Saturday, December 8, 2018

ሃምሳ ሆቴል ይገነባባታል የተባለችው ሙስና የተበላባት የአፋር ክልል ከተማ

ለሃምሳ #የኮኮብ #ሆቴሎች የታጨችው አብዓላ የት ትገኛለች? በስሟ የተነገደባትን ከተማ ተዋወቋት፡፡
አብዓላ የሰሞኑ መናጋገሪያ ናት፡፡ በከተማዋ ሆቴል እንገነባለን ብለው በስሟ ከቀረጥ ነጻ ያስገቡ ግለሰቦች #በስሟ ብረት የበሉባት፣ በስሟ የነገዱባት፣ በስሟ #የከበሩባት ከተማን ያውቋታል?

ይህቺን ከሃምሳ በላይ የሚሆኑ ባለ ኮኮብ ሆቴሎች እንገንባባት ብለው በስሟ የነገዱባት ከተማ መገኛዋ አፋር ክልል ነው፡፡ ከመቀሌ በኩሓ በኩል አሸጎዳን አልፈው የሚያገኟት ከተማ ናት፡፡
ክልሏ# አፋር ይሁን እንጂ ከመቀሌ ያላት ርቀት ሰባ አምስት ኪሎ ሜትር አይሆንም፡፡ ከትግራይ ክልል ድንበር ደግሞ አስር ኪሎ ሜትር ገደማ ርቃ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ በነዋሪዎቿ ሸኽት በሚል ስም ትታወቃለች፡፡ በራሱ የጎብኚ መዳረሻ አይደለችም፡፡ ዳሉልና ኤርታኤሌ የሚሄዱ ጎብኚዎች ግን ያልፉባታል፡፡

በሕይወት ያሉት ራስ መንገሻ ስዩም ናቸው የቆረቆሯት ሜዳ ላይ ያረፈች ከተማ ስትሆን ከመቀሌም፣ ከሰመራም ከዳሉልም አስፋልት መንገድ የሚያገናኛት ትንሽ ከተማ ናት፡፡

የገቢዎችና ጉምሩክ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ አብዓላ ላይ ደረጃውን የጠበቀ ባለ ኮኮብ ሆቴል እንገነባለን በሚል የኢንቨስትመንት ፍቃድ ያወጡት ባለሃብቶች ምን እንዳነሳሳቸው ለማወቅ ከባድ ነው፡፡ የአብዓላ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄ አንስተው ተዳፍኖ ቀርቷል፡፡ አፋር አይደለንም ትግራይ ነን የሚሉ ጠያቂዎች በአብዓላ ዛሬም የመብት ጥያቄ ያነሳሉ፡፡

የአፋር ክልልን #ከቀረጥ ነጻ ኮታ #ቅርጥፍ አድርጋ የበላችው ይህቺ ትንሽ ከተማ ለዝርፊያ ለሚመች # ፕሮጀክ #የሆቴልት #የታጨችው እንዲሁ በሜዳ ነው፡፡
ሃምሳ አምስት የሚሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችን ለመገንባት በስሟ ብረት ገብቷል፡፡ ሆቴሉ አልቋል ብለው አልጋም አስገብተው ይሆናል፡፡ የሆነውን የምንሰማው ዘግይተን ነው፡፡ ከቀረጥ ነጻ የገባው ብረት ተሽጧል፡፡ ሲያምርሽ ይቅር ያሏት አብዓላ ዛሬ ትንንሽ ሻይ ቤቶች፣ ጠላ ቤቶችና ጫት ቤቶች ብቻ እጇ ላይ ቀርተዋል፡፡

ራስ መንገሻ ለአትክልት ልማት የመረጧት ስፍራ በልዑሉ ብርታት ከተማ ለመሆን በቅታለች፡፡ በደርግና በኢህአዴግ ዘመን ያገኘችው ነገር ቢኖር በስሟ #ከቀረጥ ነጻ የገባ ቁስ እዳ ውስጥ ስሟ መስፈሩ ነው፡፡

ጥቂት ሺ ነዋሪዎች ያሉባት ከተማ ለሃምሳ አምስት ሆቴሎች ስትታጭ ደብዳቤውን ይጽፍ የነበረ አካል፤ ከቀረጥ ነጻ የፈቀደው ሹመኛ እና ተከታትሎ ግንባታውን ያላየው ፈቃጅ ሳይጠየቁ መቅረታቸው አብዓላን በስሟ ተነግዶ እንዲቀር አድርጓታል፡፡

No comments:

Post a Comment