"ቅንጅትም አይደለም ፤ ግንባርም አይደለም " ፦
ህብረ ብሄራዊ ፓርቲዎች የመሰረቱት ይህ ዜግነትን መሰረት ያደረገ ፓርቲ ከዚህ በፊት በ97ቱ ምርጫ ተሞክሮ ከከሸፈው "ቅንጅት " ትምህርት የተወሰደበት ይመስለኛል። በበፊቱ ቅንጅት አባል የሆኑት ፓርቲዎች እኩል ድምጽ የመበራቸው ሲሆን የራሳቸውን ድርጅታዊ ማንነትንም ይዘው ቀጥለዋል። ኢህአዴግም "ግንባር " ሲሆን አራቱም አባል ድርጅቶች የራሳቸውን ህልውና ይዘው ሲቀጥሉ በህወሃት በሚመራው ኢህአዴግና በአዴፓ በሚመራው ኢህአዴግ መሃል ልዩነቱ የሚታይ ነው። ይህ አሂን ህብረ ብሄራዊ ፓርቲዎች የመሰረቱት ግን "ቅንጅትም " አይደለም "ግንባርም " አይደለም ተብሎአል ይህም ውስጣዊ አንድነቱን ለመጠበቅ የሚያስችለው መላ ነው።
"ቅንጅትም አይደለም ፥ ግንባርም አይደለም ውህደት ነው "።በዚህ ውህደት ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን ማክሰሙን ገልጾአል ።ይሁንና ግን አንድነት ሲባል ልዩነት የለም ማለት አይደለም ግን አንድነት ከልዩነት ይበልጣል ነው ሃሳቡ። ይህ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ አዲስ ይዞት የመጣው ሃሳብ በተለይም ምንም አይነት የፖለቲካ ውክልና ለሌለው ከተሜ አማራጭ ሊሆን ይችላል ።
በቦለቲካው ዓለም የአቁዋም ለውጥንና ማሻሻያን ወይም ተሃድሶን ብሎም የአመራር ለውጥን እያደረጉ መቀጠል አዲስ ነገር አይዶለም። ለምሳሌ በአሜሪካን አገር የጥቁር መብት ተከራካሪና ተራማጅ ተደርጎ በአብረሃም ሊንከን በ1860ዎቹ ግዜ የሚወሰደው ሪፐብሊካን ፓርቲው ሲሆን አሁን ደግሞ የሰራተኛውና የጥቁሮች የተሻለ ይወክላል እሚባለው #ዲሞክራቲክ ፓርቲው ነው። #adapt ማድረግ #flexibility ለፖለቲካ ፓርቲዎች ህልውናን ለማስቀጠልና ለአዳዲስ ጉዳዮች ጋር አብሮ ቀጥሎ ዘላቂ የሆነ የህዝብ ድጋፍን ይዞ ለመቀጸል ይረዳል።
Monday, December 31, 2018
የፓርቲዎች ውህደት
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment