Tuesday, November 6, 2018

justice system ethiopia



የኢትዮፒያ የፍትህ ስርአት የፍትህ ሥርአት ማሻሻያ  
ፀሃፊው ስሜነህ ተረፈ
የቀድሞው ጠቅላይ / መልካም አስተዳርን ለማስፈን ጥረት አድርገው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በፍትህ ስርአቱ ላይ ትኩረትን አለማድረጋቸው ሳይሳካላቸው እንዲቀር ምክንያት ሆኗል ፡፡ ከዚህ ቀደም በአቶ ለማ መገርሳ የተመራው ኦህዴድ በኦሮሚያ ክልል የፍትህ ስርአቱን መልሶ ያዋቀረ ሲሆን ይህም በፌደራል ቢደገም መልካም ነው ሲባል ነበር ፡፡ የአሁኑ ጠቅላይ / ዶ/ር አብይ የህግ ክፍተቶችን በመድፍን ወደ ስራ በመግባት ነበረባቸው ተብሎ በተደጋጋሚ ሲነሳ የነበረ ሲሆን እንደዚሁም መልካም አስተዳደርን ለመድፈን መቼም ቢሆን ከፍትህ ስርአቱ ላይ አይናቸውን መንቀል የለባቸውም ለቀድሞው / ሚር አቶ ሃይለማርያም አስተዳደር አለመሳካትና የህዝብ ቅሬታ ምንጮች በመሆን / ቤቶች ዋነኛ አሉታዊ አውዳሚ ሚናን መጫወታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው
በፌደራል ደረጃ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የፍትህ ስርአት ማሻሻያ እንደተጀመረ / ቤት አመራሮችን በመተካት ተጀምረዋል። እርምጃው የዘገየ ቢሆንም ለውጡ ግን አዋጆችን በማሻሻል መታገዝ አለበት በተለይም የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አዋጅ ሳይውል ሳያድር ሊሻሻል ይገባዋል። ይህ አዋጅ ይሻሻላል ጥፋትን የፈፀሙ ዳኞችን እስከ ወንጀል ድረስ ለመጠየቅ የሚያስችል ነው ተብሎ በአቶ ዳኜ መላኩ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም የት እንደደረሰ አይታወቅም አዋጁ።
አመራር በመለወጥ ብቻ ሳይወሰን 60 አመታት ያህል የቆዩትን የፍትሃ ብሄርና የስ//ህጉ እንዲሁም የወንጀለኛ መቅጫ የስ//ህጉ መሻሻል የሚገባቸው ሲሆን አዳዲስ መውጣት ያለባቸውም ማውጣት ለፍትህ አሰጣጥ አመቺ ያልሆኑ ነባር  ህጎችን መፈተሽ ያስፈልጋል። እንዲሁም ያመራር ለውጡ ወደ ታችኛው /ቤቶች አመራሮች ማለትም የመ/ ድረጃና ከፍተኛ /ቤት አመራሮች በነካ እጃቸው ይለወጡ።
/ሚር / አብይና አዲሲቷ የጠ/ፍ ቤት ፕ/ት በነካ እጃቸው ወደ ታች ያለው የስር ፍርድ ቤት አመራሮችን ማንሳት ይገባቸዋል ። የፍርድ ቤቶች ዳኝነት ተበላሽቶ የከፋ ደረጃ የደረሰው ባቶ ተገኔ ጌታነህ የጠ/ ቤት / በነበሩበት ወቅት ሲሆን በእርሳቸው የፕ/ትነት ዘመን በርካታ ፍርደ ገምድል ውሳኔዎች ተወስነዋል በርካቶችም በሙስና የተነካኩበትና ተጠያቂነት የጠፋበት ሁኔታ ነበረ። ከእርሳቸው በሁዋላ የተሾሙት አቶ ዳኜ መላኩም / ቤቱን ለማሻሻል ጥረትን አድርገዋል የጠ/ ቤቱ ፕሬዝዳንቶቹ ጥቅማ ጥቅምም እጅጉን ተሻሽሎአል ይሁን እንጂ አቶ ዳኜ በርካታ ቅሬታ የሚቀርብባቸውን የስር /ቤት አመራሮችን አልነኩም ስለዚህ የእርሳቸው ጥረት የሚፈለገውን ለውጥ ሳያመጣ ቀርቶአል። የአሁኑዋ / / መአዛ አሸናፊም በቶሎ የስር /ቤት አመራሮችን በማንሳት ስራቸውን መጀመር አለባቸው አለበለዝያ ከላይ የእርሳቸው ጥረት ብቻውን ለውጥን አያመጣም። አዋጆችን ማሻሻል በእጅጉ አስፈላጊ ሲሆን ይሻሻላሉ የተባሉ አዋጆችም በፍጥነት መሻሻል አለባቸው ፡፡
ይህ ብቻ አይደለም ህግን የመተርጎም እንደ ህገ መንግስታዊ / ቤት ሆኖ ስልጣን የተሰጠው ለፌዴሬሽን / ቤት መሆኑ በራሱ ለህግ አተረጓጎም ችግርን ፈጥሯል ፌዴሬሽን ም/ ቤት ራሱ የአስፈጻሚው የገዢው ፓርቲ አካል ሆኖ መልሶ ከፍ / ቤቶች በላይ ህግ ተርጓሚ መሆኑ ህገ መንግስታዊ ትርጉም ያስፈልጋቸዋል የሚባሉ ጉዳዮች ወደ /ቤቱ የሚሄዱ ሲሆን የህግ አውጭውን የአስፈጻሚውንና የህግ ተርጓሚ የመንግስት አካላት ስራን የሚያደበላልቅ ነው ፡፡ ከዚህም አልፎ ስራውን የጀመረው የህገ መንግስታዊ አጣሪ ኮሚሽን የተባለው ተቋም ስራ መጀመሩ መልካም ሲሆን በርካታ የህግ ክፍተቶች ባሉት የፍትህ ስርአቱ ፍርደ ገምድል ውሳኔ ተወስኖባቸው አጣሪ ኮሚሽኑ ያስተካከላቸው እንዳሉ ይታወቃል ይሁንና ይህ ተቋም የበላይ ሃላፊዎቹ ፍርዱን የፈረደው ተቋም የጠ/ / ቤት ሃላፊዎች መሆናቸው ራሱ ፍርድን የሰጠው ሰው መልሶ ቅሬታውን የሚያየው መሆኑ አሁንም የአጣሪ ኮሚሽኑን ነጻነቱንና ተጠያቂነት አጠያያቂ ያደርገዋል ስለዚህ ይህ ሁሉ ጉዳይ የአዋጆች መሻሻልንና የአዲሲቱዋ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ የቤት ስራ ይሆናል ማለት ነው ፡፡

