Friday, May 17, 2013

ጦርነትና የአለም ሰላም

ሰላም የሚመጣው አንዱ መንገድ በሰዎች መሀከል እርስ በእርስ መተዋወቅና መግባባት ሲኖርና ልዩነቶችን ማክበር ሲቻል ነው ። ለምሳሌ ቱሪዝም መጓዝን ስለሚጨምር አእምሮን ያድሳል ፣ በሩቅና ሩቅ አካባቢ ያሉ ሰዎችን ሳይቀር ያስተዋውቃል ። ብዙውን ግዜ ልዩነቶችን ቀለል አድርገን ብንወስዳቸውም ልዩነቶች ቀላል አይደሉም ። በሰዎች መሀከል በርካታ ልዩነቶች አሉ ። በአስተሳሰብ ፣ በሀይማኖት ፣ በፆታ ፣ በሀብት ፣ በትምህርት ደረጃ በመሳሰሉት ልዩነቶች አሉ ። እነኚህን ልዩነቶች መረዳት በጣም አስፈላጊ ሲሆን ሰላም የሚሰፍነው እነኚህን ልዩነቶች በመረዳት ፣ በማወቅና በማክበር ነው ።

ሌላው ደግሞ ግልፅ የሆነ ልዩነትን የሚፈጥሩ ለምሳሌ የጥቅም ግጭቶች ፣ የመሳሰሉት ደግሞ ይበልጥ ነገሩን መረዳትና አርቆ ማሰብን የሚፈልጉ ናቸው ። according to Plato peace exists only in name . «ሰላምን የሚፈልግ ለጦርነት ይዘጋጅ» የሚል የቆየ አባባል አለ ።

በነገራችን ላይ በሰዎች መሀከል ያሉ ልዩነቶች በአግባቡ ካልተያዙ ሊያስከትሉት የሚችሉት መዘዝ እጅግ ከባድ ነው ። እንሰሶችም እርስ በእርሳቸው ይጋደላሉ ፣ ይበላላሉ ። በአለም ላይ ለቁጥር የሚያታክቱ ዝርያዎች ተፈጥረል በርካቶቹም በእርስ እርስ ውድድር ፣ ወይም በተፈጥሮ አደጋ ጠፍተዋል። የሰውን ልጅ እርስ በእርሱ የሚያደርገውን ውድድርና ፉክክር አደገኛ የሚያደርገው ነገር የሰው ልጅ ራሱንና አለምን የሚያጠፋ የቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ የደረሰ ፍጡር በመሆኑ ነው ። ዋነኛው የጦርነት መንስ ኤ ሀብትን ፣ የተፈጥሮ ሀብትን ለመቆጣጠር ነው ይባላል ። ነገር ግን በዚህ ብቻ አይወሰንም የሰው ልጅ ድብቅ የሆኑ ስሜቶቹን ለመወጣትምና ለማርካትም ጭምር ወደ ጦርነትን ያስነሳል ። ለምሳሌ ፣ ቅናት ፣ በቀል ፣ ጥማት ፣ ለበላይነት ስሜት ሀብትን ለመቆጣጠር በተጨማሪ ተብለው የሚደረጉ ጭምር ናቸው ።

እንሰሶች ግፋ ቢል እርስ በእርስ ቢበላሉ ሲሆን በዚህች ምድር በሚሊየን በሚቆጠሩ አመታት ውስጥ ራሱንና አለምን ለማጥፋት የሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅምና ብቃት ላይ የደረሰ ብቸኛው ፍጡር ሰው ብቻ ነው ። ከዚህም ሌላ ደግሞ ሰው ማሰብ የሚችል ብቸኛው ፍጡር በመሆኑ ለምድሪቷና በሷም ላይ  እንሰሳትና ህይወት ላላቸው ፍጡራን የሀላፊነት ስሜት ሊኖረው ይገባል ። ለራሱም ሆነ ለሌሎቹ ፍጡራንና ለምድሪቷ ደህንነት ሀላፊ መሆን አለበት እንጂ ወደ ጥፋት መሄድ አይገባውም ።

ጦርነት በሁለት ወይንም ከዛ በላይ በሆኑ ወገኖች መሀከል ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊና ድርድር በተሞላበት መንገድ መፍታት ሳይችሉ ሲቀሩ የሚገቡበት ነገር ነው ። ቮን ክላውሽዊትዝ የተባለ ጀርመናዊ የጦርነት ስልት ነዳፊ እንዳለው ከሆነ ጦርነት የፖለቲካ ቅጥያ ነው ። ይህም ማለት ልዩነቶች በፖለቲካና በድርድርና በዲፕሎማሲ ሊፈቱ ካልቻሉና የመጨረሻው መፍትሄ የማግኛው መንገድ ጦርነት ይሆናል ። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ካለው ዘመናዊ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ አንጻር ጦርነቶች እጅግ አውዳሚ ናቸው ። ቀድሞ በአንደኛውና በሁለተኛው የአለም ጦርነቶች ሲነፃፀሩ እነንኳን ከአንደኛው የአለም ጦርነት ይልቅ የሁለተኛው የአለም ጦርነት እጅግ አውዳሚ ነበረ ።

