Tuesday, March 12, 2013

የአመራር ድክመቶች እና መነሻዎቻቸው


አንዳንድ መሪዎች ችግሮችን መፍታት ሲያቅታቸው ወይንም ችግሩን ለመፍታት የሚያስፈልገውን ለውጥ ወይንም ጥገናዊ ለውጥ (Reform) ማድረግ ሳይፈልጉ ሲቀሩ የተከታዮቻቸውን ወይንም የህዝባቸውን የአትኩሮት አቅጣጫውን ለማስቀየር የተለያዩ ነገሮችን ያደርጋሉ ይሁን እንጂ አንድ ችግር ወይንም መሻሻል ያለበት ነገር በመሰረታዊነት መስመር ካልያዘ ወይንም ካልተፈታ ችግሩ ለጊዜው ተድበስብሶ እንዲቀርና በረጅም ጊዜግን የከፋ መዘዝ የሚያስከትል ሆኖ ብቅ እንዲል ብቻ ነው እሚያደርገው


ሀላፊነትን በትክክል አለመወጣት አንዱ የአመራር ወይንም የመሪነት ድክመት ነው አንድ መሪ ተሳስቶ ይሁን ወይንም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አግባብነት የሌለው ውሳኔን ከወሰነና የሚመራውን ተቋም ወይንም ድርጅት ሀገር ላይ ጉዳትን ካመጣ ብዙ ጊዜ ያንን ቦታውን እንዲያጣ ይደረጋል። በተለይም በምእራቡ አለም መሪዎች ከተሳሳቱና ውሳኔያቸው ጉዳትን ካስከተለ በቶሎ ከዛ ቦታ እንዲነሱ ይደረጋል።ይሄም ተገቢ አሰራር ሲሆን ለዚህም ሰው እዛ ቦታ ለረጅም ጊዜ ከቆየ የሚያስከትለውን ጉዳት በመገመትና በመረዳት ነው። ለዚህም በምእራቡ አለም ጠንካራ የመገናናኛ ብዙሀኖች ስላሏቸው በዛ አማካኝነት ከህዝብ ቢደበቅ እንኳን ይፋ ስለሚያደርጉት የህዝብ ግፊት ስለሚያይል ነገሩን በቶሎ ለማስተካከል ይረዳቸዋል።ይህ አሰራር በተለይም ቀድሞ ብዙም ተጠያቂነት ባልነበረባቸው በትላልቆቹ ኮርፖሬሽኖችና ባንኮችም ጭምር ውስጥ ተግባራዊ እየሆነ ሲሆን ኩባንያው የህዝብን አመኔታን እንዲያጣ ያደረጉ የግዙፍ ኮርፖሬሽኖች ሀላፊዎች ከሀላፊነታቸው እንዲለቁ ሲደረጉ በተደጋጋሚ ተስተውሏል


ለውጥ ከሁለት አቅጣጫ የሚመጣ ሲሆን ከላይ ወደታች (Top Down) እና (Bottom Up) ወይም ከላይ ወደታች ነው ከላይ ወደ ታች እሚመጣው የለውጥ አይነት በመሪዎች የራስ ተነሳሽነት የህዝቡ ግፊት ቢኖርም ባይኖርም ራሳቸው መሪዎቹ አምነውበት የሚገፉት የለውጥ አይነት ሲሆን   ሁለተኛው አይነት ከለውጥ ደግሞ ከራሱ ከህዝቡ በራሱ ግፊት የሚመጣና ሀገሩ የምትሄድበትን አወቅጣጫ ራሱ እሚመራበትና እሚጠቁምበት ነው ብዙ ጊዜ ከታች የሚመጣን የለውጥ ግፊት ከላይ ያሉ መሪዎች በማይቀበሉ ከሆነ ከብዙ ትችግስት በኋላ የለውጥ እንንቅስቃሴዎች ብሎም አብዮቶች ሁሉ ሊካሄዱ ይችላሉ


ስለዚህ ምንግዜም ቢሆን መሪው የለውጡን አቅጣጫና አካሄድ አስቀድሞ መገመትና መጠበቅ መቻል ሲኖርበት በአንደ በኩል የለውጡን ጥቅም ማየት ከቻለ ምንም እንኳን የራሱን ግላዊ ስልጣን እሚቀንስና እሚያሳጣ ሆኖ ቢገኝ ነገር ግን በታሪክ የሚኖረውን ስፍራውን በመልካም ለማስፈርና አይቀሬም ከሆነም ያንን ለውጥ ለማገዝ መደገፍ አንድ አማራጭ ሲሆን ነገር ግን የለውጡ ፍላጎት የብዙዎች ሆኖ እሱ ብቻውን ለማስቆምና ለመግታት ከሞከረ ግን በታሪክ የሚኖረውን ቦታ ማበላሸት ብቻ ሳይሆን መሪነቱን ፍፁም ጥላሸት ሊቀባው እና ቀድሞ የሰራቸውን ጥሩ ስራዎች ሊጋርድበትና ይችላል

   
ሌላው ደግሞ አንድ መሪ ውድድሩን ካጠፋ የራሱን የሚመራውን ተቋም እድገት ያቀጭጨዋል ለተቋሙ ወይም ለሀገሪቱ የፖለቲካ እድገት እገዛን ሊያደርግ ይችል የነበረውን እንዲሁም ለወደፊቱ ሽግግር ወቅት ሲመጣ ሰላማዊ ሽግግር እንዲኖር የሚያስችለውን ተቋማዊና እውቀትና የሰው ሀይል እድገት እንዲቀጭጭ ነው እሚያደርገው የጤናማ ውድድር መኖር ለተቋማትም ሆነ ለመንግስታት እድገት አስፈላጊ ነው በውድድር ባለበት አለም ውስጥ የመጨረሻ አሸናፊና ተሸናፊ እሚባል ነገር የሌለ ሲሆን በየትኛውም ውድድር ምንግዜም ጊዜያዊ ተሸናፊና ጊዜያዊ አሸናፊ ናቸውረ ያሉት


ስፖርትን እንኳን ብንወስድ አንድ ቡድን በአንድ ውድድር ቢያሸንፍ በሚቀጥለው ጊዜ ደግሞ ሌላው ያልተጠበቀው ቡድን ያሸንፋል ፣ስፖርትን በውድድሩ ወቅት ካለው ትእይንት በተጨማሪ አጓጊ የሚያደርገው ይሄው ያልተጠበቀው ማሸነፍና መሸመፍ ናቸው በመሪነት ውስጥም ያልተጠበቀው ፓርቲ ተመርጦ ወደ ስልጣን ሊመጣ ሲችል የተጠበቀው ፓርቲ ደግሞ ሊሸነፍ ይችላል ስለዚህ ሽንፈትን እንደ መጨረሻ መወሰድ የሌለበት ሲሆን ማሸነፍም እንዲሁ ዘላለማዊ አይደለም አሁን ያሸነፈ ፓርቲ ከጥቂት አመታት በኋላ ተሸናፊ ሆኖ እሚገኘው እሱ ይሆናል ተሸናፊውም በሚቀጥለው ጊዜ ድሉ የእርሱ ይሆናል

የሌሎች ሰዎችን የማሰብና የማወቅ ችሎታን አሳንሶ የሚገምት መሪ መጨረሻ ላይ በርካታ ያልጠበቃቸውን ፈተናዎችን ይጋፈጣል እኔ እማውቀውን ሌሎች ሰዎች አያውቁትም ብሎ ማሰብ ወይንም ሌሎች ተወዳዳሪዎቹንም ሆነ አጋሮቹን ጭምር የራሳቸውን ጉዳይ በትክክል መፈጸም አይችሉም ብሎ ማሰብ በተለይ ለመሪ ትልቅ ስህተት ነው ።አንድ መሪ ሊፈጽማቸው ከሚችላቸው ስህተቶችም ትልቁና ዋነኛው ይሄው ነው የሰው ልጅ አእምሮ የማሰብ፣ የማወቅና የማገናዘብ ችሎታ ያለው በመሆኑ ብዙ ጊዜ ተመጣጣኝ የሆነ ነገሮችን የመረዳት ችሎታ በብዙ ሰዎች ዘንድ አለ

ሌላው ደግሞ መሪው ራሱን እንደ አይበገሬ (Invincible) አድርጎ መመልከት የለበትም ከዚያ ይልቅ ሌሎች ተወዳዳሪዎቹም ቢሆኑ ሊያደርሱበት የሚችሉትን እንዲሁም እርሱ እራሱ ነገሮችን ቢያበላሽ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ መገመት መቻል አለበት
 
መሪዎች ለረጅም አመታት በአንድ የስልጣን ወንበር ላይ ሲቀመጡ በዛ ቦታ ላይ (Burn Out) መድከምና መሰላቸት ሊያደርጉ ይችላሉ በተለይም የአገር መሪዎች ለረጅም አመታት ሲቀመጡ የመታከትና የመሰላቸት የመዛል (Burn Out) የማድረግ እድላቸው ሰፊ ነው አንዳንድ የስፖርት በተለይም የእግር ኳስ አሰልጣኞች ቡድናቸው ከፍተኛ ስኬትን በሚያስመዘግብበት ወቅት በድንገት ከአሰልጣኝነት ስራቸው ራሳቸውን ለተወሰነ ጊዜ አግልለው የሚቆዩበትም ይኀው ምክንያት ነው ።ህጉ ራሱም ስለማይፈቅድላቸው ዲሞክራሲ ባለባቸው ሀገራት ውስጥመሪዎች ከተወሰኑ አመታት በላይ በስልጣን ወንበር ላይ ስለማይቀመጡ በርን አውት የማያደርጉ ሲሆንበአንፃራዊነት በስልጣን ላይ የሚቆዩበት አመታት አጭር በመሆናቸው ነው በአንፃሩ ግን ዲሞክራሲ ባልዳበረባቸው ሀገራት ውስጥመሪዎች ለረጅም አመታት በስልጣን ወንበር ላይ ሊቀመጡ ይችላሉ ። የኩባንያ መሪዎችም ሊሰላቹ ይችላሉ አንዳንድ መሪዎች በነበሩበት ስኬትን ካመጡ በኋላ አዲስ ጀብድን በመፈለግ ወይም አዲስ ችግርን ለመፍታት በመፈለግ ከነበሩበት ትተው ወደ አዲስ ኩባንያ ለማምራት ሲፈልጉ በምእራባውያን ኩባንያዎች ታይቷል አዲስ የሚፈቱት ችግር (Adventure)  መፈለግም መሪው ቀድሞ የነበረውን ቦታ ትቶ ወደ ሌላ እንዲሄድ ሊገፋፋው ይችላል

ሌሎችን የመረዳት አስተውሎት (Emotional intelligence)



አንድ መሪ የሌሎች ሰዎችን ባህሪና ፍላጎት መረዳት መቻል አለበት ።ባለማወቅ ወይንም ሆነ ብሎ የሌሎች ሰዎችን ስሜት የሚረጋግጥ ከሆነ ይዘግይም ወይንም ይፍጠንም በሌሎች ሰዎች ያለዉ ተወዳጅነትን እያጣ መሄዱ የማይቀር ነዉ ። ኢሞሽናል ኢንተሊጀንስ በተፈጥሯቸዉ የታደሉ አሉ ይሁን እንጂ በመማርም ሊገኝ ይችላል።ልክ እንደ የመናገር ችግር ያለባቸው ወይመም ኦቲስቲክ (Autistic) የሆኑ ልጆች አይነት ። በእርግጥ ይህ ችሎታ በቀለም ትምህርት የሚገኝ ነገር አይደለም ። አንድ ሰው በከፍተኛ ደረጃ የተማረ ቢሆንም እንኳን የዚህ የሌሎችን ስሜት የመረዳት ችሎታው ግን አነስተኛ ሊሆን ይችላል ። ውስብስብ የሆኑ ስለ- ልቦናዊ ባህሪያቶችን ማወቅ አለበት ። 
 
