ስትራቴጂክ አጋሮች እነማናቸው ? ፦
የእማራ ልሂቃን አሁን በድንገት በተከሰተላቸው በዚህ ስትራቴጂክ አጋር በሚለው አስተሳሰብ ትወራ መሰረት አምራ ክልልና ኤርትራ ፥ እንዲሁም ሶማሌ ክልልና አማራ ክልሎች ስትራቴጂክ አጋሮች ናቸው። አማራ ክልል ሁለት ስትራቴጂክ አጋሮች አሉት ማለት ነው። ክልሉ ከትግራይ ክልል ጋር ባለበት የማንነት ጥያቄ ውዝግብ ሰበብ ማዶ ተሻግሮ ያሉትን ነው እሚያምነው። በእርግጥ በክልሎች መሃከል ልዩነትና ውዝግብ ኣይኖርም ማለት አይዶለም። ግን ባንድ ሃገር ያለውን ጎረቤቱን ኣላምን ብሎ ጎረቤት ኣገር ድረስ መሄዱ ግን ወዴት እየሄድን ነው ያሰኛል ጉዋዶች።
ኢትዮፒያ ራሱዋ እንደ ሃገር አንድነቱዋ ላልቶ ክፍፍል ውስጥ ስትሆን የምእራብ አውሮፓን እሚያኽል የቆዳ ስፋት ያላት አገር ወደ ትናንሽ ክልሎች ብሎም አገሮች የመከፋፈል አደጋ ስለተደቀነባት የየክልሉ ልሂቃን እንደ ዘመነ መሳፍንት አስተሳሰብ መስመርን መያዛቸው አስገራሚ አይሆንም።
ክልሎች በተጠናከሩበትና ያገር መንግስትነትን ቅርፅ በያዙበት በዚህ ሰአት አንዱ ክልል ባንድ ኣገር ውስጥ ያለውን ጎረቤቱን ኣላምን ብሎ ተሻግሮ ማዶ ከሚገኘው ክልልም ሆነ አገር ጋር ስትራቴጂክ አጋሬ ነው ወደ ሚል ስሌት መሄዱ በራሱ አስገራሚ ነው።
ለምሳሌ አንድ ካናዳን እሚያዋስን ያአሜሪክ ስቴት አሜሪካ በአንድ አገር ውስጥ ያለጎረቤት ስቴትን ትቶ ካናዳ ስትራቴጂክ አጋሬ ነች እንደማለት ነው።
ወይም ካሊፎርኒያ ጎረቤት ስቴቶቹዋን አላምን ብላ ሜክሲኮ ስትራቴጂክ አጋሬ ነች እንደማለት ነው። ወይም ቴክሳስ ካሊፎርኒያን ኣላምን ብላ ስትራቴጂክ አጋሬ ሜክሲኮ ነች እንደማለት ነው።
No comments:
Post a Comment