አንድ ጦርነት ድልን እንዲያመጣ ፖለቲካው ትክክል መሆን አለበት ። ጦርነት የፖለቲካ ተቀፅላ የሆነ ነገር ነው ። ፖለቲካው የተሳሳተ ከሆነ ጦርነቱ ድልን አያመጣም ። በሁለት ሀይሎች መሀል የአስተሳሰብ ፣ የጥቅም ፣ የአላማ መለያየት ሲኖርና አንዱ የአንዱን ህልውና ለመቀበል ፍላጎት ከሌለው ያ ልዩነታቸው በጦርን ብቻ ሊፈታ ወደሚችልበት አቅጣጫ ካመራ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ጦርነት አይቀሬ ይሆናል ። በዚህም ወቅት ጦርነትን ለሌላ ጊዜ ማሸጋገር ነው እንጂ ማስቀረት አይቻልም ማለት ነው ።

አንድ ሀገር የፈለገ ሀብታም እና ዘመናዊ የጦር መሳሪያን የታጠቀ ቢሆንምና ፣ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ባለቤት ቢሆንም ፣ በአለም ላይ በተሳሳተ የፖለቲካ አላማ የተደረጉ ጦርነቶች በሽንፈት ተደምድመዋል ። ለዚህም አይነተኛ ምሳሌ የሚሆኑ በርካታ ጦርነቶች አሉ ። ለምሳሌ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ናዚዎች በተሳሳተ አለምን የመቆጣጠር ስሌት ተነሳስተው ፣ እንዲሁም በዘር ላይ የተመሰረተ ዘረኛ ስርአትን በአውሮፓ ለመትከል ባደረጉት ጦርነት ምንም እንኳን ዘመናዊ የጦር መሳሪያና ቴክኖሎጂ የነበራቸው ቢሆንም መጨረሻቸው በሽንፈት ተደምድሟል ።

ሌላ ምሳሌ የሚሆነው ምንም አንኳን አሜሪካን የሁለተኛውን የአለም ጦርነትን ብታሸንፍም ፣ በቬትናም ግን ድል አልቀናትም ። ለዚህም ምክንያቱ ከራሳቸው ከቬትናማውያን ፍላጎት ውጪ ራሷ የፈለገችው መንገድ የራሷን ስርአት ለመትከል በመነሳቷ ፣ ምንም እንኳን ግዙፍ የጦር ሀይልን ብታዘምትምና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቬትናማያውያን ህይወት ቢጠፋም ድልን ልትጎናፀፍ አልቻለችም ከ ዚያ ይልቅ በሽንፈት ለቃ ለመውጣት ተገዳለች ፣ በኢራቅም እንዲሁ ፣ በኢራቅ የውስጥ ጉዳይ ገብታ የመንግስት ለውጥን «ሪጂም ቼንጅ» አካሂዳለሁ ብላ ብትገባም የሳዳም ሁሴንን መንግስት ማስወገድ ብትችልም ፣ በኢራቅ ከተሞች ላይ የቦምብ ውርጅብኝ የወረደባቸው ሲሆን ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራቃውያን ባለቁበት በዚህ ጦርነት አሜሪካ በሁሉም ኢራቃውያን ዘንድ ጥላቻን በማትረፏ ፣ ከጥቂት አመታት በኋላ ግን ኢራቃውያን ለቀው እንድትወጣና ጠይቀዋት ጥያቄያቸውን ሳትወድ በግድ ተቀብላ ለቃ ወጥታለች ። አምባገነኑን ሳዳም ሂሴንን ለማስወገድ ከባድ በሀብትም ሆነ በወታደሮቿ ህይወት ከባድ ዋጋን ብትከፍልም አምባገነኑን በማስወገዷ ግን ምስጋናን ግን አላገኘችበትም ። ይህ ብቻም ሳይሆን በአለም ላይ ያላትን ተሰሚነትንና አሳጥቷል ፣ ለዚህም በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንድትከሰስና እንድትወገዝ ስላደረጋት በመልካም ስሟ በኩልም ኪሳራን አስከትሎባታል ።

ስኬታማ ከሆኑ ጦርነቶች ብንወስድ ለምሳሌ የኮርያን ጦርነትን ብንወስድ የሰሜን ኮርያ ደቡብ ኮርያን ወርሮ ስለነበረ አሜሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኩል ደጋፊ ሀገሮችን አስተባብራ የሰሜን ኮርያን ወራረ በመመከትና በድንበሩ እንዲቆም ማድረጓ ፣ በድል የተደመደመ ሆኖ አልፏል ። እንዲሁም ሳዳም ሁሴን ኩዌይትን በወረረበት ወቅት እንዲሁ አሜሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኩል ሳዳም ሁሴንን ከኩዌይት ማስወጣት ችላለች ፣ ይህም ትክክለኛ የሆነና በአለምም ሆነ በአረብ ሀገራት ጭምር ድጋፍን ያገኘ ነው ። ስለዚህ ጦርነት የፖለቲካ አላማው ትክክል ከሆነ በድል የሚደመደም ሲሆን የፖለቲካ አላማው የተሳሳተ ከሆነ ግን በሽንፈት የመደምደም እድሉ ሰፊ ነው ።  

ጦርነት ከድል በኋላ ፖለቲካው መመለስ አለበት - እንጂ በጦርነቱ ድል እዚያው መቆም የለበትም ። ይህም ማለት ጦርነቱ ድል በኋላ የፖለቲካ ስራን በመስራት የፖለቲካ ስምምነትንና በረጅም ጊዜ በጋር ሰላማዊ ህልውናን ሊያስጠብቅ የሚችል መሆን አለበት ። ለምሳሌ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ከጃፓን ጋር በዚሁ መንገድ የጃፓንን ንጉስ ባለማዋረድ ፣ እንዱሁም በአውሮፓም ምንም እንኳን ናዚዎችና ፋሺስቶች ቢሸነፉ አሜሪካ ለአውሮፓውያን ምጣኔ - ሀብታቸውን ለማንሰራራት የገንዘብ ድጋፍን በማርሻል እቅድ አማካይነት በመስጠት አውሮፓ እንዲያንሰራሩ ከነበሩበት ምጣኔ - ሀብታዊ ድቀት እንዲወጡ ማድረግ ችላለች ። በዚህም አውሮፓውያንም ሆኑ ጃፓናውያን በሁለት እግራቸው ተመልሰው በመቆም የአሜሪካ ጠንካራ አጋር መሆን ችለዋል ። ይህም በጦርነቱ የተገኘውን ድል ወደ ፖለቲካዊ ድል የመለወጥ ስራን በመስራቷ አሜሪካ በተሳካ ሁኔታ ወታደራዊውንም ሆነ ፖለቲካዊውን ፈተና መወጣት ችላለች ። ከድል በኋላ የፖለቲካ ስራን አለመስራት ማለት ለሌላ ጦርነት መዘጋጀት ማለት ፣ ነው  ለሌላ ጦርነት በርን እንደ መክፈት ይቆጠራል ። ብዙውን ጊዜ በጦርነት ድልን የተቀዳጁ ሀይሎች ድላቸውን ኦንደ እንደ የመጨረሻ አድርገው ከቆጠሩ ውሎ አድሮ ተሸናፊው በበቀል ስሜት ለሌላ ጦርነት እ ንዲዘጋጅና የሚጋብዝ ነው ።

ምንም እንኳን ክላውሽዊትዝ ጦርነት የፖለቲካው ተቀጥያ ነው ቢልም ፤ የግድ የፖለቲካ ልዩነቶች ወደ ወታደራዊ ግጭት ያመራሉ ማለት አይደለም ። ነገር ግን የጠላትነት ስሜቱ እንዳለ ሆኖ ነገር ግን አውዳሚ የሆነ የፊት ለፊት ግጭት ግን ላይ ላይካሄድ ይችላል ። ይህም እጅግ የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎች መፈልሰፍ የጦርነትን ገፅታ ለውጦታል ማለት ይቻላል ። ለዚህም አይተነኛ ምሳሌ የሚሆነው የኒውክሊየርና የአቶሚክ ቦምቦች መፈብረክ ነው ። እነኚህ የጦር መሳሪያዎች የርእዮተ - አለም ልዩነት የነበራቸውና እንደ ጠላትና ተፎካካሪ እርስ በእርሳቸው ይተያዩ የነበሩትን አሜሪካንና ሶቭየት ህብረትን ብንወስድ ፣ በመሀከላቸው የነበረው ልዩነት እጅግ የሰፋ የነበረ ቢሆንም ፣ ነገር ግን  ሁለቱ ሀገራት ፊት ለፊት ጦርነት ተዋግተው አያውቁም ። ለዚህም ምክንያቱ ሁለቱም ሀገራት እጅግ አውዳሚ የሆነው የ ኒውክሊየር የጦር መሳሪያን የታጠቁ ስለነበሩ ነው ። 

የቀዝቃዛው ጦርነት ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ ሲሆን ይህም የታጠቁት እጅግ አውዳሚ እና የተራቀቀው የጦር መሳሪያ ፊት ለፊት ለመጋጠም አግዷቸው ቆይቷል ። በእርግጥ በሁለቱ መሀከል ጦርነቱ በሌላ መንገድ ቀጥሎ ነበረ ። ለምሳሌ በቀዝቃዛው ጠርነት ወቅት የፕሮፓጋንዳ አንዱ ላይ ያካሂድ የነበረ ሲሆን በሌላ ሶስተኛ አገርም እንዲሁ በተዘዋዋሪ በቀጥታ ሳይሆን በሌሎች አገራት ግጭቶች ተደርገዋል ። ይህም ሁለቱም ቀይ መስመር የተሰመረ ሶሆ ሲሆን ያንን ቀይ ሰምመር  መስርመር ሁለቱም ሳያልፉት ቆይተዋል ። (Deterrance) ወይንም ማገድ ወይም መከልከል የሚለው ፅንሰ ሀሳብ ነው ።   