አንድ መሪ የሀገር መሪ ቢሆን ራሱን ከሀገር ማስበለጥ የሌለበት ሲሆን እንደዛ ካደረገ ግን እንደ ተሞኘ ይቆጠራል ። ለምሳሌ ሙባረክ ማለት ግብፅ ፣ ተብሎ ይታሰብ የነበረ ሲሆን ልጁም ስልጣኑን እንደሚወርስ ይገመት የነበረ ቢሆንም ያ ቀርቶ በዛ ምትክ ማንም ከዛ አስቀድሞ ማንም ባላሰበውና ሊያስበው በማይችለው ሁኔታ በሰባት ሺ የግብፅ የነገስታትና የመሪዎች ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መሪዎቹ ፍርድ ቤት ለመቅረብ በቅተዋል ።
መሪው ተከታዮቹን ፍላጎትም ሆነ ባህሪ ማወቅ አለበት ፤አንዳንድ ተከታዮች ተባባሪዎችና ቀና አመለካከት ያላቸው ሲሆኑ አንዳንዶች ደግሞ ቀና አመለካከት የሌላቸውም ሁሉ ሊሆኑ ይችላሉ ፣አንዳንዶች ደግሞ ለመሪው የማይጠቅሙም የማይጎዱም ሆነው ሊገኙ ይችላሉ። ሰዎች መሪው ከሚሰጣቸው መመሪያ ይልቅ መሪው ማነው ብለው ይጠይቃሉ ።

      በአሁኑ ወቅት ከአስተዳደር ባለሙያዎች ትኩረት እየተሰጠው ያለ ጉዳይ የስብእና ፍተሻ (Personality Test) የሚባለው ሲሆን ይኀውም የተለያዩ ሰዎች ያላቸውን የተለያየ ተፈጥሯዊ የሆነ ስብእናን ትኩረት መስጠትና ለአስተዳደር ያለውን በጎም ሆነ አሉታዊ ተፅእኖ በመረዳት ነው ። የቀድሞው የአስተዳደር አስተሳሳብ በሰዎች መሀከል ያለውን ተፈጥሯዎዊም ሆነ ማህበራዊ ልዩነቶችን ትኩረት የማይሰጥና ሁሉም ሰዎች በባህሪም ሆነ በአስተሳብም አንድ አይነት ናቸው ብሎ የሚያስብ የነበረ ሲሆን ፣ አሁን በዘመናችን ግን ልዩነቶች ትኩረትን እያገኙ መጥተዋል ። ጥሩ ሌሎችን የመረዳት አስተውሎት ያለው መሪ እነኚህን የስብእና ልዩነቶችን በሚገባ የሚረዳ ይሆናል ።

      ይሁን እንጂ በቡድናዊ ጠባብ አስተሳሰብ (Group-think) እንዳይታሰርም መጠንቀቅ አለበት ። ብዙውን ግዜ ይሄ አስተሳሰብ በአንድ ቡድን ውስጥ ለሰፈነ ቡድኑ እሚሰራውን ስህተት ለማየት ያስችለው የነበረውን እይታ ያጠበዋል፤ የምናደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው በሚል ቡድናዊ እሳቤ ፣ ገሀዳዊውን እውነታና ከውጪ የሚመጡ ስህተቶችን ነቀፌታዎችን ለመረዳት ሳይችል እንዲቀር ያደርገዋል ። ከውጪ ያለ ሰው በቀላሉ የሚያያቸውን እንከኖች ለማየት ያስችል የነበረውን እድል ያሳጣዋል ። ይህ ብቻ ሳይሆን ከእውነታው ውጪ የሆነ (Delusional)የሆነ አስተሳሰብ ይፈጠራል ። ይህም ወደ ቅዠት የቀረበ አስተሳብ ሲሆን ከገሀዳዊው እውነታ ውጪ የሆነ አስተሳሰብን መያዝን ያመለክታል ፤ መሪዎችም ሆኑ ቡድናቸው የዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ከሰረፀባቸው ወደ ውድቀትና ወደ ስህተት የማምራታቸው እድል እየሰፋ ይመጣል ።

