት ተቁዋማቶቻቸውን መጀመርያ ሲያቁዋቁሙ አጋጥሞአቸው በሁዋላ ጠንካራ ለምርቆጣጠር የሚያስችላቸውን አውጥተው ፈትተውታል። ይህም ባለስልጣናት አዋጁ ይፈቅድልናል የፈለግነውን መስራት እንችላለን በሚል ሊያደፋፍር ይችላል። የፌዴሬሽን ም / ቤትም በበኩሉ ህግን ተርጉዋሚ እንጂ አንድ ህግ ወይም ደንብም ሆነ እዋጅን ህገ መንግስታዊ ነው ወይንስ አይደለም ብሎ የመፈተሽ ስልጣን የለውም። ይህም የህግ ክፍተት በቅርቡ ስለ ፍትህ ስርአቱ በተደረገ ውይይት የህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ሊኖር እንደሚገባና ተነስቶአል። ህገ መንግስቱን እሚጻረር ህግም ሆነ አዋጅ እንዳይወጣ ሊያደርግ ይችላል።
Tuesday, July 2, 2019
የህግና አዋጅ ቁጥጥር ከደህንነት አንጻር
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment