Tuesday, August 21, 2018

አክቲቪዝምና የሃገራችን የደቦ ፖለቲካ ውጥንቅጥ



ፀሃፊው ስሜነህ ተረፈ
ኢ-ሜይል smofed@hotmail.com or
smofed@gmail.com
የመብት ተሟጋችነት (አክቲቪዝም) ማለት ለአንድ የለውጥ አላማ መረጃ መስጠት፤ማንቃት ፤ማስተማር ህዝብን ማደራጀትና ማብቃት ማለት ሲሆን የመብት ተቆርቋዎች (Activist) ሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ናቸው እንጂ ወደ አመፅና ብጥብጥ አያመሩም ፣ የመብት መረገጥ ካለ አክቲቪዝም (Activism) ከተቃውሞ (resistance) ወይም ህዝባዊ እምቢ ባይነት (civil disobedience) ብሎም ወደ አስተዳደራዊ ፖለቲካ (administrative politics) እየዳበረ መሄድ አለበት ፡፡ከቀድሞዎቹ ትውልዶች በተለየ ሁኔታ የአሁኑ ትውልድ ምንም አይነት ጥይት ሳይተኩሱ አምባገነኖችን መታገል ብቻ ሳይሆን መጣልም እንደሚችል ይህ ለውጥ አመላካች ነው ፡፡ የሙዳየ ሃሳብ ተቋማት (think thank) ማለት ከዩንቨርስቲዎች የሚመነጭን ንድፈ ሃሳባዊ የሆነ እውቀትን ልክ አጣፍጠው ቀለል ባለ መልኩ የተግባር ሰዎች ለሆኑት ለፖለቲካና ቢዝነስ መሪዎች የሚያቀርቡ መለስተኛ የጥናት ተቋማት ናቸው ፤እንደ ጃዋር መሃመድ ያሉት ዋነኛ አክቲቪስት የነበሩት በውጭ የቆዩት የሃሳብ ማጥኛ ተቋማትን ለመክፈት ሃሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል ጃዋር መሃመድ በሙዳየ ሃሳብ ተቋማት የሚፈልቅን ሃሳብ ለአስፈጻሚው አካል የሚቀርብን ሃሳብ ‹‹አጤሪራ እንደማጉረስ ነው›› ሲል ይገልጸዋል ፡፡ አክቲቪዝም ወደ ሀሳብን ወደ ማበልፀግና ወደ ምርምር ተቋምነትና የፖለቲካ ሰዎች የሚመሩባቸውን አስተሳሰቦችን ወደማዳበር ደረጃ ማደግ አለበት እንጂ ወደ አመጸኝነትና ረብሻ ስርአት አልበኝነት (አናርኪ) ደረጃ መዝቀጥ የለበትም፡፡
በሶማሌ ክልል ‹‹ስልጣንህን ልቀቅ ተብያለሁ፣ስልጣኔን ከምለቅ ብሞት ይሻለኛል›› በሚል ጸረ-ዲሞክራሲዊ ስሜት አብዲ ኢሌ ወይም አብዲ መሃመድ ኡመር የተባሉት የክልሉ ፕሬዝዳንት የነበሩ ግለሰብ ያሰለጠኗቸው ሄጎ ሲባሉ ከቄሮ በተቃራኒ ሄጎዎች ለውጥን ለማደናቀፍ በሶማሌ ክልል የተደራጁ ሲሆን ‹‹ሄጎ›› የሚባሉት እነኒህ የወጣት ቡድኖች የሶማሊያን ሪፐብሊክን ሰንደቅ አላማ በመያዝ ‹‹አብዲ ኢሌ ለዘላለም ይኑር›› እያሉ መፈክርን እያሰሙ በሶማሌ ክልል ከተሞች በመዞር በከተሞች ውድመትና የሰው ህይወትን ማጥፋት ፈፅመዋል ፡፡ እንዲሁም በሻሸመኔ ጃዋር መሃመድን ለመቀበል በወጣው ሰልፍ ላይ 3 ሰዎች ሲሞቱ ወደ 71 ሰዎች ቆስለዋል ፤ ወደ መቀሌ ሊሻገር የነበረን እህል ከመኪና አውርዶ ለህዝብ ማከፋፈል ከወደ አማራ ክልል የተሰማ ሲሆን እንዲሁም በጎንደር ፣በባሌ፣በጣና በለስ፤በከፋ ሸካ ዞን -በቴፒ፣ በዶምቢዶሎ፣በደብረማርቆስ ወዘተ… የታየው ብጥብጥና ረብሻ ግን ከመስመር ያለፈ ነው ፤ በሱማሌ ክልል የጅቡቲ ዜጎች ላይ የደረሰው ጥቃት እንዲሁም በጅቡቲ ባሉ ኢትዮጲያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት አግባብነቱን የሳተና አክቲቪዝም ምን ላይ ነው መቆም ያለበት የሚለውን የሚሳስብ ነው ፡፡አንዳንዶች ይህ የምናየው የደቦ ፍርድ ‹‹በለውጥና ሽግግር ወቅት የሚያጋጥም ነገር ነው›› ሲሉ ሊያቃልሉት ይሞክራሉ ነገር ግን ‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› እንዲሉ አበው እንደ ቀይ ሽብር ዘመን ‹‹አስታጥቁን፣አታስጨርሱን›› ደረጃ ላይ ባይደርስም ‹‹ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም›› ብሎ በሱማሌ ክልል ከተፈጸመው ትምህርት በመውሰድ መፍትሄ መፈለግ ግን ያባት ነው ፡፡የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክንም ሃይ ባይ ያጡትን አንድ በሉልኝ ስትል ‹‹የመንግስት ትእግስት በዛ›› ስትል አሳስባለች፡፡
ይህ በሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት ተጠያቂነት አለመኖርን እንዲሁም መንግስት የላላ የፀጥታ አጠባበቅንና አንዳንዶች እንዲሁ መንግስት ጠንከር ካላለ ከዚህ የባሰ ይመጣል ብለው የሚሰጉ ወገኖች አሉ ‹‹ለቄሮ እናገራለሁ … ቄሮ ይቀጣችኋል›› የሚሉ አባባሎች ወጣቶች ያለ ተጠያቂነት የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ የሚል ሃላፊነት የጎደለው የተሳሳተ ስሜትን ፈጥሯል ፤ ይህም ወደ ሃገራችን ይመጣሉ የሚባሉትን የዋጋ ቅናሽ ተደርጎላቸው ወደ ሃገራቸው የዘመን መለወጫን እንዲያከብሩ የተጠሩትን ዲያስፖራና ቱሪስቶችን ቁጥር እንዲቀንስ የሚደርግ ነው ሲሉ ስጋታቸውን የባህልና ቱሪዝም ተቋማት አመራሮች እየገለፁ ናቸው ፡፡ዋነኛ አክቲቪስት የሆነው ጃዋር መሃመድ በበኩሉ ይህን በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለውን ወጣቱ በራሱ ስልጣን እየወሰደ ያለውን እርምጃ ማውገዝና ከህግና ከስርአት መውጣት እንደሌለበት በይፋ መናገር ይጠበቅበታል፡፡ጆርጅ በርናርድ ሾው እንተናገረው ‹‹ነጻነት ማለት ሃላፊነት ማለት ነው›› ነጻነት ዋጋ ተከፍሎበት እንደተገኘው ሁሉ ያለተጠያቂነት ዝም ብሎ የህግ የበላይነትን ቸል በማለት የሚከበር አይደለም፡፡   
በመልካም ጎኑ ስናየው አክቲቪዝም ለምሳሌ የባህር ዳር ወጣቶች ከመንግስት ጋር በተደረገው ግጭት ከተጎዱ ቤተሰቦች ከ17 በላይ ከሚሆኑ ባለሃብቶች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ መስጠታቸው በዜና ማሰራጫዎች ተነግሯል ፡፡ ይህ አክቲቪዝም መልካም ጎኑ ሲሆን ከዚህ ባለፈ ግን ወደ ግጭትና ረብሻ በሃገራችን በተለያዩ ክልሎች የምናያቸው ከመስመሩ የወጡና በተለይም ወጣቱ ራሱን ጆሮውን ለዚህ መስጠት የለበትም ፣ተከታይ ያፈራ አክቲቪስት በሃላፊነት ስሜት መረጃን የሚያስተላልፍ ካልሆነ አደጋን ያመጣል፡፡የዶ/ር አቢይ መንግስት በግልፅነት በሃገሪቱ የተፈጸሙትን ለምሳሌ የኢንጂነር ስመኝን ግድያ ፣ የሰኔ 16ቱን ቦንብ ውርወራ የመሳሰሉትን ለህዝብ ይፋ ማድረግና ማሳወቅ ይጠበቅበታል ፡፡ ፖለቲካ ላለማበላሸት በሚል፣የውስጥ ድርድርን በማድረግ የዚህን የመሳሰሉት ጉዳዮች ሲደበቁና ሲሸፋፈኑ በህዝብ ዘንድ ጥርጣሬን ፣ በወጣቱ ዘንድ ደግሞ በራሱ ህግን ለማስከበር ሲል የመሰለውን ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚህም ሌላ የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችንን መፈተሸና የአክቲቪዝምን ገደብና ድንበርን መለየት ያስፈልጋል ፤ ህብረተሰቡ የመጣለትን ለውጥ ለማረጋገጥ የየራሱን ድርሻ መወጣት አለበት፡፡በኢንተርኔት የተጻፈን ነገር ሁሉ እውነት ነው ብሎ መውሰድ ለጥፋት ሊዳርግ እንደሚችል ከሰሞኑ ያየናቸው ግርግሮች ምስክሮች ናቸው ፡፡ በምእራብ አገራትም ጭምር የጥላቻ ንግግሮች (hate speech) ክልክል ናቸው ፣ እንዲሁም የሚታወቁ እውነታዎችን መካድ፣አልተደረጉም ብሎ መከራከር ለምሳሌ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት አይሁዶችን ናዚዎች አልጨፈጨፏቸውም ብሎ የሆሎኮስትን (genocide) መካድ በራሱ በአውሮፓ አገራት ህግ በወንጀል ያስጠይቃል፣በሃገረ አሜሪካም ጥቁሮችን ወይም ሌላ ዘርን የሚያዋርድ ነገርን መናገር ወይም መጻፍ ያስጠይቃል ፡፡
ለዘመናት በጣም የታፈነ ጩኀት የነበረበት ሃገር እንደመሆኑ ፣ቀድሞ መጮህ ቢፈለግም መጮህ የማይቻልበት ዘመን ነበር አሁን ግን ህዝቡ ባደባባይ ስሜቱን መግለፅ ይችላል፡፡ባገሩ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ የኖረ በመሆኑ ምክንያት አሁን መተንፈሻ ያገኘው ህዝብ በተለይም ወጣቱ በገነፈለ ሁኔታ ስሜቱን እየገለፀ እንዳለ መረዳት ይቻላል፡፡ በሃገራችን ለውጥን በሰላማዊ መንገድ የመምራት ልምዱ የለንም ማለት ይቻላል፤ከዚህ ቀድሞ የደርግ መንግስት ከሃይለስላሴ ስልጣኑን ሲረከብ እርስ በእርስ ፍጅት የተካሄደ ሲሆን ኢህአዴግም ደርግን ሲተካ እንዲሁ ስልጣኑን እስከሚያጸና ድረስ ሃይልን ተጠቅሟል ፤ የአሁኑን ለየት የሚያደርገው ግን ጠ/ሚር ዶ/ር አቢይ ለስላሳ አቋምን በማሳየታቸው ምክንያት ስርአት አልበኝነቱ ሊንሰራፋ በቅቷል ፡፡የህግ የበላይነት ቀርቶ ሁሉም የፈለገውን አድርጎ ምህረት ይደረግልኛል የሚል ስሜት መኖር የለበትም ፡፡ ድምጻቸውን አጥፍተው የቆዩት ጠ/ሚሩ የመከላከያ ኮሌጅ ተመራቂዎችን ነሃሴ 12 ፣ 2010 ዓ.ም. ሲያስመርቅ እንደተናገሩት ‹‹የይቅርታው ዓላማ ባለፍንበት መንገድ ያጣነውን ለማግኘት ነው እንጂ የገነባነውን አገር ለማፍረስ አይደለም… ዘመናዊነት የህግ የበላይነትን ማክበር ነው›› ብለዋል፡፡
እነኚህ ረብሻዎች የሚያመለክቱን ሌላው ነገር ለውጡ መፍጠን እንዳለበት አመላካች ነው ፣ ለውጥ አደናቃፊዎች በዚህ ረብሻ የሚጠረጠሩትን ያህል ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ህዝቡ የሚጠብቀው ፈጠን ያለ ለውጥና መንግስት እየሄደ ያለበት የለውጥ ጉዞ ሂደት ያላረካቸው ወገኖች ትእግስት በማጣት ወደ ግርግር ሊያመሩ እንደሚችሉ መገመት ያሻል በተለይም ወጣት ስራ አጥነት በተንሰራፋበትና የንግድ መቀዛቀዝ እየተስተዋለ ባለበት ሁኔታ ፤ ፈጠን ያሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጦች፣ አጠቃላይ የፍትህ ስርአቱን ማሻሻል፣ ተዛማጅ ህጎችንና አዋጆችን መፈተሽ ፣ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርብባቸው የነበሩ አዋጆች መሻሻልና መተግበር አለባቸው ፣እንዲሁም ሹመት አሰጣጥ ላይ በቀደመው ዘመን በሙስናና በአቅም ማነስ ሲተቹ የነበሩትን ጠ/ሚሩ ስፍራ ሲያገኙላቸው ይታያል፤የአምባሳደርነት ሹመት አቅመ ቢስ ለሆኑ ባለስልጣናት ማገገሚያ መሆኑ ቅሬታን የፈጠረ ሲሆን በፓርላማ ደረጃም ተነስቶ ነበረ፤ ‹‹አዲስ ወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ›› እንዳይሆን የህዝብን የለውጥ ጥያቄን ሊያረካ በሚችል መንገድ አቅም ያላቸውን አዳዲስ አመራሮችን መሾም የሚበጅ ነው፣ በደቡብ ክልል በሸካና ከፋ ዞን የታየው ከለውጡም በኋላ አመራሩ ራሱን አለማስተካከሉ ችግሩን አባብሷል፡፡
የፌደራል መንግስቱ ምን ሲፈጠር ነው ጣልቃ የሚገባው ?
ምንም እንኳ የአንድ ክልል አስተዳደር ራሱን የሚያስተዳድር (ኦቶኖሚ) ቢሆንም ፣ በክልሉ ያለው የዳኝነት ነጻነት መከበር አለበት፤ የክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤም ይህን የሚያሟላ መሆን አለበት ፡፡ ነገር ግን የዳኝነት ስርአቱና ፖሊስ ህግና ስርአትን በክልሉ ማስከበር በማይችልበት ደረጃ በሚደርስበት ወቅት ፌደራል መንግስቱ ጣልቃ ሊገባ ይችላል፤ የፌደራል መንግስቱ ለክልሎች የበጀት ድጋፍን የሚያደርግ እንደመሆኑና ከዚህም በተጨማሪ ያገር ሉአላዊነትንና ደህንነትን የመጠበቅ ሃላፊነት ስላለበት በክልሎች የሚከናወን ህገ ወጥነትን በዝምታ ይመልከት አይባልም፡፡
በሱማሌ ክልል የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በተደጋጋሚ በህብረተሰቡ ዘንድ ይነሳ የነበረ ቢሆንም ፤ የነዳጅ ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት የተገኘበትና ለገበያ መቅረብ የጀመረበት ሲሆን ፣ክልሉ ላለፉት 27 አመታት ተገቢውን የልማት ስራ ያልተሰራበትና በሚገባው መጠን ያላደገ ሲሆን ፤ ሙስናም ተንሰራፍቶ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ሲደርስና የክልሉ ባለስልጣናት ባጀቱን ሲዘርፉት እንዲሁም የክልሉ ህዝብ ተጠቃሚ ሳይሆን የቀረበት ዘመን ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ የክልሉ ያገር ሽማግሌዎችም (ኡጋሶች) ጭምር እዚህ አዲስ አበባ በመገኘት ለጠ/ሚሩ ተደጋጋሚ ጥያቄውን ቢያቀርቡም ጥያቄያቸው ፈጣን ምላሽን ሊያገኝ አልቻለም፣በተደጋጋሚ ኢሳትን ጨምሮ በክልሉ ያለው የአብዲጊሌ አገዛዝ በክልሉ ኪራይ ብሳቢነትንና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣን ማድረጉን ሲገልፁ ቢቆይም ፣ እንዲሁም ሂዩማን ራይትስ ዎች በክልሉ ያለው የልዩ ሃይል እንዲበተን ቢጎተጉቱም ሰሚ ሳያገኙ ቆይተዋል፤ በሶማሊያ ወረራ እንኩዋን ያልተፈፀመ በደልና ውድመት ደርሷል፤ በዚህም ምክንያት ቀላል የማይባል ዋጋን አስከፍሏል ፡፡
ይህ ሁሉ ጥፋት ከጠፋ በኋላ የሶህዴፓ አመራር ባደረገው ግምገማ መሰረት ‹‹የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች፤ በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊና የዲሞክራያዊ መብቶችን ማፈን ፣ በህዝቦች መሃል ግጭቶችን በመፍጠር፣ ህዝብን ማፈናቀል ፣ የሃሰት መረጃዎችን አመራሩ በማሰራጨት የህዝብ ግጭት እንዲፈጠርና አለመረጋጋት እንዲፈጠር ማድረግ ፣ ሄጎ የተባሉ ወጣቶችን በማስታጠቅ በማስራጨትና በማስተማር በጅግጅጋ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞች እንዲሁም በህብረተሰቡና በተለያዩ የማህበራዊ ተቋማት ላይ ጥፋቶችን መፈጸም፣ ፍፁም ህገ መንግስትን በጣሰ መልኩ ሰዎችን ማሳሰርና ማሰር ፣ የዲሞክራሲን ማፈን ፣ ህዝቡን ማፈን ፣ ሁሉንም የመንግስት ተቋማትን ሽባ በማድረግ ፣ የጎሳ መሪዎችን በመንግስት መሾምና መሻር ፣ በሃሰት ማስረጃ ፣ መርህ አልባ ግንኙነትን በመፍጠር ፣የከፋ የኪራይ ሰብሳቢነትና ብልሹ አሰራር ፣ የመንግስትን ሃብት ማባከን ፣ ለጎሳ ለዘመድ ማከፋፈል ፣ ፕሮጀክቶችን ለወዳጅ መስጠት ፣ ንግድን በሞኖፖል መቆጣጠር ፣ ኮንትሮባንድ ንግድ ማካሄድ፣ የሴፍቲኔት ገንዘብን መከፋፈል፣ የአመራር መምከንንና ወደ ገዢ መደብነት መቀየር ፣ በግለሰብ አምባነናዊ አገዛዝ ስር መውደቅ ፣ የመንግስት ተቋማትን ወደ ግል ባለቤትነት መቀየር ፣በመንግስት ገንዘብ ህገ ወጥ ድርጅቶችንና የማፍያ ኔትርኮችን ማደራጀት፣ የሃሰት ሪፖርት ማሰራጨት፣ በከፋ የስነ ምግባር ችግር ፍፁም አድርባይትን በማንገስ ፣ ድብቅ የማፍያ ቡድኖች ተደራጅተውና ታጥቀው ፣ ስልጠናም ጭምር ወስዶ ነው ይህ የተደረገው›› ብለዋል፣ የክልሉን መንግስት ከላይ እስከታች እንደገና ማደራጀት ስራ እንደሚከናወን የገለፁት አቶ አህመድ ሽዴ፣ 3 ስራ አስፈጻሚና 5 ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን መታገዳቸውንና ፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ለፍርድ የማቅረቡ ሂደት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አክለዋል ፣ግምገማው ፍፁም ዲሞክራሲያዊና ግልፅ ነበረ ብለዋል፡፡ ጥያቄው ግን ይህ ሁሉ ሲሆን ፌደራል መንግስቱ በወቅቱ ለምን እርምጃ አልወሰደም የሚል ነው ፡፡
ከዚህ ሁሉ በኋላ ጣልቃ የገባውን የፌደራል መንግስቱን የሶማሌ ክልልን ራስን በራስ የማስተዳደር ስልጣኑን ደፍሯል የሚሉ አሉ - ነገር ግን የህግ ባለሙያዎች እንዳስታወቁት ከላይ የተጠቀሰው በሱማሌ ክልል የተፈፀመው ግዙፍ የሰብአዊ መብት ጥሰት ‹‹ግሮስ ሁውማን ራይት ቫዮሌሽን›› ነው በዚህ ሁኔታ ፌደራል መንግስቱ እጁን አጣጥፎ መቀመጥ እንደሌለበት የታወቀ ነው ፡፡ በክልሉ የተነሳው ረብሻ በክልሉ በሚኖሩ ዜጎች ቤትና ንብረት ላይ ዘረፋ ሲፈፀም ፤ በዚህ ብቻ ሳይወሰን በአብዲ ኢሌ የተመራው የክልሉ መንግስት እገነጥላለሁ በማለቱ ምክንያት የመከላከያ ሰራዊቱ ሊገባ ችሏል ተከትሎም ከሌላ ክልል የመጡ ብቻ ሳይሆን ጅቡቲዎችና ሱማሌዎች ጭምር የክልሉን ከተሞች በመልቀቅ ወደ ስደት ገብተዋል ፡፡
የክልሉን ፀጥታና ደህንነትን እንዲያስክብር ሃላፊነት የተጣለበት ራሱ የክልሉ ፖሊስና ልዩ ሃይል ጸጥታን ከማስከበር ይልቅ ራሱ ዝርፍያና ውድመት ውስጥ በመግባቱ የፌደራሉ ሃይል ጣልቃ ገብነት አስፈልጓል፡፡  በመጀመሪያ የፌደራል መንግስቱ ወደ አንድ ክልል ጣልቃ ሊገባ የሚችለው ምን ሲሆን ነው? የሚለውን መመልከት ያሻል፤ ሌላው ደግሞ ጣልቃ መግባት ማለት ምን ማለት ነው? የሚለው ሲታይ ወታደራዊ በሆነ መንገድ ነው ወይንስ ኢኮኖሚዊ ወይስ ሌላ ከሆነ በምን መንገድ ነው ጣልቃ መግባት ያለበት? የሚለው አነጋጋሪ ሊሆን ይችላል፤ ለምሳሌ በድሬዳዋ የተሰበሰቡ ተሰብሳቢዎች አብዲ ኢሌ በጀቱ ሊያዝበት ይገባል ሲሉ ባወጡት የአቋም መግለጫ ላይ አውጥተዋል፤በርካታ በክልሉ ነዋሪ የሆኑ ዜጎችም ከዚህ በኋላ በክልሉ ለመኖርና ለመስራት ምን ዋስትና አለን ሲሉ ጠይቀዋል ፡፡
ህገ መንግስቱ ምን ይላል ብለን ስንጠይቅ አንቀፅ 15 መሰረት ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው ፤ እንዲሁም ‹‹በህግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ህይወቱን አያጣም›› ይላል ስለዚህ አንድን ሰው ፀጉረ ልውጥ ነው በሚል ብቻ መግደል ወይም መደብደብ ህገ መንግስታዊ መብቱን መጻረር ነው ፡፡ እንዲሁም በአንቀፅ 28/1 መሰረት ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ መውሰድ ይቅርታም ሆነ ምህረትን የማያሰጥ ሲሆን፣ ክሱም በይርጋ የማይታገድ መሆኑን ፤ የሞት ቅጣት ቢፈረድበት እንኳን አጥፊው ርእሰ ብሄሩ ወደ እድሜ ልክ ብቻ ዝቅ ከማድረግ ውጪ ይቅርታም ሆነ ምህረትን ማድረግ እንደማይችልም በ28/2 ተደንግጓል፡፡
በህገ መንግስቱ ስለ አስፈጻሚው አካል በሚደነግግበት አንቀፅ 51 ንኡስ አንቀጽ 14 መሰረት ‹‹ከክልል አቅም በላይ የፀጥታ መደፍረስ ሲያጋጥም በክልሉ መስተዳድር ጥያቄ መሰረት የመከላከያ ሃይሉን ያሰማራል›› ይላል በህገ መንግስቱ መሰረት ፌደራል መንግስቱ ወደ አንድ ክልል ጣልቃ ገብ ሆኖ ሊገባ የሚችለው አንድም ክልሉ ራሱ ሲጠይቅ ወይንም ደግሞ በአንቀፅ 62 / 9 መሰረት ‹‹ማንኛውም ክልል ህገ መንግስቱን በመጣስ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፌደራሉ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ያዛል›› ይላል፤ ጣልቃ መግባት ማለት ምን ማለት ነው ፣በምንስ መንገድ ነው ጣልቃ ገብነቱ የሚለውን ህገ መንግስቱ አያብራራውም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስለ ፌዴሬሽ ምክር ቤት ስልጣን ሲዘረዝር አንቀፅ 62 ንኡስ አንቀጽ 6 መሰረት ፣‹‹በክልሎች መካከል ለሚነሱ አለመግባባቶች መፍትሄ ይፈልጋል›› ይላል፡፡
በህገ-መንግስቱ በአንቀፅ 77/ 9 መሰረት የሚኒስትሮች ም/ቤት ‹‹ህግና ስርአት መከበሩን ያረጋግጣል›› አስፈጻሚው አካል ይህ ሃላፊነት ተጥሎበታል፡፡‹‹ህግና ስርአትን የማያከብር የመንጋ ፖለቲካ ኢትዮጲያ ውስጥ መቆም ይርበታል…በመንጋ በሚሰጥ ፍርድ የፍትህ ስርአቱን በግል ስሜት መንዳት የለብንም… ህግ አልባና አመፅ የሚታገስ ስርአት እንደ አገር መቆጠራችንን ከንቱ ስለሚያደርግ አገራዊ አንድነታችንን በህግ አግባብ ማስጠበቅ የዘወትር ተልእኳችን ይሆናል…የህግ የበላይነት ህዝቦችን በጋራ የሚያስተሳስር መሰረት መሆኑን፣…መንግስት የህግ የበላይነትን ለመጣስ እየታዩ ያሉትን አዝማሚያዎችን እንደማይታገስ›› ተናግረዋል ፡ በሱማሌ ክልል የተነሳውን አይነት ሁከት በጋምቤላ ክልል ሊደገም እንደነበረና መከላከያ ሰራዊቱ እንዳከሸፈው ጠ/ሚር ዶ/ር አቢይ አህመድ የመከላከያ መኮንኖችን ሲመርቁ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በተከሰተው ግጭት የፌደራል መንግስቱ በፍጥነት ያልገባና የማረጋጋትንና ዜጎችን የመጠበቅ ስራንና እርዳታን በቶሎ የማድረስ በቶሎ ያልሰራ ሲሆን እንደ ቀብሪደሃር ባሉ ከተሞች ዜጎች ለከፋ አደጋ ሲጋለጡ ምግብና ውሃ በማጣት ለቀናት ማንም ሊደርስላቸው አለመቻሉ መንግስትን አስተችቷል ‹‹ሄሊኮፕተር የለም እንዴ›› ብለው አንዳንድ ዜጎች ጠይቀዋል ፡፡ በተጨማሪ በክልሉ የተነሳው ያልተጠበቀ ረብሻ በዶ/ር አብይ ለሚመራው የፌደራል መንግስት የመጀመሪያው ፈተና ሆኗል፡፡

Tuesday, July 3, 2018

liberalisation & privatization in Ethiopia, ethiopian airlines ወደ ግል ከመዛወሩ በፊት የኤርፖርቶች ድርጅት ከኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ መለያየት አለበት


በደፈናው የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ማዛወር የሚያስከትለው ችግር
ጸሃፊው ስሜነህ ተረፈ
ኢ -ሜይል smofed@gmail.com ወይም
መንግስት በቅርቡ ትላልቅ የመንግስት የልማት ድርቶችን ወደ ግል ለማዛወር መወሰኑ ተሰምቷል ፤ ይህ የፕራይቬታይዜሽን ሂደት መምጣቱ እሰየው ቢሆንም ነገር ግን መንግስት ሊጠነቀቅና ሊያጠናቸው የሚያስፈልጉ ጉዳዮች አሉ ከእነኚህም አንዱ በ2009 ዓ.ም በወጣው የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ / 406 ፤ 2009 ዓ.ም መሰረት በተደራጀው የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ በስሩ የኤርፖርቶች ድርጅትንና እንዲሁም ርካሽ የሰው ሃይልን በመጠቀም በሃገር ውስጥ የአውሮፕላን የተለያዩ አካላትን መፈብረክና መጠገን ለቦይንግና ለኤርባስ ለሌሎችም ኩባንያዎች የምርት አካላት መገጣጠሚያ ማእከልን በባለቤትነት መያዝን የሚያጠቃልል ነው ፤ ኤርፖርቶችን መገንባትና መጠገን፤እንዲሁም ኤሮኒተካል አገልግሎቶችንና ኤሮኖቲካል ያልሆኑ አገልግሎቶችን መስጠት ለኤር ኦፕሬተሮች የሚሰጡ አገልግሎቶችን መስጠት፤ የአቪየሽን ባለሙያዎችን ማሰልጠንን ቀድሞ በኤርፖርቶች ድርጅት እና በሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ይሰሩ የነበሩ ስራዎች ሁሉ ለአየር መንገድ ግሩፕ ተሰጥተዋል በዚህ ደንብ መሰረት የግሩፑ የተከፈለ ካፒታል 31.2 ቢሊየን በር ሲሆን የተፈቀደው ካፒታል ደግሞ 100 ቢሊየን መሆኑ ተገልጧል፡፡
 በመጀመሪያ የኢትዮጲያ አየር መንገድ የአየር ትራንስፖርት ሰጪ ድርጅት እንደመሆኑና ኤርፖርቶችን ማስተዳደርና መገንባት፤ ማስፋፋት፤መጠገን ፤ የአየር ትራፊክን መቆጣጠር እና የአውሮፕላን አካላትን መገጣጠም ስራ በሃገር ውስጥ መሰራት መጀመሩ መልካም ቢሆንም ራሱን የቻለ ድርጅት ሆኖ መቋቋም የነበረበት ነው እንጂ የአየር ትራንስፖርትን አገልግሎት የሚሰጠው አየር መንገድ እዚህ ውስጥ መግባት አልነበረበትም ፡፡ የምእራቡ ዓለም ታላላቅ ኩባንያዎች ኮር ቢዝነስ (Core Business) ማለትም የኩባንያው ዋነኛ ስራውና ዋናው የገቢ ምንጩ ከሆነውና በርካታ ባለሙያዎችና ልምድ፤ እውቀት ካለው ዘርፍ ማለትም የማጓጓዝ አገልግሎት ዘርፍ መውጣት አልነበረበትም ፡፡ ከዋናው ቢዝነስ የሚወጡ ኩባንያዎች የእነሱ ዋነኛ ሙያ ወዳልሆነው ዘርፍ በሚቀላቀሉበት ወቅት ለከፍተኛ ወጪና ኪሳራ የሚዳረጉ ሲሆን ዋናው ስራቸው ያልሆኑትን በማራገፍ ወደ ዋናው ስራቸው ሲመለሱ ተስተውሏል ፤ ዘርፉ ውድድር ያለበት እንደመሆኑ ትኩረቱ መሆን ያለበት በትራንስፖርት ዘርፍ ነው ፤ በዚህ ደንብ መሰረት አየር መንገዱ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ መሰማራቱና በሌሎች አየር መንገዶች ድርሻ መግዛቱ፤ቦንድ መሸጡ ያጠናክረዋል ከዚህ ውጭ ግን የሁለቱን ድርጅቶችን የስራ ድርሻን መጠቅለሉ ግን ተገቢ አይደለም ፡፡
በ2009 ዓ.ም በወጣው አዋጅ መሰረት ግን እነዚህን 3 የተለያዩ ድርጅቶች ይሰሩት የነበረውን ስራ የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ የሚል ስያሜ ከተሰጠው ድርጅት ጋር አለአግባብ የተቀላቀሉ ሲሆን የአየር ክልል ተቆጣጣሪ የሆነውን እንዲሁም ኤርፖርቶችን ከኤርፖርቶች ድርጅት ተከራይቶ የሚጠቀመው የኢትዮጲያ አየር መንገድን ከኤርፖርቶች ድርጅት ጋር ተቀላቅሏል ፡፡ ነገር ግን የኤርፖርቶ ድርጅት ኤርፖርቶችንና ተርሚናሎችን የሚሰራ ፤ የሚጠግንና የአየር ማረፊያ ሜዳዎችን ለአየር መንገዶች በማከራየት በርካታ ቢሊየን ብሮችን በየአመቱ ለመንግስት ገቢ የሚያደርግ ነው፡፡ ድርጅቱ የኮቴ በማስከፈል ገቢን የሚያኝ ሲሆን ፤ ከዚህም በተጨማሪ ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡና የሚወጡትን ደህንነትን መቆጣጠር ፤ መፈተሽ የመሳሰሉትን የደህንነት ስራዎችን የሚሰራ ነው ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአየር ማረፊያ ግቢ ውስጥ ያሉ ሱቆችን ቢሮዎችንና የመኪና ማቆሚያዎችን በማከራየት እንዲሁ ለመንግስት ገቢን የሚያስገባ ሲሆን ሲጀመር ከኢትዮጲያ አየር መንገድ የተለየ በመሆኑ ከአየር መንገዱ ጋር መቀላቀል አልነበረበትም ፤ አየር መንገዱን ለማሳደግ ከተፈለገ እንኳን አሁን እንደወጣው ፖሊሲ የተወሰነ ድርሻን ወደ ግል ባለሃብቶች ማዛወር እንጂ መቼም ቢሆን የአገሪቷ ንብረት የሆኑትን ኤርፖርቶችን በማቀላቀል መሆን አልነበረበትም፡፡ ይህ የተለያየ አደረጃጀት ስራውንም የተለያየ በመሆኑ ሲሆን በቅርቡ በወጣው አዋጅ ግን ተቀላቅለዋል ውህደቱ በተፈጸመበት ወቅት የኢትዮጲያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ እንደገለፁት ይህ ውህደት ወደ ኢትዮጲያ አቪየሽን ግሩፕ ወደ ሚባል የአቪየሽን መስሪያ ቤትንም ጨምሮ አንድ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን የእነኚህ 3 ወሳኝ የሆኑ ነገር ግን የተለያየ ስራን የሚሰሩ ድርጅቶችን ከተዋሃዱ በኋላ የአየር ደህንነትንና የአውሮፕላኖችን አስተማማኝነትን የፓይለቶችን የሙያ ፈቃድ የሚሰጠው፤ የሚፈትሸውና ፈቃድን የሚሰጠው የሚቆጣጠረው የአቪየሽን መስሪያ ቤትና ስትራቴጂያዊ የሆኑትን የአውሮፕላን ማሳረፊያ ሜዳዎችን በንብረትነት የያዘው ተቋምን የኤርፖርቶች ድርጅትን ጨምሮ ወደ ግል ማዛወር ከሃገሪቱን ደህንነት ጭምር አደጋ ውስጥ የሚከት ነው ፤እንኳን ለውጭ ባለሃብት ቀርቶ ለሃገር ውስጥ ባለሃብትም እሚሰጥ አይደለም ፡፡ ኢትዮጲያ አየር መንገድን ከአውሮፕላኖቹና ከቁሳቁሶቹ ጋር ብቻ በመለየት ወደ ግል ማዛወር የሚቻል ሲሆን ወደ ግል የማዛወር ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት በመላ ሃገሪቱ በርካታ የአውሮፕላን ማረፊያ ሜዳ ባለቤት የሆነው የኤርፖርቶች ድርጅት ተለይቶ መውጣት አለበት ፡፡   
አየር መንገዱ ወደ ግል ይዛወራል መባሉ አየር መንገዱን ያተጋው ይመስላል ፤ በዚህም መሰረት ፤ለረጅም ግዜ ያስራ ተቀምጠው የነበሩ በሞተር ችግር የማይሰሩ ሞተሮችን ማስነሳትና ወደ ስራ እንዲጀመር ማድረጉ ተዘግቧል ፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው ‹‹የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሮልስ ሮይስ ሞተሮች የተገጣጠሙላቸው አራት ቦይንግ 787-8 አውሮፕላኖች ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ ቆመው የነበሩ ቢሆንም፣ ከሞተር አምራቹ ኩባንያ ጋር በመነጋገር ሞተሮቹ እየተጠገኑ አውሮፕላኖቹ ወደ ሥራ በመመለስ ላይ እንዳሉ ሲገለፅ አየር መንገዱ ለቆሙት አውሮፕላኖች ካሳ እየተከፈለው መሆኑን ገልጿል››፡፡ የሁለቱ ድርጅቶች መቀላቀል ለሙስና ሰፊ በርን የከፈተ መሆኑ፤የር መንገዱ ግልጽ ባልሆነ መንገድ የገዛቸውን አውሮፕላኖችን መልሶ መሸጡ እንደገና መልሶ የሸጣቸውን አውሮፕላኖችን እንደሚከራይ ፤ የሰራተኛ አያያዙ ችግር እንዳለበት፤ እንዲሁም የስራ ቅጥርና ዝውውርን በተመለከተ የዘመዳማቾች ቤት ነው ተብሎ በሰፊው የሚተች ተቋም መሆኑ ይታወቃል ፡፡ 
የኢትዮጲያ መብራት ሃይል ቢሆን ባለፈው አመት ብቻ 128 ሚሊዮን ዶላር ለሃገሪቱ ያስገባ ሲሆን ይኀው ለጎረቤት ሃገራት መብራትን መሸጥ አትራፊና የውጭ ምንዛሬን የሚያስገኝ ሲሆን በሃገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ስርጭትንና ማከፋፈልን ለማሻሻል ሲሆን የሃገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሃብቶች ቢገቡበት የአገልግሎት አሰጣጡን የሚያሻሽለው ሲሆን ነገር ግን ወደ ውጭ የሚላከውና ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬን የሚያስገኘው ዘርፍ ግን በመንግስት እጅ ሆኖ ቢቆይ የሚያስገኘው ጠቀሜታ መታየት አለበት፡፡ በእርግጥ ሃይልን በማሰራጨትና በማከፋፈል ላይ በግል ባለሃብቶች መግባታቸው እንደ ኢትዮጲያ ላለ ትልቅ ሃገር አስፈላጊ መሆኑን ጠ/ሚሩ ገልፀዋል፡፡ የተመረተ ሃይል እያለ ነገር ግን በስርጭትና በማከፋፈል ሂደት ሃይል በተደጋጋሚ እየተቆራረጠ መሆኑና በኢኮኖሚው ላይ በተለይም በማምረትና በከተሞች አካባቢ በአገልግሎት ዘርፍ ላይ ጉዳትን እያደረሰ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ማንኛውም ሰው እንደሚገምተው የግል ባለሃብቶች  በመብራት ማከፋፈልም ሆነ ማሰራጨት ዘርፍ ሲሰማሩ አሁን ያለው ርካሽ የሃይል አቅርቦት አይኖርም ነገር ግን የሃይል መቆራረጡ ይቀንሳል ዋጋ ግን ወደድ ይላል ይህን ለህብረተሰቤ ግልፅ በማድረግ ይጠበቃል፤ በርካታ ትላልቅ የመንግስት ድርጅቶች ወደ ግል ወደ የተዛወሩባቸው ሃገራት የዋጋ መጨመር በስፋት ታይቷል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ቀድሞ የመገናኛናት ትራንስፖርት ሚ/ር ጋር የተቀላቀለና በከተማው ውስጥ ያሉ የመንግስት ህንጻዎችንና ሰፋፊ መሬቶችን የያዘ ስለሆነ እነኚህን የሃገር ንብረቶችን ከቴሌኮሙ ቁሳቁሶች መለየትና ቴሌን ከነቁሳቁሱ ማዛወርና የሃገር ሃብት የሆኑት ህንጻዎችን ግን ወደ መንግስት ንብረትነት መቀላቀል ያስፈልጋል ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም የድርጅቶቹን ሃብትና እዳ መግለጫ ለማዘጋጀት እንዲሁም በትክክል ድርጅቶቹ በገበያው ምን ያህል እንደሚያወጡ ‹ማርኬት ካፒታላይዜሽን› ምን ያህል እንደሆነ በገለልተኛ ኦዲተሮች ማዘጋጀት ራሱ እስከ አንድ አመት ድረስ ሊፈጅ የሚችል ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ወደ ግል የማዛወሩ ሂደት ለግዜው የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለማቃለልና የገንዘብ እጥረትን ለማቃለል ቢረዳም ውሎ አድሮ ግን በሚገኘው ገቢ ሌላ አቅምን የሚፈጥር እንዲሆን ማድረግ ያሻል፡፡

dr abey change in Eprdf, ethiopia



‹‹በለውጥባቡሩያልተሳፈረኢህአዴግ ፤ የኢህአዴግአባልነኝማለትአይችልም››
ዶ/ር አቢይአህመድ
እስካሁን ድረስ ለውጡን በጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣትንተከትሎምበርካታበጎየለውጥጅምሮችንእያየንሲሆንለሃገሪቱናበተስፋመቁረጥውስጥበመሆንስደትንየሙጥኝብሎለነበረውለአዲሱትውልድተስፋንየሚያጭርነው፡፡በርካታነባርአመራሮችበትግሉዘመንጭምርየነበሩስልጣንበቃኝእያሉመሰናበታቸውይበልየሚያሰኝሲሆንከደህንነቱምከመከላከያውናእንዲሁምከፓርቲውጭምርጉምቱዎቹናበህዝብዘንድተወዳጅያልነበሩቱናበሙስናዋነኛተጠርጣሪየነበሩወንበሩንትተናልማለታቸውለብዙሃኑየሃገሬሰውመልካምዜናነው ምራትየለማቲምየሚባለውናኦህዴድውስጥየተፈጠረውቡድንበድፍረትወደመድረኩበመምጣትለውጡንየመራሲሆንብአዴንምየኦህዴድንያህልአይሁንበአማራክልልፕሬዝደንትበገዱአንዳርጋቸውየሚመራውብአዴንቡድንምበክልሉህዝብዘንድድጋፍንያገኘሲሆንየለውጡንአስፈላጊነትየተረዳሲሆንደህዴንምውሎአድሮየለውጥሂደቱንመቀላቀሉአይቀርም ፡፡ለውጡንመደገፋቸውበጥርጣሬሲታዩየነበሩትና ፤ከለውጡባቡርእየተንጠባጠቡያሉትየቀድሞአመራሮችመካከልየደኢህዴንዋና ሊ/መንበርየነበሩትአቶሽፈራውሽጉጤናምክትላቸውከሊቀመንበርነታቸውመልቀቃቸውለዚህጠቋሚነው ፡፡በአንጻሩመጀመሪያበመሪነትኦህዴድቀጥሎምበድፍረትየለውጡአካልሆነውሆነውተገኝተዋልየብአዴንአመራሮችበባህርዳሩህዝባዊሰልፍያደረጉትንግግርለዚህማሳያነው ፡፡
አቶ ለማ መገርሳ ‹‹የለውጡን ሂደት በመደገፍ የኢትዮጲያን ህዳሴ እናስቀጥል ›› ሲሉ በህወሃት በኩል  ግን እስካሁን ድረስ የለውጡ አካል ነኝ ሲል አልተሰማም ፡ አመራሮቹም ሆነ ሚዲያዎቹ ለውጠን እንደግፋለንሲሉ አልተሰማም ይህ ነገር በጤና ነው ወይ ብለው አንዳንድ ሰዎች ይጥይቃሉ ፡፡ ህወሃት ቀድሞም ሁሉም ካልተሰጠኝ በሚል አኩራነቱ የሚታወቅ ድርጅት ሲሆን በአቶ መለስም ዘመን ቢሆን በፌደራል መንግስቱ ለድርጅቴ ተገቢው ስልጣን ውክልና አልተሰጠውም በሚል ተወካይ ላኩ ሲባል ተወካይ አልክም በማለት አቶ መለስንም ጭንቅላታቸውን ሲያዞር የነበረ ድርጅት ነው ፡፡ አንዳንድ የቀድሞ የፌደራል አመራሮችም የቀድሞውን የኢንሳ ስራ አስኪያጅ የነበሩት ዶ/ር ተክለብርሃን ጭምር በዶ/ ር አቢይ የለውጥ እንቅስቃሴ ጥርጣያቸውን በሚዲያ ሲገልፁ ተሰምቷል፡፡
ይህ ጉዳይ ማለትም ኢኤንንና ቲቪ ትግራይ ያሉ ሚዲያዎች የሰኔ 16ቱን ድጋፍ ሰልፍ አለመዘገባቸው ኢኤንን የተባለውን ቲቪ ጣቢያ እስከመዘጋት ያደረሰ ከባድ ዋጋን አስከፍሏል፡፡ የህወሃት የለውጡን ከልብ አለመደገፍ አንድም ከፌደራል መንግስቱ ጉዳዮች ራሱን እያገለለ እንዲሄድ ሲያደርግ ደኢህዴን ጭምር አመራሮቹን በመለወጥ የለውጥ ሂደቱ ተሳታፊ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ወይ እንደሌሎቹ የአመራር ለውጥ ማድረግ አለበት ፤ አለበለዝያ ግን ከፌደራል መንግስቱ የተለየ አቋምን መያዝ በረጅም ግዜ ለድርጅቱ አዋጭ መሆኑ አጠራጣሪ ነው ፡፡ 
በጠቅላይሚኒስትሩአበረታችየለውጥእንቅስቃሴበመነሳትከወደአሜሪካወደኢትዮጲያየውጭምንዛሬእንዳይገባ ሲደረግ የነበረው ዘመቻ መቆሙ በዜና ማሰራጫዎችተሰምቷል፡፡ ከዚህም በላይእነዳንኤልብርሃነናአላመራውየተባለውየኢኤንኤንጋዜጠኛውድሮስግንቦት 7 ጥይትተኩሶያውቃልእንዴ?››ቢሉምግንቦት 7 የትጥቅትግሉንማቆሙንምአስታውቋል ፡፡በውጭያሉኢትዮጲያውያንም‹‹ለዛፉናለግድግዳውእስኪገርመውድረስ››በተቃውሞሲናወጡየነበሩኢምባሲዎችደጃፎችአሁንበድጋፍሰልፍተጨናንቀዋል፡፡በባህርዳርየተካሄደውደማቅናታላቅህዝባዊሰልፍለጠ/ሚሩናለለውጥሃይሎችከፍተኛየሞራልስንቅእንደሚሆንይጠበቃል ፡፡ጠ/ሚሩከወጣቱዘንድያገኙትድጋፍከፍተኛሲሆንበአመፅተወጥሮለነበረውኢህአዴግምጭምርየመተንፈሻግዜንሰጥቶታል፡፡ይህንንፋታገዢውፓርቲውስጥያሉለውጥንየማይፈልጉሃይላትመልሰውእሚጠናከሩበትናከእጃቸውየወጣውንስልጣንበመልሰውበማስገባትእሚነሳሳሱበትናጊዜየሚገዙበትእንዳይሆንከጠ/ሚሩናበዙሪያቸውካሉቅንአመራሮችመዘናጋትንማስወገድያሻል፡፡
ነገርግንይህንለውጥወደኋላእንዳይመለስናእንዲቀጥልየሚፈልገውህዝብእጅግብዙሲሆንጠቅላይሚኒስትሩምወደኋላእንዳይመለስየማድረግተግባርይጠብቃቸዋል፡፡በቅርቡበአፋርሰመራተገኝተውባደረጉትንግግር‹‹የጀመርነውንነገርወደኋላየሚቀለብንስማንኛውምነገርለመሸከምዝግጁአይደለንም፤ ኢህአዴግውስጥለውጥመጥቷል፤ ተሃድሶመጥቷል ፤ 90  በመቶበላይአባልየለውጥጉዞውስጥገብቶየገባነውንቃልለመተግበርህዝባችንንይቅርታጠይቀን ፤ መካስአለብንበሚልእየተንቀሳቀስንነው…ቀድሞየነበረውጭንቀትእንዳይመለስየሚከፈለውዋጋይከፈላል…..የኢትዮጲያህልውናአደጋውስጥየሚያስገባሰላምየሚያሳጣንናጭንቀትውስጥየሚከተንሰላምየሚነሳንናእናቶችልጆቻቸውወጥተውቤትእስከሚገቡድረስእሚጨነቁባትኢትዮጲያዳግምእንዳትመለስዋጋይከፈላል፤ ጠንክረንእንወጣለንብለንተስፋእናደርጋለን››ሲሉእንዲሁም‹‹በለውጥባቡሩያልተሳፈረየኢህአዴግአባልነኝማለትአይችልም….90 በመቶየሚሆነውየኢህአዴግአባልምበለውጡባቡርየተሳፈረመሆኑን››አረጋግጠዋል ም/ጠ/ሚርደመቀመኮንንበበኩላቸውበባህርዳሩሰልፍላይሲናገሩለውጡ‹‹ወደኋላመመለስንሳይሆንማዝገምንአይታገስም…ለውጡበማይቀለበስበትደረጃደርሷልበፍጥነትእንስተካከላለን››ብለዋል፡፡
ይሁንናሁሉምየኢህአዴግአባላቶችበተለይምበቀደመውዘመንያሻቸውንያደርጉ ፤ እንዲሁምተጠቃሚየነበሩናበሙስናውየተነካኩቱበቀላሉየአዲሱን ጠ/ሚ/ር አስተዳደርይቀበላሉማለትአስቸጋሪነው ፡፡ጠ/ሚሩበርካታፈተናዎችንመወጣትየሚጠብቃቸውሲሆንድርጅታቸውአባላትይህንንየለውጥሂደትየማይደግፉትከሆነስራቸውንያከብድባቸዋልለምሳሌበየአካባቢውበተፈጠረግጭትየተፈናቀሉኢትዮጲያውንበሚሊዮንየሚቆጠሩመሆናቸውንየዓለምዓቀፍናየሃገራችንየሰብአዊተቆርቋሪድርጅቶችበሃገርውስጥበርካታዜጎቻቸውከተፈናቀሉባቸውየኣለምሃገራትአንዷሃገራችንመሆኗንአስታውቀውሚዲያዎችምይህንንበሰፊውዘግበዋል፡፡ ዶ/ር አቢይከተመረጡወዲህኢህአዴግሁለተኛዙርድርጅታዊማጥራትየሚጠብቀውይመስላል፤ በዚህምለውጡንያልደገፉትተለይተውየሚታወቁበትይሆናል፡፡
ለውጡየሰዎችናየአመራሮችብቻሳይሆንየህግጋትማሻሻያናለውጦችንይጨምራል ፤ ይሁንናግንአሁንምድረስመለቀቅየነበረባውሰዎችእንዳልተለቀቁ፤ እንዲሁምበቂሊንጦናበሌሎችማረሚያቤትየሚገኙእስረኞችበቃሊቲእስርቤትውስጥጨምሮከፍተኛድብደባእንደተፈፀመባቸውእንደሚገኙኢቢሲንጨምሮየተለያዩሚዲያዎችእየዘገቡየሚገኙሲሆንይህየፍትህስርአትበፍጥነትመስተካከልእንዳለበትናየህግማሻሻያዎችንጨምሮበተለይምአፋኝየሆኑትየሸብርህጉናየመንግስታዊያልሆኑድርጅቶች ፤ የፕሬስህጉበፍጥነትእንዲሻሻሉናየፍትህስርአቱመልሶ እንዲዋቀርየሰብአዊመብትድርጅቶችእየጎተጎቱሲሆንየህግንክፍተትእያወቁበመጠቀምየቀደሙትአስተዳሮችአገዛዛችንንያጠነክርልናልቢሉምጭራሽበመንግስትላይያለውአመኔታእንዲሸረሽርበማድረግስርአቶቹንአዳክሟልእንጂውሎአድሮአልጠቀማቸውም ፡፡የእነኚህህጎችመሻሻልየተሰደዱጋዜጠኞችወደሃገርቤትእንዲመለሱ፤ እናየሰብአዊመብትእንዲከበርበእጅጉየሚረዳስለሆነ ጠ/ሚሩህጎቹንለማሻሻልቅድሚያመስጠትይገባቸዋል፡፡ጠ/ሚሩለፍትህስርአቱየሚያሻሽልአንድኮሚሽንመቋቋሙናስራመጀመሩየተገለፀሲሆንጉዳዩግንፍጥነትንየሚጠይቅበመሆኑቅድሚያየሚሰጣቸውንህግጋትንበቶሎማሻሻልእንደሚገባየሰብዓዊመብትድርጅቶችእያሳሰቡይገኛሉ ፡፡ አስገራሚውነገርኢህአዴግምሆነደርግክፉኛየሚተቿቸውንጉሰነገስቱያወጧቸውንህግጋትከዋነውየወንጀለኛመቅጫህጉንከማሻሻልበስተቀርክፍተቶችያሉበትንየወንጀለኛመቅጫስነስርአትህጉንሳያሻሽሉሲሰሩባቸውየቆዩናአሁንምእየተሰራበትያለውየፍትሃብሄርህጉናየወንጀለኛመቅጫየስነስርአትህግጋትተጠቃሾችናቸው፤ እንዲሁምአስፈላጊናአንገብጋቢየሆኑህግጋትምሳይወጡሰፊየህግክፍተትበመፈጠሩምክንያትለሙስናናለመልካምአስተዳደርመታጣትመንስኤሆኗል፡፡የህግማሻሻያዎችንማድረግይዋልይደርየማይባልናጠ/ሚሩበህግተመስርተውእንዲሰሩናየህዝብንጥያቄበተለይምየመልካምአስተዳደርችግርንበቶሎእንዲመልሱ ፤እንዲሁምለውጥንየሚቃወሙየውስጥሃይሎችንበተግባርለማሳመንናተጨማሪየህዝብድጋፍንለማግኘትያስችላቸዋል ፡፡
ራሳቸው ዶ/ር አቢይለፓርላማውባቀረቡትሪፖርትመሰረት ‹‹የማሰርእንጂ፤የመፍታትህግየለንም›› ሲሉእውነቱንተናግረዋል ፤ በወንጀለኛመቅጫህጉመሰረትአንድሰውከተፈረደበትወንጀልነጻሆኖቢገኝእንኳንያላጠፋውንጥፋትጥፋተኛነኝብሎይቅርታጠይቆሊፈታይችልይሆናልእንጂቅጣቱንሳይጨርስከእስርቤትሊወጣአይችልም፤ የዳኝነትስርአቱየዳኝነትክለሳየማያደርግናበስህተትየተሰጠንፍርድደግሞየሚያይበትአሰራርየሌለውመሆኑነው ፡፡
ከዚህበመነሳትአፋኝየሆኑህግጋት ፤ እንዲሁምበአጠቃላይየፍትህስርአቱበጃንሆይግዜ በ50ዎቹ ከወጣውናበርካታክፍተቶችካሉበትከወንጀለኛመቅጫስነስርአቱጀምሮከዛሬነገይሻላልቢባልምበአቶሃይለማርያምግዜይሻሻላልቢባልምሳይሻሻልቆይቷል፤ የንግድህጉምበንግድምክርቤቶችይሻሻላልበሚልበጉጉትይጠበቅየነበረቢሆንምሳይሻሻልቀርቷልየፍትህስርአቱበህግክፍተትብቻሳይሆንእስከማረሚያቤትየእስረኞችአያያዝ ፤ የአቃቤህግክስአመሰራረት ፤ ይቅርታናምህረትአሰጣጥናበህግአተረጓጎምድረስሰፊየህግክፍተትእንዲፈጠርያደረጉትእነኚሑየወንጀለኛመቅጫየስነስርአትህግ፤የሽብርህጉናሌሎችምየተዛቡህግጋትመሆናቸውንበርካታየህግባለሙያዎችእየተናገሩይገኛሉ ፡፡ የምህረትአዋጅበፍጥነትመፅደቁመልካምሲሆንነገርግንበህብረተሰቡከዛሬነገይሻሻላሉበሚልየሚጠበቁትንከላይየተጠቀሱትንጊዜሳይሰጡማሻሻልተገቢነው፡፡

Tuesday, June 12, 2018

liberalism Ethiopia ethiopian Airline ethio Tel



ከፈረሱ ጋሪው የቀደመው የልማት ድርጅቶን ወደ ግል የማዛወርየ‹‹ሊበራሊዝም››ሂደት

በአሁኑ ሰአት ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ዋና ዋና የሆኑትን የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ወደ ግል ለማዛወር መወሰኑ ከዚህ ቀደም ገዢው ፓርቲ ያራምድ ከነበረው የተለየ አቋም ሲሆን እነኚህ የልማት ድርጅቶች ወደ ግል አይዛወሩም በሚል በነሱ አትምጡብኝ የኒኦ ሊበራል ሃይሎች አመለካከት ነው ይሄንን አንቀበልም ሲል የቆየ ቢሆንም አሁን ግን ብዙዎቹን ምእራባውያኑን ጭምር ያስገረመ የፖሊሲ ለውጥን አድርጓል፡፡ የፖሊሲ ለውጡ ያልተጠበቀ ሲሆን የዘገየና ትንሽ(Too little, Too Late)ፈረንጆቹ እንደሚሉት ነው፤ ከዚህ በተጨማሪ ግን የዚህን ያህል ግዙፍ የፖሊሲ ለውጥን ለማድረግ ከመነሳት በፊት ኩባንያዎቹን ለማስተላለፍና ለውጡን መምራት በህዝብ ዘንድ ተአማኒ በሆነ ሁኔታ ሽግግር እንዲደረግ አስፈላጊ የሆኑት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ነበረባቸው ፡፡
በማንኛውም ሃገር እንደሚደረገው ሁሉ አንድን ተቋም ወደ ግል ለማዛወር እንዲሁም አክስዮኖችን ለህዝብ ለመሸጥ አስቀድሞ የሚያስፈልጉ መዘጋጀት ያለባቸው መደላድል የሚሆኑየገበያ መሰረተ ልማቶች፤ደጋፊ የህግ ማእቅፎችና ተቋማት የሚያስፈልጉ ሲሆን ለምሳሌ ስለ አክስዮን ድርጅቶች የሚደነግገውናከ60 አመት በፊት የወጣው የንግድ ህግ ይሻሻላል ቢባልም ተሻሽሎ አልወጣም ፤ ከዚህ ቀደም ትላልቆቹ የመንግስት ድርጅቶች የቢራ ፋብሪካዎቹን ጨምሮ በዝግ ጨረታ ላሸነፉት የውጭ ኩባንያዎች የተሸጡ ሲሆን ይፋዊ የሆነ የአክስዮን ገበያ ባለመኖሩ ምክንያትእስካሁን ድረስ መንግስት ትላልቆቹን ድርጅቶቹን የመግዛት እድልን ያገኙት የውጭ ባለሃብቶችና እንደ ሚድሮክ ያሉት ናቸው ፡፡እነኚህ ድርጅቶች አክስዮኖቻቸው ለህዝብ ይሸጣሉ ቢባልም በየትኛው የአክስዮን መገበያያ መድረክ እንደሆነ ግልፅ አይደለም ፤ በተደጋጋሚ የንግዱ ህብረተሰብ የአክስዮን ገበያ እንዲከፈት ውትወታ ቢያደርግም በመንግስት በኩል ግን መቆጣጠር አንችልም ፤ ሃገሪቱ ለዚህ ዝግጁ አይደለችም ….ወዘተ በሚሉ ምክንያቶች ፈቃደኝነት አልታየም ፤ ኢትዮጲያ የአክስዮን ገበያ ከሌላቸው በዓለም ላይ ካሉ 40 አገራት ትልቋ መሆኗ የዓለም ሚዲያዎች የዘገቡት ጉዳይ ነው ፤የአሁኑን የመንግስት ድርጅቶችን ለህዝብ አክስዮን እሸጣለሁ የሚለው አቋም በመጀመሪያ የአክስዮን ገበያና ግልፅ የሆኑ የአክስዮን ኩባንያ ድንጋጌዎችና ፤ የንግድ ህግጋት በሌሉበት አክስዮኖቹ እንዴት እንደሚሸጡ ግልፅ ማድረግ ይጠበቃል ፡፡
በመግለጫው ላይ እንደተጠቀሰው ወደ ግል በሚዛወሩበት ሙስናን ለመከላከልጥንቃቄን እንደሚደረግ አመልክቷል፡፡በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት አባል በሆኑበት ሃገራትና በአሁኗ ራሺያ በቦሪስ የልሲን ዘመን የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል በሚያዛውሩበት ወቅት ከፍተኛ ሙስና በመፈፀሙ ዋና ዋና የሚባሉ ድርጅቶች በግለሰቦች እጅ ገብተው አሁን ቱጃር ኦሊጋርክ የሚባሉት የሃገሪቱን የሀብት ሃብት ምንጭ የሆኑትን ኩባንያዎች በርካሽ ዋጋ በእጃቸው ሊያስገቡ በቅተዋል በዚህም ሩስያና ፤ እንደ ኡክሬን ያሉ ሃገራት በሃብታሙና በደሃው መሀከል ሰፊ የሆነ የሃብት ልዩነት ከሚታይባቸው የዓለም ሃገራት ተርታ ተሰልፈዋል ፤ ብዙዎቹ የአሁኑ የሩስያና ኡክሬይን ቢሊየነሮችም በዚህ መንገድ ሃብትን ያካበቱና ፖለቲካውንና ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር በቻሉ ሰዎች ስለሆነ ዲሞክራሲን ለማስፈንም እንቅፋት ሆኗል ፤ የአሁኑ የሩስያ ፕሬዝደንት ፑቲንም በእነኚህ ዲታ ኦሊጋርኮች ጋር በመሻረክና የሃገሪቱን የተፈጥሮ ሃብት በመከፋፈል ሃገሪቱን እየገዙ እንዳለ ይታወቃል፤እነኚህ ባለሃብቶችም ሃገራቸውን ስለማያምኑ ኑሯቸውን በአውሮፓና እንግሊዝ ሲያደርጉ የሃገራቸውን ሃብትም ወደ ውጭ በማሸሽ ኪሳራን ተከትሎም የተዛባ የሃብት ክፍፍል አስከትለዋል፤ እንዲሁም በቻይናም የመንግስትን ኩባንያዎችን እንደ ሩስያ አይሁን እንጂ የኮሚኒስት ፓርቲው አባላትና ዘመዶች ሊከፋፈሏቸው በቅተዋል፡፡
ውሳኔው በገዢው ፓርቲ የተወሰነ ሲሆን ነገር ግን ይህ ቁልፍ ውሳኔ እንደመሆኑ መጠን መወሰን የነበረበት በፓርቲ መዋቅር ነው ወይንስ አስፈጻሚ በሆነው በሚኒስትሮች ም/ቤትና በህግ አውጪው መፅደቅ ነው የነበረበት የሚለው አነጋጋሪ ነው ፤ ጉዳዩ ወደ ፓርላማ ሄዶ ህግ ሆኖ በሚቀየርበት ወቅት ፓርላማው የገዢውን ፓርቲ ውሳኔ ማፅደቅ ይጠበቅበታል ማለት ነው ፡፡ትላልቅና ወሳኝ የሆኑ የኢኮኖሚ አውታር የሆኑ ድርጅቶችን ፤ወደ ግል የማዛወር ሂደት በጥንቃቄ መተግበር ሲኖርበት ከላይ የተጠቀሱትንና የሌሎችን ሃገራትን ልምድን ማስተዋል ያሻል፤ይዛወራሉ ከሚባሉት መሃከል ቴሌን ብንወስድ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ከመደረጉ በፊት ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ክፍት ተደርጎ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ሃብትን እንዲፈጥሩበትና የመወዳደር ብቃታቸውን ለማሳደግ ቅድሚያ እድል ማግኘት የሚገባቸው ሲሆን እነሱ ሲጠነክሩ ለውጭዎች ክፍት መደረግ የነበረበት ቢሆንም ለረጅም አመታት ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ጭምር ክፍት አይደረግም በሚል ግትር አቋም በመንግስት ሞኖፖሊ ለአመታት ተይዞ ቆይቷል፤ የአየር መንግዱም ዘርፍ ከአነስተኛ አውሮፕላንና ከአምቡላንስና ሄሊኮፕተር በስተቀር ለትላልቅ የግል አየር መንገዶች ፈቃድ የማይሰጥ ሲሆን መጀመሪያ ዘርፉን ክፍት በማድረግ የሃገር ውስጥ ትላልቅ አውሮፕላኖችን ለሚያንቀሳቅሱ ክፍት መደረግ ነበረበት ፡፡ አሁን ክፍት ይደረጋሉ የሚባሉት ዘርፎች በሙሉ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀሱ ቢፈቀድ ስንት ቴሌና ስንት ትላልቅ የግል አየር መንገዶች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል፡፡
የፋይናንሱን ዘርፍ ብንመለከት የግል ኢንሹራንሶችና ባንኮች መጀመሪያ ለሃገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች ክፍት የተደረገ ሲሆን አንዳንዶቹ ተቋማት ከፍተኛ ካፒታልን እስከመፍጠር ደርሰዋል አሁን የዚህ ዘርፍ ችግር ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ክፍት መሆኑና ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት አለመደረጉና ለረጅም ግዜ ዝግ ሆኖ መቆየቱ ደግሞ በዘርፉ በቂ ውድድር እንዳይኖርና የውጭ ምንዛሬን ለማፍራት በራሱ እየፈጠረ ያለው ችግር አለ፡፡ ነገር ግን አሁን ክፍት ይደረጋሉ የተባሉት ዘርፎች ቅደምተከተሉ መሆን ያለበት መጀመሪያ ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች እንዲሳተፉ ህጎችን ማውጣት የነበረበት ሲሆን በመቀጠልም በሃገር ውስጥ ካፒታልን ከፈጠሩና ከውጭ ባለሃብቶች ጋር መወዳደር የሚያስችል አቅምን በሚፈጥሩበት ወቅት የውጭዎቹ እንዲገቡ ይደረጋል፤ ነገር ግን የአሁኑን ለየት የሚያደርገው ግን ለውጭም ለሃገር ውስጥም እኩል ክፍት ማድረጉ የተለየ ያደርገዋል ፡፡በኢትዮጲያ የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል የማዛወር ሂደት ግልፅነት የጎደለውና ለሙስና የተጋለጠ ሲሆን ፤ ብዙዎቹ ትላልቆቹ ለውጭ ባለሃብት የተላለፉ ሲሆን ህብረተሰቡ ከደመወዝተኝነት ውጪ ሌላ ሃብትና ንብረትን እንዳያፈራ ሲያደርገው ከእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ መብት ለመግዛት ምንም እድልን ሳያገኝ የቀረ ሲሆን የአሁኑ ለየት የሚያደርገው ግን ለህዝቡም ድርሻን እሸጣለሁ ማለቱ ነው ይህ መልካም ሲሆን ህዝቡም ተሳታፊ መሆኑ ለግልፅነት አጋዥ ነው፡፡
የገንዘብና / ኢኮኖሚ / ትብብር ሚ/ሩ 59 ቢሊየን ብር በላይ የ2011 ዓ.ም. በጀት ጉደለት ማሳየቱንና ይህንንም ለመሙላት በሃገር ውስጥ የገንዘብ ህትመት ይሸፈናል ማለታው መጪው ግዜ የባሰ የዋጋ ግሽበት የሚታይበትና የዜጎች ኑሮ የበለጠ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገባ አመላካች ነው፡፡ የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት አሁን ካለው አሳሳቢ ከሆነውና አሁንም እየናረ ካለው የዋጋ ግሽበት አንጻር እንደ ከዚህ ቀደም ተጨማሪ ገንዘብን ወደ ኢኮኖሚው ቢለቀቅ የሚፈጥረውን ተጨማሪ ግሽበትን መቋቋም ስለማይቻል እነኚህን ድርጅቶችን መሸጥ አማራጭ የሌለው ሆኖ ተገኝቷል
እንደ ቻይና ያሉ ሃገራትም በተነሳው ብጥብጥና የፖለቲካ አለመረጋጋት ሳቢያ ወደዚህ የሚልኩትን ኢንቨስትመንታቸውን ያዝ ማድረጋቸውም ተሰምቷል ፤ ከውጭ ይገኝ የነበረው ብድር የመቀነስ አዝማሚያን አሳይቷል - በመሸጥ ካልሆነ በቀር እንደ ከዚህ ቀደሙ በብድርም ሆነ በእርዳታ በቀላሉ ከውጪ ገንዘብ ማግኘት እንደማይቻል መገመት ይቻላል ፤ስለሆነም መንግስት ካለበት የእዳ ጫናና ከከፍተኛ የበጀት ጉድለት ለማቃለል የእነዚህን ድርጅቶችን ሽያጭ እንዳሰበው መገመት ይቻላል ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ኢኮኖሚውን ለውጭ ባለሃብቶች ሊበራላይዝ›› ክፍት አድርግ የሚለውን የምእራባውያንን ግፊት መልስ ለመስጠትና የፖሊሲ ማሻሻያን በማድረግ ሊመጣ የሚችልን እርዳታንና ብድር ለማግኘት ሊሆን ይችላል ፡፡ ሃገሪቱ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል እንዳትሆን አንድ እንቅፋት ሆኖ የቆየው ይሄው ክፍት አይደረጉም የሚባሉት ዘርፎች ጉዳይ ነው ፤ ይሁንና ወደ ግል ይዛወሩ በተለይም ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ይተላለፉ መባሉ መልካም ቢሆንም ያለውን የሃብት ልዩነትን እንዳያሰፋውና ለማስተካከል በሚያስቸግር ሁኔታ ሃብት በጥቂቶች እጅ መከማቸትን እንዳይፈጥር ጥንቃቄን ማድረግ ያሻል፡፡የልማት ድርጅቶቹ ለረጅም አመታት ሞኖፖሊ በመሆን ባለሃብት አይገባባቸውም መባላቸው በሃገሪቱ እድገት ላይ የራሱን አሉታዊ ተፅእኖን ፈጥሮ ቆይቷል ፤ ቴሌና አየር መንገድ ድርጅቶች በጣም አትራፊ ስለሆኑ እንደ ኢትዮጲያ አየር መንገድ ያለው በውጭ ምንዛሬ ስለሆነ በተለይም የውጭ ባለሃብቶቹ ትርፋቸውን ወደ ውጭ ማውጣትም ይችላልበዚህም ምክንያት የውጭ ባለሃብቶችን ለመሳብ ያስችላል ፤ ነገር ግን ከቴሌ በተለየ ሁኔታ አየር መንገዱ አትራፊና የብሄራዊ መለያ እንደመሆኑ መጠን እርሱን ወደ ግል ማዛወሩ የተቻኮለ ውሳኔ ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ እነኚህ የልማት ድርጅቶች በሙስናና ውጤታማ ያልሆነን አገልግሎት በመስጠት የሚታወቁ ናቸው እንደ ቴሌ ፤ (Shipping Lines) ሺፒንግ ላይንስ ያሉት መንግስታዊ ሞኖፖሊዎች ሲሆን ተወዳዳሪ ኩባንያዎች ቢኖሩ የዋጋና የጥራት ልዩነት ሊመጣ የሚችል ሲሆን ለዚህ የገበያ ውድድር መልካም እድልን ይፈጥራል ፤ከእነኚህ ኩባንያዎች ግልጽ የሆነ የሂሳብ አያያዝ የሚጠይቅ ሲሆን የሂሳብ ሪፖርቶችንም በየሩብ አመቱ በግልፅ ማተምን ይጠይቃል፡፡ ከዚህ ቀደም ለኢትዮያ ዋነኛ አበዳሪ የሆነችው ቻይና የንግድ መርክብ ድርጅት ውስጥ ድርሻ ይሰጠኝ ብላ ጠይቃ የነበረ ሲሆን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ሲደረግ ቻይናና ሌሎች የሩቅ ምስራቅ አበዳሪዎች ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር የሚስችላቸውን ድርሻ ሊይዙ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ፡፡ መንግስት አብዛኛውን ድርሻ አሁንም ቢሆን እኔ እይዛለሁ ቢልም በሂደት ግን አንዴ መሸጥ ከጀመረ እየሸጠ መውጣቱ የማይቀርና የግል ባለሃብቶቹ ድርሻ እያየለ መምጣቱ አይቀርም ስለዚህ ቋሚ የሆነ የአክስዮን ግብይት በማቋቋም ማንኛውም ሰው ባለው አቅም አክስዮኖችን የመግዛት እድልን ማግኘት አለበት፡፡
የወጪ ንግድ ገቢ የሃገሪቱን ምንዛሬ ፍላጎትን ማሟላት ባቃተው ወቅት ድርጅቶቹን የተወሰነውን ድርሻ መሸጥ እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግል ቢችልም በዘላቂነት ግን በሽያጩ ከሚገኘው ገቢ አስተማማኝ ገቢን የሚያስገኝ አቅምን መፍጠር ዋነኛ ተግባር መሆን አለበት፡፡የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለውጡ በዚህ መገታት የሌለበት ሲሆን የሃገሪቱን ሃብት ለረጅም ዘመናት አስረው የያዙና ትርፋማ ያልሆኑ ዘርፎች ለውድድር ክፍት በማድረግ በተሻለ ሁኔታ በግል ባለሃብቶች እንዲተዳደር መደረግ አለበት ፡፡