ኢራንን ብንወስድ ግን እስራኤሎች እንደገለፁት ጉዳዩ እንደ ቀዝቃዛው ጦርነት በማገድ ብቻ ይዘጋል የሚባል አይደለም ። የኢራን የኒውክሊየር የጦር መሳሪያ እስራኤልንና ምእራባውያንን የሚያሳስብበት ምክንያት በሀይማኖታዊ ፍልስፍና በሚመራ መንግስት እጅ የዚህ አይነት አደገኛ መሳሪያ መግባት ማለት ፣ በርእዮተ - አለም ልዩነት ካላቸው ሀራት ይልቅ የበለጠ አደጋን እንደሚጋብዝ በመረዳትም ጭምር ነው ። በአንፃሩ ሶቭየት ህብረቶች አንዳንድ ጊዜ ከርእዮተ - አለማቸው ይልቅ ህልውናቸውን ማቆየትን ስለሚመርጡ የተፈራው የኒውክሊየር ግጭት ሳይካሄድ ቀርቷል ። 

ሌላው አሁን የዘመናችን የጦርነት ገፅታ ደግሞ ጦርነት በፕሮፓጋንዳ ፣ በመገናኛ ብዙሀን ፣ በጋዜ ጦችና በመሳሳለው የሚካሄድ ነገር ነው ።

ጦርነት በማታለል ላይ የተመሰረተ ሲሆን ፣ በጦርነት ወቅትም የተጋነነ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል ። ሌላው ደግሞ የጦርነት ውጤት የሚጨበጥ ነገር አይደለም ፤ ምክንያቱም በጦርነት ወቅት ሁለቱ ተዋጊ ወገኖች ሊዳከሙና ሶስተኛ ሀይል ተጠናክሮ ሊወጣ ይችላል ። በዚህም ውጤቱን የሶስተኛ ወገን ተጠናክሮ መውጣት ሲያስከትል ፤ በጦርነቱ የተሳተፉ ወገኖች በፖለቲካም ሆነ በሌላው ተዳክመው ሊወጡ ይችላሉ በተለይም በአሁኑ ዘመን ፊት ለፊት የሚደረጉ ጦርነቶች አውዳሚ እንደሚሆኑ ግልፅ ነው ።

ሌላው ለአለም ሰላም ጠንቅ ሊሆን የሚችለው አለምን የሚለውጡ ወይንም ምንግዜም ቢሆን ሊለውጡ የሚፈልጉ ሰዎች መኖር ነው ። ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲቀየር ወይም ያልተመቻቸው ሰዎች በሁለት መንገድ አለምን ለመለወጥ ሊነሱ ይችላሉ ። አንደኛው በሀሳብ መለወጥ ሲሆን ሌላው ደግሞ በተግባር መለወጥ ነው ። የሀሳብ ሰዎች ብዙውን ጊዜ አዲሱን ሀሳባቸውን በፅሁፍ ፣ ሌሎችን በማስተማር ፣ በመሳሰለው ሀሳባቸውን በመግለፅ ብቻ ሲያቆሙ ሌሎች ግን በዛ ብቻ ሳይመለሱ አዲሱን ሀሳባቸውን ሌላው እንዲቀበለው ከመንቀሳቀስ አልፈው ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ይገባሉ ። አለምን በተግባር ለመለወጥ የሚነሱ ሰዎች እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ተቃውሞ ይገጥማቸዋል ። እንደ ፕሌቶ አባባል ሰላም ያለው በስም ብቻ ነው

የመሪዎች ባህሪ እንዲሁም የተወላደገ አላማ ራሱ የአለምን ሰላም አደጋ ውስጥ ሊጨምር ይችላል ። ይህ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ መሪዎች የህዝቡን አትኩሮት ለማስቀየር ፣ እንዲሁም ውስጣዊ ችግሮች ሲያጋጥማቸው ከእነኛ ችግሮች ጊዜያዊ ማስተንፈሻን በመሻት  ጦርነትን ሊሹት ይችላሉ ። ይህ ስልት በታሪክ በተደጋጋሚ የታየና  በርካቶች የፖለቲካ ስልጣናቸውን ለማራዘም ሲጠቀሙበት የቆዪ የተለመደ ስልት ነው ። ነገር ግን ጦርነትን እስካስከተለ ድረስ ግን ሊከፍል የሚችለው ዋጋ ከባድ እንደሚሆን መገመት ይቻላል ። 

