Wednesday, December 12, 2018

ማመልክቻ

                           ቀን 4/4/2011
                           የመ/ቁ

በፌደራል ከፍተኛው ፍ/ቤት
8ኛው ፍ/ብ ችሎት
አዲስ አበባ
         ከሳሽ ................ አቶ ጀማል ኢብራሂም
           1ኛ ተከሳሽ.....  አቶ ስሜነህ ተረፈ
           2ኛ ተከሳሽ......... ወ/ሮ ትዝታ ተረፈ
ከሳሽ ግንቦት 27 / 2010 ኣ.ም ጽፈው ላቀረቡት ከ1ኛ ተጠሪ የቀረበ መልስ
&፤    ፤፥ 
በፍብ ስ/ስ/ስ/ህ/ቁ 37 እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ/ቁ 244/1 እና በ244 /2/ለ እና በ245 መሰረት የቀረበ የመጀመርያ ደረጃ መቃወሚያ
°       °        °   
በፍ/ብ/ስስ/ህ፣ቁ 37 መሰረት መሳሽ ክሱን ለማቅረብ ምንም መብት የላቸውም። አልተከራዩም እንጂ ቢከራዩ እንኩዋን የውል ግዜ ከተጠናቀቀ በሁዋላ የሚያቀርቡት ክርክር የህግ መሠረት የሌለው ስለመሆኑ በፍብስስቁ 33(2)(3)፥231(1)(ሀ) መሰረት የፌደራል ጠ/ፍቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 07 በሠ/መ/ቁ 28025፤ 34456 ቅጽ 10 ፥40336 ላይ በሰጠው የህግ ትርጉም መሰረት ቤቱን የመገልገል ማብቂያ ግዜን በመወሰን በሰጠው የህግ ትርጉም መሰረት ከሳሽ እሚከሱኝ ምክንያት ስለሌለ የተከረው ችሎት መዝገቡን ዘግቶ እንዲያሰናብተኝ አመለክታለሁ። ምክንያቱም ውልም ሆነ የውል ሰነድ እንዲሁም በውል አዋዋይ ፊት የጸደቀ የኪራይ ውል እንዲሁም ባለሃብት እሚያደርጋቸው ከእኔም ሆነ ከአውራሼ ጋር አልፈጸሙም ስለዚህ በፍብ/ስ/ስ/ቁ 244 መሰረት ክሱ ውድቅ ሆኖ ለደረሰብኝ ወጭና ኪሳራ ተከፍሎኝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ቁ 245 እንድሰናበት የተከበረውን ፍ/ቤት እጠይቃለሁኝ።
&   &     &  
የከሳሽ የክስ ምክንያት የሌለው ስለመሆኑ ፥
ከሳሽ ቤቱን በ200ኣ.ም ተከራይቻለሁ ቢሉም ያቀረቡት የውል ሰነድ የለም።ወጭ አድርጌ ሱቅ ሰርቻለሁ እያሉ የኪራይ ውሉ አሁን በህይወት ከሌለው አውራሼ ጋር በቃል ውል አለኝ ብለው በሰው ሊያስረዱ የሚችሉበት የህግ መሰረት የለም።ቤቱ አሁን በህይወት ያለችው እናቴ ሲ/ር አባይነሽ ደስታ ጋር የጋራ ሃብት ስለሆነ አውራሼ ብቻውን ሊያከራየው እንኩዋን አይችልም። በፍብህቁ 1680 መሰረት ተዋዋዮቹ በተስማማ አኩሃዋን ስምምነታቸውን ገልጸው ሲገኙ ነው። በፍህቁ 1678 መሰረት ተዋዋይ ወገኖች መሃከል ጉድለት በሌለው ሁኔታ ስምምነት መኖር አለበት ይላል። የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለማቁዋቁዋም ውል ስለመኖሩ ማስረዳት እሚቻለው በፍ ብህ ቁ 2003 መሰረት የጽሁፍ ማስረጃ በማቅረብ ብቻ ነው። ሰበር ችሎት በሰጣቸው አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች ቤትን ለመከራየትም ሆነ የቤት ባለቤት ነኝ ለማለት በውልና ማስረጃ የጸደቀ በውል አዋዋይ ፊት በተደረገ የውል ሰነድ አማካይነት ብቻ ነው። ከሳሽ ግን ከህጋዊ ባለቤቶች ጋር ስላደረጉት ስምምነት እሚገልጽ ምንም አይትነ የሰነድ ማስረጃ አላቀረቡም። ገንዘብ ተቀባብዬባቸዋለሁ የሚሉዋቸው ሰነዶች ከኔም ሆነ ከአውራሼ ጋር የተደረጉ አይደሉም እርነሱም እንደ ውል ሰነድ ሁነው ሊያገለግሉ አይችሉም።
