Monday, September 24, 2018

china ethiopia debt trap policy

የቻይናና እዳ ውስጥ የመዝፈቅ ፖሊሲና የኢትዮጲያ ወዳጅነት ሲቃኝ
ፀሃፊው ስሜነህ ተረፈ
ጠቅላይ ሚር ዶር አብይ አህመድ በቻይና ጉብኝታቸው ወቅት ቻይና ለኢትዮፒያ የሰጠቻቸውን ብድሮችን ወለዱን እንድትቀንስና የመክፈያ ግዜው እንዲራዘም የቻይና የኤክዚም ባንክ ሃላፊ ሲነግሩ የቻይናው ፕሬዝዳንትም የባህር በር ለሌላቸው ትናንሽ ደሴቶች ለሆኑ የእፍሪካ ሃገራት ተወለድ ቅነሳ ወይም ስረዛ እንደምታደር ችን ፒንግ ፍንጭ ሰተዋል። ቻይና በአበዳሪነት ተቀባይነቱዋ እንዲቀንስ አትፈልግም። ዶር አብይም በብድር የተገኝ ገንዘብን ያባከነው ሜትልክ 1 ወር ውስጥ ለሁለት እንዲከፈል ትእዛዝ አስተላልፈዋል። ቻይና ያላትን ትርፍ ተቀማጭ ገንዘብ ስራ ላይ ማዋል ትፈልጋለች ለዚህ ድግሞ ወጣት ህዝብ ያላት አፍሪካ ምቹ ናት። ቻይና አገራዊ አጠቃላይ ምርቱዋ ከአሜሪካ አልፎ የሄደ ሲሆን የአለማችን ግዙፍ ምጣኔ ሃብት ባለቤት ሆናለች። ምንም እንኩዋን በሊበራል ሞክራሲ የምትመራ አገር ባትሆንምና ውስጣዊ ዲሞክራሲ ባይኖራትም በሃገሩዋ ስራ ያጣ ህዝቡዋን አዲስ የስራ ዘርፍ ለማስገኘት አፍሪካን በእጅጉ  ትፈልጋታለች የአፍሪካ ህዝብ 1ቢሊየን ሲሆን የቻይና ደግሞ 1.3 ቢሊየን ነው። ከዚህም።በላይ ቻይና
ከትራምፕ አሜሪካ ጋር በገባችው የንግድ ጦርነት የአፍሪካን ገበያንና ድጋፍን  ትሻለች ምንም እንኩዋን አሜሪካ እየተገለለች ብትመጣምና በአለም ያላት ተሰሚነት ማዘቅዘቅ ከጀመረ ቢሰነብትም፣ በአለም አቀፍ መድረኮች ቻይና የድርሻዋን እንዳትወጣ አሜሪካ እንቅፋት ሆናባታለች በዚህ ምክንያት እንደ አፍሪካ አህጉር አገራትን ድጋፍ ትሻለች ስለዚህ ብድሮቹዋ ላይ ብትለሳለስ አስገራሚ አይሆንም። ምእራባውያን በአፍሪካ አህጉር ከቻይና ጋር መወዳደር አልቻሉም በእፍሪካ የተፈጥሮ ሃብት ያላቸውን እንድ አንጎላ፤ ዛምቢያ ታንዛንያ እንዲሁም ሰፊና ለም መሬት ያላቸውንና ቁልፍ አቀማመጥ ያላትን ( strategic)  የሆነችውን እንደ ኢትዮፒያ ያሉ ቁልፍ አገራት ቻይና በእጅጉ ትፈልጋቸዋለች።
በቅርቡ የአፍሪካ ሃገራት ከቻይና ጋር ባደረጉት ስብሰባ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢንፒንግ ለአፍሪካ ሃገራት ተጨማሪ 60 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንትና ብድር ለመስጠት ቃል ገብተዋል ፡፡ /ሚር / አብይም ለሁሉም ብድሮች ባይሆንም ቻይና ለኢትዮጲያ የሰጠችውን ብድር ወለድ እንድትቀንስና የመክፈያ ግዜውን እንዳታራዝም ጠይቀው ተሳክቶላቸዋል ፡፡ የቻይናው መሪ ደሴት ለሆኑና የባህር በር ለሌላቸው የአፍሪካ ሃገራት የእዳ ቅነሳን እንደምታደርግ መናገራቸው እፎይታን ሰቷል፡፡ ከፍተኛ የእዳ ጫና ያለባት ሃገር የሆነችው ኢትዮጲያ ከሃያ አምስት ቢሊየን ዶላር እዳ ውስጥ ወደ አስር ቢሊየን የሚደርሰው ከቻይና የተወሰደ ብድር ነው፡፡
አፍሪካዊቷ ዛምቢያ የመብራት ሃይል ኩባንያዋንና፣ አየር ማረፊያዋን ለቻይና ለማስረከብ ተገዳለች ይህችው ሃገር የቻይና ከፍተኛ እዳ ቢኖርባትም መበደሯን ግን አላቆመችም ፡፡ ቻይና ለአፍሪካ የሰጠችው እዳ ቀላል የማይባል ከመሆኑም በላይ አንዳንድ ሃራት ሲሪላንካንና ጎረቤት ጅቡቲን ጨምሮ ትልቅ እሚባውን ሃገራዊ ሃብታውን ለቻይና ማስያዝ ጀምረዋል ፡፡ የቻይና ሃገራትን በእዳ ወጥመድ ውስጥ በመክተት የመተብተብ ዲፕሎማሲ (debt trap diplomacy) ብዙ ሃገራትን አጥምዶ ይዟል፡፡ ቻይና ምንግዜም ቢሆን ከየትኛውም ሃገር ያላትን ግንኙነት በረጅም ግዜ ተጠቃሚነቱዋ አስልታ የምትገባ ሲሆን እርሷ በቀላሉ ብድርን ለአፍሪካ ሃገራት በተለይም ሰብአዊ መብትን ለማያከብሩና የአምባገነንነት ዝንባሌ ላላቸው የአፍሪካ ሀገራት ቀላል የማይባል የእድሜ ማራዘሚያን የፈጠረ ቢሆንም ሃገራቱን ግን ለከባድ እዳ ዘፍቋል፡፡ ምእራባውያን እነኚህ ሃገራት የኢኮኖሚ ሪፎርምን እንዳያደርጉ የፋይናንስ ምንጭ ሆናለች ብለው ይከሷታል ቻይና ብድር ስትሰጥ የሰብአዊ መብት ሪኮርድን አታይም ይህን አድርግ ይህን ለውጥ ብላም መንግስታትን አትጫንም ነገር ግን የተፈጥሮ ሃብትን መቆጣጠርን ታስቀድማለች፡፡
ባለፉት ኢህአዴግ መራሽ ዘመን በየአመቱ ብቻ ከውጭ በብድርና እርዳታ 2እስከ 3 ቢሊየን ዶላር ድረስ ያኝ ነበረ። ይህ ገንዘብ ኢትዮጲያም ሆነች መሪዎቻችን አይተውት የማያውቁት ነው።  በዚህ  ከውጭ በመጣ ገንዘብ የኢኮኖሚ እድገቱ ተደግፎ ቆይቶአል። ነገር ግን ገዥው ፓርቲ ራሡን ወደ ገዥ መደብነት ( oligarcy ) በመቀየር በህዝብ ስም የመጣን ገንዘብ በሙስና ከመቀርጠፍ አንስቶ ወደ ውጭ ያሸሽ ገባ አገር አስተዳድራለሁ የሚለው መንግስት የአገርን ሃብትና ንብረትን በራሡ ቁጥጥር ስር በማዋል ሙስናና ዝርፊያው ቀጠለ፣ ህዝብ  ፍትህ ማግኘት አልቻለም የተለየ ሃሳብ ያነሱ የድርጅት አባላትን ሳይቀር ቆይ ጠብ እስር ቤት ትበሰብሳለህ ይባል ገባ። በዚህ የውጭ ገንዘብ የኢኮኖሚ እድገትን አስገኛለሁ ማለት በጉሉኮስ እየተሰጠው ሆስፒታል የሚኖር ሰው ማለት ነው ።ሙስናው በወጣቱ ዘንድ ቁጣን ያስነሳ ሲሆን እውቁ ግሪካዊው ፈላስፋ እንደሚለው <<በፖለቲካ ዓለም ውስጥ ከአማልክቶች በስተቀረ ማንም ተመልካች አይሆንም››  እንደሚለው  አብዛኛው  የሃገራችንን የፖለቲካ ቲያትር ተመልካች ተደርጎ የነበረውና ጥቂት የነባር አመራሮች በሚተውኑበት ቲያትር ውስጥ በፌስ ቡክ አማካይነት ተሳታፊ መሆን <span style="font-family:Nyal
...