በአለም ላይ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ እንኳን የተካሄዱትን ጦርነቶች ብንመለከት እንደ አንደኛውና ሁለተኛው የአለም ጦርነት መጠነ ሰፊና ብዙ ሀገራትን በአንድ ጊዜ ያካተቱ አይሁኑ እንጂ የበለጠ አውዳሚ ሊሆኑ ይችሉ የነበሩ ናቸው ፣ በ960ቹ ተከስቶ የነበረው የኩባው የሚሳይል ቀውስ እንኳን ብንጠቅስ አለምን አስግቶ የነበረ ነው ። በቅርቡ እንኳን አሜሪካ በቢንላደን ጋር በገባችው ጦርነት እንኳን ከ3 ትሪሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ አውጥታለች ሌላው የፖለቲካና የወታደሮች ህይወት ኪሳራ ሳይጨመርበት ማለት ነው ።

ሌላው ቻይናዊ የስትራቴጂ አዋቂ ሱን ዙ በመባል ሲሆን የጦርነት ጥበብ የተሰኘው መጽሀፉ በአለም ላይ ሰፊ ተነባቢነትን ያገኘ ነው ። የሱን ዙ ጽሁፍ ላይ በመመስረት የአሜሪካ ወታደራዊ መኮንኖች ስልጠና የሚወስዱበት ሲሆን የቻይናን መሪዎች ባህሪ እና የዛችን ሀገር ፖሊሲዎችን አካሄድን ሊጠቁም ይችላል ተብሎ የሚገመት ነው ለመረዳት ያስችላል የሚባል ነዉ ።

በጎ ነገሮች እንዳሉ ሆኖ ፣በአለም ላይ በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ልዩነቶች እየሰፉ ይገኛሉ ። አንዳንዴ ሲታሰብ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በአደገኛው የታሪክ ምእራፍ ላይ እንገኛለን ቢባል ማጋነን አይሆንም ።በሀገሮችና በሀገሮች እንዲሁም በአንድ አገር ውስጥ እንኳን ሳይቀር ልዩነቶች ተካረው ወደ አደገኛ ምእራፍ ሲሸጋገሩ ማየት የተለመደ እየሆነ መቷል ። በፖለቲካ ፍልስፍና ፣ በሀይማኖትና በሌሎችም ጉዳዮች በአለም ላይ የሚታዩ ልዩነቶች ወደ ተካረረ ደረጃ በመድረስ ላይ ይገኛሉ ። የቀዝቃዛ ው ጦርነት ፣ እንዲሁም በሀገሮች መሀከል የፊት ለፊት ወታደራዊ ግጭት በሌለበት ሁኔታ የአለም ሀገራት ለጦር መሳሪያ የሚያወጡት ወጪ በአለም ታሪክ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ።  

ስቴፋን ሀውኪንስ የተባለ የፊዚክስ ሳይንቲስት እንደሚለው የሰው ልጅ ከአሁን በኋላ ምድርን ትቶ ሌሎች የጠፈር አካላት ላይ መስፈር መጀመር አለበት ። ወደ ሚቀጥለው ክፍለ ዘመን መሸጋገር ከፈለገ እንደ ሀውኪንስ አባባል የሰው ልጅ ሁሉንም እንቁላሎቹን በአንድ ቅርጫት ውስጥ ማስቀመጥ የለበትም ። የተፈጥሮ አደጋዎችን እንኳን ትተን የምንኖርባት ምድር ከዚህ በፊት በታሪክ ታይተው የማይታወቁ በርካታ ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተጋረጡባት ይገኛሉ ። ከአካባቢና ከአየር ንብረት መበከል ጀምሮ አስጊ የሆነ የኒውክሊየር ጦርነት ስጋቶች እየተደቀኑ ነው ። 

በዘመናዊው የአለማችን ታሪክ የናዚዎችን ያክል አለምን ለጥፋት የዳረገ የለም ። በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተፈጠሩ እጅግ መጥፎ ከሆኑ መንግስታት ዘርፍ የሚመደቡት ናዚዎች በሁለትና በሶስት አቅጣጫ ጦርነትን በመክፈት ከጦርነት ስትራቴጂ ውጪ በሆነ መንገድ በርካታ አውዳሚ ጦርነቶችን በመክፈት እንግሊዝን በአውሮፕላን በመደብደብና ሩስያን በመውረር ፣ ከጦርነቱ ጋር ንክኪ የሌላቸውን ሲቪል የአውሮፓ አይሁዳውያንን በግፍ በመጨፍጨፍና ተግባራዊ ሊሆን የማይችል የዘረኝነትን ጥንስስ በመጠንሰስ አለምን አጥፍቶ ለመጥፋት ደረጃ አድርሰው ነበረ ። በተመሳሳይም ፋሺስት ኢጣሊያም በዛው አይነት መንገድ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከተማ ብቻ 275,000 ኢትዮጲያውያንን በየጥቂት ቀናት ውስጥ በመጨፍጨፍና ሌሎችንም በርካታ ግፎችን ሰርታለች ። አስገራሚው ነገር በአዲስ አበባና እንዲሁም በ ሊቢያ ከባድ ጭፍጨፋን የፈፀመው ግራዚያኒ በጣሊያን አንዲት ከተማ ሀውልት እንዲቆምለት መደረጉ  ነው ።