Friday, November 2, 2018

የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ አስፈላጊነት በኢትዮፒያ

የምጣኔ ሃብት ማሻሻያን የማድረግ አስፈላጊነት " ፦

የፋይናንስ ዘርፉ ለኢኖቬሽን (ለስራና አዳዲስ ቴክኖሎጂ ፈጠራ) እንቅፋት መሆኑ ተገለፀ።  የሃገራችን የፋይናንስ (በተለይም የባንክ፥የኢንሹራንስ) ዘርፍ በአፍሪካ አቅም እንኩዋን ተወዳዳሪ አይዶለም። ቅርባችንን ኬንያን ብንወስድ እንኩዋን ያደገ የፋይናንስ ዘርፍ ያላት ሲሆን ያደገ ያክስዮን ገበያ እንዲሁም የሃገሪቱ ባንኮችና ኢንሹራንስ ድርጅቶች በአፍሪካ ተወዳዳሪ ሲሆኑ በምስራቅ አፍሪካ ደቡብ ሱዳንና ኡጋንዳ ድረስ ሄደው መስራት የሚሉ ባንኮች እና የፋይናንስ ተቁዋማት ባለቤት ነች። ብድር ማግኘትም የኛን ሃገር ያህል ከባድ አይደለም በሞባይል ስልኮች የባንክ ብድርን መጨረስ እሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅም አላቸው። በሃገራችን GDP የኬንያን ያለፈ ሲሆን በውጭ ኢንቨስትመንት በመሳብ ኢትዮፒያ ኬንያን አልፋለች። ይህ ሁሉ ግን ተወዳዳሪ የሆነ የባንክ ስርአትን ይፈልጋል። ይሁንና ገዥው ፓርቲ የዚህን ዘርፍ ክፍት ለማድረግ ፈቃደኛ ካለመሆኑም በላይ ሃገሪቱ የWTO ያለም የንግድ ድርጅት አባል እንዳትሆን እንቅፋት ሆኖአል።
በርካታ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ባገሪቱ ተከፍተዋል እነርሱም ያገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ያካባቢውንና ያለም አቀፍ ገበያን ይፈልጋሉ ምርቶቻቸውን ለመሸጥ። የWTO አባል መሆን ኢንዱስትሪዎቹ በቀላሉ የአለም አቀፍ ገበያ ውስጥ እንድትገባና በከፍተኛ የውጭ ብድር የተሰሩት ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመጠቀም ሃገሪቱ ብድራን እንድትከፍል ያስችላታል። ነገር ግን ፓርኩን መስራት ብቻ ሳይሆን ማሻሻያዎችን በማድረግ ፓርኮቹና ምርቶቻቸው በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስችላቸዋል ።

Wednesday, October 31, 2018

ያ ትውልድ

በ ያ ትውልድና በ ተራሮችን ያንቀጠቀጠው ትውልድ መሃከል ልዩነቱን ያውቃሉ ?

Tuesday, October 9, 2018

capitalism እና ውጤቱ

የካፒታሊዝም ስርአት በሃብት ማሰባሰብ ውስጥ ቁልፍ ሲሆን ይህ ስርአት ሃብትን ወደ ሃብታኖች እጅ እንዲከማች ሲያደርግ ፤ ከብዙሃኑ ግን እይውደኽየ እንዲሄድ ያደርጋል።
ይኽውም squeezed out the muddle classes ተብሎ እኒነቀፍ ሲሆን የካፒታሊዝም ስርአት ከፍተኛ ደረጃ በሚደርስበት ወቅት የሚህክን ነስ ።

Saturday, October 6, 2018

secret societies

the gods of our fathers were devils የሚል ጥንታዊ አነጋገር አለ ፥ መዝሙረ ዳዊት " የአህዛብ አማልክት አጋንንት ናቸው" ።

ኢህአዴጋውያንና ስፓርታውያን

የግዥው ፓርቲ ኢህአድልግ ከጥንታዊው የግሪክ ስፓርታውያን ጋር ተመሳሳይ ታሪክ እንዳለው ያውቃሉ ?
ይሁንና በታሪክ ከጥንት ግሪካውያን ስፓርታውያን በወታደራዊ ሃይላቸው ይታወቁ ነበረ። በተለይም የገነቡት እግረኛ ሃይል። በዘመኑ በዓለም ተወዳዳሪ አልነበረውም ግሪክ ከፐርሽያ ጋር ባደረገችው ጦርነት የባህር ሃይሉዋ ከፐርሽያን ድል ካደረጉ በሁዋላ ወደ ባህር ንግድ በማዞር ህልውናዋን ስታስጠብቅ ስፓርትስ ግን ይህን ጦርነትን ብቻ የሰለጠነ ሃይሉዋ ወደ ሌላ ምርታማ ዘርፍ ማዞር ስላልቻለች እንድው አቴናውያን ህልውናዋን ማስጠበቅ ስላልቻለች ልትከስም በቅታለች። 

Friday, October 5, 2018

Nation State

ወዳ ማርኛው ሲመለስ መንግስትና ሃገረ መንግስት ማለት ነው።