Monday, November 12, 2018

ግመል ሰርቆ አጎንብሶ

ግመል ሰርቆ አጎንብሶ ፦

ከሰሞኑ ሃገሪቱ የ26 ቢሊየን ዶላር የውጭ እዳ ውስጥ ተዘፍቃ የሜቴክ ሹመኞች ዋና ዋና እሚባለውን ግዙፍ ኮንትራት "ሲያሸንፉ" ለምሳሌ ያባይ ግድብን ደን ምንጣሮ የሰራው ድርጅት ሳይከፈለው ሜቴክ ተከፍሎታል። ዶ/ር አብይ ወደ ቤጂንግ ተጉዘው ቻይና ከሰጠችው ብድር ውስጥ ወለዱን እንድትቀንስ ፤ የመክፈያ ግዜውን እንድታራዝም ለቻይናው ፕ/ት በቅርቡ በተደረገው ይቻይና አፍሪካ ስብሰባ ላይ ጥያቄን አቅርበዋል። በውጭ ምንዛሬ ድርቅ የተመታች ሃገር ከየት አምጥታ ይህን ሁሉ ዕዳ ትክፈል ጎበዝ? ከ26 ቢልየን ዶላር እዳ ውስጥ ከ10 ቢልየን ዶላር የሚልቀው ከቻይና የተወሰደ ብድር ነው ችስይና ደግሞ እኔም ታዳጊ አገር ነኝ ሥለምትል እንደ ፓሪስ ክለብ የዕዳ ቅነሳን አታውቅም። ጭራሽ ብድሮቹን ወደ ግል ኢንቨስተሮች በሽያጭ አሸጋግራለሁ እያለች ነው። 

ሜቴክ የወሰዳቸው የስካር ኮርፖሬሽንና ያባይ ግድብ የኤሌክትሮሜካኒካል ስራዎች እነ ሲመንስ ወይም እነ ጄኔራሬ ኤሌክትሪክ አይነት ኩባንያዎች አይነት ካልሆነ በስተቀረ በኢንጂነሪንግ እውቀት በሌላቸው ጄኔራሎች እሚሞከር አልነበረም።

ያም ሆኖ ሰዎቹ የተያዙበት መንገድ የፍርድ ቤት ትእዛዝን አውጥቶ መያዝ ሲቻል ለስብሰባ ተጠርታችሁዋል በሚል መያዛቸው ወደ ፊት ኢሃዴግ ራሱ እርስ በእርስ ተማምኖ ስብሰባን ይቀመጣል ወይ ነው ጥያቄው። የሜቴክ አለቆች ብዙዎቹ ይህውሃት የበላይ ሹመኞች እንደመሆናቸው እነርሱንም ያነካካል ደፂን ጨምሮ።
ይሁንና ለሜቴክ ወ/ሮ አዜብ መስፍንን የቦርድ አባል አድርገው ጠ/ሚር ሹመት ስጥተው ነበረ። ያኔ ግና ወንብውራቸው ስላልተደላደለ ነበረ አሁን ግን ወ/ሮ አዜብ ቦርድ አባል ሆነው ሊያገለግሉ ቀርቶ ሊጠየቁ ስለሚችል ዶ/ር አብይ ስልጣናቸው መጠናከሩን ያመለክታል ጎበዝ።  

No comments:

Post a Comment