"በእጅ ያለ ወርቅ ፤ እንደ መዳብ ይቆጠራል "
አዲሱ ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ያደረጉትን ታላላቅ ነገሮችን ዘንግተህ ፖለቲከኛ ይሁኑ አክቲቪስቶች ባለየላቸው አትነዳ ጎበዝ ።ዛሬ ታዋቂ ሰዎች ሁሉ የፌስ ቡክ አካውንት ከፍተው ማስታወቂያ እየሰሩበት ባለበት ሁኔታ ሁሉም ካሑን በሑዋላ ''የፖለቲካ ተንታኝ ሆኛለሑ፥የታሪክ አዋቂ ነኝ " ብሎ ሲያምን ትክክልም ይሁኑ ስህተት መረጃዎች በግራ በቀኝ ያለማቁዋረጥ እየተለቀቁ ይገኛሉ።
ፈረንጆች ምን ይላሉ "Don't Miss the big Picture. "። ዋናውን ትልቁን ራዕይና ግብን መዘንጋት ተገቢ አይዶለም። በትናንሽ ነገር ሳይጠለፉ ዋነኛውን ግብና ሀገሪቱን ወደ ዲሞክራሲ የማሽጋገሩ ጉዞ እንዳይዘነጋ።
አጀንዳ መደበላለቅና መቅደም የሌለበት ነገር ወደፊት እየመጣ ተቸገርነ ጎበዝ። አለግዜው እሚነሳን አጀንዳ ከስሜት በጸዳ መልኩ ፤ መመከት ይበጃል። አላፊ በሆኑ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጀንዳ ተቀባይና ለዚህም ለዚያም ምላሽን በመስጠት ውዝግብ ውስጥ የሚከት ከመሆን ይልቅ ፥አጀንዳ ቀያሽ ወይም አጀንዳ ሰጪ #Agenda Setter መሆን የበለጠ ሊበጅ ይችላል ለመሪዎች። ሌላው ሆነ ብሎ ለፈጠረው አጀንዳ ምላሽን መስጠት አድካሚ ሊሆን ይችላል ፤ ለሁሉም ነገር ምላሽ መስጠት ኣስፈላጊ ላይሆን ይችላል።
በዲሞክራሲ ስርአት ውስጥ "የህዝብ አስተያየት" ወይም #Public Opinion ወሳኝ የሆነ ነገር ሲሆን አጀንዳ ቀያሾች ሆነ ብለው እነርሱ በሚፈልጉት መንገድ "የህዝብን አስተያየት" #Public Opinion የመቅረጽ ዕድል አላቸው -በተለይም በዚህ በሶሻል ሚዲያ እና በኢንፎርሜሽን በቴክኖሎጂ ዘመን ። ከሶሻል ሚዲያ ጋር መታገል አዋጪ አይደለም ። በርካታ ሶሻል ሚዲያዎች አሉ ፥ በአንዱ ቢዘጋበት በሌላው ብቅ ይላል።
ለምሳሌ በአሜሪካ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ የህዝብን አስተያየት መቅረጽ የቻሉ ፥ በቀላሉ ምርጫዎችን የማሸነፍ እድል አላቸው ይህ በዕርግጥ የዲሞክራሲ ስርአት ባህሪ ነው። ዛሬ ሩስያና አሜሪካ የገቡበት ውዝግብ ሩስያ ያአሜሪካን ምርጫ በማህበራዊ ሚዲያ አማካይነት ተጽእኖ አሳርፋለች #Influence አድርጋለች እሚል ነው። በአንድ ሀገር ላይ አጀንዳ የመቅረጽ ሥራ የማን ነው መሆን ያለበት።
ይህ የሽግግር ኣስተዳደር እንደመሆኑ መጠን እስከ ቀጣዩ ምርጫ መታገሥ ይበጃል።
ለማንኛውም ግን በዚህ ኣስደማሚ #Impressive ለውጥ
በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ተፈትተዋል ፥ ጋዜጠኞችም እንደፈለጉ ሃሳባቸውንም እያንጸባረቁ ነው። ከኤርትራ ጋር የሰላም ስምምነት ተደርጎአል በዚህም ከማንም በላይ ተጠቃሚው የትግራይ ክልል ነው -እየተጠቀመም ነው ። ዲያስፖራውን ማሳተፍ #Engage ማድረግ ፥ የፖለቲካ ምሕዳሩን ማሥፋት ... ተቁዋማትን ገለልተኛ ማድረግ ...ወዘተ። ሊንኮታኮት ጫፍ ደርሶ የነበረውና ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ለመክፈል እማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በዶ/ር አብይ አመራር መልሶ እያንሰራራ ነው። ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ ጎበዝ።
ሰዎች ፍትህን ሳያገኙ ይገደሉ የነበረችባት ሀገራችን ዛሬ በኢትዮጲያ ምድር ለዚህች ሀገር ታላላቅ ሥራን ሰርተው ያለፉ እነ አክሊሉ ሀብተወልድ እንደ ጥጃ እጅና እግራቸው እየተጎተተ ያለፍርድ በሌሊት ወጥተው በተገዱለበት ሀገር ፥እንዲሁም ይህ ግፍ የተፈጸመበት ቤተ-መንግስት ታድሶ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚ ቱሪስቶች እንዲጎበኙት እየታደሰ መሆኑ ታውቆአል። እናም ምስጋና ለሚገባው ምስጋና መስጠት ይገባል ። መጽሐፍ ሲናገር "የቄሳርን ለቄሳር ፥ የእግዝአብሄርን ለእግዝአብሄር " ይላል እኮ።
No comments:
Post a Comment