Tuesday, August 21, 2018

አክቲቪዝምና የሃገራችን የደቦ ፖለቲካ ውጥንቅጥ



ፀሃፊው ስሜነህ ተረፈ
ኢ-ሜይል smofed@hotmail.com or
smofed@gmail.com
የመብት ተሟጋችነት (አክቲቪዝም) ማለት ለአንድ የለውጥ አላማ መረጃ መስጠት፤ማንቃት ፤ማስተማር ህዝብን ማደራጀትና ማብቃት ማለት ሲሆን የመብት ተቆርቋዎች (Activist) ሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ናቸው እንጂ ወደ አመፅና ብጥብጥ አያመሩም ፣ የመብት መረገጥ ካለ አክቲቪዝም (Activism) ከተቃውሞ (resistance) ወይም ህዝባዊ እምቢ ባይነት (civil disobedience) ብሎም ወደ አስተዳደራዊ ፖለቲካ (administrative politics) እየዳበረ መሄድ አለበት ፡፡ከቀድሞዎቹ ትውልዶች በተለየ ሁኔታ የአሁኑ ትውልድ ምንም አይነት ጥይት ሳይተኩሱ አምባገነኖችን መታገል ብቻ ሳይሆን መጣልም እንደሚችል ይህ ለውጥ አመላካች ነው ፡፡ የሙዳየ ሃሳብ ተቋማት (think thank) ማለት ከዩንቨርስቲዎች የሚመነጭን ንድፈ ሃሳባዊ የሆነ እውቀትን ልክ አጣፍጠው ቀለል ባለ መልኩ የተግባር ሰዎች ለሆኑት ለፖለቲካና ቢዝነስ መሪዎች የሚያቀርቡ መለስተኛ የጥናት ተቋማት ናቸው ፤እንደ ጃዋር መሃመድ ያሉት ዋነኛ አክቲቪስት የነበሩት በውጭ የቆዩት የሃሳብ ማጥኛ ተቋማትን ለመክፈት ሃሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል ጃዋር መሃመድ በሙዳየ ሃሳብ ተቋማት የሚፈልቅን ሃሳብ ለአስፈጻሚው አካል የሚቀርብን ሃሳብ ‹‹አጤሪራ እንደማጉረስ ነው›› ሲል ይገልጸዋል ፡፡ አክቲቪዝም ወደ ሀሳብን ወደ ማበልፀግና ወደ ምርምር ተቋምነትና የፖለቲካ ሰዎች የሚመሩባቸውን አስተሳሰቦችን ወደማዳበር ደረጃ ማደግ አለበት እንጂ ወደ አመጸኝነትና ረብሻ ስርአት አልበኝነት (አናርኪ) ደረጃ መዝቀጥ የለበትም፡፡
በሶማሌ ክልል ‹‹ስልጣንህን ልቀቅ ተብያለሁ፣ስልጣኔን ከምለቅ ብሞት ይሻለኛል›› በሚል ጸረ-ዲሞክራሲዊ ስሜት አብዲ ኢሌ ወይም አብዲ መሃመድ ኡመር የተባሉት የክልሉ ፕሬዝዳንት የነበሩ ግለሰብ ያሰለጠኗቸው ሄጎ ሲባሉ ከቄሮ በተቃራኒ ሄጎዎች ለውጥን ለማደናቀፍ በሶማሌ ክልል የተደራጁ ሲሆን ‹‹ሄጎ›› የሚባሉት እነኒህ የወጣት ቡድኖች የሶማሊያን ሪፐብሊክን ሰንደቅ አላማ በመያዝ ‹‹አብዲ ኢሌ ለዘላለም ይኑር›› እያሉ መፈክርን እያሰሙ በሶማሌ ክልል ከተሞች በመዞር በከተሞች ውድመትና የሰው ህይወትን ማጥፋት ፈፅመዋል ፡፡ እንዲሁም በሻሸመኔ ጃዋር መሃመድን ለመቀበል በወጣው ሰልፍ ላይ 3 ሰዎች ሲሞቱ ወደ 71 ሰዎች ቆስለዋል ፤ ወደ መቀሌ ሊሻገር የነበረን እህል ከመኪና አውርዶ ለህዝብ ማከፋፈል ከወደ አማራ ክልል የተሰማ ሲሆን እንዲሁም በጎንደር ፣በባሌ፣በጣና በለስ፤በከፋ ሸካ ዞን -በቴፒ፣ በዶምቢዶሎ፣በደብረማርቆስ ወዘተ… የታየው ብጥብጥና ረብሻ ግን ከመስመር ያለፈ ነው ፤ በሱማሌ ክልል የጅቡቲ ዜጎች ላይ የደረሰው ጥቃት እንዲሁም በጅቡቲ ባሉ ኢትዮጲያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት አግባብነቱን የሳተና አክቲቪዝም ምን ላይ ነው መቆም ያለበት የሚለውን የሚሳስብ ነው ፡፡አንዳንዶች ይህ የምናየው የደቦ ፍርድ ‹‹በለውጥና ሽግግር ወቅት የሚያጋጥም ነገር ነው›› ሲሉ ሊያቃልሉት ይሞክራሉ ነገር ግን ‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› እንዲሉ አበው እንደ ቀይ ሽብር ዘመን ‹‹አስታጥቁን፣አታስጨርሱን›› ደረጃ ላይ ባይደርስም ‹‹ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም›› ብሎ በሱማሌ ክልል ከተፈጸመው ትምህርት በመውሰድ መፍትሄ መፈለግ ግን ያባት ነው ፡፡የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክንም ሃይ ባይ ያጡትን አንድ በሉልኝ ስትል ‹‹የመንግስት ትእግስት በዛ›› ስትል አሳስባለች፡፡
ይህ በሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት ተጠያቂነት አለመኖርን እንዲሁም መንግስት የላላ የፀጥታ አጠባበቅንና አንዳንዶች እንዲሁ መንግስት ጠንከር ካላለ ከዚህ የባሰ ይመጣል ብለው የሚሰጉ ወገኖች አሉ ‹‹ለቄሮ እናገራለሁ … ቄሮ ይቀጣችኋል›› የሚሉ አባባሎች ወጣቶች ያለ ተጠያቂነት የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ የሚል ሃላፊነት የጎደለው የተሳሳተ ስሜትን ፈጥሯል ፤ ይህም ወደ ሃገራችን ይመጣሉ የሚባሉትን የዋጋ ቅናሽ ተደርጎላቸው ወደ ሃገራቸው የዘመን መለወጫን እንዲያከብሩ የተጠሩትን ዲያስፖራና ቱሪስቶችን ቁጥር እንዲቀንስ የሚደርግ ነው ሲሉ ስጋታቸውን የባህልና ቱሪዝም ተቋማት አመራሮች እየገለፁ ናቸው ፡፡ዋነኛ አክቲቪስት የሆነው ጃዋር መሃመድ በበኩሉ ይህን በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለውን ወጣቱ በራሱ ስልጣን እየወሰደ ያለውን እርምጃ ማውገዝና ከህግና ከስርአት መውጣት እንደሌለበት በይፋ መናገር ይጠበቅበታል፡፡ጆርጅ በርናርድ ሾው እንተናገረው ‹‹ነጻነት ማለት ሃላፊነት ማለት ነው›› ነጻነት ዋጋ ተከፍሎበት እንደተገኘው ሁሉ ያለተጠያቂነት ዝም ብሎ የህግ የበላይነትን ቸል በማለት የሚከበር አይደለም፡፡   
በመልካም ጎኑ ስናየው አክቲቪዝም ለምሳሌ የባህር ዳር ወጣቶች ከመንግስት ጋር በተደረገው ግጭት ከተጎዱ ቤተሰቦች ከ17 በላይ ከሚሆኑ ባለሃብቶች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ መስጠታቸው በዜና ማሰራጫዎች ተነግሯል ፡፡ ይህ አክቲቪዝም መልካም ጎኑ ሲሆን ከዚህ ባለፈ ግን ወደ ግጭትና ረብሻ በሃገራችን በተለያዩ ክልሎች የምናያቸው ከመስመሩ የወጡና በተለይም ወጣቱ ራሱን ጆሮውን ለዚህ መስጠት የለበትም ፣ተከታይ ያፈራ አክቲቪስት በሃላፊነት ስሜት መረጃን የሚያስተላልፍ ካልሆነ አደጋን ያመጣል፡፡የዶ/ር አቢይ መንግስት በግልፅነት በሃገሪቱ የተፈጸሙትን ለምሳሌ የኢንጂነር ስመኝን ግድያ ፣ የሰኔ 16ቱን ቦንብ ውርወራ የመሳሰሉትን ለህዝብ ይፋ ማድረግና ማሳወቅ ይጠበቅበታል ፡፡ ፖለቲካ ላለማበላሸት በሚል፣የውስጥ ድርድርን በማድረግ የዚህን የመሳሰሉት ጉዳዮች ሲደበቁና ሲሸፋፈኑ በህዝብ ዘንድ ጥርጣሬን ፣ በወጣቱ ዘንድ ደግሞ በራሱ ህግን ለማስከበር ሲል የመሰለውን ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚህም ሌላ የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችንን መፈተሸና የአክቲቪዝምን ገደብና ድንበርን መለየት ያስፈልጋል ፤ ህብረተሰቡ የመጣለትን ለውጥ ለማረጋገጥ የየራሱን ድርሻ መወጣት አለበት፡፡በኢንተርኔት የተጻፈን ነገር ሁሉ እውነት ነው ብሎ መውሰድ ለጥፋት ሊዳርግ እንደሚችል ከሰሞኑ ያየናቸው ግርግሮች ምስክሮች ናቸው ፡፡ በምእራብ አገራትም ጭምር የጥላቻ ንግግሮች (hate speech) ክልክል ናቸው ፣ እንዲሁም የሚታወቁ እውነታዎችን መካድ፣አልተደረጉም ብሎ መከራከር ለምሳሌ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት አይሁዶችን ናዚዎች አልጨፈጨፏቸውም ብሎ የሆሎኮስትን (genocide) መካድ በራሱ በአውሮፓ አገራት ህግ በወንጀል ያስጠይቃል፣በሃገረ አሜሪካም ጥቁሮችን ወይም ሌላ ዘርን የሚያዋርድ ነገርን መናገር ወይም መጻፍ ያስጠይቃል ፡፡
ለዘመናት በጣም የታፈነ ጩኀት የነበረበት ሃገር እንደመሆኑ ፣ቀድሞ መጮህ ቢፈለግም መጮህ የማይቻልበት ዘመን ነበር አሁን ግን ህዝቡ ባደባባይ ስሜቱን መግለፅ ይችላል፡፡ባገሩ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ የኖረ በመሆኑ ምክንያት አሁን መተንፈሻ ያገኘው ህዝብ በተለይም ወጣቱ በገነፈለ ሁኔታ ስሜቱን እየገለፀ እንዳለ መረዳት ይቻላል፡፡ በሃገራችን ለውጥን በሰላማዊ መንገድ የመምራት ልምዱ የለንም ማለት ይቻላል፤ከዚህ ቀድሞ የደርግ መንግስት ከሃይለስላሴ ስልጣኑን ሲረከብ እርስ በእርስ ፍጅት የተካሄደ ሲሆን ኢህአዴግም ደርግን ሲተካ እንዲሁ ስልጣኑን እስከሚያጸና ድረስ ሃይልን ተጠቅሟል ፤ የአሁኑን ለየት የሚያደርገው ግን ጠ/ሚር ዶ/ር አቢይ ለስላሳ አቋምን በማሳየታቸው ምክንያት ስርአት አልበኝነቱ ሊንሰራፋ በቅቷል ፡፡የህግ የበላይነት ቀርቶ ሁሉም የፈለገውን አድርጎ ምህረት ይደረግልኛል የሚል ስሜት መኖር የለበትም ፡፡ ድምጻቸውን አጥፍተው የቆዩት ጠ/ሚሩ የመከላከያ ኮሌጅ ተመራቂዎችን ነሃሴ 12 ፣ 2010 ዓ.ም. ሲያስመርቅ እንደተናገሩት ‹‹የይቅርታው ዓላማ ባለፍንበት መንገድ ያጣነውን ለማግኘት ነው እንጂ የገነባነውን አገር ለማፍረስ አይደለም… ዘመናዊነት የህግ የበላይነትን ማክበር ነው›› ብለዋል፡፡
እነኚህ ረብሻዎች የሚያመለክቱን ሌላው ነገር ለውጡ መፍጠን እንዳለበት አመላካች ነው ፣ ለውጥ አደናቃፊዎች በዚህ ረብሻ የሚጠረጠሩትን ያህል ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ህዝቡ የሚጠብቀው ፈጠን ያለ ለውጥና መንግስት እየሄደ ያለበት የለውጥ ጉዞ ሂደት ያላረካቸው ወገኖች ትእግስት በማጣት ወደ ግርግር ሊያመሩ እንደሚችሉ መገመት ያሻል በተለይም ወጣት ስራ አጥነት በተንሰራፋበትና የንግድ መቀዛቀዝ እየተስተዋለ ባለበት ሁኔታ ፤ ፈጠን ያሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጦች፣ አጠቃላይ የፍትህ ስርአቱን ማሻሻል፣ ተዛማጅ ህጎችንና አዋጆችን መፈተሽ ፣ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርብባቸው የነበሩ አዋጆች መሻሻልና መተግበር አለባቸው ፣እንዲሁም ሹመት አሰጣጥ ላይ በቀደመው ዘመን በሙስናና በአቅም ማነስ ሲተቹ የነበሩትን ጠ/ሚሩ ስፍራ ሲያገኙላቸው ይታያል፤የአምባሳደርነት ሹመት አቅመ ቢስ ለሆኑ ባለስልጣናት ማገገሚያ መሆኑ ቅሬታን የፈጠረ ሲሆን በፓርላማ ደረጃም ተነስቶ ነበረ፤ ‹‹አዲስ ወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ›› እንዳይሆን የህዝብን የለውጥ ጥያቄን ሊያረካ በሚችል መንገድ አቅም ያላቸውን አዳዲስ አመራሮችን መሾም የሚበጅ ነው፣ በደቡብ ክልል በሸካና ከፋ ዞን የታየው ከለውጡም በኋላ አመራሩ ራሱን አለማስተካከሉ ችግሩን አባብሷል፡፡
የፌደራል መንግስቱ ምን ሲፈጠር ነው ጣልቃ የሚገባው ?
ምንም እንኳ የአንድ ክልል አስተዳደር ራሱን የሚያስተዳድር (ኦቶኖሚ) ቢሆንም ፣ በክልሉ ያለው የዳኝነት ነጻነት መከበር አለበት፤ የክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤም ይህን የሚያሟላ መሆን አለበት ፡፡ ነገር ግን የዳኝነት ስርአቱና ፖሊስ ህግና ስርአትን በክልሉ ማስከበር በማይችልበት ደረጃ በሚደርስበት ወቅት ፌደራል መንግስቱ ጣልቃ ሊገባ ይችላል፤ የፌደራል መንግስቱ ለክልሎች የበጀት ድጋፍን የሚያደርግ እንደመሆኑና ከዚህም በተጨማሪ ያገር ሉአላዊነትንና ደህንነትን የመጠበቅ ሃላፊነት ስላለበት በክልሎች የሚከናወን ህገ ወጥነትን በዝምታ ይመልከት አይባልም፡፡
በሱማሌ ክልል የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በተደጋጋሚ በህብረተሰቡ ዘንድ ይነሳ የነበረ ቢሆንም ፤ የነዳጅ ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት የተገኘበትና ለገበያ መቅረብ የጀመረበት ሲሆን ፣ክልሉ ላለፉት 27 አመታት ተገቢውን የልማት ስራ ያልተሰራበትና በሚገባው መጠን ያላደገ ሲሆን ፤ ሙስናም ተንሰራፍቶ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ሲደርስና የክልሉ ባለስልጣናት ባጀቱን ሲዘርፉት እንዲሁም የክልሉ ህዝብ ተጠቃሚ ሳይሆን የቀረበት ዘመን ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ የክልሉ ያገር ሽማግሌዎችም (ኡጋሶች) ጭምር እዚህ አዲስ አበባ በመገኘት ለጠ/ሚሩ ተደጋጋሚ ጥያቄውን ቢያቀርቡም ጥያቄያቸው ፈጣን ምላሽን ሊያገኝ አልቻለም፣በተደጋጋሚ ኢሳትን ጨምሮ በክልሉ ያለው የአብዲጊሌ አገዛዝ በክልሉ ኪራይ ብሳቢነትንና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣን ማድረጉን ሲገልፁ ቢቆይም ፣ እንዲሁም ሂዩማን ራይትስ ዎች በክልሉ ያለው የልዩ ሃይል እንዲበተን ቢጎተጉቱም ሰሚ ሳያገኙ ቆይተዋል፤ በሶማሊያ ወረራ እንኩዋን ያልተፈፀመ በደልና ውድመት ደርሷል፤ በዚህም ምክንያት ቀላል የማይባል ዋጋን አስከፍሏል ፡፡
ይህ ሁሉ ጥፋት ከጠፋ በኋላ የሶህዴፓ አመራር ባደረገው ግምገማ መሰረት ‹‹የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች፤ በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊና የዲሞክራያዊ መብቶችን ማፈን ፣ በህዝቦች መሃል ግጭቶችን በመፍጠር፣ ህዝብን ማፈናቀል ፣ የሃሰት መረጃዎችን አመራሩ በማሰራጨት የህዝብ ግጭት እንዲፈጠርና አለመረጋጋት እንዲፈጠር ማድረግ ፣ ሄጎ የተባሉ ወጣቶችን በማስታጠቅ በማስራጨትና በማስተማር በጅግጅጋ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞች እንዲሁም በህብረተሰቡና በተለያዩ የማህበራዊ ተቋማት ላይ ጥፋቶችን መፈጸም፣ ፍፁም ህገ መንግስትን በጣሰ መልኩ ሰዎችን ማሳሰርና ማሰር ፣ የዲሞክራሲን ማፈን ፣ ህዝቡን ማፈን ፣ ሁሉንም የመንግስት ተቋማትን ሽባ በማድረግ ፣ የጎሳ መሪዎችን በመንግስት መሾምና መሻር ፣ በሃሰት ማስረጃ ፣ መርህ አልባ ግንኙነትን በመፍጠር ፣የከፋ የኪራይ ሰብሳቢነትና ብልሹ አሰራር ፣ የመንግስትን ሃብት ማባከን ፣ ለጎሳ ለዘመድ ማከፋፈል ፣ ፕሮጀክቶችን ለወዳጅ መስጠት ፣ ንግድን በሞኖፖል መቆጣጠር ፣ ኮንትሮባንድ ንግድ ማካሄድ፣ የሴፍቲኔት ገንዘብን መከፋፈል፣ የአመራር መምከንንና ወደ ገዢ መደብነት መቀየር ፣ በግለሰብ አምባነናዊ አገዛዝ ስር መውደቅ ፣ የመንግስት ተቋማትን ወደ ግል ባለቤትነት መቀየር ፣በመንግስት ገንዘብ ህገ ወጥ ድርጅቶችንና የማፍያ ኔትርኮችን ማደራጀት፣ የሃሰት ሪፖርት ማሰራጨት፣ በከፋ የስነ ምግባር ችግር ፍፁም አድርባይትን በማንገስ ፣ ድብቅ የማፍያ ቡድኖች ተደራጅተውና ታጥቀው ፣ ስልጠናም ጭምር ወስዶ ነው ይህ የተደረገው›› ብለዋል፣ የክልሉን መንግስት ከላይ እስከታች እንደገና ማደራጀት ስራ እንደሚከናወን የገለፁት አቶ አህመድ ሽዴ፣ 3 ስራ አስፈጻሚና 5 ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን መታገዳቸውንና ፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ለፍርድ የማቅረቡ ሂደት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አክለዋል ፣ግምገማው ፍፁም ዲሞክራሲያዊና ግልፅ ነበረ ብለዋል፡፡ ጥያቄው ግን ይህ ሁሉ ሲሆን ፌደራል መንግስቱ በወቅቱ ለምን እርምጃ አልወሰደም የሚል ነው ፡፡
ከዚህ ሁሉ በኋላ ጣልቃ የገባውን የፌደራል መንግስቱን የሶማሌ ክልልን ራስን በራስ የማስተዳደር ስልጣኑን ደፍሯል የሚሉ አሉ - ነገር ግን የህግ ባለሙያዎች እንዳስታወቁት ከላይ የተጠቀሰው በሱማሌ ክልል የተፈፀመው ግዙፍ የሰብአዊ መብት ጥሰት ‹‹ግሮስ ሁውማን ራይት ቫዮሌሽን›› ነው በዚህ ሁኔታ ፌደራል መንግስቱ እጁን አጣጥፎ መቀመጥ እንደሌለበት የታወቀ ነው ፡፡ በክልሉ የተነሳው ረብሻ በክልሉ በሚኖሩ ዜጎች ቤትና ንብረት ላይ ዘረፋ ሲፈፀም ፤ በዚህ ብቻ ሳይወሰን በአብዲ ኢሌ የተመራው የክልሉ መንግስት እገነጥላለሁ በማለቱ ምክንያት የመከላከያ ሰራዊቱ ሊገባ ችሏል ተከትሎም ከሌላ ክልል የመጡ ብቻ ሳይሆን ጅቡቲዎችና ሱማሌዎች ጭምር የክልሉን ከተሞች በመልቀቅ ወደ ስደት ገብተዋል ፡፡
የክልሉን ፀጥታና ደህንነትን እንዲያስክብር ሃላፊነት የተጣለበት ራሱ የክልሉ ፖሊስና ልዩ ሃይል ጸጥታን ከማስከበር ይልቅ ራሱ ዝርፍያና ውድመት ውስጥ በመግባቱ የፌደራሉ ሃይል ጣልቃ ገብነት አስፈልጓል፡፡  በመጀመሪያ የፌደራል መንግስቱ ወደ አንድ ክልል ጣልቃ ሊገባ የሚችለው ምን ሲሆን ነው? የሚለውን መመልከት ያሻል፤ ሌላው ደግሞ ጣልቃ መግባት ማለት ምን ማለት ነው? የሚለው ሲታይ ወታደራዊ በሆነ መንገድ ነው ወይንስ ኢኮኖሚዊ ወይስ ሌላ ከሆነ በምን መንገድ ነው ጣልቃ መግባት ያለበት? የሚለው አነጋጋሪ ሊሆን ይችላል፤ ለምሳሌ በድሬዳዋ የተሰበሰቡ ተሰብሳቢዎች አብዲ ኢሌ በጀቱ ሊያዝበት ይገባል ሲሉ ባወጡት የአቋም መግለጫ ላይ አውጥተዋል፤በርካታ በክልሉ ነዋሪ የሆኑ ዜጎችም ከዚህ በኋላ በክልሉ ለመኖርና ለመስራት ምን ዋስትና አለን ሲሉ ጠይቀዋል ፡፡
ህገ መንግስቱ ምን ይላል ብለን ስንጠይቅ አንቀፅ 15 መሰረት ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው ፤ እንዲሁም ‹‹በህግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ህይወቱን አያጣም›› ይላል ስለዚህ አንድን ሰው ፀጉረ ልውጥ ነው በሚል ብቻ መግደል ወይም መደብደብ ህገ መንግስታዊ መብቱን መጻረር ነው ፡፡ እንዲሁም በአንቀፅ 28/1 መሰረት ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ መውሰድ ይቅርታም ሆነ ምህረትን የማያሰጥ ሲሆን፣ ክሱም በይርጋ የማይታገድ መሆኑን ፤ የሞት ቅጣት ቢፈረድበት እንኳን አጥፊው ርእሰ ብሄሩ ወደ እድሜ ልክ ብቻ ዝቅ ከማድረግ ውጪ ይቅርታም ሆነ ምህረትን ማድረግ እንደማይችልም በ28/2 ተደንግጓል፡፡
በህገ መንግስቱ ስለ አስፈጻሚው አካል በሚደነግግበት አንቀፅ 51 ንኡስ አንቀጽ 14 መሰረት ‹‹ከክልል አቅም በላይ የፀጥታ መደፍረስ ሲያጋጥም በክልሉ መስተዳድር ጥያቄ መሰረት የመከላከያ ሃይሉን ያሰማራል›› ይላል በህገ መንግስቱ መሰረት ፌደራል መንግስቱ ወደ አንድ ክልል ጣልቃ ገብ ሆኖ ሊገባ የሚችለው አንድም ክልሉ ራሱ ሲጠይቅ ወይንም ደግሞ በአንቀፅ 62 / 9 መሰረት ‹‹ማንኛውም ክልል ህገ መንግስቱን በመጣስ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፌደራሉ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ያዛል›› ይላል፤ ጣልቃ መግባት ማለት ምን ማለት ነው ፣በምንስ መንገድ ነው ጣልቃ ገብነቱ የሚለውን ህገ መንግስቱ አያብራራውም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስለ ፌዴሬሽ ምክር ቤት ስልጣን ሲዘረዝር አንቀፅ 62 ንኡስ አንቀጽ 6 መሰረት ፣‹‹በክልሎች መካከል ለሚነሱ አለመግባባቶች መፍትሄ ይፈልጋል›› ይላል፡፡
በህገ-መንግስቱ በአንቀፅ 77/ 9 መሰረት የሚኒስትሮች ም/ቤት ‹‹ህግና ስርአት መከበሩን ያረጋግጣል›› አስፈጻሚው አካል ይህ ሃላፊነት ተጥሎበታል፡፡‹‹ህግና ስርአትን የማያከብር የመንጋ ፖለቲካ ኢትዮጲያ ውስጥ መቆም ይርበታል…በመንጋ በሚሰጥ ፍርድ የፍትህ ስርአቱን በግል ስሜት መንዳት የለብንም… ህግ አልባና አመፅ የሚታገስ ስርአት እንደ አገር መቆጠራችንን ከንቱ ስለሚያደርግ አገራዊ አንድነታችንን በህግ አግባብ ማስጠበቅ የዘወትር ተልእኳችን ይሆናል…የህግ የበላይነት ህዝቦችን በጋራ የሚያስተሳስር መሰረት መሆኑን፣…መንግስት የህግ የበላይነትን ለመጣስ እየታዩ ያሉትን አዝማሚያዎችን እንደማይታገስ›› ተናግረዋል ፡ በሱማሌ ክልል የተነሳውን አይነት ሁከት በጋምቤላ ክልል ሊደገም እንደነበረና መከላከያ ሰራዊቱ እንዳከሸፈው ጠ/ሚር ዶ/ር አቢይ አህመድ የመከላከያ መኮንኖችን ሲመርቁ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በተከሰተው ግጭት የፌደራል መንግስቱ በፍጥነት ያልገባና የማረጋጋትንና ዜጎችን የመጠበቅ ስራንና እርዳታን በቶሎ የማድረስ በቶሎ ያልሰራ ሲሆን እንደ ቀብሪደሃር ባሉ ከተሞች ዜጎች ለከፋ አደጋ ሲጋለጡ ምግብና ውሃ በማጣት ለቀናት ማንም ሊደርስላቸው አለመቻሉ መንግስትን አስተችቷል ‹‹ሄሊኮፕተር የለም እንዴ›› ብለው አንዳንድ ዜጎች ጠይቀዋል ፡፡ በተጨማሪ በክልሉ የተነሳው ያልተጠበቀ ረብሻ በዶ/ር አብይ ለሚመራው የፌደራል መንግስት የመጀመሪያው ፈተና ሆኗል፡፡

Tuesday, July 3, 2018

liberalisation & privatization in Ethiopia, ethiopian airlines ወደ ግል ከመዛወሩ በፊት የኤርፖርቶች ድርጅት ከኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ መለያየት አለበት


በደፈናው የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ማዛወር የሚያስከትለው ችግር
ጸሃፊው ስሜነህ ተረፈ
ኢ -ሜይል smofed@gmail.com ወይም
መንግስት በቅርቡ ትላልቅ የመንግስት የልማት ድርቶችን ወደ ግል ለማዛወር መወሰኑ ተሰምቷል ፤ ይህ የፕራይቬታይዜሽን ሂደት መምጣቱ እሰየው ቢሆንም ነገር ግን መንግስት ሊጠነቀቅና ሊያጠናቸው የሚያስፈልጉ ጉዳዮች አሉ ከእነኚህም አንዱ በ2009 ዓ.ም በወጣው የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ / 406 ፤ 2009 ዓ.ም መሰረት በተደራጀው የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ በስሩ የኤርፖርቶች ድርጅትንና እንዲሁም ርካሽ የሰው ሃይልን በመጠቀም በሃገር ውስጥ የአውሮፕላን የተለያዩ አካላትን መፈብረክና መጠገን ለቦይንግና ለኤርባስ ለሌሎችም ኩባንያዎች የምርት አካላት መገጣጠሚያ ማእከልን በባለቤትነት መያዝን የሚያጠቃልል ነው ፤ ኤርፖርቶችን መገንባትና መጠገን፤እንዲሁም ኤሮኒተካል አገልግሎቶችንና ኤሮኖቲካል ያልሆኑ አገልግሎቶችን መስጠት ለኤር ኦፕሬተሮች የሚሰጡ አገልግሎቶችን መስጠት፤ የአቪየሽን ባለሙያዎችን ማሰልጠንን ቀድሞ በኤርፖርቶች ድርጅት እና በሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ይሰሩ የነበሩ ስራዎች ሁሉ ለአየር መንገድ ግሩፕ ተሰጥተዋል በዚህ ደንብ መሰረት የግሩፑ የተከፈለ ካፒታል 31.2 ቢሊየን በር ሲሆን የተፈቀደው ካፒታል ደግሞ 100 ቢሊየን መሆኑ ተገልጧል፡፡
 በመጀመሪያ የኢትዮጲያ አየር መንገድ የአየር ትራንስፖርት ሰጪ ድርጅት እንደመሆኑና ኤርፖርቶችን ማስተዳደርና መገንባት፤ ማስፋፋት፤መጠገን ፤ የአየር ትራፊክን መቆጣጠር እና የአውሮፕላን አካላትን መገጣጠም ስራ በሃገር ውስጥ መሰራት መጀመሩ መልካም ቢሆንም ራሱን የቻለ ድርጅት ሆኖ መቋቋም የነበረበት ነው እንጂ የአየር ትራንስፖርትን አገልግሎት የሚሰጠው አየር መንገድ እዚህ ውስጥ መግባት አልነበረበትም ፡፡ የምእራቡ ዓለም ታላላቅ ኩባንያዎች ኮር ቢዝነስ (Core Business) ማለትም የኩባንያው ዋነኛ ስራውና ዋናው የገቢ ምንጩ ከሆነውና በርካታ ባለሙያዎችና ልምድ፤ እውቀት ካለው ዘርፍ ማለትም የማጓጓዝ አገልግሎት ዘርፍ መውጣት አልነበረበትም ፡፡ ከዋናው ቢዝነስ የሚወጡ ኩባንያዎች የእነሱ ዋነኛ ሙያ ወዳልሆነው ዘርፍ በሚቀላቀሉበት ወቅት ለከፍተኛ ወጪና ኪሳራ የሚዳረጉ ሲሆን ዋናው ስራቸው ያልሆኑትን በማራገፍ ወደ ዋናው ስራቸው ሲመለሱ ተስተውሏል ፤ ዘርፉ ውድድር ያለበት እንደመሆኑ ትኩረቱ መሆን ያለበት በትራንስፖርት ዘርፍ ነው ፤ በዚህ ደንብ መሰረት አየር መንገዱ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ መሰማራቱና በሌሎች አየር መንገዶች ድርሻ መግዛቱ፤ቦንድ መሸጡ ያጠናክረዋል ከዚህ ውጭ ግን የሁለቱን ድርጅቶችን የስራ ድርሻን መጠቅለሉ ግን ተገቢ አይደለም ፡፡
በ2009 ዓ.ም በወጣው አዋጅ መሰረት ግን እነዚህን 3 የተለያዩ ድርጅቶች ይሰሩት የነበረውን ስራ የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ የሚል ስያሜ ከተሰጠው ድርጅት ጋር አለአግባብ የተቀላቀሉ ሲሆን የአየር ክልል ተቆጣጣሪ የሆነውን እንዲሁም ኤርፖርቶችን ከኤርፖርቶች ድርጅት ተከራይቶ የሚጠቀመው የኢትዮጲያ አየር መንገድን ከኤርፖርቶች ድርጅት ጋር ተቀላቅሏል ፡፡ ነገር ግን የኤርፖርቶ ድርጅት ኤርፖርቶችንና ተርሚናሎችን የሚሰራ ፤ የሚጠግንና የአየር ማረፊያ ሜዳዎችን ለአየር መንገዶች በማከራየት በርካታ ቢሊየን ብሮችን በየአመቱ ለመንግስት ገቢ የሚያደርግ ነው፡፡ ድርጅቱ የኮቴ በማስከፈል ገቢን የሚያኝ ሲሆን ፤ ከዚህም በተጨማሪ ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡና የሚወጡትን ደህንነትን መቆጣጠር ፤ መፈተሽ የመሳሰሉትን የደህንነት ስራዎችን የሚሰራ ነው ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአየር ማረፊያ ግቢ ውስጥ ያሉ ሱቆችን ቢሮዎችንና የመኪና ማቆሚያዎችን በማከራየት እንዲሁ ለመንግስት ገቢን የሚያስገባ ሲሆን ሲጀመር ከኢትዮጲያ አየር መንገድ የተለየ በመሆኑ ከአየር መንገዱ ጋር መቀላቀል አልነበረበትም ፤ አየር መንገዱን ለማሳደግ ከተፈለገ እንኳን አሁን እንደወጣው ፖሊሲ የተወሰነ ድርሻን ወደ ግል ባለሃብቶች ማዛወር እንጂ መቼም ቢሆን የአገሪቷ ንብረት የሆኑትን ኤርፖርቶችን በማቀላቀል መሆን አልነበረበትም፡፡ ይህ የተለያየ አደረጃጀት ስራውንም የተለያየ በመሆኑ ሲሆን በቅርቡ በወጣው አዋጅ ግን ተቀላቅለዋል ውህደቱ በተፈጸመበት ወቅት የኢትዮጲያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ እንደገለፁት ይህ ውህደት ወደ ኢትዮጲያ አቪየሽን ግሩፕ ወደ ሚባል የአቪየሽን መስሪያ ቤትንም ጨምሮ አንድ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን የእነኚህ 3 ወሳኝ የሆኑ ነገር ግን የተለያየ ስራን የሚሰሩ ድርጅቶችን ከተዋሃዱ በኋላ የአየር ደህንነትንና የአውሮፕላኖችን አስተማማኝነትን የፓይለቶችን የሙያ ፈቃድ የሚሰጠው፤ የሚፈትሸውና ፈቃድን የሚሰጠው የሚቆጣጠረው የአቪየሽን መስሪያ ቤትና ስትራቴጂያዊ የሆኑትን የአውሮፕላን ማሳረፊያ ሜዳዎችን በንብረትነት የያዘው ተቋምን የኤርፖርቶች ድርጅትን ጨምሮ ወደ ግል ማዛወር ከሃገሪቱን ደህንነት ጭምር አደጋ ውስጥ የሚከት ነው ፤እንኳን ለውጭ ባለሃብት ቀርቶ ለሃገር ውስጥ ባለሃብትም እሚሰጥ አይደለም ፡፡ ኢትዮጲያ አየር መንገድን ከአውሮፕላኖቹና ከቁሳቁሶቹ ጋር ብቻ በመለየት ወደ ግል ማዛወር የሚቻል ሲሆን ወደ ግል የማዛወር ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት በመላ ሃገሪቱ በርካታ የአውሮፕላን ማረፊያ ሜዳ ባለቤት የሆነው የኤርፖርቶች ድርጅት ተለይቶ መውጣት አለበት ፡፡   
አየር መንገዱ ወደ ግል ይዛወራል መባሉ አየር መንገዱን ያተጋው ይመስላል ፤ በዚህም መሰረት ፤ለረጅም ግዜ ያስራ ተቀምጠው የነበሩ በሞተር ችግር የማይሰሩ ሞተሮችን ማስነሳትና ወደ ስራ እንዲጀመር ማድረጉ ተዘግቧል ፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው ‹‹የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሮልስ ሮይስ ሞተሮች የተገጣጠሙላቸው አራት ቦይንግ 787-8 አውሮፕላኖች ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ ቆመው የነበሩ ቢሆንም፣ ከሞተር አምራቹ ኩባንያ ጋር በመነጋገር ሞተሮቹ እየተጠገኑ አውሮፕላኖቹ ወደ ሥራ በመመለስ ላይ እንዳሉ ሲገለፅ አየር መንገዱ ለቆሙት አውሮፕላኖች ካሳ እየተከፈለው መሆኑን ገልጿል››፡፡ የሁለቱ ድርጅቶች መቀላቀል ለሙስና ሰፊ በርን የከፈተ መሆኑ፤የር መንገዱ ግልጽ ባልሆነ መንገድ የገዛቸውን አውሮፕላኖችን መልሶ መሸጡ እንደገና መልሶ የሸጣቸውን አውሮፕላኖችን እንደሚከራይ ፤ የሰራተኛ አያያዙ ችግር እንዳለበት፤ እንዲሁም የስራ ቅጥርና ዝውውርን በተመለከተ የዘመዳማቾች ቤት ነው ተብሎ በሰፊው የሚተች ተቋም መሆኑ ይታወቃል ፡፡ 
የኢትዮጲያ መብራት ሃይል ቢሆን ባለፈው አመት ብቻ 128 ሚሊዮን ዶላር ለሃገሪቱ ያስገባ ሲሆን ይኀው ለጎረቤት ሃገራት መብራትን መሸጥ አትራፊና የውጭ ምንዛሬን የሚያስገኝ ሲሆን በሃገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ስርጭትንና ማከፋፈልን ለማሻሻል ሲሆን የሃገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሃብቶች ቢገቡበት የአገልግሎት አሰጣጡን የሚያሻሽለው ሲሆን ነገር ግን ወደ ውጭ የሚላከውና ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬን የሚያስገኘው ዘርፍ ግን በመንግስት እጅ ሆኖ ቢቆይ የሚያስገኘው ጠቀሜታ መታየት አለበት፡፡ በእርግጥ ሃይልን በማሰራጨትና በማከፋፈል ላይ በግል ባለሃብቶች መግባታቸው እንደ ኢትዮጲያ ላለ ትልቅ ሃገር አስፈላጊ መሆኑን ጠ/ሚሩ ገልፀዋል፡፡ የተመረተ ሃይል እያለ ነገር ግን በስርጭትና በማከፋፈል ሂደት ሃይል በተደጋጋሚ እየተቆራረጠ መሆኑና በኢኮኖሚው ላይ በተለይም በማምረትና በከተሞች አካባቢ በአገልግሎት ዘርፍ ላይ ጉዳትን እያደረሰ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ማንኛውም ሰው እንደሚገምተው የግል ባለሃብቶች  በመብራት ማከፋፈልም ሆነ ማሰራጨት ዘርፍ ሲሰማሩ አሁን ያለው ርካሽ የሃይል አቅርቦት አይኖርም ነገር ግን የሃይል መቆራረጡ ይቀንሳል ዋጋ ግን ወደድ ይላል ይህን ለህብረተሰቤ ግልፅ በማድረግ ይጠበቃል፤ በርካታ ትላልቅ የመንግስት ድርጅቶች ወደ ግል ወደ የተዛወሩባቸው ሃገራት የዋጋ መጨመር በስፋት ታይቷል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ቀድሞ የመገናኛናት ትራንስፖርት ሚ/ር ጋር የተቀላቀለና በከተማው ውስጥ ያሉ የመንግስት ህንጻዎችንና ሰፋፊ መሬቶችን የያዘ ስለሆነ እነኚህን የሃገር ንብረቶችን ከቴሌኮሙ ቁሳቁሶች መለየትና ቴሌን ከነቁሳቁሱ ማዛወርና የሃገር ሃብት የሆኑት ህንጻዎችን ግን ወደ መንግስት ንብረትነት መቀላቀል ያስፈልጋል ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም የድርጅቶቹን ሃብትና እዳ መግለጫ ለማዘጋጀት እንዲሁም በትክክል ድርጅቶቹ በገበያው ምን ያህል እንደሚያወጡ ‹ማርኬት ካፒታላይዜሽን› ምን ያህል እንደሆነ በገለልተኛ ኦዲተሮች ማዘጋጀት ራሱ እስከ አንድ አመት ድረስ ሊፈጅ የሚችል ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ወደ ግል የማዛወሩ ሂደት ለግዜው የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለማቃለልና የገንዘብ እጥረትን ለማቃለል ቢረዳም ውሎ አድሮ ግን በሚገኘው ገቢ ሌላ አቅምን የሚፈጥር እንዲሆን ማድረግ ያሻል፡፡

dr abey change in Eprdf, ethiopia



‹‹በለውጥባቡሩያልተሳፈረኢህአዴግ ፤ የኢህአዴግአባልነኝማለትአይችልም››
ዶ/ር አቢይአህመድ
እስካሁን ድረስ ለውጡን በጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣትንተከትሎምበርካታበጎየለውጥጅምሮችንእያየንሲሆንለሃገሪቱናበተስፋመቁረጥውስጥበመሆንስደትንየሙጥኝብሎለነበረውለአዲሱትውልድተስፋንየሚያጭርነው፡፡በርካታነባርአመራሮችበትግሉዘመንጭምርየነበሩስልጣንበቃኝእያሉመሰናበታቸውይበልየሚያሰኝሲሆንከደህንነቱምከመከላከያውናእንዲሁምከፓርቲውጭምርጉምቱዎቹናበህዝብዘንድተወዳጅያልነበሩቱናበሙስናዋነኛተጠርጣሪየነበሩወንበሩንትተናልማለታቸውለብዙሃኑየሃገሬሰውመልካምዜናነው ምራትየለማቲምየሚባለውናኦህዴድውስጥየተፈጠረውቡድንበድፍረትወደመድረኩበመምጣትለውጡንየመራሲሆንብአዴንምየኦህዴድንያህልአይሁንበአማራክልልፕሬዝደንትበገዱአንዳርጋቸውየሚመራውብአዴንቡድንምበክልሉህዝብዘንድድጋፍንያገኘሲሆንየለውጡንአስፈላጊነትየተረዳሲሆንደህዴንምውሎአድሮየለውጥሂደቱንመቀላቀሉአይቀርም ፡፡ለውጡንመደገፋቸውበጥርጣሬሲታዩየነበሩትና ፤ከለውጡባቡርእየተንጠባጠቡያሉትየቀድሞአመራሮችመካከልየደኢህዴንዋና ሊ/መንበርየነበሩትአቶሽፈራውሽጉጤናምክትላቸውከሊቀመንበርነታቸውመልቀቃቸውለዚህጠቋሚነው ፡፡በአንጻሩመጀመሪያበመሪነትኦህዴድቀጥሎምበድፍረትየለውጡአካልሆነውሆነውተገኝተዋልየብአዴንአመራሮችበባህርዳሩህዝባዊሰልፍያደረጉትንግግርለዚህማሳያነው ፡፡
አቶ ለማ መገርሳ ‹‹የለውጡን ሂደት በመደገፍ የኢትዮጲያን ህዳሴ እናስቀጥል ›› ሲሉ በህወሃት በኩል  ግን እስካሁን ድረስ የለውጡ አካል ነኝ ሲል አልተሰማም ፡ አመራሮቹም ሆነ ሚዲያዎቹ ለውጠን እንደግፋለንሲሉ አልተሰማም ይህ ነገር በጤና ነው ወይ ብለው አንዳንድ ሰዎች ይጥይቃሉ ፡፡ ህወሃት ቀድሞም ሁሉም ካልተሰጠኝ በሚል አኩራነቱ የሚታወቅ ድርጅት ሲሆን በአቶ መለስም ዘመን ቢሆን በፌደራል መንግስቱ ለድርጅቴ ተገቢው ስልጣን ውክልና አልተሰጠውም በሚል ተወካይ ላኩ ሲባል ተወካይ አልክም በማለት አቶ መለስንም ጭንቅላታቸውን ሲያዞር የነበረ ድርጅት ነው ፡፡ አንዳንድ የቀድሞ የፌደራል አመራሮችም የቀድሞውን የኢንሳ ስራ አስኪያጅ የነበሩት ዶ/ር ተክለብርሃን ጭምር በዶ/ ር አቢይ የለውጥ እንቅስቃሴ ጥርጣያቸውን በሚዲያ ሲገልፁ ተሰምቷል፡፡
ይህ ጉዳይ ማለትም ኢኤንንና ቲቪ ትግራይ ያሉ ሚዲያዎች የሰኔ 16ቱን ድጋፍ ሰልፍ አለመዘገባቸው ኢኤንን የተባለውን ቲቪ ጣቢያ እስከመዘጋት ያደረሰ ከባድ ዋጋን አስከፍሏል፡፡ የህወሃት የለውጡን ከልብ አለመደገፍ አንድም ከፌደራል መንግስቱ ጉዳዮች ራሱን እያገለለ እንዲሄድ ሲያደርግ ደኢህዴን ጭምር አመራሮቹን በመለወጥ የለውጥ ሂደቱ ተሳታፊ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ወይ እንደሌሎቹ የአመራር ለውጥ ማድረግ አለበት ፤ አለበለዝያ ግን ከፌደራል መንግስቱ የተለየ አቋምን መያዝ በረጅም ግዜ ለድርጅቱ አዋጭ መሆኑ አጠራጣሪ ነው ፡፡ 
በጠቅላይሚኒስትሩአበረታችየለውጥእንቅስቃሴበመነሳትከወደአሜሪካወደኢትዮጲያየውጭምንዛሬእንዳይገባ ሲደረግ የነበረው ዘመቻ መቆሙ በዜና ማሰራጫዎችተሰምቷል፡፡ ከዚህም በላይእነዳንኤልብርሃነናአላመራውየተባለውየኢኤንኤንጋዜጠኛውድሮስግንቦት 7 ጥይትተኩሶያውቃልእንዴ?››ቢሉምግንቦት 7 የትጥቅትግሉንማቆሙንምአስታውቋል ፡፡በውጭያሉኢትዮጲያውያንም‹‹ለዛፉናለግድግዳውእስኪገርመውድረስ››በተቃውሞሲናወጡየነበሩኢምባሲዎችደጃፎችአሁንበድጋፍሰልፍተጨናንቀዋል፡፡በባህርዳርየተካሄደውደማቅናታላቅህዝባዊሰልፍለጠ/ሚሩናለለውጥሃይሎችከፍተኛየሞራልስንቅእንደሚሆንይጠበቃል ፡፡ጠ/ሚሩከወጣቱዘንድያገኙትድጋፍከፍተኛሲሆንበአመፅተወጥሮለነበረውኢህአዴግምጭምርየመተንፈሻግዜንሰጥቶታል፡፡ይህንንፋታገዢውፓርቲውስጥያሉለውጥንየማይፈልጉሃይላትመልሰውእሚጠናከሩበትናከእጃቸውየወጣውንስልጣንበመልሰውበማስገባትእሚነሳሳሱበትናጊዜየሚገዙበትእንዳይሆንከጠ/ሚሩናበዙሪያቸውካሉቅንአመራሮችመዘናጋትንማስወገድያሻል፡፡
ነገርግንይህንለውጥወደኋላእንዳይመለስናእንዲቀጥልየሚፈልገውህዝብእጅግብዙሲሆንጠቅላይሚኒስትሩምወደኋላእንዳይመለስየማድረግተግባርይጠብቃቸዋል፡፡በቅርቡበአፋርሰመራተገኝተውባደረጉትንግግር‹‹የጀመርነውንነገርወደኋላየሚቀለብንስማንኛውምነገርለመሸከምዝግጁአይደለንም፤ ኢህአዴግውስጥለውጥመጥቷል፤ ተሃድሶመጥቷል ፤ 90  በመቶበላይአባልየለውጥጉዞውስጥገብቶየገባነውንቃልለመተግበርህዝባችንንይቅርታጠይቀን ፤ መካስአለብንበሚልእየተንቀሳቀስንነው…ቀድሞየነበረውጭንቀትእንዳይመለስየሚከፈለውዋጋይከፈላል…..የኢትዮጲያህልውናአደጋውስጥየሚያስገባሰላምየሚያሳጣንናጭንቀትውስጥየሚከተንሰላምየሚነሳንናእናቶችልጆቻቸውወጥተውቤትእስከሚገቡድረስእሚጨነቁባትኢትዮጲያዳግምእንዳትመለስዋጋይከፈላል፤ ጠንክረንእንወጣለንብለንተስፋእናደርጋለን››ሲሉእንዲሁም‹‹በለውጥባቡሩያልተሳፈረየኢህአዴግአባልነኝማለትአይችልም….90 በመቶየሚሆነውየኢህአዴግአባልምበለውጡባቡርየተሳፈረመሆኑን››አረጋግጠዋል ም/ጠ/ሚርደመቀመኮንንበበኩላቸውበባህርዳሩሰልፍላይሲናገሩለውጡ‹‹ወደኋላመመለስንሳይሆንማዝገምንአይታገስም…ለውጡበማይቀለበስበትደረጃደርሷልበፍጥነትእንስተካከላለን››ብለዋል፡፡
ይሁንናሁሉምየኢህአዴግአባላቶችበተለይምበቀደመውዘመንያሻቸውንያደርጉ ፤ እንዲሁምተጠቃሚየነበሩናበሙስናውየተነካኩቱበቀላሉየአዲሱን ጠ/ሚ/ር አስተዳደርይቀበላሉማለትአስቸጋሪነው ፡፡ጠ/ሚሩበርካታፈተናዎችንመወጣትየሚጠብቃቸውሲሆንድርጅታቸውአባላትይህንንየለውጥሂደትየማይደግፉትከሆነስራቸውንያከብድባቸዋልለምሳሌበየአካባቢውበተፈጠረግጭትየተፈናቀሉኢትዮጲያውንበሚሊዮንየሚቆጠሩመሆናቸውንየዓለምዓቀፍናየሃገራችንየሰብአዊተቆርቋሪድርጅቶችበሃገርውስጥበርካታዜጎቻቸውከተፈናቀሉባቸውየኣለምሃገራትአንዷሃገራችንመሆኗንአስታውቀውሚዲያዎችምይህንንበሰፊውዘግበዋል፡፡ ዶ/ር አቢይከተመረጡወዲህኢህአዴግሁለተኛዙርድርጅታዊማጥራትየሚጠብቀውይመስላል፤ በዚህምለውጡንያልደገፉትተለይተውየሚታወቁበትይሆናል፡፡
ለውጡየሰዎችናየአመራሮችብቻሳይሆንየህግጋትማሻሻያናለውጦችንይጨምራል ፤ ይሁንናግንአሁንምድረስመለቀቅየነበረባውሰዎችእንዳልተለቀቁ፤ እንዲሁምበቂሊንጦናበሌሎችማረሚያቤትየሚገኙእስረኞችበቃሊቲእስርቤትውስጥጨምሮከፍተኛድብደባእንደተፈፀመባቸውእንደሚገኙኢቢሲንጨምሮየተለያዩሚዲያዎችእየዘገቡየሚገኙሲሆንይህየፍትህስርአትበፍጥነትመስተካከልእንዳለበትናየህግማሻሻያዎችንጨምሮበተለይምአፋኝየሆኑትየሸብርህጉናየመንግስታዊያልሆኑድርጅቶች ፤ የፕሬስህጉበፍጥነትእንዲሻሻሉናየፍትህስርአቱመልሶ እንዲዋቀርየሰብአዊመብትድርጅቶችእየጎተጎቱሲሆንየህግንክፍተትእያወቁበመጠቀምየቀደሙትአስተዳሮችአገዛዛችንንያጠነክርልናልቢሉምጭራሽበመንግስትላይያለውአመኔታእንዲሸረሽርበማድረግስርአቶቹንአዳክሟልእንጂውሎአድሮአልጠቀማቸውም ፡፡የእነኚህህጎችመሻሻልየተሰደዱጋዜጠኞችወደሃገርቤትእንዲመለሱ፤ እናየሰብአዊመብትእንዲከበርበእጅጉየሚረዳስለሆነ ጠ/ሚሩህጎቹንለማሻሻልቅድሚያመስጠትይገባቸዋል፡፡ጠ/ሚሩለፍትህስርአቱየሚያሻሽልአንድኮሚሽንመቋቋሙናስራመጀመሩየተገለፀሲሆንጉዳዩግንፍጥነትንየሚጠይቅበመሆኑቅድሚያየሚሰጣቸውንህግጋትንበቶሎማሻሻልእንደሚገባየሰብዓዊመብትድርጅቶችእያሳሰቡይገኛሉ ፡፡ አስገራሚውነገርኢህአዴግምሆነደርግክፉኛየሚተቿቸውንጉሰነገስቱያወጧቸውንህግጋትከዋነውየወንጀለኛመቅጫህጉንከማሻሻልበስተቀርክፍተቶችያሉበትንየወንጀለኛመቅጫስነስርአትህጉንሳያሻሽሉሲሰሩባቸውየቆዩናአሁንምእየተሰራበትያለውየፍትሃብሄርህጉናየወንጀለኛመቅጫየስነስርአትህግጋትተጠቃሾችናቸው፤ እንዲሁምአስፈላጊናአንገብጋቢየሆኑህግጋትምሳይወጡሰፊየህግክፍተትበመፈጠሩምክንያትለሙስናናለመልካምአስተዳደርመታጣትመንስኤሆኗል፡፡የህግማሻሻያዎችንማድረግይዋልይደርየማይባልናጠ/ሚሩበህግተመስርተውእንዲሰሩናየህዝብንጥያቄበተለይምየመልካምአስተዳደርችግርንበቶሎእንዲመልሱ ፤እንዲሁምለውጥንየሚቃወሙየውስጥሃይሎችንበተግባርለማሳመንናተጨማሪየህዝብድጋፍንለማግኘትያስችላቸዋል ፡፡
ራሳቸው ዶ/ር አቢይለፓርላማውባቀረቡትሪፖርትመሰረት ‹‹የማሰርእንጂ፤የመፍታትህግየለንም›› ሲሉእውነቱንተናግረዋል ፤ በወንጀለኛመቅጫህጉመሰረትአንድሰውከተፈረደበትወንጀልነጻሆኖቢገኝእንኳንያላጠፋውንጥፋትጥፋተኛነኝብሎይቅርታጠይቆሊፈታይችልይሆናልእንጂቅጣቱንሳይጨርስከእስርቤትሊወጣአይችልም፤ የዳኝነትስርአቱየዳኝነትክለሳየማያደርግናበስህተትየተሰጠንፍርድደግሞየሚያይበትአሰራርየሌለውመሆኑነው ፡፡
ከዚህበመነሳትአፋኝየሆኑህግጋት ፤ እንዲሁምበአጠቃላይየፍትህስርአቱበጃንሆይግዜ በ50ዎቹ ከወጣውናበርካታክፍተቶችካሉበትከወንጀለኛመቅጫስነስርአቱጀምሮከዛሬነገይሻላልቢባልምበአቶሃይለማርያምግዜይሻሻላልቢባልምሳይሻሻልቆይቷል፤ የንግድህጉምበንግድምክርቤቶችይሻሻላልበሚልበጉጉትይጠበቅየነበረቢሆንምሳይሻሻልቀርቷልየፍትህስርአቱበህግክፍተትብቻሳይሆንእስከማረሚያቤትየእስረኞችአያያዝ ፤ የአቃቤህግክስአመሰራረት ፤ ይቅርታናምህረትአሰጣጥናበህግአተረጓጎምድረስሰፊየህግክፍተትእንዲፈጠርያደረጉትእነኚሑየወንጀለኛመቅጫየስነስርአትህግ፤የሽብርህጉናሌሎችምየተዛቡህግጋትመሆናቸውንበርካታየህግባለሙያዎችእየተናገሩይገኛሉ ፡፡ የምህረትአዋጅበፍጥነትመፅደቁመልካምሲሆንነገርግንበህብረተሰቡከዛሬነገይሻሻላሉበሚልየሚጠበቁትንከላይየተጠቀሱትንጊዜሳይሰጡማሻሻልተገቢነው፡፡