አንድ
ነገር
እየተደረገ ካለበት ጊዜ ይልቅ ካለፈ በኋላ ይበልጥ ጥሩነቱ ወይንም መጥፎነቱ መሆኑ ጎልቶ ይታያል ። መጥፎ ስራ ጊዜ
እያለፈ
በሄደ ቁጥር መጥፎነቱ ይበልጥ እየጎላ ይሄዳል ሲሄድ በአንፃሩ ደግሞ ጥሩ ስራ ከሆነ ደግሞ ጊዜ ጥሩነትን ይበልጥ
እያጎላው ይሄዳል
። ለዚህም በርካታ መጥፎ ስራዎች መጥፎነታቸው ተደጋግሞ የሚነሳና በርካታ አመታትም ካለፉም በኋላም ቢሆን መጪውም
ትውልድ ጭምር
የሚያፍርባቸው ሲሆኑ ፣ ጥሩዎቹም ዘመን ባለፈ ቁጥር ጥሩነታቸው እየጎላና ህብረተሰቡ የሚኮራባቸው ነው ። ስለዚህ
የሚያደርጋቸውን ነገሮች የአጭርነ ና የረጅም ጊዜ አንድምታ ለይቶ ማወቅ አለበት ። እነኚህም የሚከናወኑት
በታክቲኮችና በስትራቴጂዎች አማካይነት ነው ።
አንድ
መሪ በተለይ ግቡን ለማሳካት ስታራቴጂዎችንና ታክቲኮችን ማወቅ አለበት ። አንድ መሪ ስትራቴጂንና (Strategy)
እና ታክቲክን (Tactic) ለይቶ ማወቅ ሲኖርበት ፣ ስትራቴጂ ማለት የመሪው
ዋነኛው የረጅም ጊዜ ግቡ ወይም በረጅም ጊዜ እደርስበታለሁ ብሎ የሚያስበው ሲሆን ፣ በአንፃሩ ግን ታክቲክ ማለት ስትራቴጂውን እሚያስፈፅምበት
የአጭር ጊዜ ብልሀቶችና መንገዶች ናቸው ። ስለዚህ የታክቲኮች ስኬታማነት ተሰባስቦ የስትራቴጂን ውጤማነትን ያረጋግጣል ። የታክቲኮች
መውደቅም የስትራቴጂውን አለመሳካት ሲያመለክት ።
ይሁን
እንጂ (the End Justifies the Means)የሚል
አቋም ያላቸውና አንድ መሪ ስትራቴጂውን ለማሳካት ማንኛውንም ነገር ማድረግ አለበት ብለው የሚያምኑ አሉ ። መጨረሻ ግቡ ትክክል
እስከሆነ ድረስ ፣ መሪው ግቡን ለማሳካት ማንኛውንም ነገር ወንጀል ሊሆን የሚችልንና ሌሎች ሰዎችን ሊጎዳ የሚችል ነገርን ጨምሮ
መፈፀምና አላማውን ማሳካት አለበት ብለው የሚያምኑ ናቸው ። ነገር ግን ይህ አስተሳሰብ እጅግ አደገኛ ሲሆን ሊያስከትል የሚችለው
ቀውስ ከባድ በመሆኑ ከፍተኛ የማመዛዘን ችሎታን ይጠይቃል ። ታላቁ ስትራቴጂ ወይም ዋነኛው ግብ የሚባልም አለ ።
የአጭር
ጊዜ የታክቲክ አዋቂ መሆንና የረጅም ጊዜ የስትራቴጂ ቀያሽ መሆን በጣም የተለያዩ መሆናቸውን መረዳት ያስፈልጋል ። ብዙ ጊዜ የአጭር
ጊዜ ታክቲኮች ረጅም መንገዶችን የማያስኬዱ ሲሆኑ ለአጭር ጊዜ ጥቅምን ሊያስገኙ ቢችሉም በረጅም ጊዜ ግን ጉዳታቸው አመዛኝ ነው
። የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ ግን የረጅም ጊዜ ግብን ወይም ስኬትን አልሞ የሚጓዝ ሲሆን በሂደትም አንድ መሪን ከመንገዱ ከሚያጋጥሙ
ከብዙ አላስፈላጊ ችግሮች የሚጠብቅ ነው ነው ። የአጭር ጊዜ ታክቲክ ከረጅም ጊዜ ስትራቴጂው ያፈነገጠ መሆን የለበትም ። ብዙውን
ጊዜ የአጭር ጊዜ ታክቲክን ብቻ የሚጠቀሙ ሰዎች ረጅም ርቀት መሄዳቸው
አጠራጣሪ ነው ። መሄድ ከቻሉም ብዙ ዋጋ በሚያስከፍል መንገድ ሊሆን ይችላል ። ይህም በተደጋጋሚ በብዙ መስኮች በታሪክ የታየ አጋጣሚ
ነው ።
ለአጭር
ጊዜ እሚጠቅም ነገርን ማስፈንና ለረጅም ጊዜ ዘላቂ የሆነ ነገርን ማስፈን በጣም የተለያዩ ነገሮች ሲሆኑ እሚጠይቁት ጥረትና እሚኬድባቸው
ጎዳናም የተለያየ ነው ። ብዙ ጊዜ ምእራባውያን የረጅም ጊዜውን በማየት
ነው እሚንቀሳቀሱት ።
በነገራችን
ላይ ምእራባውያንም በአንድ ወቅት የአጭር ጊዜ ታክቲክን እንደ ትክክለኛ አማራጭ የሚወስዱበት ጊዜ የነበረ ሲሆን ይህንንም አፍሪካን
በቅኝ ግዛት ሲይዙና ከዚያም በኋላም ቢሆን ምንም እንኳን ሀገራቱ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ወጡ ቢባልም ብዙዎች ሀገራት ግን እውነተኛ
ነፃነት አልነበራቸውም በተለይም የኢኮኖሚ ነፃነታቸው በምእራባውያን
እጅ ሆኖ ለዘመናት ሲቆይ ፣ ነገር ግን የቀድሞ ታዳጊ ሀገራት በመባል ይታወቁ የነበሩት እነኚህ ሀገራት በምጣኔ - ሀብታቸው እያደጉ
ሲሄዱና ፣ በአንፃሩ ግን ምእተራባውያን የምጣኔ - ሀብት የበላይነታቸውን እያጡ ሲመጡ እነኚህ ታዳጊ ሀገራት ነፃነታቸውን ማስመለስ
መጀመራቸው ይታወቃል ተጠቅመውበታል።ሆኖም ግን አሁን ጉዳቱን በአመዛኙ ሰለተረዱት እየተውት መጥተዋል ።
No comments:
Post a Comment