ውል ሳይኖራቸው ይባስ ብለው የቤት ኪራይ ይከፈለኝ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ የቤቱ ህጋዊ ባለቤቶች እየኖርንበት ያለ ሲሆን ለእርሳቸው ኪራይ የምንከፍልበት የህግ አግባብ የለም። ስለዚህ ክሱ በፍብ/ስ/ስ/ቁ 33/3 እና 231/1/ሀ መሰረት የክስ ምክንያት የለውም ተብሎ ውድቅ እንዲደረግልኝ አመለክታለሁ።
2. ከፍ ብሎ የቀረበው መቃወሚያ አይታለፍም እንጂ የሚታለፍ ከሆነ የሚከተለውን የፍሬ ነገር መልስ አቀርባለሁኝ።
1.1 ከሳሽ በራሳቸው ውስጥ በግልጽ እንዳመለከቱት ተከራይ ነኝ አሉ እንጂ ባለቤት ነኝ አላሉም ። ይህ ከሆነ በምንም መልኩ በሌላ ሰው ይዞታ ላይ የኪራይ ውል ሳይኖራቸው እንዲሁም ባለቤቶቹ አልፈቀድንም እያሉ እንድገነባ  ፈቅደውልኛል የሚሉት ሃሰተኛና የተቀነባበረ ነው።
1.2 ከሳሽ ምንም አይነት የይዞታ/የባለቤትነት ማረጋገጫ ፥ወይም ውክልና ሳይኖር በሰው ግቢ ገብተው ቤት ሊገነቡ አይችሉም። በመንግስት አሰራር ህጋዊ ውክልና ወይም ካርታ ሳይኖር ግንባታ እንዲካሄድ ወረዳውና ክፍለ-ከተማው ግንባታን እንደማይፈቅዱ ይታወቃል። ይህ የግንባታ ፈቃድ ሳይኖር እርሳቸውም እንደሌላቸው ባመኑት ህጋዊ ባለይዞታው ፥እንዲሁም ወረዳውና ክፍለ ከተማው ሳይፈቅዱ ሰራሑ ሲሉ ሃሰተኝነታቸውን ይገልጻል።
1.3 ከሳሽ ባቀረቡት እርስ በእርስ በተምታታ ክስ በአንድ በኩል ሱቅ ሰርቻለሁ ቤቱ ይለይልኝ ሲሉ ያቀረቡት ክስ ሱቅ አልገነቡም እንጂ ያለፈቃድ ለመገንባት ሙከራን ቢያደርጉ ኖሮ ሁከትን ተግባር ሊያነሳሳ የሚችል ይሆን ነበረ። ይህ ብቻ ሳይሆን በአንድ በኩል ተከራይ ነኝ እያሉ በሌላ በኩል ኪራይ ይከፈለኝ ሲሉ ምን ያህል ከእውነተኛው ዓለም የራቀ አእምሮ እንዳላቸው አመላካች ነው።  አለአግባብ ለመበልጸግ ያላቸውን ጉጉት ያሳያል።በፍብህቁ 2001 መሰረት ውል ወይም ግዴታ ይፈጸምልኝ ብሎ እሚጠይቅ ሰው ለግዴታው መኖር የሰነድ ማስረጃ ማቅረብ አለበት። ከአምስት መቶ ብር በላይ ከሆነ ደግሞ ሊረጋገጥ የሚችለው ህጋዊ ውል በማቅረብ ብቻ ነው።
ከሳሽ የገነባው ቤት የለውም እንጂ ሰራ ቢባል እንኩዋን ምንም አይነት ውል ሳይኖረው ከዛሬ አስር በፊት ያረፉት አውራሻችንን ስም እየደጋገመ በበርካታ ችሎቶች በማንሳት እያንከራተተን ይገኛል። ቢከራይ እንኩዋን እሱ ለኛ ኪራይ ይከፍላል እንጂ ጭራሽ ዞሮ የቤት ኪራይ ይከፈለኝ ሲል ግፈኝነቱንና ህገ-ወጥነቱን አሳይቶአል።
1.4 እርስ በእርስ ተመሳጥረው ከአቶ መሃመድ ኑር ጋር ተዋዋሉ የሚለው ሃሰት ሲሆን ከአቶ መሃመድ ኑር ጋር ህጋዊ ውል በወኪላችን ሲ/ር አባይነሽ ስናደርግ ህጋዊ በውልና ማስረጃ የጸደቀ ውል ተከራይቶን ቤቱንም ከሳሽ በእርሱ ላይ በተከፈተው መዝገብ የመቃወም አመልካች ሆነው በመግባት ያለምንም ክፍያ ለ6 አመታት ያህል አንከራትቶን በመጨረሻም ህጋዊ ውል አቅርብ ብለውት ሰበር ችሎት ድረስ በ/መ/ቁ 109422 ተከራክረን ራሱም ወደ ቄራ ምድብ ችሎት ሄዶ በመ/ቁ 50647 ሌላ መዝገብ ቢከፍትም ህጋዊ የኪራይ ውል ማቅረብ ስላልቻለ ከብዙ ምልልስ በሁዋላ መዝገቡ ሊዘጋባቸው በቅቶአል።

