Friday, November 16, 2018

እርካብና መንበር

"እርካብና መንበር " ፥
ነበረ ለካንስ የምር ።
*     *          *
ፍትህ ለታሰሩቱ ፥
....ለተደበደቡቱ ፥
ሰላም ዲሞክራሲ ሰፍኖአል ባገሪቱ ፥
ሲሉን ባመቱ ፥
ሌላ ሆኖ ተገኘ እንጂ እውነቱ ፥
መብት ጥሰቱ ፥
"ሁለተኛ አይደገምም "
በድጋሚ ይህ አይፈጸምም ፥
አልተባለም ወይ ?
*           *      *
ሁለተኛ እንዳይደገም ፥
ሰርተናል ሙዝየም።
*           *        *
ካለፈው የማይማር ፥
በቃ በቅጣት ይማር ።
*    *     *
የህግ የበላይነት ሲባል ፥
ለካ ነበረ ለይምሰል ?
ካሁን በሁዋላ መብትህ አይደፈርም ፥
ሁለተኛም ያለፍርድ አትታሰርም ፥
ተብሎ ሲያበቃ ፥
ዘንድሮ ካለፈው ብሶ ተገኘ በቃ ፥
ፈጣሪ ግፉን አይቶ ሲያበቃ ፥
ላከልን አብይ የመብት ጠበቃ ፥

የግፍ ጽዋው ሞልቶ
ይግፉ ዝጽዋ ሞልቶ ሲይበቃ
እንባውን አይቶ
*   *    *
ያለፈው ተረስቶ እንዳይደገም ፥
ሠርተናል ማስታወሻ ሙዚየም።
**     *        *    *
ሰላም ዲሞክራሲ ስፍኖአል ሲባል
መስሎን ነበረ እውነት።

No comments:

Post a Comment