ሌሎችን የመረዳት አስተውሎት (Emotional Intelligence)



አንድ መሪ የሌሎች ሰዎችን ባህሪና ፍላጎት መረዳት መቻል አለበት ።ባለማወቅ ወይንም ሆነ ብሎ የሌሎች ሰዎችን ስሜት የሚረጋግጥ ከሆነ ይዘግይም ወይንም ይፍጠንም በሌሎች ሰዎች ያለዉ ተወዳጅነትን እያጣ መሄዱ የማይቀር ነዉ ። ኢሞሽናል ኢንተሊጀንስ በተፈጥሯቸዉ የታደሉ አሉ ይሁን እንጂ በመማርም ሊገኝ ይችላል።ልክ እንደ ኦቲስቲክ (Autistic) ልጆች አይነት ። በእርግጥ ይህ ችሎታ በቀለም ትምህርት የሚገኝ ነገር አይደለም ። አንድ ሰው በከፍተኛ ደረጃ የተማረ ቢሆንም እንኳን የዚህ የሌሎችን ስሜት የመረዳት ችሎታው ግን አነስተኛ ሊሆን ይችላል ። ውስብስብ የሆኑ ስለ- ልቦናዊ ባህሪያቶችን ማወቅ አለበት ። 
 
አንድ መሪ የሀገር መሪ ቢሆን ራሱን ከሀገር ማስበለጥ የሌለበት ሲሆን እንደዛ ካደረገ ግን እንደ ተሞኘ ይቆጠራል ። ለምሳሌ ሙባረክ ማለት ግብፅ ፣ ተብሎ ይታሰብ የነበረ ሲሆን ልጁም ስልጣኑን እንደሚወርስ ይገመት የነበረ ቢሆንም ያ ቀርቶ በዛ ምትክ ማንም ከዛ አስቀድሞ ማንም ባላሰበውና ሊያስበው በማይችለው ሁኔታ በሰባት ሺ የግብፅ የነገስታትና የመሪዎች ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መሪዎቹ ፍርድ ቤት ለመቅረብ በቅተዋል ።

መሪው ተከታዮቹን ባህሪ ማወቅ አለበት ፤አንዳንድ ተከታዮች ተባባሪዎችና ቀና አመለካከት ያላቸው ሲሆኑ አንዳንዶች ደግሞ ቀና አመለካከት የሌላቸውም ሁሉ ሊሆኑ ይችላሉ ፣አንዳንዶች ደግሞ ለመሪው የማይጠቅሙም የማይጎዱም ሆነው ሊገኙ ይችላሉ። ሰዎች መሪው ከሚሰጣቸው መመሪያ ይልቅ መሪው ማነው ብለው ይጠይቃሉ ።

      በአሁኑ ወቅት ከአስተዳደር ባለሙያዎች ትኩረት እየተሰጠው ያለ ጉዳይ የስብእና ፍተሻ (Personality Test) የሚባለው ሲሆን ይኀውም የተለያዩ ሰዎች ያላቸውን የተለያየ ተፈጥሯዊ የሆነ ስብእናን ትኩረት መስጠትና ለአስተዳደር ያለውን በጎም ሆነ አሉታዊ ተፅእኖ በመረዳት ነው ። የቀድሞው የአስተዳደር አስተሳሳብ በሰዎች መሀከል ያለውን ተፈጥሯዎዊም ሆነ ማህበራዊ ልዩነቶችን ትኩረት የማይሰጥና ሁሉም ሰዎች በባህሪም ሆነ በአስተሳብም አንድ አይነት ናቸው ብሎ የሚያስብ የነበረ ሲሆን ፣ አሁን በዘመናችን ግን ልዩነቶች ትኩረትን እያገኙ መጥተዋል ። ጥሩ ሌሎችን የመረዳት አስተውሎት ያለው መሪ እነኚህን የስብእና ልዩነቶችን በሚገባ የሚረዳ ይሆናል ።

      ይሁን እንጂ በቡድናዊ ጠባብ አስተሳሰብ (Group-think) እንዳይታሰርም መጠንቀቅ አለበት ። ብዙውን ግዜ ይሄ አስተሳሰብ በአንድ ቡድን ውስጥ ለሰፈነ ቡድኑ እሚሰራውን ስህተት ለማየት ያስችለው የነበረውን እይታ ያጠበዋል፤ የምናደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው በሚል ቡድናዊ እሳቤ ፣ ገሀዳዊውን እውነታና ከውጪ የሚመጡ ስህተቶችን ነቀፌታዎችን ለመረዳት ሳይችል እንዲቀር ያደርገዋል ። ከውጪ ያለ ሰው በቀላሉ የሚያያቸውን እንከኖች ለማየት ያስችል የነበረውን እድል ያሳጣዋል ። ይህ ብቻ ሳይሆን ከእውነታው ውጪ የሆነ (Delusional)የሆነ አስተሳሰብ ይፈጠራል ። ይህም ወደ ቅዠት የቀረበ አስተሳብ ሲሆን ከገሀዳዊው እውነታ ውጪ የሆነ አስተሳሰብን መያዝን ያመለክታል ፤ መሪዎችም ሆኑ ቡድናቸው የዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ከሰረፀባቸው ወደ ውድቀትና ወደ ስህተት የማምራታቸው እድል እየሰፋ ይመጣል ።

መሪነትና ስራ ፈጣሪዎች (Leadership & Entrepreneurship)




ጥሩ መሪዎች ጥሩ (Enteperuner) ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ ። የስራ ፈጠራ ጥበብ ባለሙያውዎች አዳዲስ ነገሮችን የሚፈጥሩ ወይንም የነበረውን አሻሽለው የሚያቀርቡ ሰዎች ናቸው ። ነገር ግን የሁለቱ ችሎታ አንድ ላይ አብሮ በሚገኝበት ጊዜ ማለትም የመሪነትም (Enterperuner) ችሎታ ለአንድ መሪ ስራ መሳካት አስተዋጽኦን ያደርጋል ።

መሪነት የግለሰብ ብቻ ሳይሆን የህብረተሰብም ጭምር ነው ። ህዝቡ በተለይ በሀገር ጉዳይና ሰፊ ማህበራዊ ተሳትፎን በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ ቀዳሚ መሪ ሊሆን ይችላል። ግለሰብ መሪዎችም ያስፈልጋሉ ። በርካታ ግለሰብ መሪዎች ሀገራቸውን፣ የሚመሩትን የንግድ ተቋም ፣ ወዘተ ወደ ተሻለ ቦታ በመምራት የሚታወቁ ሰዎች አሉ ። በመሆኑም የግለሰብ መሪዎች ሚና በበጎም በመጥፎም ቀላል አለመሆኑን መዘንጋት የለብንም ።አንድ መሪ ለሌሎች ሰዎችን ችግር የሚረዳና ግላዊ የሆነው ህይወታቸውንም ጭምር የተሳካ እንዲሆን የሚጥር መሆን አለበት ።

በአሁኑ ወቅት በርካታ (Enterperuner) ኢኮኖሚያቸው እያደጉ ባሉ ሀገራት ውስጥ እየወጡ ይገኛሉ ።ለዚህም አይነተኛ ምሳሌዋ ቻይና ስትሆን እያደገ ባለው ግዙፍ ኢኮኖሚዋ በርካታ አንተርፐርነሮች እየወጡ ይገኛሉ ። ስራ ፈጣሪዎች እያገደ ባለ ምጣኔ - ሀብት ውስጥ በቀላሉ ድልን የማግ ኘት እድል ሲኖራቸው ፣ እድገታቸውን በጨረሱና እየተጓተተ ባሉ የምእራብ ሀገራት ግን አዳዲስ ስራ ፈጣሪዎች ወደየነበረውን ገበያ ድርሻ ነው እሚቀራመቱት ፣ ምክንያቱም  ሀብቱ እያያደገ ባለመሆኑ አዳዲስም ሆነ ነባር ኩባንያዎች በነበረው የገበያ ድርሻ ላይ በመወዳደር ፣ የተካረረ የገበያ ውድድር በማድረግ አንዱ አንዱን ከገበያ የማስወጣት ወይም እስከ መዋዋጥ ደረጃ የደረሰ የገበያ ውድድር ያደርጋሉ ። አዲስ የገበያ እድል ጠባብ ስለሆነ በነበረው ገበያ ላይ የገበያ ድርሻቸውን ለማሳደግ የጠነከረ ውድድርን ለማድረግ ይገደዳሉ ። 

መሪነትንና ኢንተርፐርነርሺፕ በጣም የተለያዩ ሲሆኑኢንተርፐርነርሽፕን ብንወስድ አንድ ኩባንያ በራሱ አንድ ነገርን መፍጠር ቢያቅትው እንኳን ፣ ከሌሎች መማር ይችላል ። በምእራቡ አለም ፣ ትላልቅ የሆኑ ኩባንያዎች ፣ ትናንሽና አዳዲስ የሆኑ ኩባንያዎችን በመግዛት አዳዲስ ሀሳቦችን መውሰድ ሲችሉ ፤ ለተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ምርምር የገንዘብ ድጋፍን በማድረግም እንዲሁ ፣ አዳዲስ ሀሳቦችን ማግኘትና ፈጠራዎችን ማመንጨት ይችላሉ ። ኢንተርፐርነርሽፕ ከገበያ ሊገዛ የሚችልም ነገር ሲሆን ፤ አንድ ኩባንያ የአዳዲስ ሀሳቦች ቢያልቁበት ፣ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችን ሊያመነጩ ከሚችሉ የምርምር ተቋማት ወይም ግለሰቦች ሊያገኝ ሲችል ፤ ይህ የሚያሳየው አንድ ድርጅት የሚያስፈልጉትን በገበያው ውስጥ ለመወዳደር የሚያስችሉትን አዳዲስ ሀሳቦችን ማግኘት ቢያቅተው በተለየ መንገድ ሊያገኝ እንደሚችል ነው ።

ትላልቅ ኩባንያዎች ከትናንሽ የተለያዩ የፈጠራ ሀሳቦችን (Patents)፣ የባለቤትነት መብቶችን (Copy write) በግዢ ማግኘት ይችላሉ ። ይህ በተለይም በኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በግልፅ የሚታይ ሲሆን ግዙፎቹ የኢንፎርሜሽን ኩባንያዎች አዲስ የተፈጠሩ (Start Ups) ኩባንያዎችን በመግዛት ወደ ራሳቸው በመቀላቀል ወይንም እራሳቸውን እንደቻሉ እንዲቀጥሉ በማድረግ ራሳቸው ሊፈጥሯቸው የማይችሏቸውን  ሀሳቦችን ከውጪ በቀላሉ የሚያገኙበትና ወደ ራሳቸው የሚያዋህዱበት ስልት ነው ።


ይህ ብቻ ሳይሆን የስራ ፈጠራ ጥበብ ባለሙያዎች (Enteperuners) ከነሱ ጋር ተመሳሳይ አላማ ያላቸውን ባለሙያዎችን ማሰባሰብ ይችላሉ ። ይህም በአለም ላይ ያተሱ ታላላቅ ኢንተርፐርነሮች የተለያዩ ምርቶችንና አገልግሎቶችን የፈጠሩት ሁሉን ነገር ብቻቸውን ሰርተው እንዳልሆነ ይታወቃል ። ዋናው የስራ ፈጠራ ጥበብ አላማው ሀብትን ወይንም እሴትን መፍጠር ነው ፣ ከእሱ ጋር ተመጣጣኝ እውቀትን ወይንም የበለጠ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች በማሰባሰብ አላማውን ማሳካት ነው ። 