ከተከበረው ችሎት የምንጠይቀው ዳኝነት ፥
2.1ከሳሽ ያልሰራቸውንና የእርሱ ያልሆኑትን ለሱቅ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶች ባለቤት አይደሉም። ሱቆቹንም አልሰሩዋቸውም ፥አልገዙዋቸውምም የባለሃብትነት ውል ከእኔም ሆነ ካውራሼ ጋር እንዲሁም የቤቱ ባለቤት ከሆነችው እናቴ ጋር አልፈጸምም ፥ግብር የምንከፍልበት ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታው በእጃችን ሲሆን እርሱ የሱቆቹ ባለቤት የሚሆንበት ምንም የህግም ሆነ የውል መሰረት የለውም።የተከበረው ፍ/ቤት በሱቆቹ ላይ ከሳሽ ምንም መብት የለውም እንዲባልልን በአክብሮት እንጠይቃለን ።
2.2 ከሳሽ ያቀረበው የሰው ምስክር ብቻ ሲሆን በፍብህቁ 1723 መሰረት የኪራይ ውል በጽሁፍ የተደረገና በውል አዋዋይ ፊት የተደረገ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል።ትተከራየ ቢባል እንኩዋን በፍብ/ህ/ቁ 1987 መሰረት ወራሾቹ (ባለቤት የሆኑት)ወደ እነሱ በተላለፈው መብት መሰረት በሚሰጠው መብት ኪራይ (ትርፍ) ይጠቀማሉ እንጂ አውራሹ ስለሞተ ተከራይ ያልሰራውን ቤት ባለቤት ወይም ባለሃብት አይሆንም።
ከሳሽ ውል በሌለው ሁኔታ 936ሽህ ብር ይከፈለኝ ሲል በምን ውል ኖሮአቸው ነው ኪራይ ይከፈለኝ የሚሉት ?ቢከራይ እንኩዋን ላከራዩ (ለባለቤቱ) እሱ ነው እንጂ እሚከፍለው ውል ሳይኖራቸው ይከፈለኝ ያሉት ብር አለአግባብ ለመበልጸግ ስለሆነና ህጋዊ ውል ስለሌለን ኪራይ ልንከፍል አይገባም። የተከበረው ችሎት ለከሳሽ ኪራይ መክፍል የለባቸውም ብሎ እንዲወስንልን።
2.3 ቤታችን በእርግጥም የውርስ ሃብታችንና እኛም ከወረስነው በሁዋላ ያሻሻልነውና አሁንም ከእናታችንና ከህጻናት ልጆቻችን ጋር የምንኖርበት በእጃችን የሚገኝ ሢሆን ሳይሰራ ሱቅ ሰራሁ ማለቱ ከህግ ውጭ ስለሆነ ራሳችን ለሰራነው ቤት ለከሳሽ ግምት መክፈል የሌለብን ሲሆን የተከበረው ችሎት ግምት መክፈል የለባቸውም ብሎ መዝገቡን እንዲዘጋልን።
2.4 ለዚህ ክርክር ያወጣነውን ወጭና ኪሳራን ከሳሽ እንዲከፍል እንዲወሰንልን።

የማስረጃ ዝርዝር ፦
የፌደራል መ/ደረጃ ፍ/ብልት የመቁ 209623 ፥ እንዲሁም የሰ/መ/ቁ 109422 ፥የቂርቆስ ምድብ ችሎት 50647
ከፌደራል የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት በወቅቱ ተከራይ የነበሩት አቶ መሃመድ ኑር የተባሉ ግለሰብ ቤቱን ህጋዊ በሆነ መንገድ ያስረከቡበት ህጋዊ ሰነድን አያይዘን አቅርበናል።

ምስክሮች ፦
1) ሲ/ር አባይነሽ ደስታ
2) ወ/ሮ ትዝታ ተረፈ
3 )አቶ መሃመድ ኑር
4) አቶ ስሜነህ ተረፈ
5 ) አቶ ጌታቸው ገ/ማርያም
6)ወ/ሮ ዘቢደሩ ቸርነት

No comments:

Post a Comment