ወጣት
ችግርም ሲመጣ መስዋእትነትን የሚከፍለው እሱ ስለሆነ ያገሩ ጉዳይ ከሌሎቹ የትውልዱ አካላት በበለጠ ሊያሳስበው ይችላል ።በሀገራችን
በ1950ዎቹና 60ዎቹ ብዙ
ጊዜ የነበረው ትውልድ ይደነቃል ። ሆኖም ሁሉም ትውልድ የየራሱ የሆኑ ታሪካዊ ግዴታዎችና ሀላፊነቶች አሉበት እንደየዘመኑና ወቅቱም
ይለዋወጣሉ ።በአንድ ወቅት የነበረ ችግር በሌላ ጊዜ ላይኖር ይችላል፣ ወቅቱ የሚጠይቀው ፈተናም እንደዛው ለየቅል ነው ። ሁኔታዎች
ስለሚቀያየሩ የሚፈልጉትም መፍትሄ እንደዛዉ ይለያያል።
ቻይናውያን
ሰፊ የአመራር ልምድ ያላቸው ሲሆኑ የመተካካት ባህላቸው እድሜን እያስቆጠረ የመጣና ሲሆን መተካካቱም በመንግስት ስልጣን ላይ ብቻ
ሳይሆን በፓርቲውስጥም እስካሉት ከፍተኛ የአስፈፃሚዎች ድረስ ነው ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማካይ በየአስር አመቱ የፓርቲው ከፍተኛ
ስራ 9 ከሚሆኑት ውስጥ 7 ወይም 8 የሚሆኑት ይተካሉ ስለዚህ ይህ በፓርቲው ውስጥም ሆነ በመንግስት ውስጥ የሚደረገው የአመራር
ለውጥ ከዋናዎቹ መሪዎች ጀምሮ ነው ።
ይሁን
እንጂ በመሪነት ውስጥ እሚመከረው ከሶስቱም ትውልዶች የተለዩ ትውልዶች ሰዎች መኖር አለባቸው ። ከወጣትም፣ ከመካከለኛው እድሜም
፣ እንዲሁም የረጅም ዘመን ልምድ ካላቸው የተውጣጣ እንዲሆን ነው ።ለምሳሌ የረጅም ዘመን ልምድ ያላቸው ሰዎች ከሌሉ ለወጣቶቹ ተሞክሮን
እሚያስተላልፍላቸው አይኖርም ፣ መሀል ላይ ያለውም ባይኖር በእድሜ ከበለፀጉት በቅርብ ሊረከብ የሚችል አይኖርም ። የረጅም ዘመን
ልምድ ያላቸው ሰዎች ብቻ ቢኖሩ ከአዲሱ ለውጥ ጋር ለመጓዝ አስቸጋሪ ይሆናል ። ስለዚህ ትውልድ ሰንሰለት ነው እንደሚባለው ሁሉ
በመሪነት ውስጥም እንደዛው ሰንሰለቱን ጠብቆ እየተተካካ መሄድ አለበት ።
No comments:
Post a Comment