ኩባንያዎች አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙት የውጭ አማካሪዎችንም ሊቀጥሩ ይችላሉ ። ነገር ግን አማካሪዎች ኩባንያውን ወይንም ድርጅቱን በቋሚነት የሚመሩ ሳይሆኑ ለአጭር ጊዜ ተቀጥረው ምክራቸውን ለግሰው የሚሄዱ ስለሆኑ የራሱን የድርጅቱን አመራር ሊተኩ አይችሉም ። ይህ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውም የአማካሪዎቹ ብቃት እንዳለ ሆኖ ምክራቸውም አስተዳደሩ ሙሉ ለሙሉ ተረድቶ ተግባር ላይውል የሚችልበት እድልም እንዳለ ሆኖ ማለት ሙሉ በሙሉ ተግባር ላይ ሊውል መቻሉም ሊያጠራጥር ይችላል ።

በአንፃሩ ግን መሪነት ከኢንተርፐርነርሽፕ የበለጠ ከበድ ይላል ምክንያቱን አንድ ነገርን ከመፍጠር ወይም አንድ መሪነት የበለጠ ውስብስብና ብዙ ነገሮችን ማገናዘብንና መረዳትን ስለሚጠይቅ ነው ። ይህ የሚያሳየን መሪነት በጣም እጅግ አስፈላጊና እንደ ኢንተርነርሽፕ ከውጭ ሊገኝ የማይችል ፣ እንዲሁም አማካሪዎችን በመቅጠርም ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ የሚቻል አይደለም ስለዚህ አንድ ድርጅት መሪዎች ይህንን መረዳት ሲኖርባቸው ፣ የራሳቸውን የመሪነት ብቃትን ማሳደግ በምንም የማይተካ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን መረዳት ያሻል ። በአንፃሩ ግን ኢንተርፐርነሮች አንድ ስራን ፈጥረው ለአስተዳደር ሰዎች በማስረከብ ያ ነገር ትርፍን እንዲያመጣና ቀጣይ እንዲሆን ማድረግ ይችላሉ ።

ብዙዎቹ ኢንተርፕርነሮችም በፈጠሯቸውና ከትንሽ አንስተው በገነቧቸው ኩባንያዎች ውስጥ ብዙም የማይቆዩ ሲሆን ፣ ነገር ግን የአስተዳደር ሰዎች ግን እነኛን በኢንተርፐርነሮቹ ሀሳብ የተፈጠሩትን ድርጅቶች በማስቀጠል ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲቀጥል ማስቻል ስራቸው ነው ። ለምሳሌ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን ብንወስድ ፣ እንዲሁ የአፕል መስራችን ስቲቭ ጆብስን ብንወስድ በጀመሯቸው ኩባንያዎች ውስጥ ለረጅም ጊዜ አልቆዩም ፣ ነገር ግን ጀምረውት ለአጭር ጊዜ ቆዩ እንጂ ሌሎች አስተዳዳሪዎች (Managers) ናቸው እነኚህን ድርጅቶችን ማስቀጠል የቻሉት ። ስለሆነም የድርጅቶቹ ፈጣሪዎች ኢንተርፐርነሮች ሲሆኑ ፣ ድርጅቱን እለት በእለት የሚያስተዳድሩት የአስተዳደር ሰዎች ናቸው ።


አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመሪነትን ጥበብንና ፣ ኢንተርፐርነርሽፕን ችሎታ አቀናጅተው የያዙ ሰዎች አሉ ፤ እነኚህም ሰዎች ቁጥራቸው ብዙም አይደለም ። ለምሳሌ የአፕል ሶፍትዌርና ኮምፒውተር መስራችና ባለቤት ስቲቭ ጆብስ ፣ እና ቢል ጌትስ የመሳሰሉ ሁለቱንም አጣምረው የያዙ ናቸው ፣ ኢንተርፐርነርም ነበረ ፤ እንዲሁም የድርጅቱ መሪዎችም ነበሩ ። ነገር ግን በዚህ አይነት ችሎታ የተፈጠሩ ሰዎች ቁጥራቸው እምብዛም አይደለም ።