ፈላስፋው ዘርአያቆብ "እስራኤላውያን በእግዝአብሄር የተመረጡ ሕዝቦች ናቸው የሚለውን" የሙሴን መሠረታዊ አስተምህሮን አይስማማበትም ። መናፍቁ እና ጠርጣራው #Heretic Philosopher ፈላስፋው ዘርአያቆብ የሙሴን መሰረታዊ አስተምህሮቶችን ይጠራጠራል ።
ዘርአያቆብ እግዝአብሄር ለአህዛብ ሚስጥሩን መችልም አይገልጥላቸውም የሚለውን በሙሴ የተጻፈውን የመዝሙረ ዳዊትን ጥቅሥ አይስማማበትም ። ይሁን እንጂ ጸሀፊው የካቶሊክ ቄስ ከሆነ ለአይሁድ ባላቸው ጥላቻን ማንጸባረቁ ሊሆን ይችላል ።
በመዠመር ያዘርአያቆብ ማነው ? ትውልዱስ እንፍራንዜ (ጎንደሬ) ወይስ የአክሱሜ ? ወይስ የካቶሊክ ካህን ? ። ይሄ መታወቅ አለበት። ማንነቱን ማወቅ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ጸሐፊው ኢትዮጲያዊ ላይሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ ስላለ ነው።
ፕሮፌሰር ጌታቸው በጻፉት መጽሀፍ እንፍራንዜ ሲያደርጉት ሌሎች በተረጎሙት ደግሞ በወቅቱ በነበረው በካቶሊኮችና ኦርቶዶክሶች የሃይማኖት ውዝግብ ከአክሱም በሃይማኖት ክፍፍል ምክንያት ሸሽቶ ወደ ጎንደር የተሰደደ ትግሬ ያደርጉታል ።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለ ዘርአያቆ ትውልድ ስፍራ የትውልድ ስፍራ የራሱን ሃሳብ ሲገልጽ ፦
" የዘርአ ያእቆብ የዓለም ስሙ ‹ወርቄ› ነው፡፡ ‹ወርቄ፣ ብርቄ፣ ድንቄ› የሚሉ የስም አወጣጦች በአማራው አካባቢ እንጂ በአኩስም አካባቢ የተለመዱ ስሞች አይደሉም፡፡ ኡርቢኖ በደብረ ታቦር አካባቢ ሲኖር የሰማውን ስም መሆን አለበት የተጠቀመው፡፡" ይላል በዳንኤል ክብረት እይታ ዘርአያቆብ የጎንደሬ ስም ነው የተጠቀመው ።
ዲያቆን ዳንኤል ሲጠቅሥ " እንዲያውም ‹እንደዚህ ከሀገር ወደ ሀገር ስሄድ ወደ አኩስም እመለስ ዘንደ አልፈቀድኩም፤ የካህኖቿን ክፋት ዐውቅ ነበርና›(ያሬድ፣25) ይላል፡፡ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት እይታ "ዘርአ ያእቆብ በምንም መልኩ አኩስማዊ አይደለም ፡፡ አክሱምን በዚህ መጠን የሚጠላ አኩስማዊም ሊኖር አይችልም፡ በምክንያት የሚያምን ሰው ለዚህ ጥላቻው በቂ ምክንያት አላቀረበም፡፡ ዋና ማዕከላቸውን በአድዋ አድርገው ለነበሩት ካቶሊካውያን አኩስማውያን ቦታ ሊሰጧቸው አልፈቀዱም ነበር፡፡ የካቶሊክ ሚስዮናውያን መሠረት ሊጥሉ የፈለጉት በአኩስም ነበር፡፡ነገር ግን የአኩስም ካህናት አልፈቀዱም፡፡ይህንን ጥላቻ ነው ኡርቢኖ ያንጸባረቀው፡፡" ይላል።
ሌላው አብዛኛው ዘርአያቆብ እሚጠቅሳቸው ጥቅሦች ከመዝሙረ ዳዊት የተወሰዱ መሆናቸው ሌሎቹን የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎችን በጥልቀት ያውቃል ወይ ሊያስብል ይችላል።
ዘርአ ያእቆብ ሙሴን ሲወቅስ ‹ወሙሴሰ ይቤ ኩሉ ሩካቤ ርኩስ ውእቱ - ሙሴም ሩካቤ ሁሉ ርኩስ ነው አለ› ይላል(215,9a)፡፡ ነቢዩ ሙሴ ራሱ በጋብቻ ጸንቶ የኖረ ነቢይ ነው፡፡ በምን መልኩ ይህንን ሊል አይችልም፡፡ ሙሴ ይህንን ነገር ለመናገሩ መጽሐፋዊም ትውፊታዊም ማስረጃ የለም፡፡ ዘርአ ያዕቆብ ዳዊት ከማወቅ (እርሱንም ሲደበቅ ደጋግሞ በማንበቡ)፣ ሐዲስን ከማንበብ የዘለለ የብሉይ ትምህርት የለውም ይላል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡፡
ከሙሴ ይልቅ ግን ሐዋርያው ጳውሎስን በዚህ ጉዳይ ቢጠቅሥ ይመረጥ ነበረ ልምን ቢባል ጳውሎስ ከቻላችሁ እንደኔ አታግቡ ማለቱ በመልእክቶቹ የሚታወቅ ሲሆን ሐዋርያውም ራሱ ግን በዚህ ሊወቀስ የሚችል አይደለም ይህን ያለው ራሳቸውን በቅድስና ለሚለዩቱ ቅዱሳን ነው ፥ ምክንያቱም እርሱም ቢሆንም ግን የጋብቻን ክቡርነትንና የትውልድ መቀጠልን ነው ያስተማረው። ጌታ እየሱስም ጭምር "አንድ ሴት ለአንድ ወንድ" ብሎ ነው ያስተማረው። ጋብቻ ከሌለ ትውልድ ሊቀጥል እንደማይችል በጥንት ዘመንም የሚታወቅ ቀላል እውነት መሆኑ ይታወቃል ። ስለዚህ ዘርአያቆብ የቱ ቦታ ላይ ነው ሙሴ ሩካቤ ሁሉ እርኩስ እንዳለ ምንጩን አይጠቅሥም። በሙሴ ግዜ እንደውም እስራኤላውያን ህዝቡም ሆነ ነገስታቱ በርካታ ሚስቶችን ያገቡ ነበረ። ሙሴ ለነገስታቶች በሰጠው ምክር "ንጉሡ ሚስቶችን አያብዛ " የሚል ነው። በሃዲስ ኪዳን በአንድ ስለመወሰን ከመደንገጉ በስተቀር በብሉይ ዘመን ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እንደሚቻል ከብሉይ መጽፍሐት መረዳት ይቻላል ። በሙሴ ህግ የሚመሩት የእስራኤል ነገስታት ከአንድ በላይ ሚስቶችን አግብተው በርካታ ልጆችን እንደወለዱ መጽሐፈ ነገስት ያትታል ። ለምሳሌ።ንጉስ ዳትዊንስ የንጉስ ሰለሞን ልጅ ኢዮርብአም በርካታ ሚስቶች እንደነበሩዋቸው ማንበብ ይቻላል ።
ዘርአያቆብ መዝሙረ ዳዊት ላይ ብቻ ትኩረትን ስላደረገ ከብሔረ ኦሪት አሟልቶ መጥቀስ አልቻለም፡፡ የካቶሊክ ሚስዮናውያን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ቤተ ክርስቲያኒቱን የከሰሱበት አንዱ ክስ ‹ኦሪታዊት ናት› የሚል ነው፡፡ ለእነርሱ በንጉሥ ገላውዴዎስ ዘመን የነበሩት ሊቃውንት መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ዘርአ ያእቆብ የእነርሱ ወገን ካልሆነ በቀር ሙሴን በዚህ መልኩ አይጠቅሰውም፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዘርአያቂብ ማለት ኡርቢኖ የተባለ የካቶሊክ መነኩሴ ነው።
ሌላው ዘርአያቆብ ስለ ንጉሥ ፋሲለደስ ያለው አመለካከት ነው ። "በዐመሉና በደም ማፍሰስ ጸና፣በጎ ላደረጉለት፣ ቤተ መንግሥትንና ያማሩ ቤቶችን ለሠሩለት፣ በጥበብ ነገር ሁሉም መንግሥቱን ላሣመሩለት ፈረንጆችን ጠላቸው› ይላል " ፋሲለደስ ቤቶችን ይወርስ ነበረ ሴቶችን አብሮአቸው ካደረ በሁዋላ ይገድላቸው ነበረ ሲል ንጉስ ፋሲልን ግፈኛ አድርጎ ያቀርበዋል።
በራሱ አንደበት እንዲህ ይላል " ፋሲለደስ ክፉን ነገር የሚሠራ ሆነ፡፡ ሰዎችን ያለ ፍርድ ይገድል ነበር፡፡ አመንዝራነትም ያበዛ ነበር፡፡ ሴቶችንም ከእነርሱ ጋር ካመነዘረ በኋላ ይገድላቸው ነበር፡፡ ዐመጻን የሚያደርጉ ሠራዊትንም ልኮ የድኾችን ሀገሮችና ቤቶች እንዲቀሙ ያደርግ ነበር፡፡
እግዚአብሔር ለክፉዎች ሕዝቦች ክፉውን ንጉሥ ሰጥቷቸው ነበርና፡፡ ስለ ንጉሡና ስለ ሕዝቡም ኃጢአት ረሀብና መቅሰፍት መጣ፡፡ ከረሃብ በኋላም ቸነፈር ሆነ፡፡ ብዙዎችም ሞቱ፡፡ ሌሎችም ፈሩ፡፡" ዘርአያቆብ በወቅቱ ለነበረው ማህበረሰብ በጎ አመለካከት አልነበረውም የህዝቡ ክፋት ፋሲለደስ የተባለ ክፉ ንጉስ እንደሰጣቸው አፍርጎ ነው የተረዳው።
ይሁንና ግን ፋሲለደስ በአጼ ሱስንዮስ ዘመን የነበረውን የሃይማኖት ውዝግብን ያስቆመና ፤ግራኝ አህመድን ወረራ ለመመከት መጥተው ነገር ግን ከግራኝ ሽንፈት በሁዋላ የኦርቶዶክስ እምነትን ወደ ካቶሊክ ለመለወጥ የሞከሩትን ፖርቱጋሎችን ያስወጣ ነው።