የአሁኑ ወቅት በርእዮተ - አለም ፣ በፍልስፍናና በኢኮኖሚ ጥቅሞች ልዩነቶች የሚደረጉት ትግሎች እንደተለመደው ረቀቅ ባለ መንገድ ቀጥለዋል ። በአሁኑ ጊዜ በተለይ ሚዲያዎች ትልቅ መሳሪያ ሆነዋል። ይህንንም ለመረዳት ሚዲያውን የመረዳት ብቃትን (ሚዲያ ሊትሬት) መሆንን ሲጠይቅ እንዲሁም በርካታ የሚዲያ ታክቲኮችን የመረዳት ችሎታን ይጠይቃል ። በተለይ የግዙፍ የሚዲያ ተቋማትና የኢንተርኔት መገናኛ ባለቤትቶች የሆኑት የምእራብ ሀገራት በመገናኛ ብዙሀን ጡንቻቸዉን በመጠቀም በማይፈልጓቸው ሀገራት ላይ ጫናቸውን በማሳረፍ ላይ የገኛሉ።

በአጠቃላይ ሲታይ ግን በየመሀከሉ የሚታየዉ ሰላም የሚቀጥለዉ ጦርነት መዘጋጃ ነዉ ቢባል ማጋነን አይሆንም ። ይሁን እንጂ ለአለም ሰላም ዋስትና የሚሆነው ነገር እጅግ በርካታ የጦር መሳሪያ ማከማችት፣ግዙፍ ወታደራዊ ተቋም መገንባት ሳይሆን ሰዎች እርስ በእርስ መተዋወቅና መግባባት ፣ ሀሳብ ምንግዜም አደገኛ የሆነ ነገር እንደመሆኑ አስተሳሰባዊ እና ፍልስፍናዊ ልዩነቶን በጣም አክብዶ አለመውሰድ ናቸው ። ለዚህም አይነተኛ ማሳያ የሚሆነው በመካከለኛው ምስራቅ የሚታየው ጉዳይ በዛ ክልል መልካም ነገርን ጠቋሚ አይደለም ።

ነገር ግን ጦርነትን ከመጀመር ይልቅ መጨረሱ ከባድ ነው ። እንኳም ዲሞክራሲ በሌለበት በዲሞክራሲ ስርሰአት ውስጥ እንኳን ይሄን ማድረግ ከባድ ነው ። አሜሪካ በቬትናምም ሆነ በኢራቅ የጦርነት ወቅት ጦርነቱን  የጀመሩት መሪዎች ከተወገዱ በኋላ ነው ፣ በአዳዲስ እና ከተቃራኒው ፓርቲ በመጡ መሪዎች አማካይነት ብቻ ነው ጦርነቶቹ ሊጠናቀቁ የበቁት ። በኢራቅ ጦርነት ወቅት ፕሬዝዳንት ቡሽ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ ጦርነቱን ለማስቆምም ሆነ ፣ ሰራዊታቸው ለማስወጣት ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው ፣ ቀጥሎ በተደረገው ምርጫ ፣ በኦባማ አስተዳደር አሜሪካ ከኢራቅ ልትወጣ የቻለችው እንዲሁም ፣ ከአፍጋኒስታንም ያላትን ወታደራዊ እንቅስቃሴንም ለማቆም ቃል የገባችው ።   

ለምሳሌ የጃፓኑ መሪ ጄኔራል ኮረቺት አናሚ ምንም እንኳን የመኖር እድል ቢኖረውም ። የንጉሱ የክብር ዘብ አዛዥና የንጉሱ ረዳትም ነበር ። በመጨረሻም የጃፓን ጦር ሚኒስትር ሆነ ። በጄኔራል ማካርተር የሚመራው የአሜሪካን ጦር በአሸናፊነት እየገሰገሰ ነው ። ጃፓኖች በጦርነት ወቅት እጅግ አስደናቂ ገድልን ጀብድን የሚያጋንኑና ሞትን የሚንቁ ሲሆኑ ። ይሁን አንጂ የባለቃል ኪዳን ሀጋራት የጃፓንን ጦር እየቆራረጡ ደምስሰውታል ። ይሁን እንጂ ለጃፓን መሪዎች እጅ የመስጠቱን ሀሳብ አንቀበልም ብለው ነበር። ስለዚህ ጃፓን ያለምንም ድርድር እጇን እንድትሰጥ የተጠየቀች ይሁን እንጂ ጃፓን እምቢ በማለቷ ሁለቱ የጃፓን ከተሞች በአቶሚክ በቦምብ ተደበደቡ ።

