"የሜቴክ ነብሮች በቁጥጥር ሥር ዋሉ "፦
የሜቴክ ነብሮች እስከ 35% ድረስ የወለድ ምጣኔ የሚታሰብባቸውን የውጭ ብድሮች አብዛኛው ከህንድና ምህረት የለሽ አበዳሪ ከሆነችው ከቻይና የተወሰደን ብድር ገንዘብ "ነብር አየኝ በል" ብለውታል። የቻይናው ፕ/ት " Catching the Tigers & Flies " በሚለው አባባላቸው ይታወቃሉ። Tigers የተባሉት ትላልቅ ባለስልጣናት ሲሆኑ flies ደግሞ ትናንሽ ባለስልጣናት ናቸው።
እስካሁን ያገራችን የሙስና መረብ ዝንቦችን ብቻ እንጂ ሲይዝ የታየው ነብሮችን ይዞ አያውቅም ነበረ ጉዋዶች አሁን ግን ይህ መረብ እነኝህን ጉዶችን በቁጥጥር ስር አዋለ።
ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ ከብዙ ማንራገር በሁዋላ የቀድሞ አለቆቻቸውን የሜቴክ ነብሮችን በቁጥጥር ስር ማዋለቸው "ዝንቦችን " ብቻ ሳይሆን "ነብሮችን" መያዝ መጀመራቸው ይበል የሚያሰኝ ነው ጉዋዶች። እስካሁን ዝንቦችን ብቻ ሲይዝ የነበረው የጸረ - ሙስናው መረብ በሜቴክ ብቻ ሳይሆን ወደ ሌሎችም ነብሮች ይሸጋገር።
Transparency International ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮፒያ ከ176 አገሮች 108ኛ ደረጃ ላይ ስትሆን ፥ ከመቶ ያላት ውጤት 34 ብቻ ነው። በውጤት አሰጣጡ መሰረት 0 ከፍተኛ በሙስና የተዘፈቀ ሲሆን 100 ከሙስና የጸዳ ነው።ይህ የቻይና ውጤት 40 ነው በመጠኑ ከኢትዮፒያ ትሻላለች።
ባሃገሪቱ ጉቦኝነትና ሙስና ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ተንሰራፍቶአል ፥ ዜጎችና ተቁዋማት በሙስና ክፉኛ እየተሰቃዩ ነው ይላል ሪፖርቱ። ይህ ሙስና ተቁዋማትንና ዜጎችን ክፉኛ እያሽመደመደ ሲገኝ ኢንቨስትመንትንም እያዳከመ እና ያገሪቱ ሃብት ወደ ውጭ እንዲሸሽ እያደረገ ይገኛል።
“people are deprived of basic needs while the powerful and corrupt enjoy lavish lifestyles with impunity". ይላሉ። በሙስና ምክንያት ዜጎች መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንኩዋን ተነፍገው ማሙዋላት ባቃታቸው ሁኔታ ፥ ባለስልጣንስትና ሃያል ሃብታም ግለሰቦች ሲበዛ የቅንጦት ኑሮን ይገፋሉ ይላል ሪፖርቱ።
ያም ሆኖ ግን ይህ ዘመቻ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን እግረ መንገድን ለማጽዳት ስራ ላይ መዋል የለበትም። የቀድሞ ጠ/ሚር በሙስና ሰበብ በርካታ ተቃዋሚዎችን ለማስወገድ ተጠቅመውበታል።
There has been speculation on whether the campaign has also been used to purge political rivals, which he has denied, or merely holding those in power to account. Only time will tell.
No comments:
Post a Comment