የጃፓን የጦር አዛዦችም እጃችንን ከምንሰጥ ሞትን እንመርጣለን አሉ ። እንደ አማልክት የማየው ህዝብ 10000 የሚሆን ህዝብ እጁን ከሚሰጥ ራሱን አጠፋ። የጦር ሚኒስትሩ ሲጠየቅም ሁኔታው በጃፓን ምድር ጦርነቱን እቀጥላሁ አለ ። ወደ ጄኔራል አናሚ ሄደው አንዳንድ የጦር ጄኔራሎች ንጉሱን ለመገልበጥ ጠየቁት ይሁን እንጂ ይህንን ሀሳባቸውን ሳይቀበላቸው ቀረ ። የተወሰኑት ጠቅላይ ሚኒስትሮች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመግደል ሄዱ ሲያጡትም ቤቱን አቃጥለው ሄዱ ። የጃፓኖች እምቢተኝነት ከፍተኛ ደረጃ እስከዚህ ድረስ ነበር ።

እንደ አዛዥነቱ ሀገሩን ለድል ሳይሆን ለሽንፈት በመምራቱ ልቡ አዝኗል ። ሴቲኩ የሚባል ባህል አለ በዚህ ባህል አንድ ሰው ራሱን መግደል ይችላል ። ነገር ግን ጠላት እጅ ወድቆ ለሀገሩ ውርደትን እንዳያመጣ እራሱን ገደለ ። ጄኔራል አናሚ የወራሪዋ የጃፓን ጦር አዛዥ ነው ብለው የሚተቹት ይኖራሉ ። ይሁን እንጂ እሱም እራሱን በመግደሉ ማግስት የጃፓን ንጉስ ጃፓን ራሷን መስጠቷን አስታወቁ ። የባህር ሀይልም በእርሱ ስር ህይወታቸውን ላጡ 4000 የጃፓን አብራሪ ቤተሰቦች ይቅርታ ተይቋል ።

በውጤቱን የቃል ኪዳን ጦር ጃፓንን ተቆጣጠረ ። ሂሮሂቶ ዋናው ተጠያቂው እኔ ነኝ ብሎ ለማካርተር ነግሮታል ። መቼም አሜሪካኖች ከዛሬው ይልቅ የወደፊቱ ያሳስባቸዋል የሚከሰሱትም የንጉሱን ስም እንዳያነሱ ተደርጓል ። አሜሪካኖች እሚጠቅማቸው እስከ ሆነም ድረስ ምንም ነገርን ከማድረግ አይመለሱም ።

ጦርነትን ለመጨረስ አብርሆትን የተጎናፀፉ (Enlightened) መሪዎች ያስፈልጋሉ ። እነኚህም የረጅም ጊዜውን ጥቅምና ጉዳትን ማስላት የሚችሉ ናቸው ። ለዚህም አይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው ይኀውም የጃፓንና የአሜሪካን በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ያደረጉት ጦርነት ሲሆን ፣ አሜሪካኖች ጃፓን የአሜሪካን ወዳጅ ሀገር ልትሆን እንደምትችል በማሰብ የጃፓንን ንጉስ ከማዋረድ ተቆጥበው ፣ በጃፓን ህዝብ ዘንድ ሊመጣባቸው ይችል የነበረውን በታሪክ ሊተላለፍ ይችል የነበረን ጥላቻን በማስቀረት በአሁኑ ወቅት በአሜሪካና በጃፓን መካከል በጣም ጥብቅ ወዳጅነት መፍጠር ችለዋል ። አውሮፓውያኑም ጀርመን ፣ እንግሊዝና ፈረንሳይም በሁለተኛ የአለም ጦርነት ወቀት የመረረ ጦርነትን ቡያደርጉም የረጅም ጉዜ ጥቅቸውን በማሰብ ወደ ዘላቂ ሰላም መድረስ ችለዋል ።

በአንፃሩ በእስልምና አክራሪዎች እንዲሁም በእስራኤል እና በፍልስጥኤም መካከል የሚደረገው ጦርነት ጋብ የሚል አይነት ሳይሆን ለበርካታ አመታት እየቀጠለ ያለና አሜሪካንና ምእራባውያንን እየጨመረ የመጣ ነው ። አሜሪካ ከአልቃኢዳ ጋር ያላት ጦርነትም እንዱሁ ለብዙ አመነታት የሚቀጥልና በቀላሉ ወደ ሰላም የሚመጣ አይደለም ። ለምሳሌ እስራኤል ከፍልስጥኤማውያንና ከአረቦች በኢራን ጋር ያላት ውዝግብ ለበርካታ ትውልዶች የተላለፈና ፣ አሁንም እየተካሄደ ያለ  ነው ።

peace world

ጦማረ ሀሳብ

Wednesday, May 8, 2013

የአየር ንብረት ለውጥና ምጣኔ-ሀብት

            የአየር ንብረት ለውጥ በምጣኔ-ሀብት እድገት ላይ የፈጠረው አሉታዊ አንድምታ በአሁኑ ዘመን በመታየት ላይ ነው ። ላለፉት በርካታ መቶዎች አመታት አውሮፓውያን የኢንዱስትሪ አብዮትን ካንቀሳቀሱ ወዲህ በአየር ንብረትና በአካባቢ ላይ የደረሰው ውድመት እጅግ ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ሳይንቲስቶች እንዳረጋገጡት በአለም ላይ እየታየ ያለው የሙቀት መጨመር ላለፉት 4 ሚሊ ዮን አመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ነው ።

               የአየር ንብረት አስከፊ በሆነ ሁኔታ መለወጥ የፖለቲካ ጉዳይ ከመሆኑ አገራትን ሊያስማማ  አልቻለም ። ለምሳሌ ቻይናና አሜሪካ በዚሁ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ላይ በመሐከላቸው ሰፊ ልዩነት ያለ ሲሆን ፣ አሜሪካም በበኩሏ ከራሷ ይልቅ ሌሎች አገራት ወደ ከባቢ አየር የሚለቁትን የልቀት መጠን እንዲቀንሱ ትፈልጋለች ።  

              በአንፃሩ እንደ አፍሪካ ያሉት ደሐ አህጉራት ደግሞ በዚህ የአየር ንብረት ለውጥ በተለይም በከባቢ አየር ሙቀት መጨመር በእጅጉ ተጎጂዎች ናቸው ። በእርሻ ስራ ላይ ምጣኔ-ሀብታቸው የተመሰረተው ገና በማደግ ላይ ያሉት ሐገራት  የአየር ንብረት ሙቀት በሚጨምርበት ወቅት የግብርናው ምጣኔ-ሀብታቸው በእጅጉ እንደሚዳከም የታወቀ ነው ። ይሄውም የህዝብ ቁጥራቸው ሲጨምር ቁጥሩ እያደገ ላለው ህዝባቸው የምግብ ሰብል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ። 

            ይህ ሁሉ ሲሆን በአካባቢ ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ከጉዳቱ ለማገገም ተፈጥሮ በቀላሉ አያገግምም የሚል የሳይንቲስቶች ግምት አለ ። የአንድ ዲግሪ ሴንትግሬድ የአለም ሙቀት መጨመርን ለመቀነስ አንድ ሺህ አመት ያስፈልጋል ። ይህ ብቻ ሳይሆን የሚጠፉና ተመልሰው የማይገኙ የእንሰሳና የእፅዋት ዝርያዎችም አሉ ።

               ያደጉት ሐገራት ለሚለቁት የካርቦን መጠን  ፣ የካርቦን ግብርን ለመክፈልም ሙሉ ፈቃደኝነትን ማሳየታቸውም አጠራጣሪ ነው ።

Thursday, May 2, 2013

የመዋቅራዊ ለውጥ ፈተናዎች

የምጣኔ-ሐብት መዋቅራዊ ለውጥ መሰረታዊ ለውጥ ሲሆን ይህም በውስጡ ፈተናዎችን ይዟል ። የኑሮ አለመመጣጠን ፣ የከተሞች መጣበብ ፣ እና የህዝብ ቁጥር መጨመር የመሳሰሉት ናቸው ።

ለአንድ ታዳጊ ለነበረ ፡ ነገር ግን በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኝ አገር የምጣበኔ-ሀብቱ መዋቅር እየተለወጠ ሲመጣ ፈተናዎችም ይጋረጣሉ ። 

ፕሬዝዳንት ኦባማና አፍሪካ

ፕሬዝዳንት ኦባማ በመጀመሪያ ተመርጠው ወደ ስልጣን ሲመጡ በርካቶች የአፍሪካን አህጉር ትኩረት ያደርጋሉ ብለው ተስፋን ሰንቀው የነበረ ቢሆንም የኦባማ ትኩረት ግን አሜሪካ ላይ ሆኖ ቀርቷል አሜሪካ 1930 ዎቹ ወዲህ በታሪኳ ከታላቁ የምጣኔ-ሀብት አዘቅት ለመጀመሪያ ጊዜ የገባች ሲሆን ይህም ኦባማን ትኩረታቸውን በአሜሪካ የውስጥ ጉዳይ ላይ እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል

በአንድ በኩል አሜሪካ ራሷ በገጠማት ከባድ ምጣኔ-ሀብታዊ ቀውስና የመካከለኛው ምስራቅ ማለትም በኢራቅና በአፍጋኒስታን ባካሄደቻቸው ወታደራዊ ዘመቻዎች ሳቢያ የኦባማ አስተዳደር ትኩረቱን ወደ ውስጥ ለማድረግ ተገዷል    

ምንም እንኳን ፕሬዝዳንት ኦባማ በተመረጡ ሰሞን ወደ ጋና ብቅ ብለው ለአፍሪካ አምባገነኖች ምንም አይነት ቸልተኝነት እንደማይኖር ገልፀው የነበሩ ቢሆንም በተግባር ግን የአሜሪካ ፖሊሲ ከአፍሪካ ዲሞክራሲ ይልቅ ለራሷ ብሄራዊ ጥቅም ሆኖ ዘልቋል ። « ጥቅም እንጂ ወዳጅ የላትም» የምትባለው አሜሪካ የአለም አቀፍ ግንኙነት መርሆዋ ብሄራዊ ጥቅሟን ማስከበርን ያስቀደመ እንደሆነ አለም ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል ።